Telegram Web Link
የኦሮምያ ክልል መንግስት የአመራር ለውጥ ሊያደርግ ነው‼️

በኦሮምያ ክልል መንግስት ከዘርፍ ቢሮዎች አንስቶ እስከ ዞን ድረስ በሁሉም መዋቅሮች የአመራር ለውጥ ሊደረግ መሆኑን ዋዜማ ከሁነኛ ምንጮቿ ሰምታለች።

የክልሉ ምክር ቤት  (ጨፌው) ትናንት መደበኛ ስብሰባውን የጀመረ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ስለመወያየቱ ግን ማረጋገጥ አልቻልንም። የብልፅግና ፓርቲ የክልሉን ብሎም የተጎራባች ክልሎችን የፀጥታ ይዞታ በገመገመበት ወቅት በቀረበው ምክረ ሀሳብ መሰረት የኦሮምያ ክልል አመራሮችን መበወዝ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኗል።

የአመራር ለውጡ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር እና ምክትል ርእሰ መስተዳድሮችን ይመለከታል ወይ ብለን ነሳነው ጥያቄ ; የመረጃ ምንጮቻችን በዚህ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ባይሆኑም : በብዙ የክልሉ መዋቅሮች የአመራር ለውጥ እና ሽግሽጉ እንደሚከናወን ; እንዲሁም በዞን እና መሰል መዋቅሮች አመራሮችን ከተወለዱባቸው አካባቢዎች ውጭ በአመራርነት እንዲመደቡ የማድረግ ዕቅድ እንዳለ ነግረውናል።

የኦሮምያ ክልል በኢትዮጵያ “የፖለቲካ ለውጥ” ከመጣ ወዲህ ከተፈጠሩ ሰፊ የጸጥታ ችግሮች ባለፈ ማንነት ተኮር የሆኑ የነዋሪዎች ግድያ እና ማፈናቀሎች በተደጋጋሚ መከሰታቸውን በሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሳይቀር ተረጋግጧል።

ለነዚህ ቀውሶች መነሻውም በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ያሉ አመራሮች የተወለዱበትን  አካባቢ ስለሚመሩ አካባቢያዊነትን መነሻ በማድረግ የገቡበት ፖለቲካዊ ብልሽት አንዱ መነሻ መሆኑን ክልሉ ያምናል መባሉን ሰምተናል።

በሚደረገው አዲስ የአመራር ለውጥም የአመራሮች ምደባ እና የትውልድ ስፍራቸው ስብጥር ከግምት እንደሚገባም ሰምተናል።

የክልሉ መንግስት የዞንና ወረዳ አመራሮች የተወለዱባቸውን አካባቢዎች መምራታቸው ማንነት ተኮር ሰብአዊ ጥቃት እንዲያደርሱ መንገድን ከፍቷል የሚል ግምገማ ቢኖረውም : ከተወለዱበት ቦታ ርቀው በአመራርነት የተመደቡ ግለሰቦች በሚያስተዳድሯቸው አካባቢዎችም ተመሳሳይ ማንነት ተኮር ማፈናቀሎች ተጸጽመዋል የሚል ትችትን የሚያነሱ አሉ። ሆኖም የክልሉ መንግስት በቅርቡ በሚተገብረው የአመራር  ምደባ የአመራሮችና የተወዱበትን ቦታ  ማሰባጠርን ለክልሉ የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ እንደ መፍትሄ ወስዶታል።

የኦሮሚያ ክልል ልክ እንደ አማራ ክልል ሁሉ በተለያዩ ቦታዎች በመንግስት እና በታጣቂ ሀይሎች ግጭት የሚደረግበት ሆኖ ቀጥሏል።
የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋጋት ከሚወሰዱ እርምጃዎች ጎን ለጎን በፌደራልና በክልል ደረጃ ተከታታይ የሹም ሽር እንደሚኖር ለመንግስት ቅርበት ያላቸው ምንጮች ነግረውናል።

Via:ዋዜማ
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጨፌ ኦሮሚያ የአቶ ታዬ ደንደአን ያለመከሰስ መብት አነሳ

ጨፌ ኦሮሚያ የአቶ ታዬ ደንደአን ያለመከሰስ መብት በ439 ድጋፍ እና በ14 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁን ኦቢኤን ዘግቧል።በም/ቤቱ 7 አዳዲስ ሹመቶች ፀድቀዋል።

ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው 6ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለየዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-
1. ዶ/ር አብዱላዚዝ ዳውድ  ---የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈትቤት ሃላፊ
2. ዶ/ር አብዲ ዩያ  --------የኦሮሚያ ክልል ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሸነር
3. መሰረት አሰፋ --------- የክልሉንግድ ቢሮ ሃላፊ
4. መብራት ባጫ --------- የክልሉ የሕጻናት እና ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ
5. አቶ ማቲዎስ ሰቦቃ ----- የክልሉ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
6. ኢ/ር ኤባ ገርባ --------- የክልሉ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ ጀማል ከድር ---------- የክልሉ የሕብረት ሥራ ማህበራት ኤጀንሲ ሃላፊ ሆኖ የቀረበለትን ሹመት ጨፌው አጽድቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማጠናከር፣ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ግብረ-ኃይሉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራቱ ለተገኘው ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብሏል መግለጫው። ለጉባኤው የመጡ እንግዶች በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እጀባና ጥበቃ ማድረጉን የገለፀው የጋራ ግብረ-ኃይሉ መሪዎቹም በሰላም ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በግብረ-ኃይሉ የተሠራው ፀጥታ የማስከበር ተግባር አፍሪካን ሊወክል እና ሊያኮራ የሚችል በመሆኑ ሀገራችን የአፍሪካ ኅብረትን ለማጠናከር ያላትን ሚና እንዲሁም ቁርጠኝነት ያሳየ ነበር ብሏል መግለጫው።

መላው የሀገራችን ሕዝብ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንግዶችን በክብር ከመቀበል ጀምሮ በየሆቴሎቹ ደረጃውን የጠበቀ መስተንግዶ በማድረግ፣ የሚያልፉባቸው መንገዶች ሲዘጉ በትዕግስት ቅድሚያ ሰጥቶ በማሳለፍ, ከፀጥታ ኃይሉ የሚሰጠውን መመሪያ በቅንነት በመቀበል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን በማሳየታቸው, የፀጥታና ደህንነት አመራሮችና አባላትም በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመወጣታቸው ጉባኤው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላምና በስኬት በመጠናቀቁ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ችግር ውስጥ ናቸው‼️
ያለወረቀት መገኘት በዝቅተኛ አምስት አመት ያሳስራል‼️
በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ስደተኞች ቢሮ የጥገኝነት ጥያቄቸውን በአብዛኛው ውድቅ እያደረገው ሲሆን ካለ ወረቀት መንቀሳቀስ የማይቻሉበት ደረጃ ተደርሷል።
ወረቀት የሌላቸው ላይ የተወሰነው እስር ከባድ ነው ከእስር ወጥቶ ወደ ሀገር ዲፖርት ለመደረግ ከፍተኛ ክፍያ ይጠየቃል።
ወላጆች ሲያዙ ከልጆቻቸው ከትዳር አጋሮቻቸው እየተነጠሉ አስጨናቂ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።
በ2024 እ አ አ የሚተገበረው የግብፅ ስደተኞችን የተመለከተ መመርያ በተለይ በኢትዮጵያዊያን ላይ አስጨናቂ መከራን አስከትሏል የድረሱልን ጥሪም አሰምተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በትናንናው ዕለት በሰሜን ሸዋ ዞን #ኤፍራታና #ግድም ወረዳ መነሻቸው #አጣዬ ከተማ በማድረግ መዳረሻቸው #ይምልዎ ወደሚባል አካባቢ በባጃጅ ተሳፍረው ሲሄዱ የነበሩ (5) አምስት ንፁሀኖች በታጣቂ ቡድኖች መገደላቸው የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰውናል።

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወጣት ከተገደሉት ወጣቶች መሀከል አንዱ ነው ።
ከሰንበቴ የተነሱ ታጣቂዎች ይህን ድርጊት መፈፀማቸው ምንጮች ነግረውናል(ሸገር ፕረስ)።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርዓዊ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ከጥር 20 እስከ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች የተገደሉ ንፁሃን ቁጥር ከ45 በላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል።

በአማራ ክልል (ኢሰመኮ) ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለባቸው ብርሃኑ ለአራዳ ኤፍ ኤም እንዳሉት፥ ግድያው በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ከተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ በኋላ የመንግስት ወታደሮች ቤት ለቤት በመግባት መፈጸማቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።

ህብረተሰቡ በፍራቻ ውስጥ በመሆኑ መረጃ ለማግኘት ቀላል አለመሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፥ ምርመራችንን አላጠናቀቅንም በመግለጫ ያወጣነው የመጀመሪያ ግኝታችንን በመሆኑ ምርመራው ቀጥሏልም ነው ያሉት።

አራዳ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ወጣቱን “ፋኖ ሰልጥነሃል፤ ዘመድህ ፋኖ ነው” በሚል ወከባ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከጦርነቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስቱ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው ይገባልም ብለዋል ነዋሪዎቹ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ይቅርታ ቢደረግላቸው‼️

ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ በነበረው ስብሰባ የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ የነበሩትን አቶ ታዬ ደንደዓ ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ መዘገባችን ይታወሳል።

አንድ የምክር ቤት አባል የሚከተለውን ተናግረው ነበር።

«አቶ ታዬ ሰው ናቸው ሊያጠፉ ይችላሉ፣ ለፓርቲውም ለሀገርም የሰሩት በርካታ ጥሩ ጥሩ ነገሮች አሉ፣
በምርጫ ወቅትም ወጣቶችን የፓርቲውን ማኒፌስቶ በማስገንዘብ ትልቅ ስራ ሰርቷል፣ አንድ ጊዜ ይቅርታ ብናደርግላቸው አሪፍ ነው፣ ለምሳሌ በትግራይ ክልል በሀገር ደረጃ ትልቅ ወንጀል እራሱ የፈፀሙ ሰዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው ወደ ፌዴራል ስልጣን ሊመጡ ነው፣
እኛ ለምን እንጨካከናለን አሁን ይቅርታ ተደርጎላቸው ከስልጣን ዝቅ ብለው ቢሰሩ እላለሁ» ሲሉ የምክር ቤት አባሉ የተናገሩ ሲሆን።

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል

«ውስጣችን ማፅዳትን አለብን የሚለው የሁል ጊዜ ጥያቄ ነው፣
ውስጣችንን ካላፀዳን ጠላትን ማሸነፍ አንችልም፣
የትግራይ ሌላ ጉዳይ ነው እዛ እያስተዳደረ ያለው የኛ ፓርቲ አይደለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃዎች‼️

የዕለቱ ሰበርና ወቅታዊ መረጃዎችን በዩትዩብ ገፃችን ይመልከቱ👇👇

በዚ ሊንክ ጎራ ይበሉ👇
https://youtu.be/jGo62lij038
https://youtu.be/jGo62lij038
ያሳዝናል‼️

ምን አይነት የጭካኔ ጥግ ነው ‼️
ምን አይነት ፍጡሮች ናቸው ግን
እንዴት በዚን ያህል ተጨካከንን

ትናንት ጠዋት በአማራ ክልል ከአጣዬ ወደ ይምሎ በባጃጅ ሲመጡ የነበሩ ሰዎችን ሰንበቴ አቅራቢያ አምስት ንፁሀኖች መገደላቸው ዘግበንላቹ ነው።

ቪድዮው እጅግ በጣም የሚዘገንን ስለሆነ እዚ ገፅ ላይ ከመለጠፍ ተቆጥበናል።

በሚያሳዝን ሁኔታ ወጣቶቹን ከላይ በምስሉ ላይ በምትመለከቱት አሰቃቂ በሆነ መልኩ ነው  አርደው የጣሏቸው።

የባጃጅ ሹፌሩን በዚህ መልኩ ነው የገደሉት መግደል አልበቃ ብሏቸው ራቆቱን ሲጎትቱትም ተስተውሏል።

ምን አይነት የጭካኔ ጥግ ላይ ደረስን ግን(Sheger_press)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ያሳዝናል ‼️

ምን አይነት የጭካኔ ጥግ ነው ‼️
ምን አይነት ፍጡሮች ናቸው ግን
እንዴት በዚን ያህል ተጨካከንን

በአሰቃቂ ሁኔታ ገለው ሲጎትቱት የሚያሳየው አጠር ያለ ቪድዮ👇👇

በዚ የቴሌግራም ሊንክ ይመልቱ👇
https://www.tg-me.com/merkato_media/488
https://www.tg-me.com/merkato_media/488
ጥቆማ‼️

አሁን ላይ ፌክ ቻናሎች በበዙበት በዚ ሰዓት ትክክለኛና የተረጋገጡ #የጦር ግንባር ዜናዎችንና የተለያዩ ወቅታዊ እና እውነተኛ መረጃዎችን በታማኝነትና በፍጥነት ፈልፍሎ የሚያቀርብ የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማቹ 👍

"የመረጃ ቋት ቻናል ነው"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇
https://www.tg-me.com/+sx8GYG1oT3lmZmFk
https://www.tg-me.com/+sx8GYG1oT3lmZmFk
መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘት ተጠቅሞበታል ሲል ከሰሰ‼️

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን "ታዋቂ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን" በማሰር ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ለማፈን ተጠቅሟል ሲል ከሷል።

በአማራ ክልል ባለፈው አመት ሀምሌ ወር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜው ሲጠናቀቅ መንግስት "የሚቀሩ ሰራዎች" መኖራቸውን በመጥቀስ ጥር መጨረሻ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም አድርጎታል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መራዘም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ የአውሮፖ ህብረት እና አሜሪካ በሰብአዊ መብት ጉዳይ ችግር ይፈጥራል ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዋጁ ተግባራዊ በሆነባቸው ባለፉት ስድስት ወራት የመንግስት ባለስልጣናት ተጠርጣሪዎችን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲይዙ፣ ሰአት እላፊ እንዲጥሉ፣ የመንቀሳቀስ መብት እንዲገድቡ እና ህዝባዊ ስብሰባ እንዲከለክሉ እንዳስቻላቸው ገልጿል።

በመግለጫው የድርጅቱ የምስራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻንጉታህ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ መሰረታዊ መብቶችን መገደብ ማቆም አለበት ብለዋል።ዳይሬክተራ አክለውም እንደገለጹተ "የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ገና በነጋሪት ጋዜጣ አልታተመም። ይህ የግልጽነት ችግር መረጃ የማግኘት እና የህጋዊነት መርህን የሚጥስ ነው እንዲሁም ኢትዮጵያውን ህግ እየተከበረ ስለመሆኑ እንዳያውቁ ያደርጋቸዋል።"

ድርጅቱ በመጀመሪያው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስድሰት ወራት ወቅት እና ከተራዘመ በኋላ መንግስትን የተቹ አምስት ፖለቲከኞች እና ሶስት ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ከቤተሰቦቻቸው ማረጋጠጡን ጠቅሷል።ድርጅቱ እንደገለጸው የታሰሩት ፖለቲከኞች የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ አቶ ካሳ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዩሀንስ ባያለው፣ የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ ታየ ደንደአ ሲሆኑ የታሰሩት ጋዜጠኞች ደግሞ አባይ ዘውድ፣ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናየ ናቸው።

ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተራዘመ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን በመተቸት የሚታወቁትን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል የነበሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን ማሰሩን ገልጿል።
ዳይሬክተሯ የመንግሰት ባለስለጣናት በጅምላ ማሰራቸውንም ማቆም አለባቸው ብለዋል።ዳሬክተሯ መንግስት ታዊቂ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሁሉም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩ ሰዎች ክስ እንዲመሰረትባቸው ወይም እንዲለቀቁ በማድረግ ሀገራዊ አለምአቀፋዊ ህጎችን ማክበር እንደሚገባው አሳስበዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረዶበት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ሰኞ ዕለት እንዳስታወቀዉ 41 የአልሸባብ ቡድን አባላት እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡

ፍርዱ ከተላለፋቸው መካከል የወታደራዊ መሪዉ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል ነዉ የተባለዉ፡፡

ብይኑን የሰጠዉ በድሬዳዋ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ምድብ ችሎት ሲሆን፤ ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክር አላቀረቡም በሚል የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ናቸው፡፡

ሁሴን አልመድ/ኤሊያስ ሁሴን/ የመጀመሪያ ተከሳሽ ሲሆን፤ እንደ መንግስት ገለጻ ከሆነ ለአሸባሪዉ ቡድን እንደ መሪ ሆኖ ሲሰራ ነበር፡፡

ሁለተኛዉ ተከሳሽ  ኢብራሂም ጂብሪል የሚባል ሲሆን የበታች ወታደራዊ መሪ ነበር ተብሏል፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ጉዳዮች ክፍል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል 57 ምስክሮችን እንዲሁም 3መቶ96 የጽሁፍ ማስረጃዎችን ከተመለከተ በኋላ በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ መስርቶባቸዉ ነበር፡፡

ሁሉም 41 ተከሳሾች ከ2019 ጀምሮ ሶማሊያ የሚገኘዉ የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን አባላት ናቸዉ ያለ ሲሆን፤ ልምምዳቸዉን ካጠናቀቁ በኋላ በ2021 በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጸመ ጥቃት ተሳታፊ ነበሩ ብሏል፡፡

በአፍዴር ዞን የተለያዩ አከባቢዎች በስፋት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ደርሼበታለሁ ያለዉ ዳይሬክቶሬቱ፤ በኢትዮጵያ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በማሰብ አብዛኛዎቹ የጦር መሳሪያዎችን ጭምር ሲያቀርቡ ነበር ነዉ ያለዉ፡፡

በወቅቱም 2መቶ65 ንጹህን ዜጎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አባላትን ጨምሮ 3መቶ23 ሌሎች ዜጎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚገልጸዉ ደግሞ 13 ሚሊየን 5መቶ ሺህ የሚደርስ የኢትዮጵያ ብር የንብረት ዉድመት ደርሷል ነዉ የተባለዉ፡፡

ተከሳሾቹ ከሽብርተኝነት ወንጀል በተጨማሪ ደግሞ የአልሸባብ ቡድን አባላት በመሆናቸዉም ጭምር ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

መንግስት እንደሚለዉ ከሆነ ተከሰሾቹ 5ጊዜ የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ዕድል ተሰጥቷቸዉ ነበር፡፡

የቡድኑ መሪ ሁሴን አልመድ የዕድሜ ልክ እስራት ሲፈረድበት፤ 19 ተከሰሾች 11 እና 12 አመት ያለ ይግባኝ፤ 8 ተከሳሾች 8 እና 9 ዓመት እንዲሁ ያለ ይግባኝ እና ቀሪ 10 ተከሰሾች ደግሞ 7 እና 8 ዓመት ያለ ይግባኝ ተፈርዶባቸዋል፡፡(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እናት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ያበረታታል የተባለውንና የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ አገራት ከአውሮፓ ኅብረት ጋር የተፈራረሙት የሳሞአ የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት እንዳያጸድቅ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

ፓርቲዎቹ፣ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ይሄንኑ ስምምነት "ትውልድ አምካኝ" እና "አገር እና ማንነትን አጥፊ" ብለውታል። ምክር ቤቱ የስምምነቱን መጽደቅ ማስቀረት ካልቻለ፣ ቢያንስ ከግብረ ሰዶም ጋር የተያያዙ አንቀጾች ከስምምነቱ "እንዲወገዱ" ወይም "እንዲታረሙ" እንዲያደርግ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

ስምምነቱ "ለግብረ ሰዶምና ግብረ ሰዶማዊነት በተዘዋዋሪ መልኩ ጥበቃ የሚያደርጉ፣ የሚደግፉና የሚያበረታቱ" አንቀጾችን አካቷል ያሉት ፓርቲዎቹ፣ ኢትዮጵያ ስምምነቱን እንዳታጸድቅ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በጋራና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተናጥል ጭምር ያሰሙት ተቃውሞ በከንቱ ሊታለፍ እንደማይገባም አሳስበዋል።

ምክር ቤቱ የሳሞአ ስምምነትን ካጸደቀ ግን፣ "የታሪክ ተጠያቂነት ይከተለዋል" በማለት ፓርቲዎቹ አስጠንቅቀዋል። የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የግብረ ሰዶማዊነት ተግባርን ወንጀል አድርጎ ደንግጓል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"እናቴ ፀሎት ታድርግልኝ ብሎ መልዕክት ልኮልኛል"

ወጣት ንጉስ ምን ሆኖ ነው??ይህ ወንድማችን ንጉስ ቃኘው ይባላል!ሀምሌ ወር 2015ዓ.ም ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ በስታስቲክስ ትምህርት ተመርቋል!

በሸዋ መንዝ ቀያ አካባቢ ዘመሮ በሚባል ገጠራማ ቦታ የምትኖረው ምስኪን እናት በመከራ ያሳደገችው የመጀመሪያ ልጇ በመመረቁ ደስ ብሏት ኑሮዋ እንደሚሻሻል ተስፋ አድርጋ በቶሎ ስራ እንዲይዝላት ደግሞ በፀሎት ታግዘው ጀመር!!

ብዙም ሳይቆይ ፀሎታቸው ሰምሮ ልጅ ንጉስ ወርሀ ህዳር 2016ዓ.ም "ስራ አግኝቻለሁ "ብሎ በቅርቡም እንደሚገናኙ ለቤተሰብ ቃል ገብቶ ወደ ሀዋሳ ይሄዳል!

ከአንድ ወር በኋላ ታህሳስ18 ግን አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ‼️

ሀሙስ ጠዋት 2ሰዓት አካባቢ ለእናቱ ጎረቤት የሆነች ስልክ ያላት ሴት ጋር ደውሎ " እየወሰዱኝ ነው እናቴን ሳላገኛት መሄዴ ነው😭እንዳትጨነቅብኝ ፀሎት እንድታደርግልኝ ንገሪያት፣ደህና እንድሆን ለማርያም ተሳይልኝ በያት"ብሎ ስልኩን ዘጋው!!

ከዛን ቀን በኋላ የንጉስ ስልክ አይሰራም፣የት እንዳለ ምን እንደገጠመው አይታወቅም!ስራ ቦታው የት እንደነበርም አልነገራቸውም!እናት አበቡ ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷት በየቀኑ አምላኳን በእንባ እየተማፀነች አለች! እኛም በፀሎትና በሼር አይዟችሁ እያልን እናግዛቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0938481336
0909986025
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሐመር ዛሬ በመቀሌ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና ከሌሎች የአስተዳደሩ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ አሜሪካ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲኾን በርትታ እንደምትሠራ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ሐመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የመሩት ልዑካን ቡድንና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት ከመከሩባቸው ዝርዝር ጉዳዮች መካከል፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን ኹኔታ፣ አንዳንድ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት መመለስ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን መበተንና መልሶ ማቋቋምና ድርቁ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚገኙበት የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ሞሊ ፊ፣ ሐመር እና አምባሳደር ማሲንጋ፣ ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ከርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ጋር በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ መወያየታቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር መረጃ‼️

ኦነግ ሸኔ በዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት አባቶችን መግደሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ት አስታወቀች‼️

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኢኦተቤ ቴቪን ዋቢ በማድረግ ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ

1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) መናገራቸውን ሸገር ፕረስ ሰምቷል፡፡

የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት  መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በቅጽል ስሙ ልጅ ያሬድ በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለ

የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ነው

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር

ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃውን አቅርቧል።

የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።

ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።

ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 19:27:08
Back to Top
HTML Embed Code: