Telegram Web Link
ወይ ዘንድሮ‼️

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወጣት ቢኒያም ከበደ ይባላል።

ሴት መስሎ ራሱን ከቀየረ በኋላ ቃል ብላችሁ ጥሩኝ በማለት በሚቀጠርባቸው ሆቴልና ሬስቶራንቶች ሰዎች ይተዋወቃል።

ከ 6 ወር በፊት በጋምቤላ ሴት መስሎ ተቀጥሮ ስራ እየሰራ እንዳለ ብዙም ሳይቆይ በሰራተኞቹ ጥቆማ ተይዞ ታሰሮ ነበር።

ይህ አልበቃ ያለው ወጣቱ ከዚያ ሲወጣ ደግሞ ዛሬ በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ሴት ነኝ ብሎ ህብረተሰቡን ሲያታልል ለ2ኛ ጊዜ ተይዟል::

ፖሊስ ወንድ ነው ብሏል!!

ትክክለኛ ስሙ ቢኒያም ከበደ ሲሆን
የሴት ስሙ ደግሞ ቃልኪዳን ወርቁ ነው።

ቢኒያም በቀጣይ ለ3ኛ ጊዜ የት ክልልና ከተማ እንደሚሄድ አልታወቀም::

የት ይሄድ ይሆን መልስ ያልተገኘለት ጉዳይ ሆኗል ሸገር ፕረስ።

@sheger_press
@sheger_press
በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገጣጠሙ የመጀሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ!!

አውቶብሶቹን ወደ ስራ ያስገባው በቅርቡ 20 በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ ሚኒባሶችን ወደ ስራ ያስገባው በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ እህት ድርጂት ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ነው። ዛሬ ስራ የጀመሩት አውቶብሶች መነሻቸው ቦሌ ሲሆን መዳረሻቸው በእስጢፋኖስ አራት ኪሎ ስድስት ኪሎ ሽሮ ሜዳ ነው።

@ethio_mereja_news
አሳዛኝ ዜና‼️

በምዕራብ አርሲ ዶዶላ ከተማ ላይ ትላንት ማታ 3:00 አከባቢ የሸኔ ታጣቂዎች አንድ ካህንን ከእነቤተሰቡ እንዲሁም ካገባ ገና ሶስት ወር እንኳ ያልሞላውን ዲያቆን እና አብራው ስትኖር የነበራቸውን እህቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸው ሄደዋል ተብሏል።
ከሁለቱ ቤተሰቦች አጠቃላይ ሰባት ሰዎችን ገድለዋቸው ሄደዋል ብለዋል። አንድ ህፃን እንደ አጋጣሚ ያለቤተሰብ ቀርታ ተርፋለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለስራ ከሲዳማ ክልል የመጡ አራት ወጣቶችም ተገድለዋል ብለዋል። አጠቃላይ 11 ሰው ሞቷል ብለዋል።ጥቃቱ የተፈፀመው ከገብረክርስቶስ ቤተክርስቲያን 50ሜርቀት ላይ ነው ብለዋል። ግድያውን የፈፀሙት በቢለዋና በጥይት ነው ሲሉ የአዩዘሀበሻ ምንጮች ተናግረዋል(አዩዘሀበሻ)።
ነፍስ ይማር

@ethio_mereja_news
የሰአቱ መደመጥ ያለበት መረጃ👇👇
https://youtu.be/GX7O1m9fR2w?si=jrxvHchyWupYiKWp
ለባንክ ጥበቃ የተረከበውን መሳሪያ  ይዞ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ኡፋ ከተማ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት የተሰጠዉን ኃላፊነት ወደጎን በመተዉ  በጥበቃ ሰራተኝነት ከሚሰራበት ቦታ መሳሪያ ይዞ የተሰወረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በደብቡ ምዕራብ  ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር  ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በዳሸን ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ በሚሰራበት ቦታ  ለጥበቃ ስራ አገልግሎት ተሰጥቶት የነበረዉን አንድ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይትና ከአንድ ካርታ ጋር ተረክቦ የነበረው ይዞ መሰወሩ ተገልፆል፡፡

የካፋ ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ የሙስና ነክ ወንጀሎች ተከሳሽ አንዱአለም ብረሃኑ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በፈፀመዉ በስራ ተግባር የሚፈፀም የመዉሰድና የመሰወር ወንጀል ክስ መሰርቶበታል።የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን ሲመለከት ቆይቶ ተከሳሹ በፈፀመው የሙስና ወንጀል በሰዉ እና በኤግዚቢት ማስረጃ  በመረጋገጡ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል ።

በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን ባስቻለዉ የችሎት ተከሳሽ አንዱአለም ብረሃኑ በ1 ዓመት እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲሉ  ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
New_No_repayment_alphabet_593858077e.pdf
339.6 KB
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ አልመለሱም ያላቸውን 565 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል ከታች ያለውን አታችመንት ይመልከቱ።

👆🏼👆🏼👆🏼👆🏼

@sheger_press
መልካም ዜና ለአንባብያን በሙሉ‼️

የሴራ እርካብ!!
የደም መንበር‼️

በታተመ በጥቂት ቀናት ውስጥ በ #Amazon ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሸጥ የነበረው የጋዜጠኛ ያየሰው ሺመልስ መፃፍ እኛ ጋር በpdf ያገኙታል።

ለጥቂት ቀናት በሚቆይ ልዩ ቅናሽ ከኛ ይሸምቱት

መፃፉን ለመግዛት በዚ
አድራሻ ያነጋግሩን 👉 @ethio_journalist
በድሬዳዋ ከተማ ሀዘን ላይ ከነበሩ ወላጆቿ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የዘረፈችው ግለሰብ  በቁጥጥር  ስር ዋለች!!

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም  ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አራት ልዪ ስሙ መብራት ሃይል  አብዩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሀዘን ላይ  ከተቀመጡ ወላጆቿ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት  ዘርፋ ለማምለጥ  የሞከረችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላለች።

ወላጆቿ የስርቆት ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ለፖሊስ አመልከተው የነበረ መሆኑን የአካባቢው  ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ አስተባባሪ  ተወካይ ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን  ተናግረዋል።

ተከሳሿ ግለሰብ በአንድ ትምህርት ቤት አብሯት የሚማሩ ጓደኞቿን ከቤተሰቦቿ ንብረቱን እንዲዘርፉ በመንገር  እና ንብረቱን ሸጠው ከተማ ቀይረው የራሳቸውን ህይወት እንደሚመሩ አሳምናቸው  የነበረ መሆኑ ተጠቁሟል።

ቤተሰቦቿ ሀዘን ላይ ባሉበት ሰዓት ከጓደኛዋ ጋር ተባብራ በሳጥን ተቀምጦ  የነበረ ወድ የሆነ ጌጣጌጥ እና ንብረት ሰርቀው በደላላ አማካኝነት ወርቁን በማሽን አስፈትሸው አብሯት የሰረቀችውን ጨምሮ ሁለት ጎደኞቿን ወደ ሀረር ከተማ  የላከቻቸው መሆኑ ተረጋግጧል ።

ወላጆቿ ጉዳዩን ለፖሊስ ማመልከታቸውን ያወቀችው ልጅ ድርጊቱን መፈጸሟን ፖሊስ ጥርጣሬው ውስጥ  እንዳስገባት ስታውቅ  ድርጊቷን አምና ቃሏን  እንዲሁም ጎደኞቿ ያሉበት ቦታ ልታመለክት ችላለች ።

የድሬዳዋ ፖሊስ ከሀረሪ ፖሊስ ጋር በመነጋገር ባደረገው ጠንካራ ክትትል  በሀረር ከተማ ሆቴል ውስጥ ተከራይተው  በቁጥጥር  ስር ሊውሉ መቻላቸውንና  መዝገቡም እየተጣራ እንደሚገኝ  ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች🕯

አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል 🕯

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና  አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ  ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት  ሰጥቷል።

አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር። (ባላገሩ ቴሌቪዥን)

ኢትዮ መረጃ ለወዳጅ፣ ቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል። Rest In Peace🕯

@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
በድሬዳዋ ከተማ የሶስት አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ለአስራ አንድ ወራት ከህግ ተሸሽጎ እንደነበር የገለጸው የድሬደዋ ፖሊስ
ህጻን ቢሊሱማ መሃመድ የ3 ዓመት ታዳጊ ክፉን እና ደጉን በቅጡ ለይታ የማታውቅ መሆኑን ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ  የእንጀራ አባቷ/ ሲሆን ይሄንን የጭካኔ በትር ከመሰንዘሩ በፊት
የቢሊሱማ መሃመድ እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል አልቻለችም በመሃከላቸው መግባባት ባለመኖሩ ተለያይተዋል።

የቢሊሱማ መሃመድ እናት ወደ ሀሮማያ ከተማ በመምጣት ሌላ ትዳር ትመሰርታለች። ለአጭር ቀናት ቢሆንም ቢሊሱማ መሃመድም በእንጀራ አባቷ ማደግ ግድ የሆነባት ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብ /እንጀራ አባቷ/ አስከፊውን የወንጀል ደርጊት ፈጽሞ እስከተሰወረበት ቀን ድረስ አብራ በጋራ ትኖር ነበር ፡፡

መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን ግን ተከሳሽ የሶስት ዓመት ህጻን ቢሉስማ አስገድዶ ከደፈራት በኃላ ህይወቷን በማጥፋት ከአካባው ይሰወራል፡፡
ግለሰብቡ ድርጊቱን በመፈጸም ከአካባቢው ተሰውሮ ድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ መቆየቱን የመልካ ጀብዱ ፖስ ጣቢያ አዛዥ ም/ኮማንደር ሻምበል ተካኝ ተናግረዋል፡፡

ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው ግለሰብ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡

ተከሳሹ ግለሰብ/እንጀራ አባቷ/ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለምን  ህጻን አስገድዶ በመድፈር ሊገላት እንደቻለ ሲጠየቅ ‹‹ሰይጣን አሳሳተኝ›› በማለት ምላሽ መስጠቱን ፖሊስ አስታውቃል፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ የልጄ ደም ፈሶ እንዳይቀር ስላደረገው ጥረት አመሰግናለሁ ያሉት የቢሊሱማ መሃመድ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሮዳ በክሪ ልጄን አጥቼ በሃዘን ተቆራምጄ ባለሁበት ጊዜ የድሬዳዋ ፖሊስ የልጄን ገዳይ ስለያዘልኝ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አወ‍እሮፕላን በሱማሌላንድ አየር ክልል እየበረረ በሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረ የኤሚሬትስ አውሮፕላን ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ከመጋጨት ለጥቂት ተርፏል ተባለ

በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ  አየር መንገድ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ከነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በድጋሚ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፍ ተሰማ።

ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሰጠዉ ትዕዛዝ በተመሳሳይ የጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ የነበሩት ንብረትነታቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የኢትዮጵያ መንግስት የሆኑት አዉሮፕላኖች በድጋሚ ከመጋጨት አደጋ መትረፋቸው የሶማሌላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለስልጣን ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ባለፈው የካቲት ወር በተመሳሳይ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ አውሮፕላኖች ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ይታወሳል።

እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን UAE722 እና በተመሳሳይ በ 37,000 ከፍታ ላይ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ETH690 ለመጋጨት ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀራቸዉ የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ባደረጉት ጥረት አብራሪው በፍጥነት ከፍታውን በመቀየር ወደ 39, 000 ጫማ ከፍ እንዲል በማድረግ የተፈራው አደጋ ለጥቂት ሳይደርስ እንዲቀር አድርጓል።

በድጋሚ ለተፈጠረዉ ክስተት የሶማሌላንድ የሲቪል አቪዬሽን እና አየር ማረፉያዎች ባለስልጣን  የሞቃዲሾ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የወቀሰ ሲሆን።

መሰል ቸልተኝነት እና የእውቀት ማነስ ሞቃዲሾ በሚገኙ የሱማልያ የአቪዬሽን ባለሞያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ መሆኑን አለም ይወቅ ሲል አክሏል።

ሁኔታውም የአየር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ሁኔታውን ኮንኗል።

Via ካፒታል

@ethio_mereja_news
2024/10/03 17:25:50
Back to Top
HTML Embed Code: