Telegram Web Link
በወላይታ ለሰባት አመታት መፀዳዳት የማይችለው ታዳጊ የተጠራቀመው ሰገራ በቀዶ ህክምና ወጣለት

ህክምናው የተሰጠው የህክምና ዘመቻ በማድረግ ላይ በነበሩ አለም አቀፍ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በጎ ፈቃደኞች መሆኑን ተነግሯል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ከምትሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የህክምና አገልግሎት አንዱ በመሆኑ የህክምና ቡድኑ በነበራቸው የዘመቻ ስራ ታዳጊውን ለሰባት ዓመት መጸዳዳት ባለመቻሉ ሆዱ አካባቢ ከፍተኛ እብጠት ነበረበት፡፡በወላይታ በባዴሳ ነዋሪ የሆነው ህጻን አንዱዓለም አላሮ ከተወለደ ጌዜ ጀምሮ ባጋጠመው ህመም ምክንያት መጸዳዳት የማይችል ሲሆን ታዳጊው በዚህ ምክንያ ከፍተኛ ህመም እና ስቃይ እንደነበረው በወላይታ አለም አቀፍ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ውስጥ በህክምና ቡድን ውስጥ ነርስ ሳምራዊት ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

የታዳጊው የስቃይ ምንጭ ወደ ውጭ መውጣት የነበረበት ሰገራ በሆዱ በመጠራቀሙ ምግብም ሲመገብ ሆነ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ተግዳሮት ፈጥሮበታል፡፡ ሰባት ዓመት ሙሉ በሆዱ ሲጠራቀም የነበረውና መወገድ የነበረበት ሰገራ ስለማይወጣ በትልቁ አንጀት (colon )ውስጥ ይከማች  ስለነበር ከባድ ህመም ውስጥ እንደነበር ተነግረዋል፡፡

አለም አቀፍ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ባለሙያዎች እና የህክምናውን ወጪ በቻሉ በጎ ፍቃደኞች የገንዘብ ድጋፍ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኝ  ግሬስ ሆስፒታል ሶስት ሰአት በላይ በወሰደ ቀዶ ህክምና ህጻን አንዷዓለም አንጀት ውስጥ ተጠራቅሞ የነበረን ሰገራ ማስወገድ መቻሉን ሲስተር ሳምራዊት ጨምረው ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡ታዳጊው አሁን ላይ የተጠራቀመው ሰገራ ይውጣለት እንጂ ኮሎስቶሚ ወይም በሆድ በኩል ተቀዶ በጎኑ ለሶስት ወራ እንዲጸዳዳ የተደረገለት ሲሆን ከሶስት ወራት በኃላ በሚደረግለ ተከታታይ ህክምና በመደበኛ መልኩ እንዲጸዳዳ የማድረግ ህክምናው ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በቀዶ ህክማናውም በርካታ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ፣ ጠቅላላ ሀኪሞች እና ነርሶች ያቀፈው ይህ አለም አቀፍ አድቬንቲስት ቤ/ያን በጎ ፈቃደኞች የሉዑካን ቡድን በጋራ መስራታቸውን የቤተክርስቲያኗ ኮሙኒኬሽን ጋላፊ አቶ ዳግም እያሱ ለብስራት ተናግረዋል፡፡ታዳጊው ከአሁን በፊት በሪፈር አዲስ አበባ ሄዶ ህክምና እንዲያገኝ ሌሎች የጤና ተቋማት ቢላክም ወላጆቹ አቅም የሌላቸው በመሆኑ ህክምናውን ሳያገኝ መቆየቱንም አንስተዋል፡፡

አቶ ዳግም በቀዶ ህክምናው የተሳተፉትን ዶ/ር ተመስገን የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት፤ ዶ/ር ብስራት አበበ አናስቴሲዮሎጂስት እና የግሬስ ሆስፒታል ተባባሪ ሐኪሞ ና ነርሶች ለላቀ ትብብራችሁ  ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ህጻኑ አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንደማይዘጉ አስታወቁ!

ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ በግዛቶቻቸው የሚገኙትን ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንዲዘጉ የተሰጠውን ትዕዛዝ እንደማይቀበሉ ዛሬ አስታወቁ።ሶማሊያ፣ በሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሀገር ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን፣ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ትላንት ኀሙስ፣ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር።

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን በመግለፅ ክስ ያሰማው የሶማሊያ መንግሥት፤ ሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰአት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መጠየቋን እና አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም መጥራቷን ትናንት አስታውቃ ነበር።በተመሳሳይም ከሶማሊያ የተገነጠለችውን የሶማሊላንድ ግዛት እና ከፊል ራስ ገዟን ፑንትላንድ በዚያ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሰባት ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ አዛለች።

ይሁንና ሶማሌላንድ በዋና ከተማዋ ሀርጌሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ሞቃዲሾ ያቀረበችውን ጥያቄ የሶማሌ ፌደራል መንግሥት እንደዚያ ያለ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ ውድቅ አድርጋለች።ሶማሊያ ኢትዮጵያ ባለፈው ጥር ወር ከሶማሌላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የባህር በር የተመለከተ ስምምነት፣ “ህገ-ወጥ” እና ሉአላዊነቴን የጣሰ ነው ስትል ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቷም ይታወቃል።

Via VoA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ይህ ፓስታ ሳይሆን ሐዋሳ ከተማ ከ8 ዓት ህፃን ጉሮሮ በቀዶ ህክምና የወጣ ትል/ፓራሳይት/ ነው።

ትሉ የልጁን ጉሮሮ በመዝጋት ከተበከለ በኋላ በቀዶ ጥገና ተወግዷል።

እነዚህ ትሎች/ፓራሳይቶች/ ወደ አንጀታችን የሚገቡት የእጃችንን ንፅህና ባለመጠበቅ ነው። በተጨማሪም ንፁህ ያልሆኑ/የተበከሉ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በመመገብ ወደ እኛ ይተላለፋል።

ስለዚህ የምግብ ንፅህናን በመጠበቅ እራሳችንን እና ሌሎችን ከበሽታው እንጠብቅ!
(ዶክተር ናፊያ)
ፎቶ:ሀኪም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ዕዝ፣ ከደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ደሴ ከተማ የሚወስደው መንገድ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚከፈት አስታውቋል።

ማዕከላዊ ዕዙ መንገዱ እንዲከፈት የወሰነው፣ ባካባቢው ያለው የሰላም ኹኔታ መሻሻል በማሳየቱና ኅብረተሰቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረቡ እንደኾነ ገልጧል።

የጸጥታ ዕዙ መንገዱ እንዲዘጋ የወሰነው፣ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ መውሰድ በመጀመራቸው እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
የፍኖተ ጽድቅ መስራችና የስራ ኃላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ ጠየቁ።

ፍኖተ ጽድቅ አገልግሎትና የማህበሩ ሚዲያ በአሠራጫቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥርዐተ አምልኮና የትውፊት ጥያቄዎች ሲቀርቡበትም ነበር።

በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ጉባኤና በጉባኤው በሚመደቡ መምህራንና መዘምራን፣ በጉባኤው በሚሰጡ ትምሀርቶችና በሚዘመሩ መዝሙራት፣ በመዝሙር መሣሪያዎች አጠቃቀምና የአዘማመር ስልቶች ላይ ጥያቄዎች ሲነሡና አንዳንድ ጊዜም የቤተ ክርስቲያን ልጆች መካከል የልዩነትና የውዝግብ ምክንያት ሲሆንም ታይቷል።

ይህን ተከትሎም የፍኖተ ጽድቅ ማኅበር ኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነትን፣ ሥርዐተ አምልኮንና ትውፊትን ብቻ ማዕከል አድርጎ ማገልገል በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምሀራነ ወንጌልና በማኅበራዊ ሚዲያ በፍኖተ ጽድቅ ላይ አተኩረው የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወንድሞች፤ የፍኖተ ጽድቅ መሥራች ከሆኑት ከአቶ ጸጋዬ ደበበና ከማኅበሩ አመራሮች ጋር ለበርካታ ጊዜያት ውይይትና ምክክርም ሲያደርጉም ቆይተዋል።

በውይይቱም መሰረት ፍኖተ ጽድቅን በተመለከተ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል

👉 በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር በመደበኛ መምህርነት ተቀጥረው የሚያስተምሩ መምሀራን ማስተማር አቁመው በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ገዳም ሔደው ጥሞና እንዲወስዱና በሚመደቡላቸው ኦርቶዶክሳውያን መምሀራን ሥልጠና እንዲወስዱ።

👉 ከኦርቶዶክሳዊ መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮና ትውፊት ያፈነገጡ መዝሙራትም ሆኑ ያልሆኑ ከፍኖተ ጽድቅ የዩቱብ ቻናል ሙሉ በሙሉ እንዲወርዱ።

👉 ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለመዝሙር አገልግሎት ከምትጠቀማቸው የዜማ መሣሪያዎች ወጭ ያሉት የሙዚቃ መሣሪያዎችና ማቀናበሪያዎች በሙሉ እንዲወገዱ።

👉 በኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና የዜማ መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ የፍኖተ ጽድቅ የጎብረት ዘማርያንና የዜማ መሣሪያ ተጫዋቾች ሥልጠና እንዲወስዱ።

👉 ፍኖተ ጽድቅ ወደፊት በሚሰጣቸው የትምሀርትና የመዝሙር አገልግሎቶች ኦርቶዶክሳውያን መምሀራንና ዘማረያን ብቻ እንዲያገለግሉ።

👉 የፍኖተ ጽድቅ መስራችና የስራ ኃላፊዎች ኦርቶዶክሳውያንን ይቅርታ እንዲጠይቁ።

👉 በፍኖተ ጽድቅና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ላይ አተኮረው የሰሩ ቲክቶከሮች የሰሯቸውን ቪዲዮዎች እንደያወርዱ፤ መምሀራኑም እንዲሁ እንዲያደርጉ።

በእነዚሀ የጋራ ስምምነት መሠረትና የወደፊቱን አገልግሎት በማሰብ ፍኖተ ጽድቅ ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነት ፣ ሥርዓት እምልኮ ፣ ትውፊት የተላለፋም ሆኑ ያልተላለፋ መዝመሮች በሙሉ ከዩቱብ ቻናል እንዲውርድ ተደርጓል።

Via:FastMereja

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የፀሀይ ግርዶሽ!!

ነገ በፈረንጆቹ April 08, 2024 አንዳንድ ሰዎች ዓለም ትጨልማለች እያሉ ይገኛል።ነገሩ ግን ሌላ ነው ነገ በአሜሪካ ና በአንዳንድ የሰሜን አሜሪካ ሀገራት በጥዋቱ ክፍለ ዘመን የፀሀይ ግርዶሽ ያጋጥማል ይህም የፀሀይ ግርዶሽ ለ4 ደቂቃ ከ28 ሰከንድ ፀሀይ በጨረቃ ሙሉ በሚባል ደረጃ የምትዋጥ ስለሚሆን
ለ4 ደቂቃ ከ28 ሰከንድ በቀን ጨለማ ይሆናል።ይህን ክስትት ከዛሬ 4 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ በላሊበላ አጋጥሞ እንደነበር ይታወሳል።

ነገ በአሜሪካ እና በአሜሪካ ጎረቤት ሀገሮች ይህ ነገር የሚያጋጥም ሲሆን ይህ ክስተት በህይወት ካለን በፈረንጆቹ በ2099 ከ75 ዓመት በኃላ ያጋጥማል ተብሏል::

በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በከፊል ግን በቅርብ ይሆናል ተብሏል።ሙሉ በሙሉ ግን ከ14 ዓመት በኃላ እንደሚያጋጥም ይታመናል::ህይወትን በፍቅር ና መሞት የማይፈልጉት አሜሪካኖች ገና ካሁን ተጨንቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
📍ባህርዳር

በአማራ ክልል መዲና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።

ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት ፥ አቶ ሙሄ ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ ፣ ሽኩር ሙሄ ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው‼️

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ ፤ በመሆኑም የዒድ አልፊጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

ነገ ማክሰኞ የረመዷን የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።

@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጋራ መስራት ባለመቻላቸው ከ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ታጥቷል ተባለ

6ኛ ዙር 3ኛ አመት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬዉ እለት በ2014/15 በጀት አመት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮጀክት አፈጻጸምን በተመለከተ በክዋኔ ኦዲት ዉጤት መሰረት ሪፖርት በዛሬዉ እለት ቀርቧል።

በቋሚ ኮሚቴዉ በቀረበዉ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋማት በጋራ ባለመስራታቸው በአማካይ ከ 1 ቢሊዮን 270 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለዉ ሀይል ለሀገርዉስጥ እና ለዉጭ ገበያ አለመቅረቡ በሪፖርቱ መነሳቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

በተጨማሪም ቋሚ ኮሚቴዉ በኦዲት ግኝቱ መሰረት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ምላሽ እንዲሰጡባቸዉ በርከት ያሉ ጥያቄዎችን አቅርቧል። ከነዚህም ዉስጥ የአላማጣ - ኮምቦልቻ - ለገጣፎ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ሲከናወን በዲዛይኑ መሰረት ስለመከናወኑ ክትትል ባለመደረጉ የተፈጠሩ ስህተቶች እዲሁም በበጀት ፣ በተባለዉ ጊዜ አለማጠናቀቅ ፣ በሚያጋጥመዉ ስርቆት ዙሪያ እና ሌሎች በርካታ ስራዎች በደረጃዉ ልክ ለምን አልተጠናቀቁም የሚሉት ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ወጪዉን የማያዉቅበት እና ያልመዘገበበት ፕሮጀክት አለ የተባለም ሲሆን በዉጭ ምንዛሪ የተገዙ እና ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቅ ከግንባታ የተረፉ ቁሳቁሶችም ካለጥቅም ሳር በቅሎበቸዋል በሚል በተቋሙ ላይ ትችት ተሰንዝሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጋምቤላ ክልል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 4 ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በመንግስትም ሆነ በፓርቲ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን 4 ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት ማንሳቱን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡

ከኃላፊነታቸው ከተነሱት ውስጥ ሶስቱ የክልል አመራሮች እና አንዱ የዞን አመራር መሆኑን ዳጉ ጆርናል ከክልሉ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

በዚህም መሰረት

1ኛ. የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አኳይ ኡቡቲ

2ኛ. የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቾል ኩን

3ኛ. የክልሉ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢተው ዳክ እና

4ኛ. የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቡኝ ኜል ናቸው።

የክልሉ መንግስት እና ፓርቲው የሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት ባልቻሉ አመራሮች ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የክልሉ መንግስት አሳዉቋል፡፡ በጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ የጸትታ ችግሮች ሲከሰቱ የተስተዋለ ሲሆን ዳጉ ጆርናልም በተደጋጋሚ ሲዘግብባቸዉ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተያዙ‼️

ለሽብር ተግባር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአልሸባብ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

የሶማሌ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድ ትናንት በሰጡት መግለጫ መላው የክልሉህብረተሰብ የጋራ ሰላምና ደህንነቱን ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመግለጫቸው በክልሉ ሁከትና ሽብር ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአልሸባብ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፁት ሀላፊው እንዲህ አይነት እኩይ ተግባር ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ በኩል ሰላም ወዳዱ የሶማሌ ክልል ህብረተሰብ በተለይም ባለሆቴሎችና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ይሄ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ሀገርና ኢኮኖሚ የሚጎዳ ህገወጥ ንግድ  ላይ ባለመሳተፍ የተሳተፉ አካላትንም ለህግ አካላት በመጠቆም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው የቢሮው ኃላፊ ማሳሳባቸውን ገልፆ  በሌላ በኩል አደገኛ የሆነውና እየተስፋፋ የመጣ የአደንዛዥ እፅ ዝውውር መኖሩን እና  በዚህ ላይም የፀጥታ አካላት አስፈላጊ የሆነውን ክትትል እና እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ገልፀው  በዚህ ሀገር እና ትውልድ በሚያመክን ተግባር ላይ በየትኛውም ደረጃ በሚሳተፉ ላይ የክልሉ መንግስትና የፀጥታ አካላት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰዱ ኃላፊው ማስጠንቀቃቸውን ከመግለጫው ለመመልከት ተችሏል።
via Somali Fast Info.

@sheger_press
@sheger_press
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በክልሉ የሚካሄደው ግጭት በተለይ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከቶታል ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መጋቢት 29፣ ባሕርዳር ቀበሌ 14 ውስጥ ሶላት ሰግደው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ የነበሩ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች እንደተገደሉ ምክር ቤቱ ገልጧል።

ምክር ቤቱ፣ የሟቾቹ አንድ ጎረቤትም በተመሳሳይ በወቅቱ እንደተገደሉም ጠቅሷል፡። መጋቢት 28፣ በጎንደር ከተማ ማክሰኝት በተባለ አካባቢ አራት ሙስሊሞች ላይ ግድያ እንደተፈጸመም ምክር ቤቱ አመልክቷል፡፡

ከመስከረም ወር ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ሙስሊሞች ተገድለዋል ያለው ምክር ቤቱ፣ መንግሥትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ድርጊቱን እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ነገ የሚዘጉ መንገዶች‼️

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የዒድ አልፈጥር ሰላት እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች!!

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማዋ የዒድ አልፈጥር ሰላት ተሰግዶ እስከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም የይለፍ ፈቃድ ከሌላቸው ተሽከርካሪዎች በስተቀር ከሌሊት 10 ሰዓት ጀምሮ የዒድ ሰላት እስከሚጠናቀቅ

📍 ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
📍 ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው  አጎና ሲኒማ ላይ
📍 ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
📍 ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ፡፡
📍 ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
📍 ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
📍 ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል  አጠገብ
📍 ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ  አቧሬ ሴቶች አደባባይ  ላይ
📍 ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
📍 ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ
📍 ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
📍 ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር  ወደ ብሔራዊ ቴአትር  ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ
📍 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ  የሚዘጉ ይሆናል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቅርቡ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና ማሽኖችን ወደ መገጣጠም እንደሚዘዋወር ተገልጿል፡፡

በነዳጅ እና ቤንዚን የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም ከዚህ በኋላ አስተማማኝ ስራ አይደለም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ ወደሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ፊታችንን ማዞር አለብን ብለዋል፡፡

ከዉጪ የሚገቡ በነዳጅ እና ቤንዚን የሚሰሩ መኪኖችን ለማቆም ዉሳኔ ላይ የተደረሰዉ በአገር ዉስጥ ያሉ ትላልቅ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታታት ነዉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕም እንደዚሀ ዓይነት መኪኖችን ለመገጣጠም አቅም እና ልምድ ያለዉ ነዉ ብለዋል፡፡

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር ሱለይማን ደደፎ በበኩላቸዉ ፤ ግሩፑ የተለያዩ መኪኖችን እና የኢንዱስትሪ ማሽኖችን መግጠም በሚችልበት ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም

@ethio_mereja_news
2024/10/01 19:28:21
Back to Top
HTML Embed Code: