Telegram Web Link
ስለ ባህርዳር‼️

በአማራ ክልል ርዕሰመዲና ባህርዳር ከተማ ዛሬ ነሀሴ 10 በተለይ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል፣የንግድ ቤቶች ተዘጋግተው ተመልክተናል ብለዋል።

የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ጉዳዩን አስመልክቶ ከሰዓት በፊት መግለጫ የሰጡ ሲሆን "ባህርዳር ላይ ምንም አይፈጠርም፣ የፀጥታ መዋቅሩ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል" ሲሉ ተደምጠዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ባህርዳር ላይ ምንም የተፈጠረ የፀጥታ ችግር የለም፣ ህዝቡ ተረጋግቶ የተለመደ የዕለት ከእለት ተግባሩን እንዳያከናውን ጥሪ አቅርቧል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ትናንት ጀምሮ የፋኖ ሀይሎች ወደ በባህርዳር ከተማ እንገባለን፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል በሚል ለመዝጋት እንደተገደዱ ገልፀውልኛል።

የከተማዋ አንድ ነዋሪ "ምሳ አዝዤ ATM ደርሼ ስመለስ ሹሮ ቤቱ ተዘግቶ አገኘሁት ሲል ገልፆልኛል። መሰራታዊ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልገሎት መስጠት አቁመዋል ብለዋል። ሰሞኑን ከፍተኛ የሆነ የቦንብ ፍንዳታ ይሰሙ እንደነበር ጠቁመዋል።

ውጊያ አለ ወይ
እስካሁን ምንም አይነት ተኩስ አልሰማንም፣አብዛኛው በስጋት ምክንያት ነው የዘጉት ያሉ ሲሆን ህዝቡም በቤት ውስጥ ለመቀመጥ ተገዷል፣ ግራ ገብቶናል" ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ለአዩዘበሀሻ ሰጥተዋል።
ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው መረጃ ይህ ነው።(ayu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
<<ተሳትፎ ነው ላልነው ይቅርታ እንጠይቃለን።ኦሎምፒክ ግን ተሳትፎ ነው።>> ዶ/ር አሸብር

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪስን ኦሎምፒክ አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለእነ ዶ/ር አሸብር ከጋዜጠኞቹ የቀረቡት ጥያቄዎች ሲጠቃለሉ... "ይቅርታ ጠይቃችሁ ስልጣን ልቀቁ?" የሚል ነበር።

ዶክተር አሸብር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶክተር) ከሰጧቸው ምላሾች መሐከል ...

📌 ተሳትፎ ነው ላልነው ይቅርታ እንጠይቃለን ።ኦሎምፒክ ግን ተሳትፎ ነው።

📌 ከIOC ከመቶ ሺህ ዶላር በታች ነው የተሰጠን።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ያካሄደው  ምርጫ ትክክለኛ ነው።

📌 የቀረበብን ክስ ሰምተናል ግን አንደነግጥም።

📌 አትሌቶችን ጥሩ ሆቴል አስቀምጠናል። ሆቴል ውስጥ ደግሞ አስረን አላስቀምጥናቸውም።

📌 የቦክስ ተወዳዳሪው በኦሎምፒክ ያልተሳተፈው ፓስፓርት ስለሌውና ስደተኞች መጠለያ ስለሆነ ነው።

📌 አትሌት ገዛኸኝ አበራ ሶስት ጉዞዎችን ሰርዞ በአራተኛው ጉዞ ነው ፓሪስ የመጣው። ያቀረበው ክስ ውሸት ነው። ዋሽቷል።

📌 አትሌት ፍሬህይወት ከፓሪስ የቀረችው በዶፒንግ ምክንያት ነው። ተገቢውን ምርመራ አድርጋ ውጤቷን ማሳወቅ አልተቻለም።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የጣሰው ምንም አይነት ደንብ የለም።

📌 የፌዝ ሪፖርት አላቀረብንም። የፌዝ ሪፖርት አቀረባችሁ በመባሉ ስሜታችን አይነካም።

ሥልጣን አልለቀም!

📌 እንደ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሰልፍ ሳይ አልሮጥም። ኃይሌ በሰልፍ ወረደ በሰልፍ ሊመለስ ይፈልጋል ።

📌 የሚያግደን ምንም ኃይል የለም።

📌 ደሀ ስለሆንን አነስተኛ ልዑክ ይዘን የሄደነው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ነው።

📌 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፌዴሬሽንን ያፈረሰው ኃይሌ ገ/ሥላሴ ነው።

📌 ለኃይሌ ስንል የሽግግር መንግስት እናቋቋም እንዴ? ...እኔ ከዚህ ጋ ብነሳ ኃይሌ በፍጹም እዚህች አይደርሳትም።

📌 “ ከሀላፊነት በመውረድ እና በመውጣት የሚመጣ ለውጥ የለም እግር ኳሱን ምሩ ብዬ ጥዬ ወጥቼ የመጣ ለውጥ የለም።  
 
📌 ጉዳፍ ፀጋይን ለማግባባት ሞክረን ነበር ፣ ነገር ግን አቋሟ ጥሩ ስለነበር በሦስቱም ርቀቶች እወዳደራለሁ ስላለች ትተናታል።" 
 
📌 እኔ ከኃላፊነት ብለቅ እንኳ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የሚገባበት መንገድ የለም።  
 
📌 ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠብቅሃል ተብዬ ነበር ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው ፣ እንደ ኃይሌ ሰልፍ ሳይ አሮጥም።  
 
📌የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከማንም በላይ ጉልበት አለው ፣ ጉባኤው ጠንካራ ነው።  
 
📌 ሕግ ላይ አጥብቀን ስለምንሰራ ብዙ ጊዜ አልሸነፍም ! 

📌 የኔ ሸልማት የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር ነው!

ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠቃሏል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ  ምክንያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ  አልተገኘችም።

“ በህዝቡ ከኃላፊነት እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው ፣ በባንዲራው ስም ይልቀቁ!" ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ከኃላፊነት አለቅም “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
Via Befekadu Abay

@sheger_press
@sheger_press
ህወሃት የእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀስ አግጃለሁ ብሏል‼️

በህወሃት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ቡድን ዛሬ ባወጣም መግለጫ በ14ኛ ያልተሳተፉ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ማለትም የነ ጌታቸው ረዳ  ቡድን፥  ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም መድረክ በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀሱ ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ስልጣን ለሚፈልጉ ኣካላት መሳርያ ሊሆኑ ኣይገባም”-ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ


ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በወቅታቸው ጉዳይ ላይ ዛሬ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

ዋና ዋና ነጥቦች:-

👉 ጉባኤው ውጤት እንደሌለው ስለምናቅ ወዳልተፈለገ መሳሳሰብ ላለመግባት ጉባኤው እንዳያካሂዱ አልከለከልንም።

👉 ምንነቱ ያልታወቀ ሃይል ደጀን ይሆነናል ብለው ተማምነው እያደረጉት ያለ ጉባኤ ነው ነገር ግን ወዳልተፈለገ ችግር የሚያደገባ ነው።

👉 የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመንጠቅ እንቅስቃሴዎች ሊያደርጉ ይችላሉ ብለን እንጠብቃለን።

👉 የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ስልጣን ለሚፈልጉ ኣካላት መሳርያ ሊሆኑ ኣይገባም።

@sheger_press
@sheger_press
ባህር ዳር

ፌቨን የ7 ዓመት ህፃን ነች።እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘው ጌታቸው የተባለ የ3 ልጆች አባት ህፃኗን በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ደፍሮ ገድሏት ተገኘች።

የ7 ዓመት ህፃኗ ልጅን ግቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፏ ውስጥ አሽዋ በመጨመር ለመግለፅ በሚከብድ ሁኔታ አሰቃይቶ እንደገደላት እናት አስረድታለች።

25 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ቢሆንም በይግባኝ ለማስወጣት እየሠሩ ነው።እኔን አስፈችው በማለት ዛቻና ማስፈራሪያው ከአቅሜ በላይ ሆኗል።ህዝብ ይፍረደኝ እያለች ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ደስ የማይል ቀን ነው

ዛሬ በሶሻል ሚዲያው በስፋት እየተዘዋወረ የሚገኘውን የ 7 አመቷ ታዳጊ የፌቨንን መረጃ አመሻሽ ላይ አይቼ ነበር ፤ እናም በእውነት ልብ ሰባሪ ነው ብዙዎችንም በጣም ያሳዘነ አስነዋሪ ተግባር ነው በዚህች ታዳጊ ላይ የደረሰው

አይደለም ለ 7 አመት ልጅ ማንም ላይ ቢከሰት ልብን የሚሰብር አይነት መረጃን ነው ያየነው ::

ኢትዮ መረጃ እንደ ቻናል በሰባት አመቷ ታዳጊ ፌቨን ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል ይቃወማልም ያወግዛልም

ነገር ግን መቃወም እና ማውገዙ ፍትህን ማስገኘት መቻል አለበት ፤ ሁላችንም ፌቨን ላይ የተደረገውን ነገር መቃወም አለብን ። በውጪው አለም ታዳጊ ህፃናትን ፆታዊ ጥቃት አድርሶ መግደል ይቅርና የወንድ ልጅ መብት ከውሻ ራሱ ያነሰ ነው የሴቶች መብት ደግሞ በአንደኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል ።

እኛ ሀገር ደግሞ እንደዚ አይነት ችግሮች ሲከሰቱ ለቀናት ይወራል ከዛ ፍትህ ሰፈነ የሚለው ተረስቶ ታሪክ ሆኖ ይቀራል

ፍትህ ፍትህ

@sheger_press
@sheger_press
#ፍትህ_ለሔቨን

ይህቺ ብላቴና ምን በወጣት ይሄን ሁሉ በደል በሷ ላይ...?

ፍትህ ፍትህ ፍትህ

@sheger_press
የአማራ ክልል የ2016 ዓ.ም የ6ኛ  እና 8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል‼️

ውጤት ለማየት

👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች
https://amhara.ministry.et/#/result

👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች
https://amhara6.ministry.et/#/result
የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) በማስገባት ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ትልቅ የማፊያ ስራ ተሰርቷል!"

ዶ/ር አሸብር ምን እያሉን ነው?

በጋዜጠኛ ዐቢይ ወንድይፍራው ለመሠረት ሚድያ

ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስን ሳውቃቸው በሚዲያ ፊት የሚናገሩትን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስሜታዊ አይደሉም። የሚጠቀሟቸው ቃላትም የአጋጣሚ አይደሉም። ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ ሁለት መድረኮች (ከፓሪስ መልስ በሰጡበት ጋዜጣዊ መግለጫ እና ትናንትና ኢቲቪ ባዘጋጀው ውይይት ላይ) እንደዋዛ ጣል ያደረጉት “ክስ”ቀልቤን ስቦታል።

ዶክተሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ በተለይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሲፋን ሀሰን እንድታሸንፍ ሆን ተብሎ ደባ መሰራቱን ገልጠው “ትልቅ የማፊያ ስራ ተሰርቷል" ብለዋል። ይህ ተንኮል የሚሰራውም በሀገር ውስጥ አትሌቶቹን ከሚያዘጋጁ አሰልጣኞች ጋር በመሻረክ እንደሆነ ጠቅሰው ጋዜጠኞች ከሜዳ ላይ ዘገባ ባለፈ እንዲህ ያሉ ከሜዳ ውጪ ያሉ ችግሮች ላይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ እንዲሰሩ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንቱ ጉዳዩ በሀገር ውስጥ ሚዲያው የጠበቁትን ያህል ትኩረት አለማግኘቱን ተመልክተው በማግስቱ (ትናንት) ጠንከር ባሉ ቃላት ሀሳቡን ደግመውታል። በኢቢሲው ፕሮግራም ኦሊምፒክ/አለም አቀፍ ሻምፒዮናዎች ላይ Match Fixing (የውድድርን ውጤት አስቀድሞ መወሰን) ይፈፀማል፣ ጉዳዩም 'ከገንዘብ ጋር ይያያዛል' ብለዋል።

[ሰውየው በዚህ ክስ (አጀንዳ) ምን ኢላማ አድርገዋል?]
***

1/ ሀይሌ ገ/ስላሴ

ዶክተሩ በዚህ ክሳቸው አንድም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋነኛ ዒላማቸው የሆነውን ሀይሌ ገብረስላሴ ማጥቃት እንደፈለጉ ግልጥ ነው። ከኢቲቪው ማብራሪያቸው አስቀድመው ሀይሌን ተጠያቂ ያደረጉበት የብሔራዊ ቡድን መፍረስ አሰልጣኞችን እሳቸው አለም አቀፍ ማፊያ ላሉት ቡድን መጠቀሚያ አድርጓል በማለት በተዘዋዋሪ ጣታቸውን ወደ ቀድሞው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጠቅመዋል።

2/ ገዛኸኝ አበራ

ከኦሊምፒክ ኮሚቴና ሰዎች ጋር የከረረ አተካሮ ውስጥ የገባው የቀድሞው አትሌት ገዛኸኝ አበራ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ይሁን እንጂ በፓሪሱ ኦሊምፒክ ዝግጅት ወቅት የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነበር። ይህ ኮሚቴ ለአትሌቶች ብቻ ሳይሆን ለብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞችን ዝርዝር የሚወስን በመሆኑ ሰብሳቢው ገዛኸኝን በክስ መዝገባቸው ለማካተት ያስችላቸዋል።

3/ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ባስመዘገበቻቸው ስኬቶችና ቀደም ባለው ጊዜ ትሰጣቸው በነበሩ አስተያየቶች ምክንያት ስሟ በቀላሉ ትኩረት ያገኛል። ስለዚህም ውጤቶቿ በተቀናጀ ተንኮል የተመዘገቡ ናቸው የሚል አጀንዳ በቀላሉ የሀገር ውስጥ ሚዲያውን ቀልብ ስቦ በእርሳቸው እና በተቋማቸው ላይ ያነጣጠረውን ትኩረት ሊበትንላቸው እንደሚችል ያሰሉ ይመስላል። ለዚህም ጉልበት እንዲጨምርላቸው በሚመስል መልኩ አይኖቻችሁን ክፈቱና መርምሩ እንጂ በማለት ሚዲያውን ለመኮርኮር ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ተስተውለዋል።

[የፌዴሬሽኑ ምላሽ - ዝምታ?]

የዶ/ር አሸብር ክስ እውነት ላይ የተመሰረተ ይሁንም አይሁን ጉዳዩ ከሌሎችም ጋር ያነካካቸዋል። ሌላው ቀርቶ ከእርሳቸው ጋር በአጋርነት የቆመ የሚመስለውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (ፕሬዚዳንቷ ደራርቱ ቱሉ) ወይም የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞችም እንዳልሰሙ ማለፍ አይችሉም /የለባቸውም። ዶክተር አሸብር አትሌቶቻችን የሚሰለጥኑት ሌሎች የተመረጡ አትሌቶች እንዲያሸንፉ ታስቦ በተዘጋጀ ቀመር ነው ሲሉ ደራርቱ ከጎናቸው ነበረች። ሌሎች አሰልጣኞችም በፕሮግራሙ ላይ ታድመዋል። ቢያንስ ተቀርፆ በዩቱብ በሚታየው ቪዲዮ ላይ አንዳቸውም ይህንን ሲያስተባብሉ አላየንም።

[የዶክተሩ ንግግር ጣጣ አያመጣባቸውም?]

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (IOC) በየሀገራቱ ያሉ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቋማትን የኦሎምፒክ ንቅናቄ አምባሳደሮቼ ይላቸዋል። እነዚህን ተቋማት የሚመሩ ሃላፊዎችም የኦሊምፒክ ዕሴቶችን ማስተዋወቅ ይጠበቅባቸዋል። ተግባሮቻቸው እና መግለጫዎቻቸውም መከባበርን እና ወዳጅነትን ጨምሮ የኦሊምፒዝምን ዕሴቶች እንዲያሳድጉ ይጠበቃል።

ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ንግግር ከዚህ ጋር አይሄድም:: በአምባሳደርነት የሚወክሉት IOC በሚያዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ ድግስ የፍትሃዊነትና ተአማኒነት ጥያቄ አንስተዋል:: ንግግራቸውን ስሟ የተጠቀሰው አትሌት ሲፋን ወይም የኔዘርላንድስ ስፖርት ሀላፊዎችም ታዝበውት በቀላሉ አያልፉትም ይሆናል::

በእርግጥ ይህ ክሳቸው የተነገረው ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ባላቸው የሚዲያ ሰዎች ተወካዮች በተገኙበት እና በውጪ ሀገር ቋንቋዎች አለመሆኑ ለጊዜ ረድቷቸው ይሆናል:: እንደዚያ ባይሆን ኖሮ ምናልባት ለሀገር ውስጥ ባላንጣዎቻቸው የለኮሱት ክብሪት ሙቀት ከቁጥጥር ወጥቶ መልሶ ራሳቸውን ሊፈጃቸው ጥቂት ሰዓታት በቂ ነበሩ።


ምንጭ:- መረጃን ከመሠረት ሚዲያ

@sheger_press
ፍትህ‼️ ሁላቹም ተሳተፉ

ስለዚች ምስኪን ህፃን የወረት ተወርቶ  ዝም መባል የለበትም  ለህፃን ሔቨን ፍተህ ያስፈልጋል።

Petition 100ሺ አልፏል
እናንተም ተሳተፉ።

ወደ ሊንኩ ከገባቹ በኋላ 👉 https://chng.it/RNMNMvD4

የናንተን ስም
የአባታቹን ስም
ሶስተኛ ላይ ኢሜል

እነዚን አስገብታቹ Petition ተቀላቀሉ !!
እስቲ ሁላችንም ይሄንን Petition እንሳተፍ

ለምታውቁት ሰው ሁሉም ሊንኩን ሼር አድርጉ !

ሊንክ 👉 https://chng.it/RNMNMvD4

@sheger_press
@sheger_press
ያሳፍራል ያልተጠበቀ ምላሽ ‼️

እናንተ ምንም በሉ ምንም እኛ ግን አንተወውም።

በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀ፡፡

ከሰሞኑ የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህር ዳር ከተማ የሰባት ዓመት እድሜ ያላት ህጻን ሔቨን የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ከተፈጸመባት በኋላ ህይወቷ እንዳለፈ የህጻኗ እናት ለተለያዩ ሚዲያዎች ተናግራለች፡፡

በርካቶችን ያስቆጣው ይህ ድርጊት ወንጀሉን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ በተፋጠነ ምርመራ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ የ25 ዓመት እስር እንደተላለፈበትም ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎ ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ላይ የተላለፈበት ውሳኔ በቂ ካለመሆኑ በላይ ግለሰቡ ፍርዱ እንዲቀነስለት ይግባኝ ማለቱም ተነስቷል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተፈጸመ የተገለጸው ይህ ወንጀል ጉዳዩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ሲሆን ተቋማት ሳይቀር በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫዎችን በማውጣት ላይ ናቸው፡፡

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው በሕፃን ሔቨን ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ወንጀል ማዘኑን ገልጾ ድርጊቱም ከሃይማኖትና ከባሕል ያፈነገጠ በመሆኑ በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል።

ይሁንና በኢትዮጵያ ወንጀል እና ወንጀለኛ የሚዳኝበት ሕግና ስርዓት እያለ እና ጉዳዩም በዳኝነት አካሉ በይግባኝ እየታየ ባለበት ሁኔታ የዳኝነት ነጻነት እና የሕግ የበላይነት መርህን የሚጥስ የሚዲያ ዘመቻ መደረጉ ስህተት መሆኑን አስታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 11:26:17
Back to Top
HTML Embed Code: