Telegram Web Link
ረመዷን ነገ ይጀምራል።

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ሰኞ ይጀምራል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አጫጭር ዜናዎች‼️

1፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሱማሊያ ቢወጡ የአገሪቱ ፌደራል መንግሥት ሞቃዲሾ ውስጥ ተቀምጦ ይቆያል ብለው እንደማይገምቱ ከመንግሥታዊው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ባኹኑ ወቅት ከግማሽ በላይ የሱማሊያን ግዛት ጸጥታ በመጠበቅ ላይ መኾናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ገልጸዋል። የሱማሊያ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ወታደሮች የጸጥታ ጥበቃ ሚና ላይ የሚሰጧቸውን አንዳንድ አስተያየቶችንም፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ "ውለታ ቢስነት" በማለት ገልጠውታል። የሱማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሐምዛ ባሬ፣ ለመልካም ጉርብትና ስንል ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ስምምነት በመፈራረሟ የኢትዮጵያን ወታደሮች ከግዛታችን እስካሁን አላስወጣንም በማለት ባለፈው ሳምንት መናገራቸው ይታወሳል።

2፤ ኦብነግ፣ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት የሚደገፍ "ሕጋዊነት የሌለው" አንድ ቡድን ሰሞኑን በግንባሩ ስም ያሠራጨው መግለጫ፣ ትክክለኛ አቋሜን አያንጸባርቅም ብሏል። ኦብነግ፣ "ፋና ብሮድካስት የተረጋገጡ መግለጫዎቼን ችላ በማለት አሳሳቹን መግለጫ ማሠራጨቱ፣ የሴራው ተባባሪ መኾኑን ያሳያል" በማለት ከሷል። ሕጋዊ ድምጾችን ወደ ጎን የመግፋት አካሄድ፣ የአገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰና ለንግግር እንቅፋት እየሆነ ነው በማለትም ኦብነግ ወቅሷል። ኦብነግ፣ በክልሉ የንጹሃን ደም እየፈሰሰ ነው በማለት ባላፈው ስምንት አጭር መግለጫ አውጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ፋና ብሮድካስት በበኩሉ የኦብነግ ምክትል ሊቀመንበር የፈረሙበት በሚል የግንባሩን ኦፊሴላዊ መግለጫ የሚቃረን ደብዳቤ ማሠራጨቱ ይታወሳል።

3፤ ቡና አቅራቢዎች፣ ከአብዛኞቹ ቡና ላኪዎች በወቅቱ ክፍያ ስለማያገኙ ከገበያ እየወጡ መኾኑን መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ቡና ላኪዎች የተሸጠልን ቡና የቡናና ሻይ ባለሥልጣን መስፈርቶችን አያሟላም በማለት ክፍያ ለረጅም ጊዜ እንደሚያዘገዩ ሰሞኑን በዘርፉ ላይ በተካሄደ ምክክር ላይ እንደተገለጠ ዘገባው አመልክቷል። ቡና አቅራቢዎች የተወሰኑ ቡና ላኪዎች ገበያውን እንደተቆጣጠሩት በመግለጽ፣ ከውጭ ገዥዎች ጋር በቀጥታ የሚተሳሰሩበትን መንገድ መንግሥት እንዲያመቻች መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ቡና አቅራቢዎች፣ ባንኮች ለቡና ላኪዎች ብቻ ብድር መፍቀዳቸውም ትልቅ ችግር ኾኖብናል ብለዋል ተብሏል።

4፤ የኢትዮጵያና ሱማሊያ ልዑካን ቡድኖች በኬንያ አሸማጋይነት ናይሮቢ ውስጥ ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መጀመራቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር ስምምነት "ኦፊሴላዊ ባልሆነ መንገድ" እንደምትሰርዝ ገልጣለች ያሉት ዘገባዎቹ፣ ሱማሊያ ግን ኢትዮጵያ ስምምነቱን መሰረዟን በይፋ ለዓለም ታሳውቅ የሚል አቋም መያዟን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ፣ ስምምነቱን መሰረዟን ለሱማሌላንድ አሳውቂያለኹ በማለት ለአሸማጋዮች ተናግራለች ተብሏል። ኹለቱ አገሮች በጉዳዩ ላይ ንግግር ስለመጀመራቸው ያሉት ነገር የለም፤ ገለልተኛ ምንጮችም የሱማሊያ ዜና ምንጮችን ዘገባዎች አላረጋገጡም።

5፤ አዲሱ የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪሎ፣ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ግብጽ፣ ኡጋንዳ፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ኢምሬቶች ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 14 ጉብኝት እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል። ፔሪሎ፣ በአዲስ አበባ፣ ካምፓላ፣ ናይሬቢና ካይሮ ቆይታቸው የተለያዩ የሱዳን ሲቪል ኃይሎችና ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችን እንደሚያነጋግሩ መስሪያ ቤቱ ገልጧል። ፔሪሎ፣ የሱዳኑ ጦርነት እንዲያበቃ ማድረግ በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ ከቀጠናዊና ዓለማቀፍ አጋሮች ተወካዮች ጋር ጭምር ይወያያሉ ተብሏል። [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዛሬ በይፋ ተጀምረዋል‼️

እስላም ክርስቲያኑ ገጠመ ጦማቸው
ወደ አምላክ ለመሄድ ቀጠሮ እንዳላቸው
አምላክ ይሄን አይቶ ምነው በረዳቸው
የመቻቻል ነበር ጥንትም ትዳራቸው💚💛

ለመለው የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታሏቆቹ የዓብይ ፆም እና የረመዳን ፆም በሰለም አደረሳችሁ !

ፆሙ የበረከት ፣ ከፈጣሪያችን ጋር የምንታረቅበት ለሀገራችን ሰላም የሚያመጣልን ይሁንልን 🇪🇹

መልካም የፆም ወቅት ❤️

ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን 🙏

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አማራ ክልል‼️

ትምህርት እና የጦርነት ጉዳቶች በአማራ ክልል

ከ2·6 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በጦርነቱ ምክንያት ወደ ትምህርት አልገቡም።

አል ዓይን እንደዘገበው በክልሉ 298 ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል ወድመዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መጠሪ ቀበሌን በመቆጣጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እና የመንግስት ሹመኞች ከምዕራብ ጉጂ ወደ ኮሬ ዞን መሸሻቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች፣ የቀበሌ አመራሮች እና ሚሊሺያዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወደሚገኘው ኮሬ ዞን መሸሻቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ።

ሰዎቹ የሸሹት ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላት በገላና ወረዳ የምትገኘውን መጠሪ ቀበሌ ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው።

ከሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ብዛት አላቸው ያሏቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት  ወደ ቀበሌው በመግባት መንደሮችንና አገናኝ ጎዳናዎችን  መቆጣጠራቸውን  ሀሰንና ገልገሎ ገልጸዋል፡፡

የቀበሌውን በታጣቂዎቹ መያዝ ተከትሎ እነሱን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ፣ የቀበሌ አመራሮች እና  ሚሊሺያዎች በሥጋት ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን  መሸሻቸውን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የኪሌ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አበበ ጣሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ከአጎራባች የገላና ወረዳ ወደ ኬሌ ከተማ መግባታቸውን ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል የተመለሱ ተፈናቃዮች በባለስልጣናት የተገባላቸው ቃል አለመፈጸሙን እና ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ኑሯቸውን እየገፉ እንደሚገኙ ተናገሩ።

ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ውስጥ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መፈጸማቸውን በርካታ የመብት ተቋማት ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወሳል።የአማራ ተወላጆች ጥቃቱን ሸሽተው የተሻለ የደህንነት ዋስትና እናገኛለን ወደሚሉት አማራ ክልል ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲገቡ ቆይተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል አሁን ላይ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ እና በአማራ ክልል የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ቦታቸው የመመለስ ስራ ጀምሯል።አልዐይን አማርኛ ከአንድ ወር በፊት የተጀመረው ይህ ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ ምን እንደሚመስል ወደ ቀድሞ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰዋል የተባሉ ተፈናቃዮችን አነጋገሯል፡፡ለደህንነታቸው በመስጋት ስማችን አይጠቀስ ያሉ እና ከ15 ቀናት በፊት ከደብረብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ወለጋ ዞኖች የተመለሱ ግለሰብ "የኦሮሚያ ክልል መንግስት አመራሮች መጠለያ ካምፓችን ድረስ መጥተው አካባቢያችሁ ሰላም ሆኗል እንመልሳችሁ ሲሉን እሺ ብለን ተመለስን" ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት ከበፊቱ መንደራችን ከመመለስ ይልቅ መጠለያ ካምፕ ሰርቶ ነው ያስቀመጠን ያሉን እኝህ አስተያየት ሰጪ ኑሯችንን በመጠለያ ለመምራትስ የነበርንበት ደብረብርሃን ይሻለን ነበር ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ከበፊቱ ኑሯችን በባሰ ሁኔታ እየኖርን ነው ያሉት አስተያየት ሰጪው ምግብ እና ውሃ ችግር ባይኖርም የሰላሙ ሁኔታ ግን አስጊ ነው ብለዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሊቢያ መሪዎች አንድ መንግስት ለመመስረት ተስማሙ

የሊቢያ
ሁለቱ ተቀናቃኝ መንግስታት መሪዎች አንድ ወጥ የሆነ መንግስት ለመመስረት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ከአስር አመታት በላይ የዘለቀውን የፖለቲካ አለመግባባት ለማስቆም ስምምነቱ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። መሪዎቹ እሁድ እለት በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ምርጫዎችን የሚቆጣጠር እና "ሉዓላዊ ቦታዎችን አንድ የሚያደርግ" አዲስ የተዋሃደ መንግስት ለመመስረት ተስማምተናል ብለዋል።

ውይይቱ የተካሄደው በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ሲሆን በአረብ ሊግ ዋና ፀሃፊ አህመድ አቡል ጊይት የተመራ ነበር። ድርድሩ የሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና መቀመጫውን ትሪፖሊ ላይ የሚገኙትን የከፍተኛ ግዛት ምክር ቤት ሃላፊን እንዲሁም በተቀናቃኙ ቤንጋዚ ላይ የተመሰረተው አስተዳደር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤን ያካተተ ነበር።

ሊቢያ እ.ኤ.አ በ2011 የሊቢያ የረዥም ጊዜ ገዢ የነበሩት ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ አገዛዝ ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ለሁለት የመከፈል አደጋ ውስጥ ወድቃለችም።አገሪቱ በትሪፖሊ በጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ዲቤባህ በሚመራው በምእራቡ ዓለም ዘንድ ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው መንግሥት እና በቤንጋዚ መቀመጫውን ባደረገው በወታደራዊ ኃይል መሪው ካሊፋ ሃፍታር የሚደገፍ አስተዳደር በምስራቅ በኩል ተከፋፍላ ትገኛለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ "በትግራይ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም መስፈኑ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣናም ቁልፍ የሰላም ድርሻ ይኖረዋል" በማለት ትናንት በተጀመረው የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር ግምገማ ላይ ተናግረዋል።

ፋኪ፣ ስብሰባው “ተግዳሮቶችንና ገና ያልተፈቱ ጉዳዮችን" ለመፈተሽ ጥሩ አጋጣሚ እንደኾነ አስምረውበታል። ፋኪ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሃት “ያልተፈቱ ጉዳዮችን ነቅሰው እንዲያወጡና ሊፈቱ የሚችሉበትን አግባብ እንዲያስቀምጡ” ጠይቀዋል።

በተለይ የፖለቲካ ውይይት ሂደት፣ የሽግግር ፍትሕና የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ መበተንና መልሶ የማዋሃድ ጉዳይ የኹለቱን ወገኖች ትኩረት እንደሚሹ ፋኪ ጠቁመዋል።(wazema)

@sheger_press
@sheger_press
በመውጫ ፈተና ኩረጃና ሌሎች የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ‼️

በመውጫ ፈተና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት፣ መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን #የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 (አንድ መቶ አስራ አራት) ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሠረዙን እና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑ ሚኒስቴሩ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል።

ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119, 145 ተፈታኞች ፈተናውን መውሰዳቸውን ሚኒስቴሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ አመላክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን ተገንዝቧል።

አየር መንገዱ ከክቡራን ደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል ቆይቷል።

በመሆኑም እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን ለማሣወቅ እንወዳለን።

ይህንንም ተከትሎ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁልጊዜም ጥረቱ ለውድ ደንበኞቹ ቀልጣፋ እና ምቹ አገልግሎት መስጠት ነው። አሁንም የክቡራን ደንበኞቹን ጥቆማ ተቀብሎ አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ ይህንኑ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@ethio_mereja_news
የአማራ ክልልን ግጭት በንግግር ለመፍታት…

መንግስት የትኛውም አይነት ጥያቄ አለኝ ከሚል ኃይል ጋር ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ዛሬ በሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ በኩል አረጋግጧል።

በአማራ፣ ኦሮሚያና ሌሎችም አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በሃሳብ የበላይነት መፍትሔ ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራ ስለመሆኑም ሚንስትር ዲኤታው አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ጋር በመተባበር በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ ማክሰኞ መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአማራ ክልል የተከሰቱ ግጭቶች እያስከተሉት ያለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት በተመለከተ በመድረኩ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር መደረጉን ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በተረቀቀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ረቂቁን ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

መንግሥት በ1967 ዓ፣ም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ በመቀየር አዲስ ረቂቅ አዋጅ ያዘጋጀው፣ ነባሩ አዋጅ የሕዝብ በዓላቱን ዝርዝር የአከባበር ስነ ሥርዓት የማይገልጽና በዓላቱ ሊሰጣቸው የሚገባቸውን የመገናኛ ብዙኀን ሽፋን የማይዘረዝር በመኾኑ እንደኾነ ተገልጧል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ታስበው ለሚውሉ ኹለት አገር ዓቀፍ በዓላት፣ አራት ብሄራዊ በዓላት እና ስምንት የሐይማኖት በዓላት ዕውቅና የሰጠና የአከባበር ስነ ሥርዓታቸውን የደነገገ ነው። ረቂቅ አዋጁ ግንቦት 20ን በአገር ዓቀፍ ደረጃ ከሚከበሩ በዓላት ዝርዝር ውስጥ አስወጥቶታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኦነግ ፣ መንግሥት ያቋቋመው ሚስጢራዊ የጸጥታ ኮሚቴ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚፈጽማቸው ግድያዎች እንዲቆሙ ጠየቀ

ኦነግ፣ መንግሥት ያቋቋመው ሚስጢራዊ የጸጥታ ኮሚቴ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚፈጽማቸው ግድያዎች እንዲቆሙ ሕዝቡ፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

የጸጥታ ኮሚቴው አባላት ለፈጸሟቸው ተግባራት ተጠያቂ እንዲኾኑ እነዚኹ አካላት ጥረታቸውን እንዲቀጥሉም ኦነግ ጥሪ አድርጓል። ኦነግ ጨምሮም፣ በአብዛኞቹ የክልሉ ዞኖች ከፍርድ ውጭ የኾኑ ግድያዎች፣ የዘፈቀደ እስሮች፣ ስቃይ እና ምዝበራ እንደቀጠለ ነው ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተካተቱበት ሚስጢራዊ የጸጥታ ኮሚቴ የሚያስፈጽማቸውን ከሕግ ውጭ የኾኑ ግድያዎች ሮይተርስ በጥልቅ ምርመራ በቅርቡ አጋልጧል ያለው ኦነግ፣ የሚስጢራዊው ኮሚቴ መዋቅር እስከ ዞን፣ ወረዳ፣ ከተማ እና ቀበሌ አስተዳደሮች ድረስ የተዘረጋ መኾኑን ጠቅሷል።

Via ዋዜማ ራዲዮ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጴጥሮስ መስርተናል " በሚል መግለጫ የሰጡትና በእስር ላይ የነበሩት አባቶች ከእስር ተለቀቁ።

" መንበረ ጴጥሮስ መስረተናል " ያሉት 10 አባቶች እና ሌሎች አብረዋቸው የነበሩት አስተባባሪ ግለሰቦች በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ለአንድ ወር ከ18 ቀን ከታሰሩ በኃላ ትላንት እያንዳንዳቸው በ5000 ብር ዋስ ከእስር መፈታታቸውን ቪኦኤ ሬድዮ ጠበቃቸውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

እንዳ ጠበቃቸው ገለጻ ፖሊስ የተጠረጠሩበት ወንጀል ብሎ ያቀረበው ፦
1ኛ.  " ያልተፈቀደ መግለጫ ሰጥታችኃል "
2ኛ. " ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር አጋጭታችኃል "
3ኛ. " ህዝብን በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ አድርጋችኃል " የሚል ነበር።

በሸገር ከተማ ሆነው " መንበረ ጴጥሮስ መስርተናል " የሚል መግለጫ በሰጡ በሰዓታት ውስጥ የታሰሩት የሃይማኖት አባቶቹ በዋስ ከእስር ተለቀዋል።

ለእስር ተዳርገው ከነበሩት መካከል ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ማዕረጋቸውን ገፍፌዋለሁ " ያለቻቸው አባ ገብረማርያም ነጋሳ፣ አባ ወልደ ኢያሱስ ኢፋ እንዲሁም አባ ወልደኢየሱስ ተስፋዬ እንደሚገኙበት መናገሩ የሚዘነጋ አይደለም።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን   " መንበረ ጴጥሮስ "  አቋቁመናል ብለው መግለጫ በሰጡበት ወቅት በሌላቸው ክህነት መግለጫ እንደሰጡና ድርጊቱንም እንደምታወግዝ ገልጻ ፤ በሕገወጥ ድርጊታቸው ቀጥለዋል ያለቻቸውን ቡድኖች  በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 31 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ሰላሳ ስምንት የትራፊክ  አደጋዎች  መድረሱን የክልሉ የትራፊክ ቁጥጥር እና ደህንነት ክፍል አስታውቋል።

አደጋዎች የተመዘገቡት ከየካቲት 25 እስከ መጋቢት 2  ባሉት ቀናቶች ነው። በነዚሁ አደጋዎች የ32  ሰዎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት  ኢንስፔክተር  መሰለ  አበራ በተለይ  ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

አጠቃላይ በተከሰቱት 38 አደጋዎች የ31 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከባድ የአካል ጉዳት 17 ቀላል የአካል ጉዳት ደግሞ በ18  ሰዎች ላይ መድረሱም ተጠቁሟል።

የአደጋዎቹ መንስኤ  ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት ፣ ያለመንጃ ፍቃድ ማሽከርከር፣ በፍጥነት ማሽከርከር ፣ ላልተፈቀደ አገልግሎት ጨለማን ተገን አድርጎ ማሽከርከር መሆናቸውም ተነግሯል።

አደጋዎቹ   በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እና ዞኖች ላይ የተከሰቱ ናቸው  ።  በተጨማሪም በአጠቃላይ በደረሱ አደጋዎች በስምንት ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት  ደርሷል ። 

በቄለም ወለጋ  አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በጭነቱ ላይ 21 ሰዎችን አሳፍሮ  የደረሰ አደጋ ሲሆን በዚህ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  14 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሱዳን ጦር መንግስታዊውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች በመንጠቅ ዳግም በእጁ ማስገባቱን አስታወቀ

የሱዳን ወታደሮች ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በናይል ማዶ በምትገኘው ኦምዱርማን የሚገኘውን የመንግስት ብሮድካስት ዋና መሥሪያ ቤትን መልሰው መያዛቸውን ጦሩ አስታውቋል። ሠራዊቱ ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ጋር ባደረገው የ11 ወራት የእርስ በርስ ጦርነት በኃላ የተገኘ ስኬት ነው ተብሏል። ጦርነቱ መቀስቀሱን ተከትሎ አርኤስኤፍ ዋና የቴሌቪዥን መሥሪያ ቤቱን ከሰራዊቱ በመቀማት በእጁ አስገብቶ ነበር።

በሱዳን ያለው ግጭት ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚሄድም ማስጠንቀቂያዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተጋሩ ያሉ ቪዲዮዎች እንዳመላከቱት ወታደሮች በኦምዱርማን ከመንግስት ማሰራጫው በራፍ ላይ ድላቸውን ሲያከብሩ ይታያሉ። ሰራዊቱ በመግለጫው “ትልቅ ድል” ብሎታል። ባለፈው ሚያዚያ ወር የመገናኛ ብዙሃን ህንጻውን የአርኤስኤፍ  ኃይሎች ቢነጥቁም ስርጭቱን ማስተላለፍ ግን አልቻሉም ነበር። የመንግስት ቴሌቪዥኑ ከሌላ ማሰራጫ ሰራዊቱን የሚደግፉ ይዘቶችን ማሳየቱን ቀጥሏል።

ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ጦሩ እና አርኤስኤፍ ካርቱምን እና በአቅራቢያው ያሉትን ከተሞች ለመቆጣጠር ተዋግተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በተከበረው የረመዳን ወር የተኩስ አቁም ጥሪ ቢያቀርብም፣ በመዲናይቱ በርካታ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያ ቀጥሏል። ግጭቱ የተፈጠረው ባለፈው ሚያዝያ ወር በጦር ኃይሉ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና በአርኤስኤፍ ሃላፊ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም በቅፅል ስሙ ሄሜቲ መካከል በአለም አቀፍ ደረጃ የተደገፈ የፖለቲካ እቅድ ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው።

ግጭቱ ሚሊዮኖችን ከማፈናቀሉም በላይ ካርቱምን አውድሟል፣ ሰብዓዊ ቀውስ አስከትሏል እንዲሁም በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል በዳርፉር በጎሳ ላይ ያነጣጠረ ግድያ አስከትሏል። የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማመቻቸት በርካታ ዓለም አቀፍ ሙከራዎች ቢደረጉም አልተሳኩም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተማሪዎች በትራማዶል ሱስ ተለክፈዋል!
“ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል“

(ዶ/ር መስፍን በኃይሉ)

ትራማዶል የሚባለው የህመም ማጥፊያ መድሐኒት ያለ አግባብ በወጣቶች ኪስ ተዘውትሯል። ከስምንተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በዚህ መድሐኒት ሱስ ተለክፈዋል። መድሐኒቱ ያለ በቂ ምክንያትና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት ይሸጋገራል።

አንድ የገጠመኝ ተማሪ በቀን 26 ትራማዶል ክኒን መውሰድ ደረጃ የደረሰ ነበር። በቀን 26 ማለት ለመውሰድ ቀርቶ ለመቁጠር የሚታክት ነው። ሱስ የማያደርገው የለምና እያደረገ ቆይቷል። ከዚህ ደረጃ የደረሰው በአንድ ቀን አልነበረም። በቀን አንድ ተጀምሮ ቀስ በቀስ መላመድ ስላለው የሚፈለገውን የሱስ ቃና ስለማያስገኝ መጠኑን እንዲጨምር በሱስ ትዕዛዝ ሁለት፣ አራት፣ ስድስት፣.....እያለ ሀያ ስድስት ክኒን ላይ ደርሷል።

የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኝ አደገኛ የስነ አእምሮ ችግር ነው። ከመድሐኒት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የስነ አእምሮ ችግር የማይነካው ማዕዘን የለም። የግለሰብ፣ የቤተሰብና የማህበረሰብ ጤና፤ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብሮችን አደጋ ላይ ይጥላል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 09:18:33
Back to Top
HTML Embed Code: