Telegram Web Link
በመዲናዋ በመፍረስ ላይ ያሉ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ" ናቸው - #የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው #ከአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት የሚያሟሉ ባለመሆናቸው" ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የቅርስ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁሉ የተመዘገቡ መኖራቸውን አስታውሰው፤ በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልክ የቅርስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት የተመዘገቡ በቅርስነት የሚቀጥሉ ሲኖሩ በመመሪያው መሰረት መስፈርቱን የማያሟሉ ደግሞ የማይቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከቀናት በፊት ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት የቀደመ ስያሜና አገልግሎታቸው እንዲቀጥል እንደሚደረግ ማስታወቁን ፕሬስ ድርጅት መዘገቡ ይታወሳል።

ቤቶቹን በቅርስነት ለመመዝገብ ያላቸው ታሪክ፣ አሁን ያሉበት ውጫዊ እና ውስጣዊ ገፅታ፣ እድሜያቸው፣ አርክቴክቸርን ጨምሮ በርካታ መስፈርቶች መቀመጣቸውን ገልጸዋል። በተቀመጡት መመዘኛዎች መሰረት ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጣ በቅርስነት እንደሚመዘገብ እና በአንጻሩ ከ50 በታች የሆነ ቤት ቅርስ ተብሎ ሊመዘገብ እንደማይችል ጠቁመዋል። ለየሀገር ከፍተኛ ትርጉም ያላቸውን ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር በኮሪደር ልማቱ የሚፈርሱ ቤቶች ላይ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ተገልጿል።
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።

በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።

ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦
ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ሌለው ውሳኔ የተላለፈበት ጉዳይ የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ላይ ሲሆን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።

ከዚህ በተጨማሪ " የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል " ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ፦
- ለጎዳና ህይወት ፤
- ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል።

Via : tikvahethiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ ዜና‼️ ሐዋሳ

በትራፊክ አደጋ የበርካታ ሰው ሕይወት አልፏል

ዛሬ 9:00 ሰዓት አከባቢ በሐዋሳ ከተማ ከሐዋሳ የሚጓዘው ዶልፊን መኪና በተቃራኒ ከሚመጣው ቅጥቅጥ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው የበርካታ  የተሳፋሪዎቹ ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

ከባድና ቀላል የሚባል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች ወደ ሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የሟቾቹን መጠን እስካሁን ግልፅ ያልተደረገ ቢሆንም የሆስፒታል ምንጮች ከ14ሰዎች በላይ ህይወት ማለፉን ገልፀዋል።

ከፖሊስ ኮሚሽን የተሟላ መረጃ ሲደርሰን የሚናቀርብ ይሆናል። በአደጋው ምክንያት በደረሰው አደጋ ህወይታቸውን ላጡት ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?

ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ከተዘረዘሩ ድንጋጌዎች ውስጥ፤ “የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል ዘመንን” የሚመለከቱት የሚጠቀሱ ናቸው።

“የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም” ሲል የደነገገው አዋጁ፤ ይህ የተደረገበትን ዋነኛ ምክንያት በማብራሪያው ላይ አስፍሯል።

“የአዋጁ ዓላማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ በመሆኑ፤ [ውሉ] ከሁለት ዓመት ያነሰ ቢሆን አከራዩ ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ ላይሆን ስለሚችል፤ ተከራይ በየጊዜው በቀጣይ ስለሚከራየው ቤት በመጨነቅ የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ያደርገዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ አትቷል። “ከሁለት ዓመት ያለፈ ዘመን ይኑረው ቢባል ደግሞ የአከራይን መብት እንዳይጫን፤ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የውል ዘመኑ ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንዲሆን” መደረጉን የአዋጁ ማብራሪያ አስገንዝቧል።

“አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ከሁለት ዓመት በታች የተደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች ላይ ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይሆን፤ በውላቸው ላይ ያጸደቁት ቤት ኪራይ የውል ዘመን ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል” ሲል ማብራሪያው አክሏል። ከዚህ በተጨማሪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ፤ የአንድ ቤት ባለቤትነት “በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት” ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው “ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራይ በመስጠት ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ እንደሚቻል ማብራሪያው” ደንግጓል።(ኢትዮጵያ-ኢንሳይደር)

 
በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የቀጠሉ ግጭቶችና የመብት ጥሰቶች በጣም እንዳሳሰቧቸው 43 አገራት ትናንት ለተካሄደው 55ኛው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ባስገቡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል።

ኹሉም የግጭቶች ተሳታፊ ወገኖች በንግግር ሰላምን እንዲሽቱና በአገራዊ የውይይት ሂደቱ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

አገራቱ፣ በኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ለማስፈን ተዓማኒነት ያለው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲና ተጠያቂነት አስፈላጊ መኾኑንም አውስተዋል።

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፉ፣ እውነተኛ ተጠያቂነትን፣ እውነት አፈላላጊነትን፣ ካሳ እና ጥሰቶች ድጋሚ ላለመፈጸማቸው ማረጋገጫ መስጠትን ማካተት እንዳለበትም አገራቱ አሳስበዋል። (wazema)

@ethio_mereja_news
ጁምዓና ከተራን ጨምሮ አራት ቀናት ሥራ ዝግ ሆኖ እንዲከበሩ ጥያቄ ቀረበ!!

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ መቅረቡን ሪፖርተር አስነብቧል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና፣ የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ውይይት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ምሁራንና ሌሎች ተቋማት ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹ ምን ጥያቄ አቀረቡ?

- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ በእስልምና አንድ ሰው 3 ተከታታይ ጁምዓ ካልተገኘ በመናፍቅነት የሚያስፈርጅ ከባድ ጉዳይ በመሆኑ፣ ዓርብ (ጁምዓ) ቀን ሥራ ዝግ እንዲሆን፣ ወይም ደግሞ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ከአምስት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት ተኩል በአዋጁ መካተት አለበት ብለዋል።

- ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያሪክ የሕግ መምርያ ኃላፊ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት፣ እየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ ሄዶ መጠመቁን የሚያሳየው የቃል ኪዳኑን ታቦት በመያዝ ጥር 10 ቀን የሚከበረው ከተራና ከጥምቀት በኋላ ጥር 12 ቀን የሚከበረው ቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ከሥራ ዝግ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

- በተጨማሪም የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ታስቦ ከመዋል ይልቅ ከሥራ ዝግ ሆኖ መከበር ይገባዋል ያሉት ደግሞ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ናቸው፡፡

የተሰጡ አስተያየቶች ረቂቅ አዋጁን ለማጎልበት እንደሚያግዝ ሲገለፅ፣ አዋጁ ኢትዮጵያውያንን እንዲመስል ዘላቂነት ያለው ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር አባረረች

👉🏼በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችንም ዘግቻለሁ ብላለች


ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን አስታዉቃለች።

ሶማሊያ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የገጠማትን ዉዝግብ ተከትሎ የተለያዩ ዲፕሎማያው እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ሮይተርስ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ሶማሊያ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር ያባረረች ሲሆን ለውሳኔው መነሻ የሆነው ደግሞ ከሶማሊላንድ ጋር ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ባደረገችው የወደብ ስምምነት ምክንያት ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ሶማሊያ ፤ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችንም ዘግቻለሁ ብላለች።

@ethio_mereja_news
የራይድ አሽከርካሪውን ገለው መኪናውን ይዘው ተሰወሩ!!

ሶፎንያስ አስራት ይባላል የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ ለሊት 8 ላፍቶ አካባቢ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ኖሆም ሆቴል አካባቢ የሰፈሩ ስም ላፍቶ ቦሌ ሚካኤል ውሰደን ብለውት ጓደኞቹን ደርሼ መጣው ብሎ እንደወጣ በዛው ቀረ።

በማግስቱ እናቱ ስልኩ ላይ ስደውል አይሰራም ጓደኛው ጋር ስደውል ቦሌ ሚካኤል ብሎ እንደወጣ እና እንዳላገኘው ይነግራታል።

የፈለገ ነገር ቢፈጠር ከእናቱ ጋር ይደዋወል ነበር የልጇ ደብዛ መጥፋት ያስጨነቃት እናት ቦሌ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ትጠይቃለች የተመዘገበ ነገር ካለ እናሳውቅሻለን ይሏትና ተመልሳ ላፍቶ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ጠየቀች እነሱም ተመሳሳይ ነገር ነገሯት እና የአቃቂን ቃሊቲን ስልክ ይሰጧታል።

ስደውል ስልኩን ለሌላ ሰው ስጪ ብለው ያለውን ነገር ማለትም ወጣቱ መገደሉን እና አስክሬኑ ማሰልጠኛ አካባቢ እንደተገኘ እንዲሁም ለምርመራ ጳውሎስ እንደተወሰደ ይነግሯታል።

ዛሬ 5 ሠሀት አካባቢ አስክሬን ተቀብለው ወደ መኖርያ ቤት ወደ ላፍቶ ኮንደሚኒየም ወሰዱት ገዳዮቹ አልተገኙም መኪናውንም ይዘው መሠወራቸውን የሟች ሶፎንያስ የቅርብ ወዳጆች መረጃውን አድርሰዋል።(የኔታ ቲዩብ)

@sheger_press
@sheger_press
የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ ነው"ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ፣ ሰሞኑን ትግራይ ክልል ከአማራ ክልል ጋር በሚወዛገብባቸው አካባቢዎች የሚያሳየው አዝማሚያ “ተገቢነት የሌለው" እና የግጭት ማቆም ስምምነቱን የሚጥስ ነው በማለት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል፣ የአስተዳደር ወሰኖችን በኃይል ለማስከበር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለትግራይ ሕዝብ አይበጅም ብለዋል።

ዶ/ር ለገሠ ይህን የተናገሩት፣ በራያ አላማጣ አካባቢ ባንዳንድ ቀበሌዎች ውስጥ በትግራይ ኃይሎችና ባካባቢው ታጣቂዎች መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች መካሄዳቸውን ተከትሎ ነው።

የአማራ ክልል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰሞኑ ከወሰን ጋር ተያይዞ እርስ በእርስ በሚያወጡት መግለጫ እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል።

በመግለጫው “ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በኩል በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚታየው አዝማሚያ ተገቢነት የሌላውና የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ ነው” ብለዋል።

ሁለቱ ክልሎች በመግለጫ እርስ በእርስ ከመወቀቃቀስ ይልቅ በአብይ ኮሚቴ ታግዘው በጠረጴዛ ዙሪያ ችግሮቻቸውን መፍታት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ወደ ኦሮሚያ ክልል የተመለሱት ተፈናቃዮች አሁንም ድረስ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ከአማራ ክልል ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን  ኦሮሚያ ክልል የተመለሱት ተፈናቃዮች አሁንም በፀጥታ ችግር ሳቢያ ወደ ቤታቸው መመለስ አለመቻላቸውን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

ተመላሽ ተፈናቃዮቹ እንደገለፁት አብዛኛው ተመላሽ  የሚገኘው በከተማ ውስጥ በተዘጋጀ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ነው።

ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተሰደዱትን ተፈናቃዮች የፌደራል እና የክልል መንግስታትን ጥሪ ተቀብለው  ከአንድ ወር በፊት ነበር ለበርካታ ጊዜ ተጠልለው ከነበሩበት ደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን የተመለሱት።

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሀርቡ እና ጃራ መጠለያ ጣቢያ  ከነበሩት ተፈናቃዮች መካከል  ወደ 315 የሚደርሱ ተፈናቃዮች ከሁለት ወር ገደማ በፊት ወደ ጊምቢ ወረዳ መመለሳቸው ይታወሳል።

Via ዶቼ ቬለ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተሰምቷል።

ኢፍትሃዊ ያሉትን የመማር ማስተማር ሂደትን በመቃወም ላይ የነበሩት ተማሪዎቹ በጸጥታ ሃይሎች መበተናቸውም ተነግሯል።

የተማሪዎቹ ዋና ጥያቄያቸው ላለፉት በጦርነት ምክንያት የባከኑ የትምህርት ክፍለጊዜዎች እሚሰጠው የማካካሻ ትምህርት በትምህርት ሚኒስተር መመርያ መሆን አለበትም እሚል እንደሆነም ተገልጿል።

በፀጥታ ሀይሎች የተበተኑት ሰላማዊ ሰልፈኞች "ለዲግሪ 8 አመት መማር  ፍትሃዊ አይደለም" የሚሉ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን ከራያና አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምንለይበት ምንም ምክንያት የለም ማለታቸውንም ሰምተናል።
NewsAlert‼️

10 ተማሪዎች ታስረዋል።

ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስራት ተፈፀመባቸው

ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን  የትግራይ የፀጥታ ሐይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል።10 ተማሪዎች ደግሞ መታሰራቸው ተገልጿል።

እንደ ተማሪዎቹ ገለፃ በፖሊስ  የሐይል እርምጃ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ፤ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው ።

via ፦ Dw
@sheger_press
@sheger_press
በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ለአሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

👉 ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

👉 ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ

👉 ከቦሌ አቅጣጫ  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ

👉 ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

👉 ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና  ሲኒማ

👉 ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ  ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት

👉 ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት

👉 ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት

👉 ከሃራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ

👉 ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

👉 ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

👉 ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81፤ በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ ጥሪ ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን አስተላልፏል።

@sheger_press
@sheger_press
2024/10/01 17:27:04
Back to Top
HTML Embed Code: