Telegram Web Link
በምስራቅ ጎጃም ጣቢት ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም አንድ አባት በገጀራ ተመተው ህይወታቸው አለፈ!

በምስራቅ ጎጃም በአዋባል ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካነ ቅዱሳን ጣቢት ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም የካቲት 20/2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት ሲሆን ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ወደ ገዳሙ ገብተዋል።

ግለሰቦሻቹ የእቃ ቤቱን በማንኳኳት የእናቶችንና የአባቶችን ገዳም ቤቶችን በር ሲመቱ ቆይተው አባ ገ/ሥላሴ ታመነ የተባሉትን በገጀራ መተው ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል።

ዲ/ን ዮሐንስ ሶማ እና አብርሃም አያና የተባሉ አገልጋዮች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርስውባቸዋል። 15 የሞባይል ስልክ ከፀበልተኛው ወስደዋል፣ በቁጥር ያልታወቁ ገንዘብና ንብረት መዘረፉን የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አስታውቋል።

በሌላ በኩል በማቻክል ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዋሻ አምባ አቡነ ተ/ሃይማት አንድነት ገዳም ታህሳስ 22/2016 ዓ.ም ሌሊት ማንነታቸው ያልታወቁ 8 ግለሰቦች ከገዳሙ ውስጥ በመግባት፡-

የገዳሙን አመሰራረትና የገዳሙን ሙሉ ታሪክ የያዘ የፊልም ዶክሜንት፣ የገዳሙ መጠበቂያ የሆነ 2 ዘመናዊ ክላሾች ከእነ ሙሉ ተተኳሹ፣ በጥሬ ገንዘብ ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ፣ ወርቅ በግራም 20 ግራም የሚመዝን፣ ለመነኮሳቱ በየጊዜው የሚሰፋላቸውን ሙሉ ጣቃ ልብስ፤ ዘመናዊ ተች የእጅ ስልኮች ብዛት 5፣ አምስት ጠገራ ብርና የአንገት ጌጣ ጌጦች፣ የጥበቃ ክፍሉን መጸሐፍና ብር 2000፣ በአጠቃላይ የተዘረዘሩትን የገዳሙን ንብረቶች ከመዘረፋቸውም በላይ ገዳማውያኑን በማንገላታትና የገዳሙን አበምኔት እማሆይ ወለተ ማርያም ገላውን አፍነው /አግተው/ በመውሰድ ከፍተኛ እንግልት አድርሰውባቸዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ አስታውቋል።

ስለዚህም በ2ቱም ገዳማት ላይ ከፍተኛ የግድያ፣ የድብደባና የንብረት ዝርፊያ እየተፈጸመ ስለሆነ ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያናችንና በገዳማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመን ስለሆነ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን ስንል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናሳስባለን በማለት የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአድዋ ድል በዓልን ለማክበር ወጥተው በፖሊስ ታግተው የዋሉት 25 ጋዜጠኞች!

ነገሩ እንዲህ ነው፣ ዛሬ "አድዋን በባዶ ዕግር" በሚል መሪ ቃል ለ5ኛ ጊዜ ተገናኝተው በባዶ እግር ትንሽ ተጉዘው፣ ፎቶ  ተነስተው ለመለያየት ከፋና፣ ከኢቢሲ፣ ከአዲስ ቲቪ፣ ከሀገሬ ቲቪ፣ ከኢዜአ እና ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተውጣጡ 25 ጋዜጠኞች በጠዋቱ ይገናኛሉ።

ይሁንና ገና 6 ኪሎ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አጠገብ ተገናኝተው "አድዋ" የሚል ፅሁፍ ብቻ ያለበትን አረንጓዴ ቲሸርት ለብሰው ፎቶ ሲነሱ የጉለሌ ፖሊስ አባላት ከበዋቸው በመንገድ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ አስቁመው በግድ ጫኗቸው።

ከጠዋቱ 1 ሰአት የታገቱት ጋዜጠኞቹ እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ቆይተው ተይዘው ምንም በማያዉቁት እና ባላጠፉት ነገር በሰው ዋስ አስይዘው ወጥተዋል።

ይህ አንድ ማሳያ እንጂ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተይዘው እንደተወሰዱ፣ ማምሻውን የተወሰኑት እንደተለቀቁ፣ ሌሎቹ ግን የት እንኳን እንደተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁ የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Elias meseret

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
" ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን 2 ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ ! " - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትናንት  በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ በነበረው የዓድዋ ድል በዓል  ላይ እምባ እየተናነቃቸው 😭 ንግግር አድርገው ነበር።

እሳቸው በእንባ ንግግር ሲያደርጉ የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ ከፍተኛ የሀዘን ስሜቱ ከፊቱ ይነበብ እንደነበር በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምን አሉ ?

" ዛሬ ወደ ትግራይ ስመለስ በህሊናዬ የሚመጡብኝ ብዙ ትዝታዎች አሉብኝ።

ይቅርታ አድርጉልኝና አጋጣሚውን ተጠቅሜ ማንሳት እፈልጋለሁ።

በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው ከነበሩ ወገኖች መካከል አንዷ ፈንጠር ብላ የተቀመጠች አንዲት ሴት ለማነጋገር ሞክሬ ነበር።

በተፈናቃዮች ካምፕ ጉብኝት ልብን የሚሰብር  ነው። ከቤት ንብረታቸው ወጥተው ፣ ክብራቸውን አጥተው ቁጭ ብለው ጉብኝት .. እኛ ደግሞ እንመጣለን ልናያቸው።

ታዲያ ያችን ሴት ጠጋ ብዬ ሳነጋግራት፤ በጥሩ አልመለሰችልኝም። ጥቂት ያመጣሁትን እቃ እንድታከፋፍልልኝ ነበር ልጠይቃት የነበረው ' ያንቺን እቃ አልፈልግም ' አለችኝ።

በሆስፒታል እና በመጠለያ ጣቢያቸው ሄጄ ያየዋቸዋን ሴቶች በእጅጉ አስባቸዋለሁ። እቺን ሴትዮ ለምንድነው የምትመልሽልኝ ስላት ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን ሁለት ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ መልስ የለኝም ፤ አይመልስም ብቻ ነው ያልኳት።

ጦርነቱ ተዛምቶ በአፋር ክልል ሰመራ ሆስፒታል ህክምና ላይ የነበሩ የተማረኩ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን አግኝቻቸዋለሁ ሳናግራቸው ያሉኝ ከልቤ አይጠፋም ፤ ቦታቸው እዛ አልነበራም ትምህርት ቤት ነው።

ያሉኝ ' እኛ መመለስ የምንፈልገው ወደ ትምህርት ቤት ነው ' ይሄንን ወግቼ ያንን አሸንፌ የሚል ዓላማ አልነበራቸውም። በክፍላቸው ግርግዳ ላይ የፃፉት የለጠፉት የአፋር ህዝብ እንዴት ደግ እንደሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያዊ እንዴት እንደሚረዳዳ ነው።

ሌሎችም አሉ ብዙ እርጉዝ ሆነው ሶስት ልጅ ወልደው ሲንከራተቱ የነበሩ ... ለማንኛውም ብዙ መንከራተት ነበር።

ዛሬ እዚህ ቆሜ የትግራይ እናቶች ያሳለፉትን ሰቆቃ በእውነቱ እረዳለሁ ለማለት ነው ይሄን ሁሉ የምናገረው። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥዎ !!

ዞሮ ዞሮ የማንኛውም ግጭት መጨረሻው ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የሰላም ስምምነት መፈረሙ አይቀርምና ይህ ሳይሆን ተጨራርሰን ተጨካክነን ፣ ዘርና ሃይማኖት መለያያ አድርገን ሃይማኖቶችን ከፋፍለን ሳይሆን በቅድሚያ መከላከል እንዳለብን መገንዘብ አለብን።

የዓድዋ ባለቤቶች እንዳልሆንን ገፅታችንን አጉድፈን አበላሽተናል። "

via Tikvahethiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሮቿን ውጫዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው-የሱማሊያው ፕሬዝዳንት‼️
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ሰሞኑን ቱርክ ባስተናገደችው የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሮቿን ውጫዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው በማለት ከሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ከመድረኩ በተጓዳኝ ዛሬ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ተገናኝተው በኹለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። ሱማሊያና ቱርክ ለ10 ዓመታት ይጸናል የተባለለትን የባሕር መከላከያ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ፣ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ የአኹኑ የመጀመሪያቸው ነው።

ኹለቱ አገራት የባሕር መከላከያ ስምምነቱን ዝርዝር ይዘት እስካኹን ይፋ ባያደርጉም፣ ቱርክ የሱማሊያን የባሕር ወሰን ከተለያዩ የውጭ ኃይሎች ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ለመከላከል መስማማቷን የአገራቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ሶማሊላንድ ግን፣ ስምምነቱ የባሕር ወሰኔ በምትለው የውቂያኖስ ዳርቻ ላይ ተፈጻሚ ሊኾን እንደማይችል በመግለጽ ላይ ናት።
(ዋዜማ)

@sheger_press
@sheger_press
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ፖለቲከኞች ከሕገ መንግሥቱ በተቃራኒ በቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት "የግል ፍላጎትና ዓላማ ለማስፈጸም" መሞከራቸው "ስህተት" እና "ተቀባይነት የሌለው" ድርጊት ነው በማለት ተናግረዋል።

አቡነ ማትያስ ትናንት በ11ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ቤተክርስቲያኗ እና የሐይማኖት አባቶች ግጭት ውስጥ ከሚገቡ ፖለቲከኞች አንዱን ወገን ደግፈው ሌላውን ከመንቀፍ መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ቤተክርስቲያኗ ባኹኑ ወቅት ባስቸጋሪ ፈተና ላይ እንደምትገኝ የገለጡት ፓትርያርኩ፣ መንግሥት ለቤተክርስቲያኗ "የሕግ ከለላና ጥበቃ" እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
" ዋነኛው ወንጀሉ እንዲፈፀም "ና" ብሎ ጠርቶ አመቻችቶ ያስበላው ተጠርጣሪ አልተያዘም " - ቤተሰቦች

ከቀናት በፊት ሚኪያስ የተባለ ወጣት መኪናውን ይዞ ለስራ እንደወጣ እንዳልተመለሰ አፋልጉኝ መቅረቡ ይታወሳል።

ነገር ግን ወጣቱ በህይወት አልተገኘም። ተገድሎ ነው የተገኘው።

ቤተሰቦቹ በሰጡት ቃል ፦

ሀሙስ የካቲት 21 -105 ተብሎ በሚጠራው ሰፈራቸው ለብዙ ዓመታት ተከራይቶ የሚኖር አንድ ሰላምተኛው ወጣት እዩኤል (ኪያ) "አሪፍ ገንዘብ የሚያስገኝ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ የምትወስዳቸው ሰዎች አሉ፣ 6000 ይከፍሉሀል" ብሎ አናግሮት አርብ የካቲት22 በተቀጣጠሩበት ሰዓት ተገናኝተው መንገድ ጀመሩ።

በሚያውቀው ሰው በጎረቤቱ አማካኝነት ያገኛቸው ሰዎች ስለሆኑ ምንም ስጋት ያልገባቸው ቤተሰብ ከሰዓታት በኋላ "የት ደርሶ ይሆን?" ለማለት ስልክ ሲደውሉለት ዝግ ሆነ፣ደጋግመው ሲሞክሩ ምንም መልስ አጡ።

ሚኪ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሲያመሽባቸው ቤት መጥቶ ያናገረውን ልጅ ፍለጋ የተከራየበት ቤት ሄዱ። እሱም የለም! ስልኩም ዝግ ነው! ወደ ቤቱ ሲገቡ ዋና ዋና የሚባሉ እቃዎቹን አውጥቶ ተሰውሯል።

" ተባባሪ ወንጀለኞች አንድ ሴትና አንድ ወንድ ገላን አካባቢ ከተደበቁበት ቤት ውስጥ በጭካኔ ገድለውት ከሰረቁት መኪና ጋር በፖሊስ ብርቱ ጥረት ተይዘዋል። ዋነኛው ወንጀሉ እንዲፈፀም "ና" ብሎ ጠርቶ ያመቻቸው ተጠርጣሪ እዩኤል እስካሁን አልተያዘም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል የተከሰተው የጸጥታ ቀውስ 2.6 ሚሊዮን ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ውጭ አድርጓል ተባለ

በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ቀውስ ምክንያት 2.6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሲሆኑ፤ ከ3000 በላይ ትምህርት ቤቶችም በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ተዘግተዋል።
በፌደራል መንግስት እና #በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ውጊያ ለዚህ አሳሳቢ ችግር ዋነኛ መንስኤ ነው።

በድርቅ በተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች በዚህ የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ ባለስልጣናት የተገኙ ሪፖርቶች አመልክተዋል።

በተራዘመ ድርቅ በተጎዳው በ #ዋግ_ኅምራ ዞን የሚገኙ ትመህርት ቤቶች፤ እየጨመረ ካለው የተማሪዎች ከትመህርት ገበታ ውጭ መሆን ጋር እየታገሉ ነው።

ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎችም ስፍራውን ለቀው ወደ ሌላ አካባቢ የሚንቀሳሰቁ ነዋሪዎች መኖራቸውን ተከትሎ ለጆቻቸው ትምርታቸውን ለሟቋረጥ ተገደዋል።
አዲስ ስታንዳርድ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ግብጽ፣ ለሕዳሴ ግድብ ድርድር መክሸፍ ዋነኛዋ ተጠያቂ ኢትዮጵያ ናት በማለት በድጋሚ ወቅሳለች።

ግብጽ ይህን አቋሟን በድጋሚ ያንጸባረቀችው፣ የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜ ሽኩሪ ለባሕረ ሰላጤው ምክር ቤት አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በሕዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ ሪያድ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ትናንት ገለጣ ባደረጉበት ወቅት ነው።

የባሕረ ሰላጤው አገራት የትብብር ምክር ቤትም፣ የግብጽና ሱዳን የውሃ ደኅንነት የዓረቦች ብሄራዊ ደኅንነት አካል እንደኾነ ገልጧል።

የምክር ቤቱ አባል አገራት፣ ግብጽና ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ ያላቸውን ጥቅም የሚጎዳ ማናቸውንም ድርጊት እንደሚቃወሙም አቋማቸውን አስታውቀዋል።

ግብጽ፣ በግድቡ ውሃ ሙሌትና አስተዳደር ላይ የተጀመረው የሦስትዮሽ ድርድር "በኢትዮጵያ ግትርነት" ከሽፏል በማለት ባለፈው ታኅሳስ መግለጧ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሶስት ሰራተኞች በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ ህይወታቸዉ ሲያልፍ አራት ሰራተኞች  ከባድ የአካል ጉዳት አጋጠማቸው

በዛሬዉ እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሶስት ሰራተኞች በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ ህይወታቸዉ ማለፉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። በአደጋዉ ሌሎች አራት የባንኩ ሰራተኞች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ዳጉ ሰምቷል።

አደጋዉ ከጎንደር ወደ ሁመራ ሲያቀና የነበረ ኮድ 3 ኢቲ 70110 የሆነ የባንኩ ንብረት የሆነበረ ተሽከርካሪ ላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ ትክል ድንጋይ በተሰኘዉ አካባቢ ባጋጠመዉ አደጋ የሰራተኞቹ ህይወት ማለፉን ሰምተናል። በአደጋዉ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ለማወቅ ችለናል።

በአደጋዉ የሁመራ ዲስትሪክት ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቢተዉ አስፋዉ ፣ የዳንሻ ቅርንጫፍ የብድር ብተና የቡድን ስራአስኪያጅ የነበሩት አቶ ያሬድ ከልካይ እና አቶ አሰፋ ሀይለማርያም በወቅቱ የነበሩት አሽከርካሪ በአደጋዉ ወዲያዉኑ ህይወታቸዉን አጥተዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሰራተኞቹ ህልፈት የተሰማዉን ሀዘን ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተፈጸሙ እስሮች በአገሪቱ ማንም ከዘፈቀደ እስር ነጻ ሊኾን እንደማይችል ማረጋገጫ ነው ሲል አዲስ ባወጣው አጭር መግለጫ ስጋቱን ገልጧል።

ድርጅቱ፣ የኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች መንግሥት የሚፈጽማቸውን እስሮች እና ለተቃውሞ የሚያሳየውን ትዕግስት የለሽነት እንዲያወግዙ ጠይቋል።

ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቶን ጋሊንዶ ጋር በቅርቡ የታሠሩት የኦነግ የፖለቲካ ኃላፊ በቴ ኡርጌሳ፣ በድጋሚ በመጭው ረቡዕ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እንደተቀጠሩ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራይ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሐላፊ ረዳኢ ሐለፎም፣ የኤርትራ መንግሥት የትግራይ አንዳንድ አካባቢዎችን በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ አረጋግጧል በማለት ለዶይቸቨለ ተናግረዋል።

ረዳዒ ይህን ያሉት፣ ብሪታኒያ የሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ የኤርትራ ጦር ባድመን ጨምሮ በዓለማቀፉ ድንበር ኮሚሽን ከተወሰኑለት "ሉዓላዊ" አካባቢዎች ውጭ በትግራይ ምድር ውስጥ አይገኝም በማለት ባለፈው ሳምንት መግለጡን ተከትሎ ነው።

ሐለፎም፣ የኤርትራ ጦር በኃይል የያዛቸውን የትግራይ መሬቶች ከመለሰ በኋላ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በሕጋዊ አግባብ ይፈጸማል ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በጉዳዩ ላይ ፌደሬል መንግሥቱ የሚጠበቅበትን ነገር በይፋ እንዲገልጽ ረዳዒ መጠየቃቸውን ዜና ምንጩ ጨምሮ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሆቴል ውስጥ በተከሰተ የእሳት አደጋ አልጋ ተከራይተው የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ህይወት አለፈ

በትላንትናው እለት የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:08 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሁለት ቁጥር አዉቶቢስ ማዞሪያ አካባቢ አዲሱና ቤተሰቦቹ  በተባለዉ ሆቴል ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

ህይወታቸዉ ያለፈዉ  ወጣቶች መሆናቸው ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የተናገሩት አቶ ንጋቱ ማሞ እድሜያቸዉ 28/30 ዓመት የተገመቱ ሲሆን በሆቴሉ አልጋ ተከራይተዉ ተኝተዉ የነበሩ ናቸዉ ብለዋል።

የእሳት አደጋዉን  ለመቆጣጠር  ሰባት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከሰላሳ ሁለት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋ ወደ ሌሎች የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርሰ መቆጣጠር ተችሏል።

አደጋዉ የደረሰበት ቦታ የአደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችን የማያስገባ በመሆኑ የአደጋ መቆጣጠር ስራውን አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበር ኮሚሽኑ አስታውቃል።

በሌላ በኩልም ትላንት በለ ሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ስምንት በአንድ ሬስቶራንት ላይ የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ በተነሳ የእሳት አደጋ ሶስት ሰዎች  ጉዳት ደርሷአል።

ህብረተሰቡ በተለይም የሆቴልና የንግድ ተቋማት ለእሳት አደጋ መከሰት የሚያጋልጡ አሰራሮችን  በማስወገድ  ቅድሚያ ለደህንነት እንዲሰጡ አቶ ንጋቱ እያሳሰቡ  ማናቸዉም አደጋዎች ሲያጋጥሙ አደጋዉ ሳይባባስ በ939 የአደጋ ጥሪ መቀበያ ስልክ ቁጥር  ፈጥነዉ እንዲያሳዉቁ መልክት አስተላልፈዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ማንም ከመሬት ተነስቶ የሚያፈርሰዉ ተራ ዉል አይደለምእኛ የተቋረጠዉን ዉል እንዲቀጥል እፈልጋለሁ"ፐርፐዝ ብላክ

ፐርፐዝ ብላክ ለህንፃዉ ቅድመ ክፍያ 1 ቢሊዮን 150 ሚሊዮን ክፍያ መፈፀሙን አስታዉቋል።

ዉሉ ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ  ተቋርጧል ያለዉ ፐርፐዝ ብላክ ዉላችን በዉልና ማስረጃ መፅደቅ ሲገባዉ በቢጂአይ በኩል ይህ ሳይሆን ቀርቷል ሲል ከሷል ።

በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ በትላንትናው ዕለት መቋረጡ ይታወቃል ።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነትና አላሳየም ቢልም ፐርፐዝ ብላክ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ቢጂአይን ተጠያቂ በማድረግ በሁለተኛ ዙር ለክፍያ የተዘጋጀውን 2 ቢሊዮን 500 ሺህ ብር በመፈፀም ዉሉን በድጋሚ መዋዋል ፍላጎት አለኝ ብሏል።

ማንም ከመሬት ተነስቶ የሚያፈርሰዉ ተራ ዉል አይደለም ያለዉ የፐርፐዝ ብላክ ዋና ቦርድ ሰብሳቢ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለቢጂአይ በወሎና ማስረጃ ለመፈራረም ጥያቄ ቢቀርብም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርቷል።

ነገር ግን በድጋሚ ዉሉን የማይፈረሙ ከሆነ ይህ ጉዳዩ ወደ  ፍርድቤት ያመራል ሲሉ ተደምጠዋል።
Via:- Capital

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትራማዶልን ተገቢ ባልሆነ መንገድ መጠቀም ለድንገተኛ ሞት ያጋልጣል ተባለ

ትራማዶልን ከሐኪም ፈቃድ ውጪ በአንድ ጊዜ አብዝቶ መውሰድ ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና ዕክሎች እንደሚያጋልጥ ተጠቆመ፡፡

ትራማዶል የተሰኘው ጊዜያዊ የህመም ማስታገሻ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እየተዘወተረ እና ሱስ እየሆነ የወጣቶችን ጤና እያመሳቀለ መሆኑን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር መስፍን በኃይሉ ገልጸዋል፡፡

በአብዛኛው ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በትራማዶል ሱስ እንደሚጠመዱ ጠቅሰው÷ ያለ በቂ ምክንያት እና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት እንደሚሸጋገር አስረድተዋል፡፡

የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ያለ አደገኛ የሥነ-አዕምሮ ችግር ነው ያሉት ባለሙያው÷ ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች እንደሚያስከትል አስረድተዋል፡፡

በአንድ ጊዜ በብዛት ከተወሰደም ለሞት ይዳርጋል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም የአንጎል ንዝረት፣ የኩላሊት መድከም (መባባስ)፣ ለጡንቻ መቅለጥ እና ለከፋ የሥነ-ልቦና ችግር እንደሚዳርግ አንስተዋል፡፡

አንዳንድ ወጣቶች ኪኒኑን በመውሰድ ሱሳቸውን ማብረድ ሲሳናቸው በመርፌ መውሰድ እንደሚጀምሩ አመላክተው÷ ይህ ሁኔታም ለስትሮክ እንደሚያጋልጥ ጠቁመዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መከላከያ ሚንስትር አብርሃም በላይ፣ መንግሥት የትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ አበክሮ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

አብርሃም ከመንግሥታዊው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ሌሎች ጉዳዮች ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ከመመለስ በኋላ ይደረስባቸዋል ብለዋል።

መንግሥት፣ የኤርትራ ጦር ባኹኑ ወቅት ይዟቸው የሚገኙ የትግራይ አካባቢዎችን የሚያጣራ እና መፍትሄ የሚያፈላልግ ኮሚቴ ማቋቋሙንም ሚንስትሩ ጠቁመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ከካምፖች ውጭ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ አመለከተ

በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ ከ7,000 በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ከካምፖች ዉጭ እንደሚኖሩ መሰረታዊ መጠለያ፣ ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማግኘት እየተቸገሩ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት OCHA በቅርቡ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ23,000 በላይ ተፈናቃዮች በሦስት ካምፖች ውስጥ እንደሚኖሩ፣ ወደ 7,700 የሚጠጉት ደግሞ በከተማዋ ዙሪያ በቂ መጠለያና ድጋፍ ሳያገኙ እንደሚኖሩ ዘገባው አመልክቷል። ሪፖርቱ "የእርዳታ አጋሮች የተወሰነ የመጠለያ እና የኪራይ ድጋፍ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ሰፊ ፍላጎቶችን ለማሟላት በቂ አይደለም" ይላል ሪፖርቱ።

"ከመጠለያ በተጨማሪ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡት ምግቦች መደበኛ ባልሆነ መንገድ እየተከፋፈሉ ነው፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እንደ መኝታ ምንጣፎችና ብርድ ልብሶች ያሉ የደብረ ብርሃንን ቅዝቃዜ ለመቋቋም የሚረዱ ነገሮች ናቸው።" ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሚያ ወደሚገኙበት አካባቢ ለመመለስ የመንግስት መርሃ ግብር መጀመሩንም ዘገባው ዘርዝሯል።

እ.ኤ.አ እስከ የካቲት 26 ድረስ በደብረ ብርሃን እና በደቡብ ወሎ ዞኖች ከሚገኙ ካምፖች ወደ 1,530 የሚጠጉ ሰዎች በምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ወደ ጊዜያዊ ቦታ ተወስደዋል። ነገር ግን፣ OCHA የመመለሻ ሂደቱ "ዓለም አቀፍ የተፈናቃይ የመመለሻ መርሆዎችን መከበራቸውን ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ ተግዳሮቶች እንዳሉበት" ስጋቱን ገልጿል።

ተፈናቃዮችን በሰላም እና በፍቃደኝነት የሚመለሱበትን ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ለመደገፍ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ደጋግሜ እሰራለሁ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 09:18:55
Back to Top
HTML Embed Code: