Telegram Web Link
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሁለት ጭንቅላት ያለው ህጻን ተወለደ።

በኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ ትላንት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ አንዲት እናት በተደረገላት የቀዶ ህክምና ከአንገት በላይ ሁለት ጭንቅላት (Dicephalic parapagus) ያለው ወንድ ልጅ፤ ክብደቱ 4.2 ኪ.ግ የሚመዝን በሰላም ተገላግላለች።

ልጁ የተወለደው በሲሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን በሆስፒታሉ የህጻናት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ቶኩማ ባይሳ የልጁን ቀጣይ ህይወት ለመወሰን ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል ሪፈር እንዲደረግ መወሰኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ቶኩማ አክለውም፥ እናትየው የመጀመሪያ ልጇ እንደሆነ ጠቅሰው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳለች ገልጸዋል።

ዘገባው የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
ጌታቸው ረዳ‼️

“ በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት “ - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር።

በዚህም ፤ “ የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም “ ብለዋል።

“ የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን “ ያሉት አቶ ጌታቸው “ ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው “ ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ “ ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል “ ሲሉም ገልጸዋል።

“ ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል “ ሲሉም አስገንዝበዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ “ በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን “ ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የባንኩን ስም እየጠሩ የሚሰሩ የሀይማኖት ሰባኪዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞክርበት የህግ አግባብ ካለ እንደሚያጣራ አስታወቀ

👉🏼 የባንኩ ፕሬዚዳንት " በጸሎት ገንዘብ እንዲበረክት እንጂ የሚጨመር ገንዘብ የለም" ብለዋል


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የባንኩን ሂሳብ ደብተር ረግጠዉ ፣ አላስፈላጊ እና አዋራጅ ሊባል የሚችል ድርጊት የሚፈጽሙ የሀይማኖት ሰባኪዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞክርበት አግባብ ካለ እንደሚያጣራ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለመንግስታዊዉ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ ተናግረዋል‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ቪዲዮዎችን መመልከታቸዉን ተናግረዉ በ 21ኛዉ ክፍለዘመን እንደዚ የሚያስብ ሰዉ ስለመኖሩ መገረማቸውን ተናግረዋል። በቅድሚያ ሀሰተኛ ቪዲዮ እንደመሰላቸዉ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ይህ ከሃይማኖታዊ ተግባር ያፈነገጠ እና የማይወክል መሆኑን አመላክተዋል።

"ሰርተህ ለፍተህ ያገኘኸዉ ገንዘብ እንዲበረክት መጸለይ እንጂ በጸሎት ሂሳብ ላይ የሚጨመር ገንዘብ እንደሌለ ህዝቡ መገንዘብ አለበት" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ጉዳዩ ህግ ካለዉ እና ሊፈታ ከቻለ ባንኩ ጉዳዩን እንደሚመለከተዉ በቃለምልልሳቸው ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ህዝቡ አይሳሳት ሲሉም አሳስበዋል።
የDV አሸናዎች ዛሬ ይታወቃሉ‼️

ከአጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ዛሬ ቅዳሜ  ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

ማስታወሻ:— የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 26/2016 ከምሽት 1:00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2025 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ  ይሄ dvprogram.state.gov/ESC/ ድረገጽ መሆኑን አስገንዝቧል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
 
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተፈታ‼️

ልጅ ያሬድ ተፈቷል💇‍♂

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ክብር የሚነካ ቃላት ተናገሮ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበረው ልጅ ያሬድ በዛሬው ዕለት ተፈቷል።

@sheger_press
@sheger_press
ለመላው የኢትዮ መረጃ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ   እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ  ይሆን ዘንድ እየተመኘን

በዓሉን ስናከብር ዓቅመ ደካሞችን በመርዳት ይሆን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

መልካም በዓል

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በ55,000 ብር ከገዛናው በሬ በ100,000 ብር የሚገመት ወርቅ ተገኘ።

በወላይታ ዞን በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ሻንቶ ከተማ ለትንሳኤ በዓል ለእርድ በ55,000 ብር ከተገዛው በሬ የተገኘው ወርቅ በ100,000 ብር ተሽጧል።

ከዚህ በፊት በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ ለገና ከታረዱት በሬዎች በ235,000 ብር የሚገመት ወርቅ መገኘቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ።

Via:- Bonga Ethiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን ኢሰማኮ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያቀረብኩት ጥያቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቀርቷል ብለዋል።

ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ምላሽ አላገኙም ካሏቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ "ሠራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለው የደመወዝ ክፍያ የኑሮ ዉድነቱን በፍጹም መቋቋም ያልቻሉ በመሆኑ ደመወዝ የገቢ የሥራ ግብር እንዲቀነስ ላቀረብነዉ ጥያቄ መንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ብሏል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተደነገገ ቢሆንም የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ በሚንስትሮች ምክር ቤት ባለመውጣቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያልተገባ መሆኑን ነዉ ማህበሩ ያስታወቀው።

በጦርነት ዘላቂ መፍትሒ ስለማይመጣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ግጭትና ጦርነት ቆሞ በዉይይት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች በድርድር እንዲፈቱ የጠየቀው ኢሰማኮ ለጉዳዩ አፅንኦት ይሰጠዉ ብሏል በመግለጫው።

[Capital]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሙዓለ ነዋይ ለማፍሰስ ማቀዱን በላከው መግለጫ መግለጡን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል።

ኩባንያው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ፣ አጠቃላይ የኔትዎርክ ማማዎችን ቁጥር ከ7 ሺህ በላይ ለማድረስ 5 ሺህ አዳዲስ የቴሌኮም ኔትዎርክ ማማዎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለመትከል አስቤያለሁ ማለቱን ዘገባው አመልክቷል። ኩባንያው ባኹኑ ወቅት 2 ሺህ 500 የቴሌኮም ኔትዎርክ ማማዎች በአገሪቱ ውስጥ አሉት።

1 ሺህ 500 ያህሉ የኔትዎርክ ማማዎች ኩባንያው ራሱ የተከላቸው እንደኾኑ ገልጧል ተብሏል። ቀሪዎቹ የኔትዎርክ ማማዎች፣ ኩባንያው ከኢትዮ ቴሌኮም በኪራይ የሚጠቀምባቸው ናቸው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሕወሃት ኃይሎች ከሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ውንጀላ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል።

የፈጥኖ ደራሹን ኃይል ውንጀላ "በጥብቅ እንደሚያወግዝ" የገለጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ይህን ውንጀላ ያሰማው ዓለማቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ነው በማለት አጣጥሎታል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ሕወሃት የፖለቲካ ፓርቲ በመኾኑ "የታጠቀ ኃይል ወይም ሚሊሺያ የለውም" በማለትም ምላሽ ሰጥቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ አያይዞም፣ ሱዳን በትግራዩ ጦርነት ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉን ስደተኞች ያስጠለለች እንደመኾኗ ትግራይ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ የምትገባበት ምክንያት ሊኖራት አይችልም ብሏል።

ኹለቱ ወገኖች ጦርነቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲቆጠቡና ጦርነቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“የህወሓት ወታደሮች” በሱዳን ግጭት ውስጥ ተቀጥረው እየተዋጉ ነው መባሉን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ

በኮማንደር መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ታጣቂዎች ለጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በማገዝ እየተዋጉ ነው ቢልም ህወሓት ሀሰተኛ ትችት ነው ብሏል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ካወጣው መግለጫ አዲስ ማለዳ እንደተመለክተችው የጀነራል አል ቡርሃን የሱዳን ታጣቂ ኃይል የውጭ ቅጥረኞችን ይቀጥራል የተባለ ሲሆን “ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ ጭካኔ ፈጽሟል” የተባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ኃይሎች አሁን ከአል ቡርሃን እና አጋር ታጣቂዎቹ ወግነው እያጠቁን መሆኑን በማስረጃ አረጋግጠናል ብሏል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ትላንት ባሰራጩት መግለጫ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወቀሳ “መሰረት ቢስ” ነው ያለ ሲሆን፤ ታጣቂ ኃይሉ በእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት አቅዶ ያዘጋጀው ትርክት ነው መባሉን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር መግለጫ እንደጠቀሰው ህወሓት “አንድ የፖለቲካ ድርጅት እንጂ የትጥቅ አደረጃጀት በፍጹም የሌለው እና የሚያዛቸው ታጣቂዎችም የሌሉት ስብስብ” ነው። የትግራይ ሕዝብ ከሱዳን ሕዝብ ጋር ያለው የጠበቀ ወዳጅነትም ይህን እንድናደርግ አይገፋንም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ መግለጹን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#DV 2025
የኢትዮጵያ ፕሬስ ነፃነት ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ 11 ደረጃዎች በማሽቆልቆል 141ኛ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

በየአመቱ የዓለም ፕሬስ ነፃነት ዝርዝር የሚያወጣዉ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (RSF) የኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ከ 180 ሀገራት ዉስጥ 141ኛ ደረጃ ላይ መመደቧን አስታዉቋል።

ይህ ድርጅት ትላንት ሚያዝያ 28 ፤ 2016 ዓ.ም. ባወጣዉ ሪፖርት "ከ 180 ሀገራት ዉስጥ ኢትዮጵያ 141ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ገልፆ ይህም ካለፈዉ የፈንጆቹ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ 11 ደረጃዎች ማሽቆልቆሏን አመላክቷል ።

የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነትን ምክንያት በማድረግ ደረጃዎችን የሚያወጣዉ ተቋሙ "በየሀገራቱ ያሉት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አውዶች፣ የህግ ማዕቀፍ እና የደህንነት ሁኔታ፤ ድርጅቱ ደረጃዎቹን ለማውጣት በጠቋሚነት የሚገለገልባቸው መመዘኛዎች" ናቸው።

በተያዘዉ ዓመት በሚዲያ ነፃነት ኤርትራ ባለፈዉ ዓመት ከነበነረችበት ደረጃ በስድስት በማሽቆልቆል 180 ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የጠቆመዉ ሪፖርቱ ሰሜን ኮሪያ ፣ አፍጋኒስታን እና ሲሪያ ከ 177 እስከ 179 ደረጃን መያዛቸውን አስታዉቋል።

እንደ ድርጅቱ ዝርዝር ከሆነ ኖርዌይ ፣ ዴንማርክ ፣ ስዊድን እና ኔዘርላንድ ከ 1 እስከ 4ኛ ደረጃን በመያዝ የሚዲያ ነፃነት ያለባቸው ሀገራት መሆናቸዉን አስመስክረዋል ።

(capital)
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከሀዋሳ አዲስ አበባ በሚበር አውሮፕላን ጭስ ቢታይም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

የበረራ ቁጥር ኢቲ 154 ዛሬ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ አውሮፕላኑ ውስጥ ጭስ ታይቷል።

ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ መጠየቁን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ራስ ገዝ የአገርነት እውቅና የመስጠት ሃሳብ እንደሌላት ለዲፕሎማቶች መግለጣቸውን ጠቅሰው የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት፣ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ተግባራዊ ሊኾን እንደተቃረበና በኹለት ወራት ውስጥ የመጨረሻው ስምምነት ሊፈረም እንደሚችል በቅርቡ መግለጣቸው አይዘነጋም።

ኾኖም የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌላንድ በኩል ለሚሰጡ መግለጫዎች በይፋ የሰጠው ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ የለም።
ዋዜማ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢትዮጲያ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ወስጥ የነበሩ ሱዳናዉያን በጥቃት ምክንያት መሰደዳቸዉ ተሰማ‼️

በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ስደተኞች በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካምፖች ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን የጥቃት ሰለባ ሆነዋል፡፡ሶስት ስደተኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከኮሜር እና ኦላላ ካምፖች የተሰደዱት ሰዎች ቁጥር 7,000 ሊደርስ ይችላል።

ሆኖም ግን ከካምፑ ተሰሰደዱ ስለተባሉት ሰዎች በገለልተኛ አካል አሃዙን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ስለ ክስተተ መግለጫ አልሰጠም። ነገር ግን በጸጥታ እጦት ቅሬታ ሳቢያ ካምፑን ለቀው የወጡ ስደተኞችን መኖራቸዉን እንደሚያውቅ አስቀድሞ መናገሩ ይታወሳል፡›፡ካምፑ ካለፈው አመት ነሃሴ ወር ጀምሮ በአካባቢው ሚሊሻዎች ከሰራዊቱ ጋር እየተፋለሙ ባለበት የኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ የአማራ ክልል ዉስጥ ይገኛል።

ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመሆኑ የበይነመረብ ግንኙነት ተቋርጧል።ስደተኞቹ እንዳሉት ካምፖች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በታጣቂዎች ጥቃት እየተፈጸመባቸው ሲሆን እገታ እየተለመደ መጥቷል።ከባለሥልጣናት ጥበቃ እጦት የተነሳ በዋናው መንገድ እና በአቅራቢያው ባለ ትንሽ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ እንዳደሩ አንድ ስደተኛ ተናግሯል።

“በድንኳኔ ብቆይ ምናልባት መጥተው በጥይት ሊመቱን ይችላሉ። በአደጋ ላይ እንዳለዉ ስለተሰማኝ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም” ፣ “በሌሊት በጣም አደገኛ ስለሆነ በዚያ ቦታ መቆየት አትችልም” ሲል አክሏል፡፡በሱዳን ጦር እና ተቀናቃኝ የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች (RSF) ጦርነት ከጀመረበት ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሱዳን ዜጎች ከሀገር ተሰደዋል።

ወደ 33,000 የሚጠጉት ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታዉቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ብዙ ዜጎቻቸውን በስቅላት የሚቀጡ ሀገራት እነማን ናቸው🤔

እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከሆነ የሞት ፍርድ ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ፍርዳቸው በስቅላት ወይም አንገታቸው ተቀልቶ የሚገደሉ እንዳሉም ተገልጿል፡፡

በ2022 ዓመት ብቻ 2 ሀገራት ዜጎቻቸውን በስቅላት ቀጥተዋል የተባለ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ መከሰት በሞት የሚቀጡ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓልም ተብሏል፡፡

ቻይና ብዙ ዜጎቿን በስቅላትበመቅጣት ከዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን በዓመት በአማካኝ 1 ሺህ ዜጎችን በስቅላት ቀጥታለች፡፡

ሌላኛዋ ሀገር ኢራን ስትሆን ከ570 በላይ ዜጎችን በስቅላት ስትቀጣ አፍሪካዊቷ ግብጽም ዜጎቿን በስቅላት ከሚቀጡ ሀገራት መካከል ተጠቅሳለች፡፡
ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካ እና ሲንጋፖር በተጨማሪነት የተጠቀሱ ሀገራት ሲሆኑ ሀገራቱ ዜጎቻቸውን በሞት እየቀጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/05 23:27:04
Back to Top
HTML Embed Code: