Telegram Web Link
አሜሪካ ለእስራኤል ተጨማሪ የጦር አውሮፕላኖችና ቦምቦች እንዲላኩ አዘዘች

ዋሽንግተን ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የጦር አውሮፕላኖች፣ 1 ሺህ 800 ኤምኬ84 እና 500 ኤምኬ82 ቦምቦችን ወደ ቴል አቪቭ እንዲላኩ ማዘዟን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል።

የባይደን አስተዳደር የጦር መሳሪያ ሽያጩን ያጸደቀው እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለው የቦምብ ድብደባ ከፍተኛ አለማቀፍ ውግዘት እያስተናገደ ባለበት ወቅት ነው።አረብ አሜሪካውያን እና የዴሞክራት ፓርቲ አባላት ጭምር አሜሪካ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዳታደርግ እየጠየቁ ቢሆንም ዋሽንግተን ተጨማሪ የጦር አውሮፕላኖች እና ቦምቦችን ለመላክ ወስናለች።

ፕሬዝዳንት ባይደን በርካታ አረብ አሜሪካውያን በጋዛው ጦርነት የሚሰማቸውን ህመም እጋራለሁ ቢሉም ለእስራኤል የሚደረገው ድጋፍ ከኔታንያሁ ጋር በገጠመው ልዩነት ምክንያት አይቋረጥም ማለታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።ዋይትሃውስም ሆነ በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ ስለአዲሱ የጦር መሳሪያ ድጋፍ መረጃ ለመስጠት አልፈለገም።

ይሁን እንጂ በአሜሪካ ለቀናት ቆይታ ያደረጉት የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ከአሜሪካ አቻቸው ሊዩድ ኦስቲን ጋር ሲመክሩ ዋነኛ አጀንዳቸው የጦር መሳሪያ ጉዳይ ነበር ተብሏል።ሚኒስትሩ ሀገራቱ የገቡበት ውጥረት እንደሚረግብና የአሜሪካ ድጋፍ እስራኤል በቀጠናው ጠንካራ ወታደራዊ አቅም እንዲኖራት ማስቻሉንም መናገራቸው ይታወሳል።

አዲሱ ስምምነት ለእስራኤል በአመት ከ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር በላይ ወታደራዊ ድጋፍ የምታደርገው አሜሪካ በጋዛው ጦርነት አጋሯን የተቃወመች ትምሰል እንጂ ጦርነቱ ይቀጥል በሚለው ዙሪያ ከኔታንያሁ የተለየ አቋም እንደሌላት ማሳያ ተደርጎ ቀርቧል።(Alain)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከአንድ ወጣት ሆድ ዉስጥ ሚስማር፣ መርፌ፣ ሽቦና የጥርስ መፋቂያን ጨምሮ 15 ባዕድ ነገሮች በህክምና ወጣለት

የወሊሶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአንድ የ28 አመት ወጣት ሆድ ዉስጥ ሚስማር፣ መርፌ፣ ሽቦና የጥርስ መፋቂያን ጨምሮ 15 ባዕድ ነገሮችን በቀዶ ህክምና ማዉጣቱን ገለጸ።

የቀዶ ህክምናዉ ቡድን መሪ ዶ/ር ኤሊያስ ሰኝ እንደተናገሩት ከታካሚዉ የሆድ ክፍል 3 ሚስማሮች፣ 2 ቀጫጭን ሽቦዎች፣ አንድ መርፌ፣ 9 የእንጨት ጥርስ መፋቂያዎችና ሌሎች ባዕዳን ነገሮች አንድ ሰአት በፈጀ ቀዶ ህክምና ሊወጣ ችሏል።

ታካሚዉ በአዕምሮ ህመም ምክንያት የህክምና ክትትል ሲያደርግና መድሃኒት ሲጠቀም እንደነበረ የሆስፒታሉ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ኤሊያስ ሰኝ አብራርተዋል።

ነዋሪነቱን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ያደረገዉ ይህ ታካሚ በፊት በአዕምሮ ህመም ምክንያት ሲከታተል የነበረዉን ህክምናና መድሃኒት አቋርጧል።

ታካሚዉ ክትትሉን ከማቋረጡም በላይ አሁን በቀዶ ህክምና ከሆዱ የወጣዉ ባዕድ ነገር ይኖራል ብሎ ያሰበም ሆነ ተገቢዉን ምርመራ ያደረ አካል አለመኖሩን ነዉ የገለጹት።

እንደ ኦቢኤን ዘገባ፤ ዶ/ር ኤሊያስ ሰኝ እንደተናገሩት መሠል ክስተቶች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ማህበረሰቡ የአእምሮ ህመም ያለባቸዉን ግለሰቦች ከተለመደዉ ክትትል በዘለለ በጤና ተቋማትና በሰለጠነ ባለሙያ ድጋፍ ሊያደርጉላቸዉ እንደሚገባ መክረዋል።

ምንጭ - ኦቢኤን
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ340 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ ቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል እና የአየር ንብረትን ለመቋቋም የሚውል የ340 ሚሊየን ዶላር የብድር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ከዓለም አቀፍ ልማት ማህበር (አይዲኤ) እንደተገኘና ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የሚከሰተው ድርቅ በአብዛኛው የአርብቶ አደሮችን ህይወት ከባድ እንዳደረገው ይነገራል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት በቆላማው አካባቢ የተከሰተ ድርቅ ከፍተኛ የሆነ የእንስሳት ሞት ያስከተለ ሲሆን÷ በእንስሳቱ ላይ ጥገኛ የሆኑ በሚሊየን የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮች ህይወት ላይም ተጽዕኖ ማሳደሩ ተመላክቷል።

አሁን ይፋ የተደረገው የቆላማ አካባቢዎች ኑሮን የመቋቋም ፕሮጀክት የአካባቢውን እምቅ አቅም በማሳደግ ለሀገራዊ እድገትና ድህነት ቅነሳ አስተዋፅዖ ያበረክታል ሲሉ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኦስማን ዲዮን ተናግረዋል።

የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ስርዓት መዘርጋት፣ የተቀናጀ አካባቢያዊ አስተዳደር እና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንዲሁም የተረጋጋ ህይወት መምራትን የማስተዋወቅ ሥራዎች የፕሮጀክቱ ቁልፍ ተግባራት እንደሆኑ ማመላከታቸውን ከዓለም ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)
የጋምቤላ ክልልን የሚፈታተኑ ችግሮች “ከመቀነስ ይልቅ እየተባባሰ እንዲሔድ የማድረግ ዝንባሌ” እንዳለ የክልሉ መንግሥት አስጠነቀቀ።

“በክልሉ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት” የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች እና መደበኛ ፖሊሶች ያካተተ “ጥልቅ ግምገማ” መጀመሩን ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የጋምቤላ ክልል ሥጋት የተጫነው መግለጫ ያወጣው ከዋና ከተማው ወደ ላሬ ወረዳ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገድለው በርካቶች በቆሰሉ በጥቂት ቀናት ልዩነት ነው። ከሁለት ሣምንታት ገደማ በፊት በጋምቤላ ከተማ አንድ ትራፊክ ፖሊስ በጥይት ከተመታ በኋላ ከፍተኛ ውጥረት ተከስቶ ነበር።

የክልሉ መንግሥት ባለፉት ሁለት ዓመታት “የክልሉን ሠላም ችግር ውስጥ በማስገባት አልፎ አልፎ በሚከሰቱ ግጭቶች ክልሉ ባሉት ፀጋዎቹ ልክ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በርካታ” ጥረቶች መታየታቸውን ገልጿል። መግለጫው እንደሚለው ከ2014 ወዲህ “የብሔር ግጭት፣ ሽብርተኝነት፣ ደረቅ ወንጀሎች እና ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር” በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ታይተዋል። አመራሮቹንም “ጫፍ የደረሰ የብሔር ጽንፈኝነት” “ተሸካሚ” ብሏቸዋል።

የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር የሚሻገሩ ታጣቂዎች “የሕይወት ማጥፋት፣ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት የሚያደርሱበት” መሆኑን የገለጸው የክልሉ መንግሥት ከፌድራል መንግሥት ጋር በመሆን ለችግሮቹ መፍትሔ ለማበጀት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አትቷል።
ለዚህም “የከፋ ችግር ውስጥ የገቡ አመራሮች ከነበሩበት የኃላፊነት ቦታ” ተነስተው ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በማሳያነት ጠቅሷል።

ይሁንና “አሁንም ችግሩ ከመቀነስ ይልቅ እየተባባሰ እንዲሄድ የማድረግ ዝንባሌ” መኖሩን የገለጸው የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት “በተለያዩ ጊዜያት በተፈፀሙ ወንጀሎች እጃቸው ያለበት በቁጥጥር ስር ውለው እንዲጠየቁ” እንደሚያደርግ አስጠንቅቋል።

@ethio_mereja_news
የትግራይና የአማራ ክልል የሚወዛገቡባቸውን አካባቢዎች በተመለከተ በሚቀጥሉት ቀናት የሚከተሉት እርምጃዎች ይወስዳሉ‼️

የወሰን
ይገባኛል የሚነሳባቸውን አካባቢዎች (የራያ ፣ ጠለምት እና ወልቃይት) በተመለከተ የትግራይና የአማራ ክልል አመራሮች የፕሪቶሪያውን የሰላም ውል ተንተርሰው በደረሱት የመተግበሪያ ስምምነት መሰረት ታጣቂዎችን ማስወጣት ተፈናቃዮችን መመለስና አዲስ የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ መታቀዱን  የሰነድ መረጃዎች ያመለክታል። 

የወሰን ውዝግቡን ለመፍታት የተሰየመው ብሄራዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባደረገው ምክክር በደረሰው ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት መከላከያ ፀጥታውንና ሂደቱን የማስተባበር ኃላፊነት ይረከባል።

ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ያለቅድመ ሁኔታ መመለስ  ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ያሰመረበት መርሀግብሩ የትግራይ ክልል የተፈናቃዮችን ቁጥርና ዝርዝር አሰናድቶ ለመከላከያ እንዲያቀርብ፣ ከተመላሾች መካከል በወንጀል የሚጠረጠሩ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንደማይከለከሉና የተጠረጠሩበት ወንጀል ካለ በተናጠል የሚታይ እንደሆነ ያትታል። 
ማናቸውንም የወንጀል ድርጊት ክስ የፌደራል መንግስቱ በሂደት የሚመለከተው ይሆናል።

የቀደመ መኖሪያቸው በአወዛጋቢዎቹ አካባቢዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ታጣቂዎች እና ሚሊሻ እንደታጣቂ ሳይሆን እንደተፈናቃይ ወደ ቦታቸው መመለስ እንደሚችሉም ከስምምነት ተደርሷል። 
የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል የተመሰረቱ የአስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅሮች ይፈርሳሉ።

ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከአካባቢው የሚወጡ ሲሆን የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ደግሞ እንደታጣቂ ሳይሆን እንደ ነዋሪ መቆየት እንዲችሉ በብሄራዊ ኮሚቴው ስምምነት ተደርሷል። 

ከጦርነቱ ተከትሎ የተፈጠሩ የአስተዳደር መዋቅሮች ሲፈርሱ የንብረትና የሰነድ መጥፋት እንዳይኖር መከላከያ ሰራዊት ጉዳዩን ተረክቦ አዲስ ለሚቋቋመው አስተዳደር እንዲያስረክብ ሀለፊነት ተሰጥቶታል።

በዕቅዱ መሰረት ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱ በኃላ ሁሉን ያካተተ የቀበሌ አመራር ምርጫ ይደረጋል። የቀበሌ አመራሮች የወረዳ አመራሮቻቸውን ይመርጣሉ። 

የአካባቢው አስተዳደር በምርጫ ከተሰየመ በኃላ የፌደራል መንግስት በጀት እንደሚመድብላቸው ስምምነቱ  ያብራራል።
ይህ ከተፈፀመ በኋላ በአመቺ ጊዜና ነባራዊ ሁኔታው ተገምግሞ በአካባቢው ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ታቅዷል። 

የራያ እና ጠለምት አካባቢዎች ጉዳይን በቅድሚያ በመፍታት የወልቃይት ጉዳይ ይህንን ተከትሎ በተመሳሳይ  እንዲፈታ ለማድረግ አስፈፃሚ ቡድን ተቋቁሞ ስራውን እንደሚያከናውን ብሄራዊ ኮሚቴው ከስምምነት ደርሷል። 

ከሁለቱ ክልልሎች የተውጣጣ  ግብረ ሀይል በአፈፃፀሙ ላይ በታዛቢነት የሚሳተፍ ሲሆን ጉድለቶችንና የማሻሻያ ሀሳቦችን በግብረመልስ የሚያቀርብ ይሆናል። 

ይህ ስምምነት በተደረስ በቀናት ውስጥ በራያ፡ አላማጣ በኩል የትግራይ ኀይሎች ከአማራ ክልል ሚሊሻ ጋር የተጋጩ ሲሆን ሁለቱ ክልሎች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ሰንብተዋል። 
ይህን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት መፈፀም ይጀምራሉ ተብሏል።
ዋዜማ 

@ethio_mereja_news
" እስከ መጭው ረቡዕ የመጨረሻ ተጨማሪ 3 ቀን ሰጥተናል " ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁንም ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ የመጨረሻ የ3 ቀናት ስለመስጡትን አሳውቋል።

ያለ አግባብ ከተወሰደው ገንዘብ ውስጥ ከባለፈው ሳምንት ተጨማሪ ብር 117,612,000 ብር ከ59 ሳንቲም በመሰብሰቡ የተከፈለ አጠቃላይ ገንዘብ 86% መድረሱን እና ያልተመለሰ ገንዘብ ወደ ብር 112,389,455 ብር ከ12 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን ገልጿል።

ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው ክፍያ የጨረሱ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 10,857 ከፍ ማለቱን ገልጿል።

የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ያልጀመሩ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 222 ዝቅ እንዳለና ከነዚህ ግለሰቦች የሚጠበቅ ገንዘብም ወደ ብር 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም ዝቅ ማለቱን ጠቁሟል።

ባንኩ ፥ አንድ አንድ ግለሰቦች ወደ ተለያዩ ተቋማት ያስተላለፉትን ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጿል።ይህ ተከትሎ ከዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተጨማሪ 3 ተከታታይ ቀናት እንደተሰጠ አሳውቋል።ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉና በከፊል ገንዘብ ያለመለሱ እንዲመልሱ 2 ጊዜ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ገደብ አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል። የስም ዝርዝርም ይፋ አድርጎ ነበር።

@ethio_mereja_news
የትግራይና አማራ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው የራያ፣ ጠለምትና ወልቃይት፣ ታጣቂዎችን የማስወጣት፣ ተፈናቃዮችን የመመለስና አዲስ የአስተዳደር መዋቅሮችን የመዘርጋት እንቅስቃሴዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጀመሩ ዋዜማ ካገኘችው ሰነድ ተረድታለች።

ውዝግቡን ለመፍታት የተሰየመው ብሄራዊ ኮሚቴ፣ መከላከያ ሠራዊት ይህንኑ ሂደትና ጸጥታውን እንዲያስተባበር ኃላፊነት እንደሰጠና የትግራይ የተፈናቃዮችን ዝርዝር ለመከላከያ እንዲሚያቀርብ በሰነዱ ላይ ተገልጧል። የትግራይ ተወላጅ የኾኑ ታጣቂዎችና ሚሊሻዎችም እንደታጣቂ ሳይኾን እንደተፈናቃይ ወደቀያቸው እንደሚመመለሱና የአካባቢው ተወላጅ የኾኑ የአማራ ታጣቂዎች እንደ ነዋሪ መቆየት እንዲችሉ ተወስኗል። ከጦርነቱ በኋላ የተመሠረቱ የአስተዳደርና የጸጥታ መዋቅሮች ፈርሰው የቀበሌና የወረዳ አመራሮች ምርጫ ይደረግና ነባራዊ ሁኔታው ሲመቻች ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል- ይላል ሰነዱ።

@ethio_mereja_news
ጌዴኦ ‼️

በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በገደብ ወረዳ በደረሰው ትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ገለጸዋል።

መጋቢት 23-2016 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ከዲላ ሲጓዝ ከነበረው ተሽከርካሪ በተቃራኒው ከገደብ ከሚመጣ ህዝባ ማመላለሻ መኪና ተላትመው የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገልጸዋል።

በአደጋው ሦስት ሰው ህይወታቸው ሲያልፍ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውና የቆሰሉት ተሳፋሪዎች በገደብ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገ መሆኑን ከገደብ ወረዳ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

ጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ከአገር ዓቀፍና ከክልላዊ ፓርቲዎች ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

የውይይቱ ዓላማ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ላይ አስተያየቶችና ትችቶችን ማሰባሰብና ለፖሊሲ ግብዓት አስፈላጊ የኾኑ እርማቶችንና ማስተካከያዎችን መለየት እንደነበር ዐቢይ ገልጸዋል።

በውይይቱ እንዲገኙ ጥሪ ከቀርበላቸው 60 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ የፓርቲዎች ኮከስ አባላት የኾኑ 13ት ፓርቲዎች ጥሪውን እንዳልተቀበሉ መስማቱን ሸገር ዘግቧል።

የኮከሱ አባል የኾነው የኅብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ግርማ በቀለ፣ ፓርቲዎቹ በውይይቱ የማይሳተፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ካኹን ቀደም ከነጋዴዎች፣ ከኃይማኖት ተቋማትና ሌሎች አካላት ጋር ያደረጓቸው ተመሳሳይ ውይይቶች የገጽታ ግንባታን ዒላማ ያደረጉ እና የገዥው ብልጽግና ፓርቲ መወድስ የሚቀርብባቸው መኾናቸውን በመረዳታቸው እንደኾነ ለሸገር ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች፣ ነገ ማክሰኞ የኔዘርላንድ መንግሥት ባዘጋጀላቸው ሥልጠና ላይ እንደሚገኙ መስማቱን ዘገባው አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
አቶ አድም ፋራህ በም/ል ጠ/ሚ ማዕረግ ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ አደም ፋራህን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበሪያ ሃላፊ አድርገው መሾማቸውን ሸገር ሰምቷል።

Via PMOEthiopia @ethio_mereja_news
ከመጋቢት 30 ጀምሮ ለሚኒባሶች የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቋረጥ ተገለጸ

ከዚህ ቀደም የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ባወጣው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ቀስ በቀስም መንግስት በነዳጅ ምርት ላይ የሚያደርገዉ ድጎማ የማቋረጥ እቅድ እንዳለዉ ይታወቃል፡፡

በሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገዉ መንግስት ድጎማን የማስቀረቱ አንዱ አቅድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ሆኖም የድጎማ ስርአቱን የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ማህበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሰልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖስ ወርቁ ከዚህ ቀደም 170ሺ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርአት ውጪ መደረጋቸዉን ተናግረዋል።

ተሽከርካሪዎቹ ነዳጅ ድጎማን በስርዓት ባለመጠቀማቸው ከድጎማው ውጪ እንዲደረጉ ምክንያት መሆኑ አመላክተዋል።

ከፊታችን መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጅምሮ በነዳጅ ድጎማው ስርአት የሀገር አቋራጭና የከተማ አውቶቢስ ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀው እነዚህም ተሽከርካሪዎችን እስከሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡


የመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አደረገ!

በባን
ኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መመለሳቸውን ባንኩ ገልጿል፡፡

ባንኩ "የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች አሉ ያለ ሲሆን ባንካችን ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንካችን ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት ተገደናል ብሏል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ባንካችን የተለያዩ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ያራዘመ በመሆኑ፣ ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ እያሳሰብን፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ የምናቀርብ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን ብሏል፡፡

ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይፋ አድርጓል።
https://combanketh.et/list-of-customers

    
አጫጭር ዜናዎች‼️

1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህን ትናንት በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አድርገው ሹመዋል። አደም አዲሱ መንግሥታዊ ሸመት የተሰጣቸው፣ ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርነት ሥልጣናቸው ሳይለቁ ነው። አደም ፋራህ በአዲሱ ሹመታቸው፣ የዲሞክራሲ ተቋማትን የማስተባበር ሃላፊነት ይኖራቸዋል።

2፤ ኢሠማኮ፣ መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይደራጁ የሚከለክለውን ሕግ እንዲያሻሽል መጠየቁን ሸገር ዘግቧል። በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይደራጁ መከልከላቸው በኅብረት መብታቸውን ለማስከበር እንዳይችሉ አድርጓል ሲሉ የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ኢሠማኮ በመንግሥት ሠራተኞች ላይ በሚደርሰው የመብት ጥሰት ዙሪያ መከራከር እንዳልቻለም ካሳሁን ገልጸዋል ተብሏል። ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅትን የመንግሥት ሠራተኞችን የመደራጀት መብት የሚፈቅደውን ሕግ ያጸደቀች ቢኾንም፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ የመደራጀት መብት ያላቸው ግን የግልና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሠራተኞች ብቻ ናቸው።

3፤ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ድርጅት ጣና ሐይቅ ላይ ለሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ ከውጭ የተገዙ ኹለት ዘመናዊ ጀልባዎች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን ትናንት ምሽት አስታውቋል። አንደኛዋ ጀልባ፣ "ጣና ነሽ ፪" የተባለች ዘመናዊ የሕዝብ ትራንስፖርት ጀልባ ስትኾን፣ ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ እንደኾነች ድርጅቱ ገልጧል። "ጣናነሽ ፪" 38 ሜትር ርዝመትና ባንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም አላት ተብሏል።

4፤ ንግድ ባንክ ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ትናንት ያልመለሱ ደንበኞቹን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ ትናንት ምሽት በድረ-ገጹና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ይፋ አድርጓል። ባንኩ ፎቶግራፋቸውን ይፋ ያደረገባቸው ደንበኞቹ፣ ከ108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ብር የወሰዱ ናቸው ተብሏል። ባንኩ፣ በተራዘመው ቀነ ገደብ ማለትም በመጪው ረቡዕ ገንዘቡን የማይመልሱ ደንበኞቹን ለሕግ እንደሚያቀርብ ገልጧል። እስከ ትናንት ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ የመለሱ ደንበኞች ብዛት 10 ሺህ 857 መድረሱን ባንኩ ጠቅሷል።

5፤ የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል፣ የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ አድሚራል ቭላድሚር ካሳቶኖቭ የመሩት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ትናንት ምጽዋ መግባቱን የኤርትራ መንግሥት አስታውቀዋል። የማነ፣ ልዑካን ቡድኑን የኤርትራ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ፊሊጶስ ወልደማርያም እንደተቀበሉት ገልጸዋል። የሩሲያ ባሕር ኃይል አንዲት ወታደራዊ መርከብ ከኤርትራ ባሕር ኃይል ጋር ለዘጠኝ ቀናት የሚቆይ ልምምድ በቀይ ባሕር ላይ ለማድረግ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ምጽዋ መድረሷ ይታወሳል። [ዋዜማ]

@sheger_press
@sheger_press
ኦሮሚያ!!

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት 6ኛ ዓመት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች በሰላማዊ ሰልፍ እየተከበረ ይገኛሉ።ሂደቱን መንግስታዊ ሚዲያዎች በቀጥታ ሽፋን ሰጥተው እያስተላለፉት እንዳሉ ተመልክተናል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ መጋቢት 24/2010ዓም ነበር ቃለመሀላ የፈፀሙት።

@ethio_mereja_news
ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በዉይይቱ ያልተሳተፍነዉ “የለበጣ እና ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር እንደማያመጣ ሰለተረዳን ነዉ” ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ

የአስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት (ሲኦፒ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት የቀረበለትን ጥሪ ውድቅ ያደረገው መንግሥት በአገሪቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር ፍላጎት ስለሌለው መሆኑን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ አይዘነጋም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ከተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም. ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የጥምረቱ አባላት ግን ሳይሳተፉም ቀርተዋል።

የጥምረቱ አባላት በውይይቱ ላለመገኘት የወሰኑት “መንግሥት አሳሳቢ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ስለማይፈልግ” መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር መረራ እንዳሉት ውይይቱ “ዝም ብሎ የለበጣ እና ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር እንደማያመጣ ሰለተረዳን እና ተቃዋሚዎችን አናገርኩ የሚል የይምሰል በመሆኑ” ላለመሳተፋቸው ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ባለፉት ስድስት ዓመታት በአገር ውስጥ እንዲሁም ኔዘርላንድ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በውጭ አገራት ከእሳቸውም እንዲሁም ከተወካዮቻቸው ጋር ድርድር ቢደረግም ፍሬ አላፈራም ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

ከገዢው ፓርቲ ጋር በተደረጉ በርካታ ንግግሮችም የተረዱት መንግሥት “መሠረታዊ እና አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መደራደርም ሆነ መነጋገር አይፈልግም” ሲሉም ፕሮፌሰር መረራ አጽንኦት ይሰጣሉ።

እሳቸው መሠረታዊ ብለው ከሚያነሷቸው ጉዳዮች አንዱ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎችን ጨምሮ በአገሪቱ ለበርካታ ሰዎች እልቂት የእየሆኑ ያሉትን ግጭቶች እና ጦርነቶችን ነው። እነዚህ ጦርነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዴት ይቋጭ? በሚለው ጉዳይ ላይ “መንግሥት መነጋገርም ሆነ ወደ መደራደር አይሄድም” ይላሉ።

በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነው “የመገደደል ፖለቲካን ማቆም” ዋነኛ እና መሠረታዊ ጉዳይም እንደሆነም ነው የሚገልጹት።

ሌላኛው ፖለቲከኛው የሚጠቅሱት ጉዳይ አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ሽግግር መክሸፉን በመጥቀስ፤ ይህንን የአገሪቱ የዲሞክራሲ የመቀልበስ ሂደት ላይም ገዢው ፓርቲ መወያየት አይፈልግም ይላሉ።

“መነጋገር ደግሞ ውል እና ማሰሪያ ያለው ነገር ይዞ መሠረታዊ ነገሮችን አንስተን ሰጥቶ በመቀበል ፖለቲካ ችግሮችን መፍታት ካልቻልን ንግግሩ ብዙም ትርፍ ስለሌለው ሕዝቡንም ላለማሳሳት ያደረግነው ነው” ብለዋል።

አገሪቷን እየናጧት ያሉ ግጭቶችንም ሆነ ሌሎች መሠረታዊ ያሏቸውን ጉዳዮች ፊት ለፊት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በማንሳት መነጋገር አይቻልም ነበር ወይ? በሚል ቢቢሲ ፕሮፌሰር መረራን ጠይቋቸዋል።

እሳቸውም ከዚህ በፊት የተደረጉ በርካታ ንግግሮች ፋይዳ እንዳልነበራቸው እና ወደየትም ያልተራመዱ መሆናቸውን በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ጦርነቱን ማስቆም አልተቻለም። መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ካልተወያየን ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር ስለማያመጣ መሳተፍን አልመረጥንም እንጂ መነጋገርንም ሆነ መደራደርን ጠልተን አይደለም” ሲሉም መልሰዋል።

አክለውም “በእነዚህ ንግግሮች የመጣ ለውጥ፣ የምናስተካክለው ነገር ወይም የምንፈይደው ነገር ስለሌለ ነው። ሕዝቡን በማይሆን መንገድ እየተነጋገርን ነው፤ በውይይይ እየተፈታ ነው የሚል አጉል ተስፋ ላለመስጠት እኛ የመሰለንንን እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት ግብዣ ላለመቀበል የመወሰናቸው እርምጃ ዋጋ የሚያስከፍላችሁ አይመስላችሁም ወይ በሚልም ቢቢሲ የጠየቃቸው መረራ “ከዚህ በላይ ዋጋ ከፍለናል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ባደረገችው ምርጫ የእሳቸው ፓርቲ እና ኦነግ “ተገፍተው” ከምርጫው እንደወጡ በመጥቀስ የከፈሉት ዋጋ መሆኑን አንስተዋል።

ኦፌኮ ብቻ ሳይሆን በምርጫው ተሳታፊ የነበረው አብን አንዳንድ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውንም ያነሱት ፕሮፌሰር መረራ “ሌሎቹም አልተጠቀሙም” ይላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት የአንድ ቀን ውይይት ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ላይ አስተያየቶችን እና ትችቶችን ለማሰባሰብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

መንግሥት እያከናወናቸው ያሉ ልማቶችን በተመለከተ ለተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ገለጻ መደረጉም ተጠቅሷል።

መረራ በበኩላቸው በእነዚህ ልማቶች ላይ ጥያቄ በማንሳትም “የሚለማው ሕዝብ ነው መሬት አይደለም። ይሄንን ገዢው ፓርቲ እንዲረዳ ካልፈለገ? ምን ማድረግ ይቻላል?” ሲሉም ይጠይቃሉ።

ሁለቱ ሰፊ የኢትዮጵያ ክልሎች የድሮኖችን ጥቃት ጨምሮ ሰፊ እልቂት እና ጦርነት እያስተናገዱ እንደሆነም የሚያነሱት መረራ፤ እነዚህን እልቂቶች “ወደ ጎን ትቶ ይሄ ህንጻ ተሠራ፣ መንገድ ተሠራ በማለት ያለውን የሕዝብ ትግል ዝቅ ማድረግ ተገቢ አይደለም” ብለዋል።

አክለውም “በግልጽ ለመንግሥት፣ ለገዢው ፓርቲም ሆነ ለሕዝቡ እያልን ያለው እየተካሄደ ያለው ጨዋታ የትም አያደርስም። ኳሱ ያለው በገዢው ፓርቲ ነው እኛ ጋር አይደለም” ብለዋል።

በዚህ ውይይት ላይ ለፖሊሲ ግብዓት አስፈላጊ የሆኑ እርማቶች እና ማስተካከያዎች ተለይተው ወደፊት ለመቀጠል በሚያስፈልጉ የትብብር ዓይነቶች ላይ ምክክር መካሄዱንም የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት የተመሠረተው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን የነጻነት ግንባር፣ ህብር ኢትዮጵያ፣ አረና ትግራይ ፓርቲ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የአፋር ሕዝቦች ፓርቲን የያዘ ሲሆን ከዚህ ቀደምም አንዳንድ የመንግሥት ውሳኔዎችን በመቃወም ይታወቃል።

በአማራ ክልል እንዲሁም በሌላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደ አስፈላጊነቱ ተግባራዊ ይሆናል የተባለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም ተቃውሞም መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

Via ቢቢሲ አማርኛ

@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረ
በአዲሱ መመሪያ መመሪያ 34 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ተደርጓል 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የቤት ሽያጭ ዋጋ ማሻሻያ ላይ ከሕብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች በመቅረባቸው፣ መመሪያው በድጋሚ እንዲከለስ ተደርጓል። 

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም  በተሠራጨው አዲስ መመሪያ በኮንዶሚኒየም ቤቶች እና በአፓርታማዎች ሽያጭ የካሬ ሜትር ዋጋ ላይ በአማካኝ 34 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

@ethio_mereja_news
በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ!

ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ወራት ታግዶ የቆየው የመሬት አገልግሎት፣ የዜጎችን መብት የጣሰ እንደነበር በመናገር  ተገልጋዮች ሲያማርሩ ቆይተዋል።

አስተዳደሩ እንደገለጸው አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከቀን ከመጋቢት 23 ቀን2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሕወሓት ዕውቅናው እንዲመለስለት ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱና ፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ መሠረት የለውም አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ዕውቅናውና ፈቃዱ እንደሚመለስ ተናግረዋል

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ የዕውቅና ፈቃዱን የተነጠቀው ሕወሓት፣ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንደተገለጸው በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንዲመለስለት ያቀረበው ጥያቄ የሕግ መሠረት የለውም ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ፍትሕ ሚኒስቴር ምላሽ ሰጡ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የፍትሕ ሚኒስቴር በአመፅ ድርጊት በመሳተፉ ምክንያት ፈቃዱ እንዲሰረዝ የተደረገው ሕወሓት መልሶ ዕውቅና የማግኘት ሕጋዊ መሠረት የለውም ቢሉም፣ ሕወሓት ግን ዕውቅናው በፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተገለው በሕገ መንግሥቱ መሠረት መፈቀድ አለበት ብሏል፡፡

ሕወሓት በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት ተሳታፊ በመሆኑ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት መፈረጁ የሚታወስ ሲሆን፣ የፓርቲነት ፈቃዱም ሆነ ስያሜው በምርጫ ቦርድ መሰረዙ አይዘነጋም፡፡ በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት፣ ጦርነቱ ከቆመ በኋላ ሕወሓት ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ ሲደረግ፣ የፓርቲነት ፈቃዱ ግን አለመመለሱ ይታወቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ባደረጉት ውይይት፣ የሕወሓት ዕውቅናና ፈቃድ መመለስ እንዳለበትና ይህንንም ለምርጫ ቦርድ በማሳወቅ በቅርቡ ችግሩ እንደሚፈታ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ቢሉም፣ በቅርቡ የተሾሙት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ሰሞኑን ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በአመፅ ድርጊት በመሳተፉ ምክንያት ፈቃዱ የተሰረዘ ፓርቲ መልሶ እንደገና ፈቃድ እንዲያገኝ የሚያስችል የሕግ ድንጋጌ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ሰብሳቢዋ አክለውም ፈቃዱን መስጠት ባይቻልም በአዋጁ መሠረት እንደ አዲስ መመዝገብ ይችላል ብለዋል፡፡

የሕጋዊነትና የፈቃድ ጉዳይ በፕሪቶሪያው ስምምነት እንደተመለከተው በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምላሽ የሚሰጠው መሆኑን ለሪፖርተር የገለጹት የሕወሓት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ተስፋዬ፣ እንደ አዲስ መመዝገብ የሚለው ጉዳይ ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ ‹‹ከፌደራል መንግሥት ጋር ባለን ግንኙነት የፓርቲውን ፈቃድ የመመለሱ ሒደት ላይ መስማማት ተደርሶ አቅጣጫ የተሰጠበት ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ነው እየጠየቅን ያለነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ዳይሬክቶሬት ረዳት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ መዓዛ ሃይማኖት እንደገለጹት በአገሪቱ ሕግ መሠረት በፓርቲነት የተመዘገበና ዕውቅና ያገኘ ፓርቲ በኃይል ድርጊት ተሰማርቶ ከተገኘ ሕጋዊ ሰውነቱን ያጣል፡፡ ሕወሓትም በዚህ ድርጊት ተሰማርቶ በመገኘቱ ምርጫ ቦርድ የወሰደው ፈቃድ የመንጠቅ ዕርምጃ ሕጋዊ መሠረት የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በአገሪቱ ባለው ሕግ መሠረት ሕወሓት የቀድሞውን ፈቃድ ማግኘት አይችልም›› ያሉት አቶ መዓዛ፣ እንደ አዲስ መመዝገብን ግን አይከለከልም ሲሉ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አጠናክረዋል፡፡

ምንም እንኳን የፍትሕ ሚኒስቴር ለሕወሓት ሕጋዊ ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ እያደረገ ባይሆንም፣ ማሻሻያው ቢደረግ እንኳን ከዚህ በፊት የተሰጠውን ውሳኔ የሚሽር አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡  

ለፍትሕ ሚኒስቴር አስተያየት ምላሻቸውን የሰጡት አቶ እያሱ፣ ‹‹የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀስን ባለንት ወቅት፣ የፓርቲውን ዕውቅና ማግኘት ከሰላም ስምምነቱ ውጪ አድርጎ መመልክት አግባብ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

Via:Reporter

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/01 19:21:07
Back to Top
HTML Embed Code: