Telegram Web Link
"በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠዉ የፋኖ ሀይሎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በፈጸሙት ዉድመት ነዉ " ሲል የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሰ

ከሰሞኑ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በደረሰ ጉዳት የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች ሀይል እንደተቋረጠባቸዉ ይታወሳል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በትናንትናው እለት ባሰራጨዉ መግለጫ ለዚሁ ዉድመት እና የሀይል መቋረጥ "ፅንፈኛ" ሲል የጠራቸዉ "የፋኖ ሀይሎችን" ወንጅሏል። ፖሊስ ኮሚሽኑ በመግለጫዉ "ፅንፈኛ አሁን ደግሞ ክልሉን ወደ ጨለማ ለመክተት አልሞ እየሰራ ይገኛል " ብሏል።

የካቲት 26/2016 ዓ/ም እኩለ ቀን አካባቢ ከባህር ዳር - ደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በንፋስ መውጫ አካባቢ አንደኛው ፌዝ በመሳሪያ በመምታቱ ከሠዓት በኋላ ጀምሮ አብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢ የመብራት አገልግሎት እንዲያጣ አድርጎታል ብሏል ፖሊስ ኮሚሽኑ። ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው እንደተመለከተዉ ፤ የፋኖ ሀይሎች በቀጣይም "የህዝብን ስቃይና ምሬት የሚጨምሩ ተግባራትን በመፈፀም መንግስት እንዲህ አደረገ ለማለት በዝግጅት ላይ እንዳለም መረጃዎች ያሳያሉ" ብሏል። ሆኖም በመግለጫው ዝግጅት እየተደረገባቸዉ ያሉ ነገሮችን ፖሊስ ኮሚሽኑ አልጠቀሰም።

ፖሊስ ኮሚሽኑ "በስንት ትግል ከአርሶ አደሩ ደጅ የደረሰውን ማዳበሪያ በነፃ ስለምትወስዱ ከመንግስት አትውሰዱ በሚል የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ከፍተኛ ብጥብጥና ፍጅት ለመፍጠር ሙከራዎችን በተለያዩ አካባቢዎች እየፈጠረ ይገኛል" ሲል መዉቀሱን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫዉ ታዝቧል። የክልሉ ነዋሪዎች መሰል ድርጊቶችን ሲያዩ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ እንዲሰጡትም ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከባህር ዳር - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ እንዲሁም ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችም ላይ  የኤሌክትሪክ ሀይል ተቋርጧል ማለቱ ይታወሳል።

በዚህም ሳቢያ ከኮምቦልቻ በባቲ በኩል ኤሌክትሪክ ኃይል የሚደርሳቸው የአፋር ክልል መዲና ሠመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል የሚያገኙት የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ዋና ከተማ ፈረስቤት ትናንት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ቀኑን ሙሉ ከባድ ውጊያ ሲካሄድ መዋሉን ዋዜማ ከነዋሪዎች ሰምታለች።

በከተማዋ መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የጸጥታ ኃይል ጋር በመተባበር፣ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ከጧቱ 1:00 ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት የዘለቀ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ሲያካሄዱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በግጭቱ በከተማዋ በርካታ መኖሪያ ቤቶች በከባድ መሳሪያ ተመተው መፈራረሳቸውንና ቤታቸው ውስጥ የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ከከተማው ወጣ ብለው በሚገኙ አንዳንድ ገጠራማ ቀበሌዎች ዛሬም የተኩስ ልውውጥ መኖሩን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ፣ በከተማዋ ግን ዛሬ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልጠዋል።

በክልሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ በፈረስቤት ከተማ ተደጋጋሚ ከባድ ግጭቶች ተካሂደዋል።(wazema)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
News Alert‼️

የተበጠሰው የባህር ዳር - ጋሸና - አላማጣ መስመር በእልህ አስጨራሽ ርብርብ መጠገኑ ሸገር ከኮምኒኬሽን ዘርፉ ሀላፊዎች ሰምቷል።

ትናንት ጉዳት ደርሶበት የተበጠሰው የባህር ዳር - ደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በከፍተኛ ርብርብ መጠገኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ፡፡

በዘርፉ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንዳስታወቁት ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በተከናወነው የጥገና ሥራ የተበጠሰውን መስመር መልሶ የማገናኘቱ ሥራ ማምሻውን ተጠናቋል።

የባህር ዳር ወልዲያ ኮምቦልቻ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክትን በመገንባት ላይ የሚገኘው ታታ ሊሚትድ ማሽነሪ ከማቅረብ ባለፈ ባለሙያዎቹ ከሪጅኑ የጥገና ባለሙያዎች ጋር እንዲሳተፉ ማድረጉን ተናግረዋል።

ጥገናውን ተከትሎ የክልሉ መዲና ባህርዳር፣ ጎንደር እና ሌሎች ከተሞች እንዲሁም የትግራይ መዲና መቀሌና ሌሎች ከተሞች ዳግም ኃይል ማግኘታቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ወልዲያ፣ ኮምቦልቻና በአካባቢው ያሉ ከተሞች እንዲሁም በኮምቦልቻ በኩል ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር መዲና ሠመራ እና ሌሎች ከተሞችን ለማገናኘት ጥረቱ ቀጥሏል።

በጥገና ሥራው ላይ ለተሳተፉ  የሪጅኑ ባለሙያዎችና ለታታ ሊሚትድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@ethio_mereja_news
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በጤናው ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ መንግሥታዊ ያልኾኑ ዓለማቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች በጸጥታ ሳቢያ ለቀው መውጣታቸውን የዞኑ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ለዋዜማ ገልጧል።

የዞኑ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አሠፋ መሥፍን፣ ዎርልድ ቪዥን፣ ዋን ዋሽ እና ኮ ዋሽን የመሳሰሉ ዓለማቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው አማጺ ቡድን በዞኑ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ከአምስት ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ለቀው ወጥተዋል በማለት ለዋዜማ ተናግረዋል።

በዞኑ በተለይ የከፋ የጸጥታ ችግር ባለባቸው ደራ፣ ያያ ጉለሌ፣ ደገም፣ ሂደቡ አቦቴ እና ኩዩን ወረዳዎች ድርጅቶች፣ የጤና አገልግሎቱን በብዙ መንገድ ሲደግፉ እንደነበር ሃላፊው ገልጸዋል።

አሠፋ፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ ከአካባቢው መውጣታቸው በጤና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የፈጠረው ክፍተት ቀላል እንዳልኾነ ጠቁመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በገላና ወረዳ የጸጥታ ችግር ወደ ሐዋሳ የሚያደርሰው መንገድ መዘጋቱ ተገለጸ

በምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ አንዳንድ ቀበሌዎች፣ “ኦነግ ሸኔ” ሲሉ በጠሩት ታጣቂ ቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የገለጹ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት፣ ከአማሮ ኬሌ- ቶሬ - ይርጋጨፌ - ዲላ ወደ ሐዋሳ የሚያደርሰው መንገድ መዘጋቱን እና የሰላማዊ ዜጎች እንቅስቅሴ መገደቡን ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የጸጥታ እና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ጂኦ፣ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ቃል ቢገቡም ስብሰባ ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጽ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ከመላክ በቀር ማብራሪያ አልሰጡንም፡፡

የምዕራብ ጎጂ ዞንን በሚያጎራብተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አበበ ጣሰው፣ ላለፉት አራት ቀናት መንገዱ የተዘጋበት ምክንያት፣ እርሳቸው ኦነግ ሸኔ ያሉት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አካባቢውን በመውረሩ እንደኾነ መስማታቸውን ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃለ አቀባይ እና በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ የሚኖሩት ኦዳ ተርቢ፤ ቡድናቸው ለተከሰሰበት ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።(#VOA)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህውሀት‼️

“ህወሓት ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው፤ ጦርነት እየቀሰቀሰ ነው” የሚሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ንግግሮች ከእውነታው የራቁ እና ተራ ስም ማጥፋት ናቸው - ህወሓት

ህወሓት ትላንት ማምሻውን ባሰራጨው መግለጫ ፣ አንዳንድ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ተመሳሳይ ኢላማ ያነገቡ አቻዎቻቸው “ህወሓት ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው፤ ጦርነትም እየቀሰቀሰ ነው” የሚል ዘመቻ ከፍተዋል ሲል መዉቀሱን ሸገር ከመግለጫው ተመልክቷል።

እነዚህ መግለጫዎችና መጣጥፎች ከእውነታው የራቁ እና ነጭ ውሸቶች ናቸውም ብሏል ህወሓት።

ዘመቻው በህወሓት ላይ ብቻ ሳይሆን በአመራሩና በትግራይ የጸጥታ ሃይሎች ላይም እየተካሄደ ነውም ብሏል። ከሰሞኑ ባይቶና ፓርቲ ፤ ህወሓት በሚቀሰቅሰዉ የትኛውም አይነት ጦርነት ራሱን ችሎ የሚዋጋዉ ነዉ ሲል መግለጹን ሸገር መዘገቡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሸኔ ቡድን ከአደረጃጀቱ እየፈረሰና ለሰራዊቱ እጅ እየሰጠ ነው ሲሉ በማዕከላዊ ዕዝ የአንድ ኮር አዛዥ ተናገሩ።

የኮር አዛዡ ብርጋዲየር ጀኔራል ደስታው ተመስገን በያዝነው የየካቲት ወር የመጨረሻ ሳምንት ብቻ 22 የሽብር ቡድኑ አባላት ለሠራዊቱ እጅ መስጠታቸውን የገለፁ ሲሆን የተሰነዘረበትን ወታደራዊ ጥቃት መቋቋም ያልቻለው አሸባሪ ቡድኑ ተበታትኖና ተደብቆ ለመንቀሳቀስ ተገዷል ብለዋል።

ኮሩ የሃገሩን ሰላም ለማረጋገጥ ተቋማዊ ተልዕኮውን በድል ለማጠናቀቅ አሸባሪዎችን ተከታትሎ የመደምሰስና ቀጠናውን ከስጋት ነፃ የማድረግ ግዳጁን በጀግንነት እየፈፀመ ነው ሲሉ ጀነራሉ መኮንኑ ተናግረዋል።

እጃቸውን ከሰጡ የአሸባሪ ሃይሉ አባላት መካከል አብዱ ከማል ( ጃል ጢቂ ) አንዱ ሲሆን አቃፊነት መገለጫው ከሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወልጀ ልዩነትን አብዝቶ ከሚሰብክ ሰላምን ከሚፀየፍና ንፁሃንን መጨፍጨፍ መለያ ባህሪው ካደረገ አሸባሪ ቡድን ጋር አባል በመሆን ያሳለፍኩት ጊዜ ስህተት መሆኑ ስለገባኝ ለመከላከያ ሠራዊቱ እጀን ለመስጠት ተገድጃለሁ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከምዕራብ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ መሆኑን መንግስት አስታወቀ!

ከምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የመንግስት ኃይል መካከል በነበረ ግጭት ከመኖሪአይ ቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ ነው ተባለ።

የብሔራዊ ዜና አገልግሎት ድርጅቱ የዞኑን ቡሳ ጎኖፋ ጽፈት ቤት ኃላፊ ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ በአንደኛ ዙር 601 አባ ወራዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው መባሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። በዚህም ከዞኑ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ 313 አባ ወራዎች ወደ መኖሪያቸው ተመልሰዋል ተብሏል።

በመንግስት በኩልም ለተመላሾች ድጋፍ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ዘገባው ተፈናቃዮቹ ከየት አካባቢ እንደተመለሱ የጠቀሰው ነገር የለም። በጥር ወር መጨረሻ በምዕራብ ወለጋ በአከባቢው የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይል በጠራው የእንቅስቃሴ ገደብ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉ የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ በወቅቱ በሰጠው መግለጫ "ሸኔ" ሊፈጥረው የነበረው መስተጓጎል "ከህዝቡ ጋር" ማክሸፍ ተችሏል ሲል መግለጹን አይዘነጋም። (አዲስ-ማለዳ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ScamAlert‼️

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ስም እየተፈፀመ ያለ የማጭበርበር ድርጊት

ከ180,000 በላይ ተከታይ ያለው አንድ ቬሪፋይድ የሆነ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እየሰበሰበ ይገኛል።

በ15 ቀን ፖስፖርት ለማግኘት 4,500 ብር፣ በ10 ቀን 6,800፣ በ5 ቀን 8,000 ብር እና በ2 ቀን 12,000 ብር በግል የንግድ ባንክ አካውንቶች እየሰበሰቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ብቻ ለኢትዮጵያ ቼክ በደረሱ ጥቆማዎች ገንዘብ እየተሰበሰቡባቸው ያሉት አካውንቶች "አስረስ" በተባለ ግለሰብ የአካውንት ቁጥር 1000533898908 እንዲሁም 'ህይወት' በተባለች ግለሰብ የአካውንት ቁጥር 1000522976303 ናቸው።

እነዚህ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኛ በመምሰል ግለሰቦችን የሚቀርቡ አጭበርባሪዎች የቴሌግራም አካውንታቸው እውነት እንዲመስል ለቴሌግራም ክፍያ በመፈፀም ቬሪፋይድ አስደርገዋል። ፖስፖርት ለማግኘት በጣም እየተንገላታ ያለውን ህዝብ ታርጌት በማድርግ እየመዘበሩ ይገኛሉ።

በዚህ ዙርያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለማናገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፣ መረጃው ግን ከማስረጃው ጋር ቀርቧል። ቢያንስ እነዚህ አካውንቶች የእነሱ እንዳልሆኑ ለህዝብ ሊያሳውቁ፣ በስማቸው ህዝብን የሚዘርፉትን ደግሞ በህግ ሊጠይቁ ይገባል እንላለን።

Via- EthiopiaCheck

@sheger_press
@sheger_press
ኦብነግ፣ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ የንጹሃን ደም እየፈሰሰ መኾኑን ዛሬ በ"ኤክስ" ገጹ ባወጣው አጭር መልዕክት አስታውቋል። "ኦጋዴን ውስጥ በሚፈሰው ደም የሚደሰቱ አካላት ይኖራሉ" ያለው ኦብነግ፣ ኾኖም እነዚህ አካላት "አንድ ቀን የእኛ ጊዜ እንደሚመጣ መርሳት የለባቸውም" በማለት አስጠንቅቋል። ግንባሩ አያይዞም፣ በሕዝባችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን ድርጊት መቼም ቢኾን አንረሳውም ብሏል።

ኦብነግ፣ በክልሉ ሕዝብ ወይም በኦጋዴን አካባቢ ሕዝብ ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ወይም ደም ያፈሳሉ ያላቸውን አካላት ማንነት ግን በስም ለይቶ አልጠቀሰም።

ግንባሩ ከሳምንት በፊትም፣ በክልሉ ውስጥ በሲቪል ተሽከርካሪዎች ላይ ይፈጸማሉ ያላቸው "ዒላማ ያልለዩ የመሳሪያ ጥቃቶች" እና "የአርብቶ አደሮችን እንስሳትና ንብረት የመውረስ ድርጊቶች" እንዲቆሙ ጠይቆ ነበር።

ከአምስት ዓመታት በፊት ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርሞ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተመለሰው የቀድሞው አማጺ ኦብነግ፣ በተለያዩ ጊዜያት በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ቅሬታ ሲያሰማ መቆየቱ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ራስ ገዝ የባሕር በር ካገኘች በምላሹ ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና ለመስጠት የያዘውን ዕቅድ ለመሰረዝ እያሰበ ስለመኾኑ ብሉምበርግ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ኢትዮጵያ ከሱማሊያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ስትል ለሶማሊላንድ እውቅና የመስጠቱን ጉዳይ ለመተው ፍቃደኛ መኾኗን ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በቅርቡ ባደረጉት ውይይት ላይ መግለጣቸውን ዘገባው ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁ ምንጮች መስማቱን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት መንግሥት ለራስ ገዟ እውቅና የመስጠቱን እቅድ ሊሰርዝ እንደሚችል ለውጭ ዲፕሎማቶች በግል አሳውቋል ተብሏል።

አፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ፣ አውሮፓ ኅብረትና በርካታ የዓረብ አገራት የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር በተደጋጋሚ የጠየቁ ሲኾን፣ አንዳንዶቹ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ከረር ባሉ ቃላት አውግዘዋል።

ሶማሊላንድ በበኩሏ፣ ለኢትዮጵያ የባሕር በር መግቢያ መሬት የምትሰጣት፣ ኢትዮጵያ የአገርነት እውቅና ከሰጠቻት ብቻ እንደኾነ በተደጋጋሚ ገልጣለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣የተራቡት ሲደገፉ፣ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

@merkato_media
@merkato_media
ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች 5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

በ450 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለሚገነባው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰራተኞች ሁለተኛ ምዕራፍ የ5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ተገለጸ።

የግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋዩን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስቀምጠዋል።
በግንባታ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ሳሙኤል ታፈሰ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታረቀኝ ገመቹና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በ17 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የቤቶቹ ግንባታ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ልዩ ሥሙ ሃያት-49 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ግንባታው በሰንሻይን ኮንስትራክሽንና በቻይናው ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) የሚከናወን ሲሆን በአራት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

በፕሮጀክቱ ከ5 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ሥፍራ፣ ትምህርት ቤት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራና የገበያ ማዕከላት እንደሚይዝ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ቤቶቹ የራሱ ጥልቅ ጉድጓድ ውኃና የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚኖረውም ተገልጿል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አርትስ ቲቪ ቃለመጠይቁን አላስተላልፍም አለ

አርትስ ቲቪ መግለጫ

“ማብሪያ ማጥፊያ” በተሰኘው ተወዳጅ የኮሜዲ ሾው አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ክፍል ላይ እንዲቀርብ ተዘጋጅቶ፣ ደምሳሽ ከተሰኘው እንግዳ ጋር የተካሄደውን ቃለመጠይቅ አስመልክቶ ከተመልካቾቻችንና ከተከታታዮቻችን የተሰጡትን ሃሳቦችና አስተያየቶች በጥሞና ተመልክተናቸዋል፡፡

ምንም እንኳን የ”ማብሪያ ማጥፊያ” ፕሮግራማችን ይዘት ፍፁም የኮሚዲና የመዝናኛ እንደመሆኑ፣ የተጠቀሰው ቃለመጠይቅ እንደመዝናኛ ኮሜዲ የተዘጋጀና የሚያዝናና እና አስቂኝ ብቻ ከመሆኑ ሌላ አሉታዊ መልዕክትም ሆነ ይዘት የሌለው እንደሆነ አረጋግጠን የነበረ ቢሆንም፣ በምንም ምክኒያት የተነሳ ከውድ ተመልካቾቻችን የሚሰጡን ቅን አስተያየቶች የማክበር ቁርጠኝነት ያለን ስለሆነ፣ በተመልካቾቻን ጥያቄ ላይ በመመሥረት የተጠቀሰው ፕሮግራም ከመተላለፍ እንዲቆም የወሰንን መሆኑን ከፍ ባለ አክብሮት ለመግለፅ እንወዳለን ብሏል።

@ethio_mereja_news
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት፣ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለረመዳን ጾም ላንድ ወር አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ብሪታንያ የቀረበችውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።

የውሳኔ ሃሳቡ፣ ኹለቱ ተፋላሚዎች በሰብዓዊ ዕርዳታ ሥርጭት ላይ የተጋረጡ እንቅፋቶችን እንዲያስወግዱና ዕርዳታ በጎርቤት አገራት በኩል እንዲገባ እንዲፈቅዱ የሚጠይቅ ነው።

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ የረመዳን ጾም ተኩስ አቁም ወደ ዘላቂ ሰላም ማምራት አለበት በማለት በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ለተፋላሚዎቹ ጥሪ አድርገዋል።

የሱዳን ጦር ሠራዊት፣ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ተዋጊዎች ከሲቪሎች መኖሪያዎች መውጣት አለባቸው ከሚል ቅድመ ኹኔታ ጋር የምክር ቤቱን ውሳኔ እንደተቀበለው አስታውቋል።

ጸጥታው ምክር ቤት፣ ከ20 ዓመታት በፊት በሱዳን ታጣቂ ኃይሎችና አንዳንድ ግለሰቦች ላይ ለጣለው የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር ማዕቀብ ለመቆጣጠር ለተቋቋመው ኮሚቴ ድጋፍ የሚሰጠውን የባለሙያዎች ቡድን የጊዜ ቆይታም ላንድ ዓመት አራዝሟል።
#UFO

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ታይተዋል ስለተባሉ ዩፎዎች ምንነት ሪፖርት አቀረበ!

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ አካላትን (ዩፎ) መታየታቸውን በተመለከተ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

በተለይ በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ እና 60ዎቹ በከፍተኛ ቁጥር የታዩት እና ዩፎዎች ናቸው ተብለው የተደመደሙት በራሪ ነገሮች የአሜሪካ መንግሥት የሠራቸው የተራቀቁ የስለላ አውሮፕላኖች እና የህዋ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤቶች ናቸው ብሏል።

የመከላከያ ባለሥልጣናት አክለውም ከሌላ ዓለም የመጡ እንግዳ ፍጡራን ማጋጠማቸውን በሚመለከት “ምንም ዓይነት” ማስረጃ የለም ብለዋል።አርብ ዕለት ለአሜሪካ ምክር ቤት የቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው፥ ዩፎ ተብለው መታየታቸው ከተገለጹት መካከል አብዛኞቹ ክስተቶች ከምድር ላይ የተነሱ የተለመዱ ነገሮች ናቸው ብሏል።

ነገር ግን የተደረገው ምርመራ ውጤት በሕዝቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ዩፎዎችን በተመለከተ ያለውን እምነት በቀላሉ የሚለውጠው እንዳልሆነ የፔንታገን ባለሥልጣናት መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።ሪፖርቱ ባለሥልጣናት “ምንነታቸው ያልታወቁ ያልተለመዱ ክስተቶች” የሚሏቸውን በራሪ አካላትን በተመለከተ ምርመራ በማድረግ ለመገንዘብ በአሜሪካ መንግሥት የተደረገ ሙከራ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1 ሺህ 445ኛው የረመዳን ፆም

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞት መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር ዶር ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በመግለጫቸው፤ ወሩ የእዝነት ፣ የምህረት እንዲሁም የፍቅርና የደስታ ፆም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የረመዷን ፆም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የተለየ ትኩረት የሚሰጠው ታላቅ ፆም መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፤ የሙስሊም ማህበረሰብ ይህን ታላቅ የሆነውን የረመዷን ፆምን የተቸገሩትን በመርዳት በጋራ ማሳለፍ እንደሚገባው አሳስበዋል።

በተለይም በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው ተፈናቅለው በየቦታው የተበታተኑ ወገኖችን በመጠየቅ ልሆን እንደሚገባም ጠይቀዋል።

ክቡር ዶር ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በተለያዩ ሀገራት ለሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰብም የእንኳን አደረሳችሁ ምኞት የገለፀው ሲሆን፤ ህዝበ ሙስሊሙ ፆሙን ሲፆም የተቸገረ ወገንን በመጠየቅ ልሆን ይገባል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 07:37:26
Back to Top
HTML Embed Code: