Telegram Web Link
ሆ ቢገባው ይህ ብር ስንት ለተቸገሩ ወገኖቻችን ሊሆን እንደሚችል አልተረዳውም።

“ ሁለት ሚልዮን ብር ለእኔ እንደ ስድብ ስለሆነ መመለስ እፈልጋለሁ“ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ

በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ግብዣ ተደርጎለት ነበር።

በግብዣ እና ሽልማት ዝግጅቱ ላይ በውድድሩ ለኢትዮጵያ ሜዳልያዎች ያስገኙ አትሌቶች እና አሰልጣኞች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ ለሀገራችን ብቸኛውን ወርቅ ያስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ ሰባት ሚልዮን ብር እና የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል።

የታምራት ቶላ እና ትግስት አሰፋ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በበኩሉ የሁለት ሚልዮን ብር ሽልማት ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

በዝግጅቱ ላይ መልዕክቱን ያስተላለፈው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ “ ፕሬዝዳንታችን እኛ አሰልጣኞች ለረጅም ጊዜ ለፍተናል ፣ ልፋታችንን አይመጥንም “ ብሏል።

አያይዞም “ ለኔ ሁለት ሚልዮን የስድብ ያህል ስለሆነ እርስዎን ካላስከፋዎት ይሄንን ሽልማቴን መመለስ እፈልጋለሁ ፣ ለሚመጣው ሁሉ እቀባለለሁ “ ሲል ተናግሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Telegram‼️

ተወዳጁ የSocial media platform Telegram በወንድማማቾቹ Pavel Durovና Nikoli Durov ከተመሰረተ እነሆ ዛሬ 11ኛ ዓመቱን ይዟል።

በ2013 ዋና መስርያ ቤቱን ጀርመን በርሊን በማድረግ ስራውን የጀመረው ቴሌግራም ለተወሰኑ አመታት ምንም አይነት ገቢ የማያስገባና በየወሩ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለስራ ማስኬጅ የሚያስወጣ Social media platform ነበር።

ከሌሎች የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች በተሻለ የተጠቃሚዎቹን መረጃ ሚስጥራዊነት  እንደሚጠብቅ የሚነገርለት ይህ አፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ በመወደድ ስኬት ማስመዝገብ ጀመረ።

ከመንግስታዊ ተፅዕኖም ነፃ በመሆኑና ከዋና ተገዳዳሪው ዋትሳፕ የተሻለ ብዙ ፊቸሮች ስለጨመረ በብዙዎች ዘንድ ለመወደድ በቃ።

http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ‼️

ለሁለት ቀናት በሱማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረዉ ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ::

ዉይይቱ በቱርኪዬ አሸማጋይነት በሁለት ዙር የተካሄደ ሲሆን አላማዉም በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ዉጥረት አርግቦ ጉዳያቸውን በንግግር እንዲፈቱት ነበር።

የሶማሊያ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ እንዳሰፈሩት ሶማሊያ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የገባችዉን ስምምነት አንቀበልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የማይዘዉን ለማግኘት እየሄደበትት ያለዉን መንገድ ሶማሊያ አትቀበለዉም ሲሉ ኢትዮጵያ የባህር በርን በሶማሊላንድ በኩል አታገኝም ለማለት ሞክረዋል። ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ እንደምትሰራ ገልጸዉ የምታላላዉ አቋም እንደሌላትም አሳስበዋል።

ሶማሊያ ድንበሯን እንደምታስጠብቅ የገለጹት የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ ሀገራዊ አንድነቷንም ለማረጋገጥ መንግስታቸዉ እንደሚሰራ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት እና ፋኖን ለማቀራረብ የሚጥረው የሰላም ካውንስል “ውጤት ማምጣት አልቻልኩም” አለ‼️

በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ  መካከል እየተካሄደ አንድ ዓመት የሆነውን ውጊያ በንግግር ለማስቆም በሚል ዓላማ የተቋቋመው የሰላም ካውንስል እንቅፋቶች እንደገጠሙት አስታወቀ።

ሁለቱ ወገኖች ለንግግር እንዲቀመጡ ለማመቻቸት እያደረገው ባለው ጥረት በተለይም የፋኖ አደረጃጀት ወጥ አለመሆን ለሚያደርጉት ጥረት ፈተና እንደሆነ የካውንስሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ከአንዱ አዎንታዊ [ምልሽ] ሲገኝ፤ ከሌላኛው አሉታዊ ይሆናል። . . . አንደኛው ጋር ጥሩ ነገር ሲገኝ ሌላኛው ጋር ደግሞ ተቃራኒ መግለጫ ሲሰጥ ይሰማል” ያሉት ኃላፊው፤ ወጥ አደረጃጀት አለመኖር የፋኖ ኃይሎች ለድርድር እንዲቀመጡ ለማመቻቸት እንቅፋት ሆኗል ብለዋል።

ምናልባት ድርድር መባሉን ተከትሎ [የፋኖ ኃይሎች] በፍጥነት ወደ ድርድር ይመጣሉ የሚል ተስፋ አድርገን ነበር። በእርግጥ አሁንም ቢሆን ሁለት ወደሚመስል አደረጃጀት ለመምጣት እሞከሩ ነው” በማለት አሁንም ተስፋቸው እንዳልተሟጠጠ ተናግረዋል።

Via BBB
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የኢትዮጵያ ህዝብና ክብርት ፕሬዝዳንትን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ" አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ

አሰልጣኝ ገመዱ ደደፎ የተሰጠውን የሁለት ሚልዮን ብር ሽልማት ያልተቀበልኩት “ ለሙያው የተሰጠው ክብር አነስተኛ በመሆኑ ነው “ ሲል ተናግሯል።
"ለአሰልጣኝ የሚሰጠው ክብር አነሰተኛ ነው" ያለው አሰልጣኙ "እኛ የብር ችግር የለብንም ፤ ለእኔ ከ ገንዘቡ ስሙ ይሻለኛል እንደ ታምራት ኒሻኑን ቢሰጡኝ በቂ ነበር" ብሏል።

"የሰው ልጅ ይሳሳታል" ያለው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ " በብዙ ችግሮች የመጣው ነገር ስሜታዊ አድርጎኝ ነው” ብሏል።

“ የኢትዮጵያን ህዝብ እና ክብርት ፕሬዝዳንትን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ" በማለትም ተናግሯል።
አሰልጣኙ በመጨረሻም አሁንም ቢሆን ነገሮች ካልተስተካከሉ ሁለት ሚልዮን ብሩን እንደማይቀበል ሲገልጽ ነገሮች ከተስተካከሉ ሽልማቱን እንደሚቀበል ተናግሯል።

© ሸገር ስፖርት ሬዲዮ

@ethio_mereja_news
አንድ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኛ በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ለገንዘብ ተብሎ ከታገተ በኋላ ግድያ እንደተፈፀመበት ታወቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ አንድ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት ሰራተኛ በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ለገንዘብ ተብሎ ከታገተ በኋላ ግድያ እንደተፈፀመበት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ቢሮው ባወጣው በዚህ መግለጫው ያሬድ መለሰ የተባለ Action for Social Development and Environmental Protection Organization (ASDEPO) በሚባል ድርጅት የሚሰራ ግለሰብ ገንዘብ በጠየቁ ታጣቂች ከታገተ በኋላ ግድያ ተፈፅሞበታል።

"በስራ ባልደረባችን ያሬድ ላይ ወንጀለኞች የፈፀመትን ይህን ግድያ አጥብቀን እናወግዛለን። የምገባ ስርዐት ባለሙያ የነበረው ያሬድ ጠንካራ እና ስራውን የሚወድ የሰብአዊ ድርጅት ሰራተኛ ነበር" ያሉት የቢሮው የኢትዮጵያ አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ ማንኛውም ጥቃት፣ ማስፈራርያ እና ዝርፊያ ተቀባይነት የሌላቸው ድርጊቶች ናቸው ብለዋል።

የአሁኑ ጥቃትን ጨምሮ በያዝነው የፈረንጆች አመት ብቻ ስምንት የሰብአዊ ድርጅቶች ሰራተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ መገደላቸው ታውቋል፣ ከዚህም ውስጥ አብዛኛው በማዕከላዊ እና ሰሜን ጎንደር የተፈፀመ መሆኑ ተመላክቷል።

በተያያዘ ዜና የአለም ምግብ ፕሮግራም የእርዳታ ምግብ የጫኑ ሁለት ተሽከርካሪዎቹ በኦሮሚያ ክልል በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደተቃጠሉበት እንዲሁም በጎንደር እና ባህር ዳር መስመር ሲጓዝ የነበረ አንድ የድርጅቱ ተሽከርካሪ ላይ በቅርቡ በተፈፀመ ጥቃት ምክንያት የተመድ ሰራተኞች በመስመሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ማቆማቸውን መሠረት ሚድያ ከሰአታት በፊት ዘግቦ ነበር።


ከመሠረት ሚድያ የተወሰደ
በእጅዎ ያለው ጥሬ ገንዘብ ዋጋ እያጣብኝ ነው ብለው ተጨንቀዎል?
የብር ዋጋ መቀነስ ወይም የዶላር ጭማሪ ሳያሳስብዎ የሚፈልጉትን ቤት ከ ዲኤምሲ ሪልስቴት ያግኙ

ዲኤምሲ ወቅቱን ባገናዘበ በከፍተኛ ዋጋ ቅናሽ ጥራታቸውን የጠበቁ ቤቶችን በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል

በእጆ የያዙት ብር ዋጋ ከማጣቱ በፊት በቋሚ ንብረት ይቀይሩት።
  -በ10% ቅድመ ክፍያ
  -50/50 የብድር አማራጭ
  -ከ8-25% ቅናሽ
  -ከስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ቤቶች እና ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍልና መታጠቢያ ጋር
❇️ለበለጠ መረጃ 0977190118 ይደውሉ
ለስድስት ወራት ደብዛቸው ጠፍቶ የነበረው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል፤ ተይዘው ከቆዩበት ተለቀቁ!

ከስድስት ወራት በፊት “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍነው” መወሰዳቸው የተነገረላቸው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ሀብታሙ በላይነህ፤ ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 7፤ 2016 መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። የአቶ ሀብታሙን ጉዳይ ሲከታተል የቆየው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤ የግለሰቡን መለቀቅ አረጋግጧል።

አቶ ሀብታሙ የአማራ ክልል ምክር ቤትን የተቀላቀሉት፤ በምዕራብ ጎጃም ዞን ከምትገኘው ቋሪት ወረዳ ተመርጠው ነው። በሰኔ 2013 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ፤ እንደ እርሳቸው ሁሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) የወከሉ ሌሎች ሁለት ተወዳዳሪዎች ከቋሪት የምርጫ ክልል ተመርጠው የምክር ቤቱ አባል ሆነዋል።

አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞውን የአብን አመራር አቶ ክርስቲያን ታደለም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመረጡት፤ ከቋሪት የምርጫ ክልል ነው። የአብን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ሀብታሙ፤ ደብዛቸው የጠፋው ከየካቲት 22፤ 2016 ጀምሮ እንደሆነ ለእርሳቸው ቅርበት ያላቸው አንድ ምንጭ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በዕለቱ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ “ሰው ላግኝ ብሎ ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም” የሚሉት እኚሁ ምንጭ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለስድስት ወራት ያህል አቶ ሀብታሙ ያሉበት ሳይታወቅ መቆየቱን አስረድተዋል። ብሔራዊው የሰብአዊ መብቶች ተቋም ኢሰመኮ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ባወጣው አንድ መግለጫ፤ አቶ ሀብታሙ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ “የት እንዳሉ እንደማይታወቅ” በተመሳሳይ አስታውቆ ነበር።

[Ethiopian Insider]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ለመቀጠር እስከ አንድ ሚሊየን ብር እጅ መንሻ እየተጠየቀ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር ባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ሥራ ለመቀጠር እንደየደረጃው ከ 3 መቶ ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እጅ መንሻ ክፍያ እንደሚጠየቅ ዋዜማ ካነጋገረቻቸው የተለያዩ ምንጮች ሰምታለች።

በተለይም በከተማይቱ፣ ትልቅ ሀብት የሚያንቀሳቅሱና ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ናቸው በሚባሉ አድባራትና ገዳማት አሥተዳዳሪ፣ ጸሐፊ፣ ሂሳብ ሹም ሆኖ ለመቀጠር ከ 3 መቶ ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እጅ መንሻ (ጉቦ) እንዲከፍሉ እንደሚጠየቁ ነግረውናል።

ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁና ከጉዳዩ ጋር ትሰሰር ያላቸው ምንጮች እንዳሉት፣ ሥራ ፈላጊዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ከ 5 እስከ 15 ዓመታት ያህል ተምረው ሥራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ወቅት እንደየሥራ ዘርፉ ክፍያ ካልከፈሉ ቅጥር የማይታሰብ ነው።

አሁን ላይ በቤተክርስቲያኒቱ ያለው የቅጥር ሁኔታ በሕግና በስርዓት ማስታወቂያ ወጥቶ ሰዎች አመልክተውና ተወዳደረው ሳይሆን ገንዘብ የመክፈል አቅም ያላው የሚቀጠርበትና ሥራ የሚያገኙበት እንደሆነ እነዚሁ ምንጮች ለዋዜማ ገልጸዋል።

ዋዜማ ካነጋገረቻቸው በርካታ ሥራ ፈላጊዎች መካከል አንዱ እንዳሉት አቋቋም፣ ድጓ እና ቅኔ የተሰኙትን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት አጠናቀውና አስመስክረው ሥራ ፍለጋ በከተማይቱ ውስጥ ባሉ በርካታ አቢያተ ክርስቲያናት ቢያመለክቱም “እጅ መንሻ ክፍያ ካልፈጸምክ ቅጥር የለም” መባላቸውን ተናግረዋል።

ሥራ ፈላጊው የመጡት ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፣በዚያ አካባቢ ባሉ ገዳማትና አድባራት ተዘዋውረው አስፈላጊውን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት መማራቸውን አስረድተዋል።

ሆኖም ሥራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነገሩ እንዳሰቡት እንዳልሆነላቸውና ሥራ ለመቀጠር 3 መቶ ሺሕ ብር ክፍያ መጠየቃቸውን ይገልጻሉ። በተለይም ከተማይቱ ውስጥ ባሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት ለመቀጠር የሚጠየቀው የገንዘብ መጠን ደግሞ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ነው ሲሉ ትዝብታቸውን አጋርተዋል።

ተቀጣሪን ከቀጣሪ የሚያገናኙ ደላላዎች የጉዳዩ ዋና ተዋናዮች ሲሆኑ ሥራ ፈላጊዎቹን ካሉበት ፈልገው በሀገረ ስብከት ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኟቸው ሲሆን፣ ደላሎቹም ከሚገኘው ገንዘብ ላይ ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ ግለሰብ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ውስጥ ባለ አንድ ትልቅ ደብር በመሪጌታነት የሥራ መደብ የተቀጠሩት ከሁለት ዓመታተ በፊት መሆኑን ያስረዳሉ።

በዚያ ወቅትም አጠቃላይ የቅጥሩን ሂደት ለመጨረስ 350 ሺሕ ብር በየደረጃው ላሉ የቤተክርስቲያኒቱ አመራሮች እጅ መንሻ ክፍያ መፈጸማቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል።

እሳቸው እንደሚሉት ይህ ጉዳይ አሁን የጀመረ ሳይሆን የሰነበተና ቀስ በቀስ ስር እየሰደደ መጥቶ አሁን ላይ ሕጋዊ እስኪመስል ድረስ በግልጽ የሚከናወን የአደባባይ ምስጢር ነው ።

እጅግ ከባድ የሚባለውን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ለበርካታ ዓመታት የተማሩና እውቀቱ ያላቸው ሰዎች የተጠየቁትን ክፍያ መፈጸም ባለመቻላቸው በአዲስ አበባ ከተማ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በርካቶች ናቸው ።

ከእነዚህ መካከል በከተማይቱ አደባባዮች ላይ ሎተሪ የሚያዞሩ፣ በጥበቃ ሥራ የሚተዳዳሩ፣የቀን ሥራ የሚሰሩ በየአቢያተክርስቲያናቱ ደጅ እየጠኑ ያሉ ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ ነው።

ይህን ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጀምሮ፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የየመምሪያው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ ሰዎች የሚያውቁትና ተደጋጋሚ አቤቱታ የቀረበበት ነው ሲሉ ጉቦ ተጠይቀናል ያሉት ግለሰቦች አስረድተውናል።

ሆኖም ግን ይህን ችግር ለመፍታትና እንደዚህ አይነት አሰራር ለማስቆም አንዳችም ጥረት ሲደረግ ተመልክተው እንደማያውቁ ያስረዳሉ።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አንድ ሌላ ግለሰብ ደግሞ በስብከተ ወንጌል የሥራ ዘርፍ ለመቀጠር አመልክተው 4 መቶ ሺሕ ብር ክፍያ መጠየቃቸውን አውስተዋል።

ሆኖም ይህን ያህል ገንዘብ የመክፈል አቅሙ ስለሌላቸው እንደተውት ገልጸዋል።

ዋዜማ በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስን ጠይቃለች።

“ከሠራተኛ ቅጥር ጋር ተያይዞ እንደዚህ አይነት ችግሮች የሉም ማለት አይቻልም” ብለዋል ዋና ሥራ አስኪያጁ።

ሥራ አስኪያጁ አክለውም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዚህ ሰዓት ሙሉ ለሙሉ የሠራተኛ ቅጥር መፈጸም አቁሟል ሲሉ አክለዋል።

ከዚሁ ችግር ጋር ተያይዞ፣ እሳቸውን ጨምሮ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲሁም ከአዲስ አበባ አገር ስብከት የተወጣጡ አባላትን ያካተተ ኮሚቴ መቋቋሙን ለዋዜማ ገልጸዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም ከዚህ በኋላ አድባራት ራሳቸው ማስታወቂያ አውጥተው ሰራተኞችን አወዳድረው ቅጥር እንዲፈጽሙ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር እንዲፈጠር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከሥራ ቅጥር ጋር ተያይዞ ቅሬታ ከሚያነሱ ሰዎች ጋርም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት፣ ውይይት መካሄዱን ሊቀ ማእምራን የማነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት የተማሩ በሙሉ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ አድባራትና ገዳማት ሥራ ለመቀጠር ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ወደ ከተማይቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚፈልሱ ጠቁመዋል።

ይህ ደግሞ አሁን ለሚነሳው ችግር እንዲጋለጡ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ሥራ አስኪያጁ ከሦስት ወራት በፊት ከቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የአዲስ አበባን አገረ ስብከት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በሥራ አስኪያጅነት የመምራት እድል እንደነበራቸው ተናግረዋል።

በዚህ ወቅት ወደዚሁ ኃላፊነት ድጋሚ ሲመጡ ተቋሙ በብዙ መልኩ ተዳክሞና የተለያዩ የአሰራር ችግሮች አጋጥመውት እንዳስተዋሉ አንስተዋል።

ከነዚህም መካከል በአገረ ስብከቱ አላስፈላጊ የሆነ የሠራተኛ ቅጥር ተከናውኖ መታዘባቸውን ጠቁመዋል።

እሳቸው ወደ አገረ ስብከቱ በሥራ አስኪያጅነት ሲመጡ፣ ከ 1 መቶ በላይ ፣በአለቅነት፣ በሂሳብ ሹምና በፀሀፊነት ጭምር የተመደቡ ትርፍ ሰራተኞች ደሞዝ ይከፈላቸው እንደነበር ገልጸዋል።

ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት “የአዲስ አበባ አገረ ስብከት የታወከ፣ጩኽት የበዛበትና መረጋጋት የተሳነው ነው”

“ወደ ኃላፊነት ስመጣ እንደ ተቋም ፈርሶ ነው ያገኘሁት” ሲሉ ተደምጠዋል።

Via ዋዜማ

@ethio_mereja_news
ሰበር‼️

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት እና ፕሬዘዳንቱ ላይ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተጠየቀ‼️

👉 በቀረበው ሰነድ ዶክተር አሸብርን ጨምሮ የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ አባላት የፈጸሟቸውን በደሎች በዝርዝር ተመልክቷል

👉አቤቱታው ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ጥሰትና ምዝበራ መካሄዱን ይገልጻል

👉 ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ያለ እሱ ፍቃድና ዕውቅና እየተቃወመ በግድ ምክትል እንዳደረጉት ተጠቅሷል።

👉 ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ያለ ምርጫ ለቦርዱ አመራርነት እንድታልፍ መደረጉም ተያይዟል።

በኢትዮጵያ ተመዝግበው ያሉ ሕጋዊ የስፖርት ፌዴሬሽኖች በሕጋዊ ወኪል ጠበቆቻቸው አማካኝነት፤ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ላይ አስዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቅ ሰነድ በዛሬው ዕለት ለኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስገብተዋል።

አቤቱታ አቅራቢ ፌዴሬሽኖቹ በሰነዳቸው ላይ ካቀረቧቸው ምክንያቶች መሐል፦

👉ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ኮሚቴው ከፌዴሬሽኖቹ እውቅና ውጪ በድብቅ ጥሪ ተደርጎ በድብቅ የተፈጸመ ስብሰባ ማካሄዱን ይገልጻል።

👉አቤቱታ አቅራቢ ፌዴሬሽኖች ባልተጠሩበት፤ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ/ም በተደረገ ሕገወጥ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ምርጫ፤ ኮሚቴ ለሚፈልጋቸው ጥቂት አባላት ብቻ ጥሪ በማድረግ፤ መተዳደሪያ ደንቡ የማይፈቅድላቸውን በድምፅም ሆና ያለ ድምፅ የጠቅላላ ጉባኤው አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አድርገዋቸዋል።

👉 ከዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ጋር የጥቅም ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጥበቡ ቸኮልን ኮሚቴው አስመራጭ በማድረግ ሕግ ተላልፏል ሲል በአቤቱታው ላይ ያስነብባል።

👉አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ዕውቅና እና ፍቃድ ድርጊቱን እየተቃወመ በሕገ ወጥ ምርጫው ላይ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተደርርጓል የሚል አቤቱታም ይገኝበታል።

👉የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫና አብላጫ ድምፅ እንደሚመረጡ መተዳደሪያ ደንቡ የሚደነግግ ቢሆንም ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ያለ ምርጫ እንድታልፍ መደረጉን በሰንዱ ተብራርቷል።

👉ለኮሚቴው ከረጂ ተቋማት የተሰበሰበ ከ300,000,000.00 (ከሦስት መቶ ሚልየን ብር) በላይ ምን ላይ እንደዋለ በኦዲት ሪፖርት እንደማያውቁት አቤቱታ አቅራቢዎቹ በሰነዱ ላይ ገልጸው በተጨማሪም ከስፖንሰር አድራጊዎች የተገኙ በውጭ ምንዛሪ ገቢ የተደረጉ ገንዘቦች ምን ላይ እንደዋሉ የሙያሳይ ግልጽ የኦዲት ሪፖርት አለመደረጉን አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጨምረው ዘርዝረዋል።

👉ሰነዱ የአትሌት ገዘኸኝ አበራንም ጉዳይም አያይዞታል።

👉 በአትሌቶች አመራረጥ ላይ ተደርጓል ስለተባለው አድሏዊ አሠራርም ተካቷል።

👉ለአገር ክብር ምልክት ከሆኑ አትሌቶች ይልቅ የአመራሮቹ ዘመድ አዝማዶች አገር ወክለው እንዲሄዱ መደረጉም ተነሥቷል።

👉 ሰነዱ የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ አባላት የቅርብ ዘመዶች በኮሚቴው ያለ አግባብ ቅጥር እንዲፈጸምላቸው በማድረግ ምንም ዓይነት ሥራ ሳይፈጽሙ ገንዘብ በመመዝበር በርካታ የፋይናንስ ጥሰት መደረጉን ጨምሮ ይገልጻል።

እነዚህን እና ሌሎችንም አቤቱታዎች ያቀረቡት ፌዴሬሽኖች

👉ኮሚቴው አሻሻልኩት ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንዲታገድ፤

👉ሰኔ 4 ተደረገ የተባለው ሕገ ወጥ ምርጫ እንዳልተደረገ ተደርጎ ቀሪ እንዲደረግላቸው፤

👉የተፈጸሙት ተግባራት ከባድ የሆነ የዲሲፕሊን ጥፋት ውጤት በመኾናቸው ቦርዱ ከኃላፊነት ታግዶ እንዲቆይ

👉 በገለልተኛ ኦዲተር ምርመራ እንዲደረግ፤ በመጠየቅ

👉ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አስተዳደራዊ ርምጃ እንዲወሰድላቸው አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጠይቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአገልግሎት ታሪፍ ላይ በየሦስት ወሩ የ10 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። የታሪፍ ጭማሪው የኢትዮጵያ መንግሥት ከአለም ባንክ ጋር ከተፈራረመው ስምምነቶች አንዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

በማሻሻያው መሠረት በመጀመሪያው ዓመት ብቻ በየሶስት ወሩ ደንበኞች ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚከፍሉት ታሪፍ ቢያንስ በ10 በመቶ ይጨምራል። አለም ባንክ ይፋ ባደረገው ሰነድ የኢትዮጵያ መንግሥት የአራት ዓመታት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ማጽደቁን አመላክቷል።
የኢትዮጲያ መንግስት በቀጣይም ውሃ፣ቴሌኮምና መሰል አገልግሎቶች ላይ ተመሳይ ማሻሺያዎችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተገደሉ‼️

በአርሲ አንድ ካህንን ጨምሮ አጠቃላይ 6 የሚደርሱ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ‼️

በአርሲ ሀገረ ስብከት አሰኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ ጠለታ ጨፋ ከተማ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ኦርቶዶክሳውያን በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ታውቋል።

ግድያው የተፈጸመው ከነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ከሞቱት በተጨማሪም 3 ሰዎች ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በታጣቂዎቹ የተገደሉትን ሰዎች አስከሬናቸውን ለማንሳትና ለመቅበር አስቸጋሪ በመሆኑ ከቤተክርስቲያኑ ራቅ ወዳለ ቦታ በመውሰድ የቀብር ሥርዓቱን ለመፈፀም ተገደዋል።

በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያንን ሲረዱ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው ሀብት ንብረታቸው መቃጠሉንና የአካባቢው ምእመናንም ቤታቸውን ትተው በዱር በስጋት ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የማራቶን አሰልጣኙ ገመዶ ደደፎ መታሰሩ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ የማራቶን ቡድንን በፓሪስ ኦሎምፒክ መርቶ ውጤት ያመጣው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ዛሬ ጠዋት የሲቪል ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋሉን መሠረት ሚድያ ሰምቷል።

ከውድድሩ በሗላ የሁለት ሚልዮን ብር ሽልማቱን አልቀበልም ያለው አሰልጣኙ የብዙዎች መነጋገርያ ሆኖ ነበር። እስሩ ከዚህ ጋር የተያያዘ መሆኑን ብዙዎች እየገመቱ ያሉ ቢሆንም በይፋ የተባለ ነገር የለም።

መሠረት ሚድያ የአሰልጣኝ ደደፎን ስልክ ደጋግሞ የሞከረ ቢሆንም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ማግኘት አልቻለም።

በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

መሠረት ሚድያ!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Update‼️

ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ጠዋት የተወሰደው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ አሁን ከመሸ ወደ ቤት መመለሱ ተነግሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ሲል ራሱን በራሱ በመጠየቅ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ

በመቐለ ከተማ ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር (GSTS) ለ3 ቀናት ያዘጋጀው ትግራይ ክልል መልሶ በማቋቋም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

በውይይት መድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታቸው ረዳ" ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ብሎ ራሱን በራሱ በመጠየቅና በመመለስ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል " ብለዋል።

" ያለውን መድረክ በመገንዘብ የመፍትሄ ሃሳብ በማስቀመጥ የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት አለበት " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሙሁራኑ ውይይት ማንኛውም ፓለቲካዊ ልዩነት ይኑር ችላ መባል እና መታለፍ የሌለባቸውን በመያዝ እንዲጠሩ መስራት ይጠበቅበታል " ሲሉ አስገዝበዋል።

ለ3 ቀናት ይቆያል በተባለው የውይይት መድረክ በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ ፣ ውይይትም ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከመላው ኢትዮጵያ ጨምሮ ፥ ከአፍሪካ ፣ አሜሪካ ፣ አወሮፓና ልሎች የዓለም ክፍሎች የተጋበዙ የትግራይ ሙሁራን በውይይት መድረኩ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተሰምቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የወደብ አማራጮችን ለማስፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው - ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

የወደብ አማራጮችን ለማስፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ባርኦ ሀሰን ከፋናቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ንግግሮች ማድረግ መቀጠሏን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከሯ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፈተናዎችን በጋራ ለማሸነፍ ያግዛል ብለዋል፡፡ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰጥቶ የመቀበል መርህ አዎንታዊ ምላሽ እየተገኘበት መሆኑንም አንስተዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

በተጨማሪም ወደቦች ላይ የሚስተዋለው ችግርን ለመቅረፍ ከጅቡቲ ጋር የጋራ ትብብር ባለስልጣን ለመመስረት ሂደቱ መጠናቀቁን ጠቅሰዋል፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ይህንኑ ያረጋገጠ ሲሆን ኢትዮጵያ በህጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ አስተማማኝ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል።

በተለይም ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ጋር የተፈጠሩ ልዩነቶች እስኪፈቱ ድርስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን እንደምትገፋበትም አምባሳደር ነብዩ ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 05:18:36
Back to Top
HTML Embed Code: