Telegram Web Link
በቤት ኪራይ ውድነት የተቸገሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ በተማሪዎች ዶርም “በጊዜያዊነት” እየኖሩ ነው ተባለ‼️

ትግራይ ክልል በሚገኘው መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑን ገለጹ። የዩኒቨርስቲው መምህራን በክልሉ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል። 

የዩኒቨርሲቲው መምህራን “የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል” የሚሉ ማመልከቻዎችን ለተቋሙ ማስገባት የጀመሩት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ቢሆንም፤ ካለፈው ሶስት ወር ወዲህ ግን በርካታ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለተቋሙ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ ማቅረባቸው ተነግሯል።

መምህራኑ ለዩኒቨርሲቲው ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተገደዱት፤ በጦርነት ወቅት ሳይከፍሉ የቀሩትን “ውዝፍ የቤት ኪራይ” አሁን እንዲያመጡ እየተጠየቁ በመሆኑ እና በክልሉ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ነው ብለዋል።(#ኢትዮጵያኢንሳይደር)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
YesCoin‼️

ሇላ እንዳይቆጫቹ አሁንኑ ጀምሩት።

List መሆኑ የተረጋገጠ ኤርድሮፕ ነው።

በዚ Link ጀምሩት👇👇
https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=PP9BDi

ለበለጠ መረጃ ይህን ቻናል
ይቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
የጨረቃ ቤቶች በአዲሱ የአከራይ ተከራይ አዋጅ የምዝገባ  ስርአት ውስጥ እንደማይካተቱ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እወቁልኝ ብሏል።(wasu)

@sheger_press
@sheger_press
በጎንደር ከተማ ከ12 ሰዓት በኋላ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ማሽከርከር ተከለከለ

በጎንደር ከተማ የሰው እገታ ወንጀል እየተባበሰ በመምጣቱ ምክንያት ከዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ከ12 ሰዓት በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ መንቀሳቀስ እንደማይችል የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የመምሪያው ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ በቡድን በሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የሰው እገታ ወንጀል እየጨመረ መጥቷል፡፡

ይህን የማህበረሰቡ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ለመቀነስ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ ወንጀሎች በከተማዋ ሲፈጸሙ ተባባሪ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 27 ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያነሱት ረዳት ኮሚሽነሩ ተሽከርካሪዎቹ ታርጋ የሌላቸው መኾኑንም ጠቁመዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መካከል አራቱ በእገታ ወንጀል ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተሽከርካሪዎች መኾናቸውን አስታውቀዋል።

በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የከተማው ማህበረሰብ ቀና ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

የብሎክ አደረጃጀትን በማጠናከር ቤት ለቤት የሚፈፀመውን የስርቆት ወንጀል ለመቀነስ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባልም መባሉን ከፋና ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@sheger_press
@sheger_press
#Tigray

" ከዚህ (ከሰላማዊ) ውጭ  ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

36ኛው ዓመት " የትግራይ የሰማእታት ቀን " ዛሬ ሰነ 15 ቀን 2016 ዓ/ም በመቐለ የሰማእታት ሀውልት ተከብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ልጆቻችን በአጋቾች ለሞት እየተጋለጡ ፣ ተፈናቃዮች በመቆያ መጠለያዎች በፀሀይና በብርድ እየተሰቃዩ ባሉበት ወቅት የሰማእታት ቃልና አደራ በተሟላ መልኩ እያከበርን ነው በማለት ማምለጥ አይቻለንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የሰማእታት ቃል አክበረናል የምንለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

" የሰማእታት ቃል ማክበር ማለት በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት እንዲከበር መስራት  ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ጥቅም መዋደቅ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አንዳንዶቻችን ይህንን በመዘንጋት ለስልጣንና ለሃብት ስንባላ መታየት አሳፋሪ ነውና ከዚሁ መውጣት ይህንን መቀየር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው " ተፈናቃዮችን በጀመርነው ሰላማዊ መንገድ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በአንድነት መንፈስ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት አለብን " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።
በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከባድ የጦር መሳሪያዎችንና ታንኮችን በመያዝ ከትናንት በስተያ ወደ ሱማሊያ ግዛት ዘልቀው እንደገቡ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ከኢትዮጵያ የተነሱት ወታደሮች ያቀኑት፣ ሒራን ወደሚባለው የሱማሊያ ግዛት እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የኢትዮጵያዊያኑ ወታደሮች ተልዕኮ ምን እንደኾነ ለጊዜው ግልጽ እንዳልኾነም የዜና ምንጮቹ ጠቅሰዋል።

የሱማሊያ ጦር ሠራዊት ባለፉት ኹለት ዓመታት ያገኛቸውን ወታደራዊ ድሎች፣ አልሸባብ ባለፉት ጥቂት ወራት ሙሉ በሙሉ እንደቀለበሳቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የአሜሪካ ዜና ምንጮች ሰሞኑን ዘግበው ነበር። የሱማሊያ ባለሥልጣናት ግን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ግምገማ የተሳሳተ በማለት እያጣጣሉት ይገኛሉ።
#ዋዜማ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአባታቸውን መኪና ጥሩምባ ለናፈቁ ልጆች የእድር ጥሩምባ ማሰማት ትልቅ በደል ነው!

በአማራ ክልል በስሜን ጎንደር ከማክሰኝት እንፍራዝ ባለው መንገድ በተከታታይ 2ቀናት 2 ሾፌሮች በዘራፊዎች ተገለዋል አንድ ሾፌር በጥይት ቆስሎ ህክምና ላይ ይገኛል 2 አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል በዚሁ እለት ጠዋት የህዝብ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎችም ተዘርፈዋል ::
ጎንደር ከተማ ብልኮ ላይ የተወለደው የነዳጂ ቦቴ ሾፌር የሆነው ከጂቡቲ ነዳጂ ጭኖ ወደ ትውልድ ከተማ ለመድረስ ሲገሰግስ ከትውልድ ቀየው መዳረሻ ላይ በ 15/10/2016 በጥይት ህይወቱን ሊያጣ ችሏል ::

ይህ ወንድማችን ናፍቆቱን ቤተሰቡ ጋር ለመወጣት በዙር የደረሰውን ወደ ትውልድ ቀየው ጭኖ የመምጣት ልጆቹን በአካል የማግኘት ዕድሉን እያመሰገነ ለቤተሰቡ ግብአቱን ለጎረቤቱ ከሰሉን ለአብራኩ ክፋዮች ብስኩቱን ይዞ በሚጓዝበት ከጂቡቲ ጎንደር 1000 ኪሎ ሜትሩን ለመጨረስ 970 ውን ተጉዞ ከቤቱ ለመድረስ 30 ኪሎ ሜትር ሲቀረው በጥይት ህልሙ በአጭሩ አስቀርቶታል ሲል የሾፌሮች አንደበት ዘግበዋል።

ይህ የ2 ልጆች አባት የሆነው ከጂቡቲ ነዳጂ ጭኖ በመምጣት ከልጆቹ ጋር ለመገናኘት የጓጓው ልጆቹን እየደወለ እዚህ ደርሻለሁ ጎንደር ቀርቢያለው በማለት በስስት በብዙ ዝግጅት ለሚጠብቁት ልጆቹ እየተናገረ ባለበት ሂደት በጥይት ነፍሱን ነጥቆ አባታቸውን ለማቀፍ ለጓጉ በጉጉት ለሚጠብቁ ልጆች ሬሳ ማስታቀፍ የግፎች ሁሉ ግፍ ነው ሲል የሾፌሮች አንደበት ገፅ ዘገባ ተመልክተናል።
አንድ ቤት ለገዛ አንድ ቤት በነፃ

‼️ከ 300ሺ ብር ጀምሮ

📞0961478081

📍አድራሻ - በደማቋ ለቡ ማብራት-ሀይል

⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ዋጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!

💸5% ቅድመ ክፍያ ብቻ
💸 50% የባንክ ብድር አገልግሎት



👉 እንደ ፍላጎቶ ሙሉ በሙሉ ያለቁ(fully-finished) ወይም እርሶ በሚፈልጉት መልኩ የሚጨርሱትን(semi-finished) ሆኖ መረከብ ይችላሉ።

🛌እስቱድዮ - 56 - 58 ካሬ
   ባለ 1 መኝታ - 77.7 - 98 ካሬ
   ባለ 2 መኝታ - 123 - 134 ካሬ
   ባለ 3 መኝታ - 146 -157 ካሬ
   ባለ 4 መኝታ - 177 - 186 ካሬ
የንግድ ሱቆች - 20- 900 ካሬ

👉ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ ከ 8% - 25%  ቅናሽ አድርገናል

📞0961478081
እስራኤል በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ100 በላይ ፍሊስጤማውያንን መግደሏ ተነገረ!!

የእስራኤል ጦር በ24 ሰዓታት ውስጥ በጋዛ ሰርጥ በተፈጸማቸው ጥቃቶች ከ100 በላይ ፍሊስጤማውያን መገደላቸውን በሃማስ የሚመራው መንግስት ባለስልጣናት አስታወቀዋል።

የእስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ሰርጥ በፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 42 ፍሊስጤማውያን መሞታቸውንም ነው በሃማስ የሚመራው መንግስት መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት። የእስራኤል ጦር የአየር ድብደባ ከፈጸመባቸው ቦታዎች መካከል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ከሚገኙ ታሪካዊ የስደተኞች መጠለያ መካከል አል አሻ የሚገኙ ቤቶች ሲሆኑ፤ በዚህ ስፍራ 24 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ሌላኛው የእስራኤል ጦር ኢላማ የነበረው በአል ቱፋህ የሚገኘው መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ላይ ሲሆን፤ በዚህ ስፍራም 18 ሰዎች መሞታቸው ነው የተገለጸው። የእስራኤል ጦር ጥቃቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫው፤ የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች በሁለት የሃማስ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እና በዚህም የሃማስ ወታደራዊ ኢላማዎችን ማውደሙን አስታውቋል። በሃማስ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ላይ በተፈጸመው የአየር ድብደባ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ በቅርቡ እለቃለሁም ብሏል የእስራኤል ጦር በመግለጫው። ሃማስ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የእስራኤል ጦር መታደራዊ መሰረት ልማቶቹን ስለ መምታቱ ያለው ነገር የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
18 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስአበባ ወደ ፍቼ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ ባጋጠመ የትራፊክ አደጋ የ 5 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ አምስት ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

18 መንገደኞችን ከአዲስአበባ አሳፍሮ ወደ ፍቼ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 28787 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እና ከጎጃም ወደ አዲስአበባ ከሰል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3B 33442 የሆነ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተዉ ፥ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዉ 50 ሜትር ጥልቀት ወዳለዉ ገደል ዉስጥ ገብቶ አደጋዉ መድረሱን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ኩመላ ደንደና ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የደረሰዉ አደጋዉ ተሽከርካሪዎቹ በሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ ወረዳ ቦሶጤ ጃቲ ቀበሌ ዱበር ወንዝ ጋር ሲደርሱ በመጋጨታቸው የተከሰተ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። በአደጋዉ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል እንዲሁም ሌሎች ስድስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የተባለ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አደጋ አድርሷል የተባለዉ የአይሱዙ አሽከርካሪ ወዲያዉኑ ከአካባቢው ተሰዉሮ የነበረ ቢሆንም ጫንጮ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል ። የአደጋዉ መንስዔ ፍጥነት መሆኑን የጠቀሱት የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊዉ በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

በአደጋዉ ሁለት ወንድ እና ሶስት ሴቶች ህይወታቸዉን ያጡ ሲሆን ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠማቸዉ ሰዎች ደግሞ በዉጫሌ እና ፍቼ ሆስፒታሎች ላይ ህክምና እያገኙ ይገኛል ሲሉ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ኩመላ ደንደና ጨምረው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Hamster‼️

ላስታውሳቹ ሀምስተር ኤርድሮፕ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት።

List መሆኑ የተረጋገጠ ትልቅ ፕሮጀክት ነው።

በjuly ወር ይጠናቀቃሉ ተብሎ ከተገመቱት አንዱ ኤርድሮፕ ነው።

ጠንክራቹ ስሩ
perhour ራቹን አሳድጉ ቢያንስ 1M አሳልፉት።

ያልጀመራቹ ካላቹ በዚ ጀምሩ👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_Kombat_bot/start?startapp=kentId7308161274
አማኑኤል ተለቋል

ለሁለት ወራት ያኽል በእስር የቆየው አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ዛሬ ከእስር ተለቆ ወደቤቱ ገብቷል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በመላዉ ኢትዮጲያ በቀጣዩ ዓመት 2.5 ሚሊዮን ኮንዶም በነጻ እንደሚከፋፈል ተነገረ

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ታማሚ ከሆኑት መካካል ራሳቸውን የሚያውቁት 84 በመቶ ብቻ እንደሆነ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ኤኤች ኤፍ ኢትዮጵያ በኤች ኤቪን  በመከላከል ዙሪያ በቅዱስ ጳውሎስ፣ አለርት ጨምሮ በ17 የመንግስት ተቋማትን  እንዲሁም በራሱ ኤ ኤች ኤፍ አዲስ የጤና ተቋም ካሉ  3600 የኤች አይቪ ታማሚዎች  ጨምሮ 60 ሺህ የኤች አይቪ ህሙማን  በማገዝ ላይ እንደሚገኝ  የኤኤችኤፍ ካንትሪ ዳይሬክተር   ዶክተር መንግስቱ  ገ/ሚካኤል በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡በአሁን ሰዓት የኤች አይ ቪ ቫይረስ በአዲስ መልኩ እተስፋፋ ያለ መሆኑን ጠቅሰው  ወጣቶች በተለየ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ይሰሩ የነበሩ  የኤች አይ ቪ   መከላከል ስራዎች  በጣም  እየቀነሱ መሆናቸው እና  ይሰጠው የነበረዉ ትኩረት በመቀነሱ በተለይም እድሜያቸው ከ15 እስከ 35 ዓመት ያሉት ለኤችአይቪ ኤድስ  ይበልጥ ተጋላጭ እየሆኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ከህክምና  እንዲሁም ከሰው መደበቃቸው እንዲሁም ወደ ጤና ተቋም አለመምጣት ፣  ህክምና ማቋረጥ  እና የኤችአይቪ ህክምና ምርመራ ያደርጉ ሰዎች  በስፋት ባለመኖራቸው በትክክል ያለው  የታማሚ ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ  እና ይህም  ለስራው ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን አንተዋል ፡፡ በመሆኑም ባለፈው ዓመት ብቻ በተደረገ ጥናት የኤች አይ ቪ ታማሚ ከሆኑት ውስጥ  84 በመቶ ብቻ የሚሆኑት  ራሳቸውን ያወቁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

Dagu
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
YesCoin‼️

100% የተረጋገጠ ነው

ኋላ እንዳይቆጫቹ አሁንኑ ጀምሩት።

List መሆኑ የተረጋገጠ ኤርድሮፕ ነው።

በዚ Link ጀምሩት👇👇

https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=D7siYr

ስለ አሰራሩ ይህንን
ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 175 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ከተመላሾቹ መካከል፣ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ 20 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል።

ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ከ49 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያዊያን ተመልሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ፣ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ኹሁኔታ ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች በሚያቀርቡለት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ፣ የቋሚ ኮሚቴዎቹን ሪፖርት መርምሮ ድምጽ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበለት የውጭ ባንኮች በአገሪቱ እንዲሠማሩ በሚፈቅደው የባንክ ሥስራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ጭምር ተወያይቶ ለዝርዝሩ እይታ ለቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካ፣ በኢትዮጵያና ሱማሊያ መካከል በባሕር በር ዙሪያ የተፈጠረው "ፖለቲካዊ ውጥረት" እና "ውጥረቱ በጋራ የጸጥታ ጥቅሞች" ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ "በእጅጉ እንዳሳሰባት" አስታውቃለች።

ትናንት በሱማሊያ ወቅታዊ ኹኔታ ዙሪያ በመከረው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ልዑክ አምባሳደር ሮበርት ውድ፣ አሜሪካ የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር አፍሪካ ኅብረትና ሌሎች አጋሮች የያዙትን አቋም ትደግፋለች ብለዋል።

አምባሳደሩ፣ በኹለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ማርገቢያው መንገድ ንግግር እንደኾነም አውስተዋል። ቀጠናዊ ውጥረቶች፣ ከአልሸባብን ጋር በሚደረገው ውጊያ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ መውጣት በኋላ ተተኪ ተልዕኮ በማሠማራቱ ሂደትና በአገር ግንባታ ጥረቶች ላይ እንቅፋት መኾን እንደሌለባቸውም አምባሳደሩ አውስተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ኢህአፓ መሪና ሌሎች በሚገኙበት መዝገብ የተከሰሱ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ እና በሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ከእሥር እንዲለቀቁ የሰጠውን ብይን አጸና።

የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ በአዋሽ አርባ ታሥረው ከነበሩ 17 ሰዎች መካከል፣ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ. ም ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ዘጠኝ ግለሰቦች የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባለፈው ሰኞ በገንዘብ ዋስትና እንዲወጡ ወስኖላቸው ነበር። በዚሁ መሠረትም፤ ለአምስቱ ተጠርጣሪዎች ሰላሳ ሺህ ብር፣ ለአራቱ ደግሞ የሃያ ሺህ ብር ዋስትና ቢከፈልም በእሥር ቆይተዋል። በተመሳሳይ ዜና "እብደት በሕብረት" የተባለው የመድረክ ተውኔት ተዋናይ አመኑኤል ሀብታሙ፣ አዘጋጁ ዳግማዊ ፈይሳ እና ሌሎችም ተጠርጣሪ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ባለፈው ሐሙስ የዋስትና መብታቸው ቢከበርም ከቀናት ቆይታ በኋላ ትላንት መለቀቃቸውን ዶቼቬለ ዘግቧል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተሽከርካሪ ሰርቃ የተሰወረችው ግለሰብ በሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች
***
ተጠርጣሪዋ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቢጫ ፎቅ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከቤተል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወቅቱ በግምት ከጠዋቱ 12:30 ሰዓት ገደማ የግል ተበዳይ በስፍራው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B32912 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪያቸውን መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ ሞተር አስነስተው እያሞቁ የነበሩ ሲሆን ወደ ስራ ለመሄድ ጃኬት ሊደርቡ ወደ ቤት በገቡበት ቅስፈት ተሽከርካሪያቸውን ከቆመበት ቦታ እንደሌለ አረጋግጠው ለፖሊስ ሪፖርት ያደርጋሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አቤቱታው ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ተሰውሮ የነበረውን ተሽከርካሪ ለማግኘት ግማሽ ቀን በፈጀ ጠንካራ ክትትልና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ተጠርጣሪዋን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር አውሏታል።

ግለሰቧ የግል ተበዳይ ወደቤት በገቡበት ቅስፈት ተሽከርካሪውን አስነስታ ብትሰወርም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ልዩ ቦታው ሰሚት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውላለች ። የተለያዩ ዘዴዎችንን በመጠቀም የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሁሉም ስው ኃላፊነት መሆኑን ያሳሰበው ፖሊስ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መኪናቸውን አቁመውና የተሽከርካሪውን ቁልፍ በውስጡ ትተው በሚሄዱበት አጋጣሚ ለተመሳሳይ የስርቆት ወንጀል ሊዳረጉ ስለሚችሉ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል

(ዘገባ ፦ ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ -አ/አ ፖሊስ)

@sheger_press
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በሚገኙ እስረኞች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት ታራሚዎች መጎዳታቸው ተነገረ

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ባለፈው ቅዳሜ በእስረኞች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት ሳቢያ፤ ቢያንስ አምስት ታራሚዎች መጎዳታቸውን የእስረኛ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረዉኛል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በዕለቱ ግጭት እንደነበር ቢያረጋግጥም፤ በክስተቱ “ቀላል ጉዳት የደረሰበት አንድ ታራሚ ብቻ ነው” ሲል አስተባብሏል።

ግጭቱን ተከትሎ በማረሚያ ቤቱ ሆነው የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ጋዜጠኞች እና ሌሎች  እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ መደረጉን የእስረኞቹ ቤተሰቦች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤቱ ግጭት ተቅስቅሶ የነበረው፤ ከሁለት ቀን በፊት ጠዋት ሶስት ሰዓት ገደማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ልጃቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደታሰረ የጠቀሱ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ ቅዳሜ ጠዋት በቤት ውስጥ እንዳሉ “የመሳሪያ ተኩስ ድምጽ” መስማታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በድንጋጤ ውስጥ ሆነው ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ማረሚያ ቤት አቅጣጫ ሲሄዱ፤ በአቅራቢያው ባሉ መንገዶች “በፓትሮል የመጡ” በርካታ የፌደራል ፖሊሶች መመልከታቸውን አስረድተዋል።

በማረሚያ ቤት የታሰረ የቤተሰብ አባላቸውን ለመጠየቅ በዕለቱ በስፍራው ተገኝተው የነበሩ የዓይን እማኝም ይህንኑ አረጋግጠዋል። “የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ማረሚያ ቤቱን ዙሪያውን ከበውት ነበር” የሚሉት እኚሁ የዓይን እማኝ፤  “ጋሻ ነገር የያዙ፣ ሄልሜት ያደረጉ፣ የታጠቁ፣ ዱላ የሚመስል ነገር የያዙ የአድማ በታኝ ፖሊሶች” በማረሚያ ቤቱ መግቢያ አካባቢ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።
(Ethiopian insider)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/06/26 04:44:25
Back to Top
HTML Embed Code: