Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@sheger_press
የአዉሮፓ ህብረት ፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር" ሲል ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ አጠበቀ

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ መክፈል አለባቸውም ተብሏል


የአዉሮፓ ህብረት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር ሲል ወቅሷል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቁን አስታዉቋል።

ዳጉ ጆርናል ከአሶሴትድ ፕረስ ዘገባ እንደተመለከተው ፤ የአውሮፓ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ ለመስራት የሚፈጅባቸዉን ጊዜ በሶስት እጥፍ መጨመሩን ነዉ።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊያን በ15 ቀናት ዉስጥ ቪዛ ያገኙ ነበር የተባለ ሲሆን በዚሁ ዉሳኔ መሰረት ወደ 45 ቀናት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኢትዮጵያ መንግስትን በህገወጥ መንገድ በአዉሮፓ ይኖራሉ የተባሉ ዜጎችን እንዲመልስ ጫና ለመፍጠር ነዉ ብሏል ዘገባው።

ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከታዘዙ ሶስት ሰዎች መካከልም አንዱ ብቻ መመለሱ በህብረቱ የመንግስትን ተባባሪነት ጎድሎታል የሚለዉን ክስ ለማሳያነት ቀርቧል። ይህም በፈቃዳቸዉም ይሆን ካለፍላጎታቸዉ ህገወጦችን ለመመለስ የሚደረገዉን ሂደት አጓቶታል ብሏል።

በዚህ ዉሳኔ መሰረትም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የቪዛ ቀናቸዉም ቢያልፍ የአዉሮፓ ምድርን ለቅቀዉ እንደማይወጡ ህብረቱ ገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን ማቋቋሚያ ሲያጸድቅ ትግራይ አልተወከለችም የሚል ቅሬታ ማቅረቡን ኮሚሽኑ እንደገለጠ ሸገር ዘግቧል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህን ቅሬታ ያቀረበው፣ ኮሚሽኑ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።

የኮሚሽኑ አንዱ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ግን፣ በወቅቱ ሕወሃት በሂደቱ አልተሳተፈም ማለት ትግራይ አልተወከለችም ማለት አይደለም በማለት ለጣቢያው ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እስካሁን በትግራይ ክልል በይፋ ሥራ እንዳልጀመረ ይታወቄል።

ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አያይዘውም፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ላይ የሚፈጸሙ እንግልቶች እንዲቆሙ ኮሚሽን ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገልጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሹመት‼️

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለአብን ከፍተኛ አመራር ሹመት ሰጡ!

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር ለሆኑት ለአቶ መልካሙ ፀጋዬ ሹመት ሰጥተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ አቶ መልካሙ ጸጋዬን የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት አፈጻጸም ዙሪያ ዛሬ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ሥራው አስተባባሪዎች ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል።

ዐቢይ፣ የከተማዋ የመንገድ ኮሪደር ልማት በከተማዋ የላቀ ምቹ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመፍጠር ጥረቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ፣ አረንጓዴ ልማትን በማስፋትና መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል የሕዝቡን ጤና ለመጠበቅና የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያስችልም ዐቢይ ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ካንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማቱ በሚገኝበት ደረጃ ዙሪያ ከከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች ጋር አጠቃላይ ግምገማ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሰመጉ፣ መንግሥት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችና ታጣቂ ቡድኖች የሚፈጽሟቸውን "ግድያዎች"፣ "ሕገወጥ እስሮች" እና "ድብደባዎች" እንዲያስቆምና ወንጀል ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ አዲስ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሚያዚያ 6 እና 7 በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሰቡ ሲሬ ወረዳ 14 ነዋሪዎችን፣ ታጣቂዎች ደሞ በምዕራብ አርሲ ሽርቃ፣ ቃርሳ እና ኢተያ ወረዳዎች 5 ሰዎች መግደላቸውን ኢሰመጉ ገልጧል።

የፌደራሉና የክልል መንግሥታት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ “አፈናዎችን” እንዲያስቆሙና “የሰዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት" እንዲያስከብሩም ኢሰመጉ ጥሪ አድርጓል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድም፣ አማራ ክልል ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማጣራት ወንጀለኞችን በሕግ እንዲጠየቁ ለመንግሥት የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ ኢሰመጉ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር የተቋቋሙ አስተዳደሮች እስከ ሰኔ 30 መፍትሔ እንደሚያገኙ ጄነራል ታደሰ ተናገሩ


የትግራይን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ተጠቅለው የተቋቋሙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች እስከ ሰኔ 30/ 2016 ዓ.ም መፍትሔ እንደሚያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል።

ጄነራል ታደሰ ባለፉት ሁለት ቀናት የፕሪቶሪያ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት አተገባበር በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመከላከያ እና ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት መሰረት በማድረግ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የተናገሩት።

የአማራ ክልል ይገባኛል በሚላቸው እና የትግራይን ጦርነት ተከትሎ ክልሉ ጠቅልሎ እንደ አዲስ ያዋቀራቸው የደቡብ ትግራይ እና ጸለምቲ ወረዳዎች መፍትሄ ለማበጀት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ መደረሱን ጄነራል ታደሰ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአማራ ክልል በኩል ወልቃይት ተብሎ በሚጠራው ምዕራብ ትግራይ እንደ አዲስ የተቋቋመው አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ባለው ጊዜ መፍትሔ ይበጅለታል ብለዋል።

በዚህም ውይይት ላይ ትጥቅ መፍታትን አስመልክቶ የትኞቹ አስተዳዳራዊ መዋቅሮች መፍረስ እንዳለባቸው እና የተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚመለሱ ዝርዝር እቅድ የወጣ ሲሆን ይህንንም የሚቆጣጠረው እና የሚያረጋግጠው የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ እንደሚሆን ተገልጿል። ኮሚቴው መቀለ ላይ ቢሮ እንዳለው ከዚህ ቀደም ጄነራል ታደሰ መናገራቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ እንደገለጹት÷ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ታራሚዎችን ከመንግስት፣ ከህዝብና ከታራሚ ጥቅም አኳያ ሲመረምር ቆይቷል።

በተደረገው ምርመራም በአጠቃላይ የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡ 978 ታራሚዎች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ 926 ታራሚዎች ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግስት ቀርቦ የይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል 920 ታራሚዎች ከእስር የሚለቀቁ ሲሆን÷ስድስቱ ደግሞ የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው ናቸው።

ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት በነበራቸው ቆይታ በአግባቡ ስለመታረማቸው፣ ስለመታነጻቸውና ስለመልካም ባህሪያቸው ምስክርነት የተሰጠባቸው መሆኑንም አመልክተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ምስጋኑ አረጋ የአውሮፓ ኅብረት ካውንስል ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ ያሳለፈው የቪዛ ገደብ ውሳኔ "የማይጠቅም ውሳኔ" ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ሚንስትር ደዔታው በ"ኤክስ" ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት፣ ጉዳዩ በኢትዮጵያና አውሮፓ ኅብረት ግንኙነት ውስጥ "አዋኪ ጉዳይ መኾን ሊኾን አይገባውም" ብለዋል። አውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ጠንካራ አጋር መኾኑን የጠቀሱት ምስጋኑ፣ ችግሩ ባስቸኳይ ሊፈታ እንደሚገባው ገልጸዋል።

ኅብረቱ በአውሮፓ አገራት ውስጥ የመቆየት ፍቃድ በሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ላይ ከጣለው የቪዛ ገደብ በተጨማሪ፣ የዲፕሎማቲክና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዳይሰጣቸው አግዷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በአስቸጋሪ ኹኔታ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 180 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መልሷል።

ትናንት ከተመለሱት ፍልሰተኞች መካከል፣ 1 ሺህ 98ቱ ወንዶች፣ 79ኙ ሴቶች እንዲኹም ሦስቱ ጨቅላ ሕጻናት እንደኾኑ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።

228ቱ ተመላሾች ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ናቸው ተብሏል።

ኮሚቴው ከሚያዝያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት በጠቅላላው 13 ሺህ 900 ፍልሰተኞችን ከሳዑዲ ዓረቢያ መልሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ሰበር
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ታውቋል።

የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም።

ምንጭ፦ የማህበረ ቅዱሳን የፌስቡክ ገፅ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ያሳዝናል‼️

ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እየሄዱ የነበሩ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤትን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከል መረጃና ስታቲክስ ክፍል ኃረፊ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ እንደገለፁት በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዞሪያ ቀበሌ ሌሊት 11 ሰዓት 40 ከወላይታ ሶዶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ፒካፕ መኪና በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ባለሶስት እግር ባጃጅ ጋር ተጋጭቶ በውስጡ የነበሩ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤት በድምሩ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል።

በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።

ከሟቾቹ መካከል ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እያመራች የነበረች እናት እንደምትገኝበት ነው ኢንስፔክተር ታምራት የገለጹት። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ኢንፔክተር ታምራት ጠቁመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተጨማሪ‼️

ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድን ጨምሮ ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ታሠሩ

በቅርቡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለሚዲያችን ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተፈታች‼️

አርቲስት አዲስአለም ጌታነህ ከ21 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተፈታለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
They predicted yesterday the DUMP of Bitcoin
Already in the channel published the dates of the next BTC PUMP!

Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈
Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈
Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈

JOIN FAST! Only the first 1000 people will be accepted! 🔥
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ማስተር ካርድ ለአምስት ዓመት የሚቆይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት በተደረገው በዚሁ ስምምነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰጠውን የካርድ ባንክ አገልግሎት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለማስፋፋት እንደሚያግዘው ተነግሯል።

በተጨማሪም አዳዲስ የካርድ አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንደሚረዳም ተጠቁሟል።በዚህ የአምስት አመት ሰምምነት መሰረት የባንኩን ደንበኞች ፍላጎት በማሟላት ላይ የሚያተኩሩ እና አለም የደረሰበትን አዳዲስ አገልግሎቶችን በሀገር ውሰጥ በማስተዋወቅ ጥሬ ገንዘብ አልባ ማህበረሰብን ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንደሚያደርግ ይገመታል።

ማስተር ካርድ ከ210 ሀገሮች በላይ የሚሰራ አለማቀፍ የክፍያ አቀላጠፊ ድርጅት ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መስራት ከጀመረ እረጅም አመታት እንደሆነ ይታወቃል።
በአቃቂ የገበያ ማዕከል ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ 16 ንግድ  ሱቆች ወደሙ

ሚያዚያ 24 ቀን2016  ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ  ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ  ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል መውደማቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የእሳት አደጋዉን  ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ  ቦቴ  የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፎቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷል።

በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው  ላይ የደረሰ ጉዳት  የለም። አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ አንዱ ነው።

በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ መቆየቱንም አቶ ንጋቱ ጨምረው ነግረውናል።ኮሚሽኑ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ
ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ከዚህ ቀደም ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ እርምጃዎች አልተወሰዱም።

በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ዳጉ_ጆርናል
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"አንዱ ሰለ ሁሉ ሞተ።" (2ኛ ቆሮ ም. 5:14)

ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳቹ። አደረሰን።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁንልን።
2024/11/06 01:56:55
Back to Top
HTML Embed Code: