Telegram Web Link
በባሌ ዞን የአልሸባብ ክንፍ ነዉ ተብሎ የተጠረጠረ ታጣቂ ቡድን የፀጥታ ሥጋት መሆኑ ተነገረ

በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የአልሸባብ ክንፍ በመሆን የሚጠረጠር የታጠቀ ቡድን መደራጀቱንና እንቅስቃሴ መጀመሩን በፀጥታ ሥጋትነት የክልሉ ባለሥልጣናት ማስቀመጣቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰማኮ) ዓርብ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ፡፡

በኬንያ፣ በኡጋንዳና በሶማሊያ ኃይሎች ጭምር ይደገፋል የሚባለው ይህ ሸማቂ ኃይል፣ በፖሊሶችና በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጥቃት መክፈቱ ችግሩን እንዳወሳሰበ ባለሥልጣናቱ ስለመናገራቸው ኢሰመኮ በሪፖርቱ አብራርቷል፡፡

የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በአራቱ ሰፋፊ ክልሎች በማሰርና በእስር አያያዝ ሒደት ባለፉት አምስት ዓመታት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በሰፊው የሚዘረዝረው የኢሰማኮ ሪፖርት፣ ከባድ የመብት አያያዝ ጉድለቶችን ማግኘቱን አብራርቷል፡፡ ኢሰብዓዊ አያያዝን ጨምሮ ጭካኔ የተሞላበት ማሰቃየት፣ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት መብታቸው በተገደበ ሰዎች ላይ ስለመፈጸሙ የኢሰመኮ ሪፖርት አሳሳቢ ጉዳይ ነው ሲል አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ነፃነታቸውን በተነፈጉ (በታሰሩ) ሰዎች ላይ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸና ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም. ባሉት አምስት ዓመታት በአራት ክልሎች የታሰሩ ሰዎችን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በገመገመበት ሪፖርት ላይ አብራርቷል፡፡

ኢሰመኮ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ ሥልታዊና የዘፈቀደ እስራት እንደሚፈጸም አስታውቆ፣ በእስር አያያዝ ሒደትም የመብት ጥሰቶች ይፈጸማሉ ብሏል፡፡

በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌና በቀድሞው አጠራሩ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በታሰሩ ሰዎች ላይ ስለሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች የሚዘረዝረው ሪፖርቱ፣ 86 ተጎጂዎችንና ምስክሮቻቸውን ማነጋገሩን ያስረዳል፡፡ በአራቱም ክልሎች አቤቱታ መቀበያ መድረኮችን በማዘጋጀትም የሕግ አካላትንና የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 365 ሰዎችን ያሳተፈ ውይይት ማድረጉንም ያክላል።

በዚህ የምርመራ ሒደትም የዘፈቀደ እስርን ጨምሮ ማሰቃየትና ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ ከሕግ አማካሪ ጋር መገናኘትን መከልከል፣ የቤተሰብ ጉብኝት ክልከላ፣ የመተዳደሪያ ገቢ ማጣት፣ ስለሰብዓዊ መብቶች በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ እንዲሁም ለጥሰቶቹ መፍትሔና ማካካሻ አለመኖርን የመሳሰሉ የመብት ጥሰቶች በታሳሪዎች ላይ እንደሚፈጸም ሪፖርቱ ማረጋገጡን ይገልጻል፡፡

መብታቸው እንዲገደብ የሚደረጉ ሰዎች የመብት ጥሰት በቁጥጥር ሥር ከመዋል ጀምሮ ባለው ሒደት እንደሚያጋጥም በሪፖርቱ ተካቷል፡፡ በፖሊሶች እየተፈጸመ ያለው ‹‹የምትክ እስራት›› ወይም ተጠርጣሪው እስከሚገኝ የቤተሰብ አባልን የማሰር ዕርምጃ፣ ከእነዚህ የመብት ጥሰቶች አንዱ አሳሳቢ ድርጊት እንደሆነ ሪፖርቱ በጉልህ መነሳቱን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል፡፡ የእያንዳንዱን ክልል የታሰሩ ሰዎችን የመብት አያያዝ በተናጠል የሚዘረዝረው በሰባት ምዕራፎች የቀረበው ባለ 113 ገጽ የኢሰመኮ ሪፖርት፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የታሰሩ ሰዎችን መብት አያያዝ ለማሻሻል ቁርጠኛ ሊሆኑ እንደሚገባ ይጠይቃል፡፡

በፈረሰው ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ለዘፈቀደ እስራትና ለተያያዥ የመብት ጥሰቶች ሲዳረጉ የቆዩ ችግሮች ከአስተዳደርና ከወሰን ጋር የተያያዙ ፖለቲካዊ ችግሮች መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ በደራሼ ልዩ ወረዳ፣ በቁጫ፣ በመስቃንና ማረቆ አካባቢዎች ያጋጠሙ ችግሮች ከዚሁ ጋር የተያያዙ ስለመሆናቸው ያብራራል፡፡

በአማራ ክልል ለዘፈቀደ እስራትና ለተያያዥ የመብት ጥሰቶች ዜጎች የተጋለጡበትን ዋና ምክንያት ከፖለቲካዊ ጥያቄ ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ሪፖርቱ ያወሳል፡፡ በርካታ ሰለባዎች ሐሳባችንን በነፃነት እንግለጽ በማለታቸው፣ ተደራጅተው ለመንቀሳቀስ በመሞከራቸው ወይም ፖለቲካዊ ተሳትፎ በማድረጋቸው መታሰራቸውን እንደተናገሩ በኢሰመኮ ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ለዘፈቀደ እስራት ወይም በእስር ወቅት ለሚገጥሙ የመብት ጥሰቶች መነሻ ከሆኑ ችግሮች ዋናው፣ በታጠቁ ቡድኖች የሚጸመው ጥቃት አንዱ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በወለጋ አካባቢ የሚፈጸመው የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት ችግሩን ካወሳሰቡት ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ያስረዳል፡፡

       Via ሪፖርተር ጋዜጣ

 
ሞስኮ ግብረሰዶምን በሸብር ዝርዝር ውስጥ ማስገባቷ ተሰማ።

ሩሲያ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን በአክራሪነት እና ሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ ማከተቷ ተሰምቷል፡፡

የተመሳሳይ ጾታ እንቅስቃሴ አራማጆች በአክራሪነትና በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ  የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘገባ ያመላክታል፡፡

ውሳኔው የግብረ ሰዶማዊያን እና ትራንስጀንደር ተወካዮችን ለእስር እና ለሽብርተኝነት ቅጣት የሚዳርግ ነው ተብሏል፡፡

የሩሲያ ውሳኔ ዓለም አቀፍ የግብረ ሰዶም ማኅበራት እንቅስቃሴ እና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ጭምር ይመለከታል ተብሏል፡፡

በሩሲያ ምድር የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴ ማድረግ ከዚህ በኋላ በሸባሪነት አስከስሶ ዘብጥያ የሚያስወርድ ከባደ ወንጀል ሆኗል፡፡

በአገሪቱ የግብረሰዶማዊ እንቅስቃሴን የሚደግፉና የሚያስፋፉ አካላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይነገራል፡፡

የእንቅስቃሴው አራማጆች መሰረት ሩሲያ ባላንጣ ካደረገቻ ቸው ከእነ አሜሪካና አውሮፓ ምድር የሚነሳ መሆኑ ደግሞ የቭላድሚር ፑቲንን አስተዳደር አስቆጥቷል፡፡

እንደ አሜሪካ ያሉ አገራት የግብረ ሶዶማዊያን እንቅስቃሴን እንደ መብት ቆጥረው እያስፋፋት ነው፡፡ ግብረ ሶዶማዊያነት ከምዕራቡ አለም አልፎ እስከ አፍሪካ የዘለቀ ሲሆን፣ አንዳንድ አገራት እንስቅቃሴውን በሕግ እያገዱ ነው።
via Andafta

@ethio_mereja_news
"ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት "ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል በአገራችን በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚያስችል ልዩ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

የድጋፍ መርሐ ግብሩን በቀጥታ በማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ መከታተል የሚቻል ሲሆን ድጋፍ ለማድረግ የሚከተሉትን የሂሳብ ቁጥሮች መጠቀም ይችላሉ።

በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፦
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
በወጋገን ባንክ - 0837331610101
በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
በአዋሽ ባንክ - 01329817420400
Gofundme
https://www.gofundme.com/f/uerc8?utm_campaign=p_cp+share-sheet&utm_medium=copy_link_all&utm_source=customer&utm_term=undefined
Wegenfund
https://Www.wegenfund.com/mknu

ለበለጠ መረጃ
. +251 9 43 00 04 03
. +251 9 26 41 31 12

@ተ.ሚ.ማ

@sheger_press
@sheger_press
ዙምባቤ

ይህ ምስል ዛሬ በሶሻል ሚድያ ሲዘዋወር የዋለ ምስል ነው።

የቀድሞው ፕ/ት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም ከልጃቸው ጋር የተነሱት ምስል ነው።

የቀድሞው አለቃ እርጅና የተጫጫናቸው ይመስላል።

@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
#Adwa

በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታፈነች / የታገተች ታዳጊን ተማሪ ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባታል። አፈናው ከተፈፀመ 5 ቀናት ሆኖታል።

የአፈናው ድርጊት አፈፃፀም እና የጉዳዩ አሳሳቢነት ምን ይመስላል ? 

እሮብ መጋቢ 11 ቀን 2016 ዓ/ም የ16 አመት ታዳጊ ተማሪዋ ማህሌት ተኽላይ ቀን ትምህርት ውላ አመሻሽ ቋንቋ ወደ ምትማርበት ማእከል ብቻዋ በመጓዝ ሳለች ባጃጅ ይዘው በመጡ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች አፍነው ወሰድዋታል።

ተማሪ ማህሌት ከቋንቋ ት/ቤት እንደልማድዋ በሰአትዋ አለመመለስዋ ቤተሰቦችዋ ተጨንቀው እያለ ወላጅ አባትዋ የልጃቸው የሞባይል ስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል።

በልጃቸው የሞባይል ቁጥር የተደወለባቸው አባት በወላጅ በስስት ' ልጄ ' ብለው ሞባይላቸው ያነሳሉ።

በሞባይል የሰሙት ድምፅ ግን ከዚህ በፊት ሰምተውት የማያውቁ የወንድ ድምፅ ነበር።  ድምፁ በመሃል የልጃቸው ለቅሶ ፣ ፍርሃትና የ 'አስለቅቁኝ ' ልመና አሰማቸው።

ቀጥሎ የልጃቸው ድምፅ በማራቅ " ልጃችሁ በቁጥጥራችን ስር ናት፤ መልሳችሁ በህይወት ልታገኙዋት ከፈለጋችሁ 3 ሚሊዮን ብር ክፈሉ ፤አለበለዚያ እንገድላታለን " የሚል የማስፈራርያ  ድምፅ ካሰሙ በኃላ ስልኩን ይዘጋሉ።

የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተማሪ ማህሌት ተኽላይ የመጥፋት ጉዳይ ወደ አባትዋ ደውሎ ይህ መረጃ እስካዘጋጀበት ቀንና ሰዓት ድረስ ታዳጊዋ ማህሌት ከቤት ወጥታ ከቀረች 5 ቀናት ተቆጥረዋል።

የታዳጊዋን ማህሌት ቤተሰቦች እንባ ለማበስና እንቅልፋቸውን ለመመለስ የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ታዳጊዋን አፍነው የወሰዱ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፍለጋ እያካሄደ ነው።

ጉዳዩ እጅግ ያሳሰባቸው የተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፥ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ጉዳይ በማንሳት እየተወያዩበት ይገኛሉ።

" ልጆች አፍኖ ገንዘብ የመጠይቅ ፋሽን መቼ ነው የሚቆመው ? " የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ባለፈው ጥቅምት 2016 ዓ.ም ሚልክያስ ፋኑስ የተባለ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ ህፃን ታግቶ ለማስለቀቅ 4 ሚሊዮን ብር  ተጠይቆበት ፤ በፓሊስ ክትትል ከ12 ቀናት ፍለጋ በኋላ ሊገኝ ችሏል።

በመቐለ ከተማ የዓይደር ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ9 አመቱ ሳሚኤል መሓሪ ከበደ ደግሞ ባለፈው ወርሃ የካቲት 2016 ዓ.ም በጠላፊዎች ታግቶ ከተወሰደ በኃላ እንደዲመለስ 4 ሚሊዮን ተጠይቆበታል ቢሆንም ፓሊስና ህብረተሰብ ባደረጉት የተቀናጀ እልህ አስጨራሽ ጥረት ከአንድ ሳምንት በኃላ ተገኝቷል። በድርጊቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                               
@ethio_mereja_news
" ካልፈረሰ ሌላ አማራጭ የለም " - ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)
**
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከታማኝ ከፍተኛ  የግብር ከፋዮች / ባለሃብቶች ጋር በነበራቸው ምክክር ወቅት ከሰሞኑን በአዲስ አበባ እየታየ ስላለው ፈረሳ አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

" ብዙ ቦታ እየፈረሰ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " ለምንድነው? የምትሉ ከሆነ የወደፊት የኢትዮጵያም፣ የአፍሪካም፣ የዓለምም የኢኮኖሚ አቅጣጫ 70 እና 80 ፐርሰንት አይቲ እና ቱሪዝም ነው። ሃብት ያለውም እዛ ነው ቱሪዝም እና አይቲ ደግሞ ኤርጎኖሚክስ በጣም ትልቅ ተፅእኖ ያደርግባቸዋል። የተስተካከለ አካባቢ ካልሆነ ይረበሻሉ " ብለዋል።

አዲስ አበባን መቀየር ካልተቻለ የሚታሰበውን ያህል የውጭ ሀብት ማምጣት አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል።

" ዱባይ እንዴት ገንዘብ እንደሄደ ታውቃላችሁ፤ መሰረተ ልማቶች የሚታዩ ነገሮች በጣም በከፍተኛ ደረጃ ሃብት ይስባሉ " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ" አሁን የሚፈርሰው እንደሚባለው አይደለም። እኛ ብዙ አንቆይም ቢገፋ 5 እና 6 ወር ነው እንጨርሳለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የቦሌው መንገድ እኛ የምናስበው ብዙ ሀገር ሲኬድ እንዳሉት ዎክ ማድረጊያ ያለው መንገድ እንዲሆን ነው " ያሉ ሲሆን የመንገዱ መስፋት አብዛኛው ሰው እግረኛ ስለሆነ እንደሚጠቅም ገልጸዋል። መንገዱ የባይክ ሩትም እንዲጨመርበትና #ሰፊ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ከቦሌው መንገድ በተጨማሪ የሚክሲኮ መንገድ፣ የመገናኛ ጫካ ሲኤምሲ መንገድ ዋና ዋናዎቹ  እንደሆኑም ጠቁመዋል።

" አዲስ አበባ ላይ ትልቁ ድህነትና ችግር ያለው መሃከል ላይ ነው፤ መርካቶ፣ ፒያሳ፣ ሜክሲኮ የሚባለው ነው። ሲኤምሲ፣ ለቡ እንደዛ አይደለም ዋናው ችግር ያለው መሀከል ነው ዋናውን ችግር ደፍረን ካፈረስነው በ5 ዓመት ከተማው ምን እንደሚመስል ታዩታላችሁ " ብለዋል።

" በዚህ ሂደት፦

-በግለሰብ ደረጃ አጥሬ ተነካብኝ ብለው የሚያዝኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ

-ባለስልጣናትም ያስቸግሩናል አጥር ሲነካባቸው የሚፈርስባቸው ብዙ ስለሆነ፣ የመንግስት ቤቶች ስለሚፈርሱ

-የመንግስት ኪራይ ቤቶች የሚያከራየውም ይጮሃል

-የቀበሌ ቤት የሚያከራየውን ይጮሃል... ብዙ ነው ጩኸት ያለው። ጨክነን ካላፈረስን ግን ሀገር አይሰራም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የአዲስ አበባን ለውጥ በአንድ አመት እናየዋለን፤ ያኔ ቱሪስት በደንብ ይመጣል። ያኔ የባላሃብቶች ንብረት ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል " ብለዋል።

እየተካሄደ ያለውን ስራ ባለሃብቶቹ እንኳን በትዕግስት እንዲጠብቁ የጠየቁት ዶ/ር ዐቢይ " ከማማት ውጡ፣ አፈረሱት ምናም የሚለውን ትታችሁ በትዕግስት ጠብቁን በአንድ ውስጥ ከተማውን ካለበት ደረጃ ከፍ እናደርገዋለን የዛኔ ልጆቻችሁን ዱባይ ከምትወስዱ ታቆያላችሁ እዚህ " ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ ጠ/ሚኒስትሩ እየፈረሱ ባሉ ቦታዎች ፋይበር እንደሚቀበር እና ውጭ ላይ የሚታዩት ሽቦዎች እንደሚቀበሩ ተናግረዋል።

" ቦሌ ላይ ይሁን ፒያሳ መንገድ የምናፈርሰው አሮጌ ቤት ብቻ አይደለም። እዛው ላይ ፋበር እንዘረጋለን፣ እዛው ላይ በየቦታው ያለውን ሽቦ እንቀብራለን፣ የውሃ መስመር እንዘረጋለን ዩቲሊቲስ በቢሊዮን እያወጡ ነው ያሉት " ብለዋል።

" አዲስ አበባ ውስጥ ከ4 ኪሎ አንስቶ እስከ ሜክሲኮ ቢነዳ ብርሃን አለ ጨለማ አለ፤ ብርሃን አለ ጨለማ አለ መብራት ዘላቂ ሆኖ አይታይም፥ ይህ መሰረተ ልማቱን ካልቀየርነው በስተቀር ሽቦው የተቀጣጠለ ስለሆነ ኃይል እና ዳታ (ኢንተርኔት) አክሰስ ማድረግ አይቻልም " ሲሉ አስረድተዋል።

አሁን እየፈረሰና እየተሰራ ያለው ስራ የሚቋረጠውን ኃይል እንዲሁም የኢንተርኔት ዳታ ችግርን ለመፍታትም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።

" ካልፈረሰ ሌላ አማራጭ የለም " ብለዋል።
tikvah እንዳጋራው

@ethio_mereja_news
ሰው መኖሪያ ግቢ ዘሎ በመግባት የመኪና ዕቃ ስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በ 5 ዓመት በፅኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሹ ኢብራሂም ሻፊ አይባላል፤ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዪ ቦታው ጦር ኃይሎች ጋና ኤምባሲ ጀርባ በሚገኘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡

የግል ተበዳይ ሃያት መሃመድ ለፖሊስ በሰጡት ቃል በግምት ከንጋቱ 11 ሰዓት የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-B-58544 የሆነ የግል መኪናቸው የግራ ሰፖኪዬ ገንጥሎ ሲያመልጥ ባሠሙት የድረሱል ጥሪ በፖሊስና በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ሊያዝ ችሏል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከአጉስታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የተከሳሽ ኢብራሂም ሻፊን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ምድብ ችሎት ተከሳሹ ከቆመ ተሽከርካሪ ላይ የዋጋ ግምቱ 30 ሺ ብር የሆነ የግራ ስፖኪዮ የሰረቀ መሆኑ በማስረጃዎች ጥፋተኝነቱን በማረጋገጥ በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

የተለያዩ ስልቶችንና አጋጣሚዎችን በመጠቀም በተለይም በለሊቱ ክፍለ ጊዜ የጥበቃ ሠራተኞች የሚዳከሙበትን ሰዓት በመለየት ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች ስለሚኖሩ ባለንብረቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ እና ተፈፅሞ ሲገኝም ወንጀለኞች በቀላሉ እንዲያዙ ለማስቻል መረጃ እና ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ በፀጥታው ስራ ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ዳጉ_ጆርናል
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ለጥንቃቄ ‼️

መርካቶ ሱማሌ ተራ፣ጭድ ተራ እስከበርበሬ ተራ ድረስ በመኪና ሲያልፉ ብዙ የመኪና ቁልፍ እያሳዩ ቁልፍ ከፈለጉ ይባላሉ:: መስታውት ወይ ስፖኬዎ ተሰብሮ ካዩም ይሄ ነገር ካስፈለገ አለን ይሏችሁ እና ዋጋ ተስማምታችሁ ስትቆሙ ሞዴሉ የሚታየው ውስጥ ነው ብለው መሪውን ከፈቱ በኋላ የሆነ ነገሩን አበላሽተው የተሰበረ እቃ እንዳለ እና መግዛት እንደሆነ አማራጫችሁ ከዛ ውጭ መኪናው መነሳት እንዳይችል በማድረግ እና በመናገር በጠራራ ፀሃይ ይዘርፏችኋል።

በደህናው ጊዜ እዚሁ አካባቢ አስርቼ አውቃለሁ በአሁኑ ግን ያጋጠመኝን ማጭበርበር ልንራችሁ። ቁልፌ ድንገት ይሰበራል ትናንት በዚሁ ሳልፍ ቁልፍ ከፈለክ ብለው ይጠሩኛል። በዚሁ ላስቀርፅ ብዬ እቆማለሁ። መኪና ብዙ ስለሆነ ማቆሚያ ማግኘት ከባድ ነው። የኔ ደግሞ ጫፉ ተሰብሮ ውስጥ ስለሆነ ወቶ ነው ተቆርጦ ከቀረው ጋር የሚቀረፅልኝ ለሱ ቦታ ይዠ መቆም ይኖርብኛል እነሱም በሚተባበር ሙድ ና ጥላው ላይ ምናምን ብለው ወደውስጥ ገባ ያለ ቦታ አስቆሙኝ እና ተሰብራ የቀረችውን ለማውጣት መሪውን ፈቶ መሪው ላይ ያለውን ቁልፍ ይፈታል።

ከዛ ቁልፉ የሚገባበት ቁልፍ አጫዋች ያሉትን ፈቶ እያሳየኝ ይሄ ተሰብሯል ጥሩ አጋጣሚ ነው የመጣህው ድንገት እየነዳህ ይቆልፍብህ ነበር ይለኝ እና እዚሁ ታገኛለህ ብሎ የተሰበረውን ይዘን ብዙ ቁልፎች እና መለዋወጫዎች ያሉበት ሱቅ ይሄ ነገር አለህ ብሎ ይጠይቃል። አለኝ በኦርጅናሉ 16 ሺህ ብር ይለኛል። ስቄ ቁልፍ ለማስቀረፅ ነው የመጣሁት ይሄኛውን ያላሰብኩት ወጭ ነው ተረጋግቼ አሰራዋለሁ መልሰህ ግጠምልኝ አልኩ።

አይሆንም አሁንማ ተነካ ይቆልፋል ግዴታ መገዛት ነው ያለበት ሌላ መኪናው የሚነሳበት አማራጭ ቆላፊ የሚባል የ 30 ሺህ ብር እቃ ቆርጦ ማውጣት እና በኤሌክትሪክ ሾርት አድርጎ ማስነሳት ነው። እሱ ከተቆረጠ ሌላ ጊዜ 30ሺህ ገዝተህ ነው ሚገጠመው አሉኝ። ሌላ 3ዐ ሺህ ከማወጣ ብዬ የ 16 ሺውን እንድደፍር ነው በዚህ መሃል 14 ሺህ አድርግለት እያሉ ይለምኑታል ሳያስበው ለቁልፍ መጥቶ አይነት እንዳዘኑ ሆነው ይከራከራሉ😁

ከዚህ በኋላ እኔ እነሱን ትቼ የማውቃቸው መካኒኮች ጋር ስልክ ደወልኩ የት ይገኛል ይሄ እቃ ስል ከ 3000 እንደማይበልጥ ግን የሄድኩበት ቦታ ስህተት እንደሆነ ነገሩኝ። እኔም ቅርብ ያለ ማውቀው ደንበኛዬን ና ድረስልኝ አልኩ እና እነሱን አትድረሱብኝ ብዬ መኪናዬ ውስጥ ተቀመጥኩ ግን ሊተውኝ ፈቃደኛ አይደሉም ከአንዱ ጋር ስጣላ አንዱ ጓደኛው መጥቶ ገላጋይ ይሆንና እሱን ተቆጥቶ በቃ እኔ በ10 ሺህ ላስመጣልህ ይላል አልፈልግም መካኒኬን ጠርቻለሁ ሲመጣ አይቶ ይገዛችኋል ብዬ ገገምኩ።

እነሱ ግን እየተቀያየሩ ሊተውኝ አልቻሉም። ሃሳባቸው እንደገባኝ ተናገሬ ካልሆነ አስጭኘ እሄዳለሁ እንጅ ምንም የምገዛቸው ነገር እንደሌለ  መኪናው መነሳት እንኳን ባይችል አስጨኘ መሄድ እንደምችል ነገርኳቸው።

እነሱ ግን  በዚህ መልኩ እየተቀያየሩ በግድ እየተደራደሩኝ 16ሺህ ያሉትን እቃ 4ሺህ አደረሱት አሁንም እንደማልከፍል ነገርኳቸው። የዚህ ጊዜ ጓ ብለው ወንድ የሆነ መካኒክ እዚህ ቦታ ይሰራል ስራችን ላይ ብለው ፎከሩ! ብዙ ስለሆኑ መካኒኩንም እንደማያሰሩት ሲገባኝ ፖሊስ መንገድ ላይ ካገኘ ይዞ እንዲመጣ አደረኩ እዛው አካባቢ ያሉ 2 ፖሊሶች አዘጋጀን።

ለፖሊሶቹ የሆነውን አስረድቼ ካላሰሩን ልንጠራቸው ተነጋግረን መካኒኩን ተቀብዬ ወደመኪናው ስንመጣ አንተ አትናገረን ብለሃል አንደርስብህም አሉኝ እና አንተ ና ብለው መካኒኩን ከበቡት እና አትገባም አሉት። ከዛ ወደኔ ዞረው ሂድ ጥራ ፖሊሶቹን አሉኝ ፖሊሶቹን ሳናግራቸውም ይከታተሉኝ ነበር ከዛ መካኒኩ አይሰራም ተብሎ ፖሊሶቹም ከነሱ ጋር ተስማማ እንደአበላሹ ያስተካክሉ ተብሎ  ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ መኪናዬን ይዠ ወጥቻለሁ። 

በጣም የገረመኝ ነገር ጭድ ተራ ጋር ነው የቆምኩት እና ይሄ የተፈጠረው። እና ይሄ የመጣልኝ መካኒክ እስኪደርስ ሌላ አንድ መካኒክ አማክሬ ወደላይ በርበሬ ተራ የሚባለው ጋር እቃውን እንደማገኝ ነግሮኝ አብሮኝ ሰው ስለነበር መኪናው ጋር እሱን ትቼ ልገዛ ሄድኩ ወደተባለው ቦታ የሁሉም መልስ አባቴ ይሄ የለንም! ነው። የት አገኛለሁ ስላቸው ያስፈታህበት ቦታ ተደራደር ነበር የመለሱልኝ እነዚህ ሌቦች ከላይ እስከታች የሚግባቡበት ኮድ አላቸው። ሌላ ሰው እንዳይሸወድ ሼር አድርጋችሁ አድርሱልኝ🙏

ባለታሪኩ Teddy Getnet ነው ።

@sheger_press
ጎንደር ላይ ዘመቻ ዉባንተ እንደቀጠለ ነዉ። ደሴ ከበባ ዉስጥ ማስገባታቸውንም የምስራቅ አማራ ፋኖ ገልፆል።👇👇
የሰአቱ ሰበር ጥብቅ መረጃ ሸር አርጉትማ https://youtu.be/9gbA9CqsWEo?si=s4kq7lM2MwvVI5gm
በመንገድ ግንባታ ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር በተለይም በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጪ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
• ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
🚨 ATTENTION 🚨

Friends, I asked for a special link from binance free vip channel, don't miss

Only 100 Members Exclusive Link 👇👇👇

https://www.tg-me.com/+tY1KS_VpiFozNWZi

LIMITED TIME OPEN LINK
የኢትዮጵያ መንግሥት “የውጭ ሀገር ሰዎች የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ” የሚፈቅድ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች ቤት እንዲገዙ የሚፈቅደው ሕግ ዝግጅት “የመጨረሻው ደረጃ ላይ” እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከሌላቸው በቀር የንብረት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚከለክለው አሰራር እንደሚቀየር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተናገሩት “ታማኝ” ከተባሉ ግብር ከፋዮች መካከል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

መንግሥት  በሚቆጣጠሯቸው መገናኛ ብዙኃን ትላንት ቅዳሜ ምሽት በተላለፈው ማብራሪያ ዐቢይ በመቋቋም ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ “ቢበዛ በሁለት ወራት ውስጥ” ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል።

ካፒታል ገበያው ሥራ የሚጀምረው የኢትዮ-ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ በማቅረብ ይሆናል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ በክልሉ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ መሬት ላልወሰዱ የክልሉ መምህራን ቦታ እንዲሰጣቸው መመሪያ ማስተላለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ከዚህ ቀደም ለክልሉ መምህራን በገጠር ተሰርቶ ያለቀ ቤት እንዲኹም በከተሞች የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መመሪያ ወጥቶ እንደነበር የጠቀሰው ቢሮው፣ ከመሬት አሰጣጥ ሂደት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ታግደው እንዲቆዩ በመደረጉ መምህራኑ መሬቱን እንዳልወሰዱ አስታውሷል።

ኾኖም በቢሮው ጥያቄ መሠረት፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት እገዳውን ላንድ ጊዜ ብቻ በማንሳት መኖሪያ ቤት የሌላቸውና የቤት መስሪያ ቦታ ያልወሰዱ መምህራን መሬት እንዲሰጣቸው ማዘዙን ቢሮው ገልጧል።

@ethio_mereja_news
የሰኞ ምሺት መደመጥያለባቸው የግንባር ዉጊያ ዉሎ መረጃዎች ከአማራ አራቱም ክፍለ ግዛቶች 👇👇👇ይከታተሉ
https://youtu.be/g79jGZs_GAE?si=hM-zVurVGQddwxKV
2024/10/03 19:28:23
Back to Top
HTML Embed Code: