Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጥያቄዬ ምላሽ ካላገኘ  ጉዳዩን ወደ  ጠቅላይ ሚንስትሩ  ዳግም እውስደዋለው አለ።

የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለኢትዮ  ኤፍ ኤም እንደተናገሩት "የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ያስገቡትን ጥያቄ ከፍትህ ሚኒስትር መልስ ካላገኙ  ጥያቄውን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚወስዱትም  ተናግረዋል።

አቶ ካሳሁን ፎሎ  " የመጨረሻ አማራጫችን  ጥያቄያችንን በድጋሚ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረብ ነው" ብለዋል ።

አቶ ካሳሁንደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛው ኑሮ ውድነቱ እሱ ከሚያገኘው በላይ እንደሆነ  አንስተው የኑሮ ውድነቱ ቢጠነክርም የደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛው ገቢ እንዳላደገ አንስተዋል።

በዚህም ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ  ጥያቄያቸው መልስ እስከሚያገኝ ድረስ  መጠየቅ እንደማያቆሙም ገልፀዋል።

ማህበሩ የደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛውን የግብር ቅነሳን በተመለከተ ለፍትህ ሚኒስትር  ጥያቄ አቅርቦ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ  መዘገባችን ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Update

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።

ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት

የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ቤተክርስቲያኒቷ ማስታወቋን ዳጉ ጆርናል ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአማራ ክልል ምክር ቤት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ምክር ቤት አባል የነበሩትን የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

@sheger_press
@sheger_press
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው "መነኩሴ "ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን ሀገረ ስብገቱ ገለጸ።

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን "መነኩሴ"በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ "መነኩሴ" መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።
ከየካቲት 12 ቀን 20916 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ " መነኩሴ "ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ"መንኩሴ "መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በህግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።

@ethio_mereja_news
"በአካባቢያችን ሰኞ እለት ተደጋግሞ በተፈፀ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ ማንነታቸውን እንኳን መለየት አስቸጋሪ ሆኖብን ያገኘነውን አካል አንስተን ቀብረናል"--- የሞጃ ወደራ ነዋሪ

"እስካሁን 8 ህይወታቸው አልፎ የመጡ ሰዎችን ተመልክቻለሁ"--- የህክምና ባለሙያ

ሰኞ እለት በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃ ወደራ ተደጋግሞ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከዚህም ውስጥ የቤተሰብ ፕሮግራም ተካፍለው በመኪና ሲጓዙ የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሚገኙበት የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

ጥቃቱ ሲፈፀም በአካባቢው ግጭት እንዳልነበር የገለፁልኝ ነዋሪው "አንዴ ብቻ ሳይሆን እየተመላለሰ ነው ጥቃት ያደረሰው፣ መሳርያ የለን፣ ተዋጊ አይደለን..." ብለዋል። አክለውም እንዲህ አይነት ግድያ አይተው እንደማያውቁ ገልፀው ጥቃቱን ተከትሎ በአካባቢው የተሽከርካሪ አገልግሎት እንደቆመ፣ የተረፉትን ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ እንኳን ሳይቻል ለበርካታ ሰአታት ቁስለኛ ይዘው እንደቆዩ አስረድተዋል።

የምሰራበትን ተቋምም ሆነ ስሜን አትጥቀሰው ያሉ አንድ የጤና ባለሙያ ደግሞ "እስካሁን 8 ህይወታቸው አልፎ የመጡ ሰዎችን ተመልክቻለሁ፣ ምንም ማድረግ አልቻልንም። የበርካቶቹ ሰውነታቸው ጠቁሮ የከሰለ አይነት ነበር" በማለት ገልፀዋል።"

Via:EliasMeseret

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት ከፋኖ ጋር ለውይይት የመገናኘት ዕድል ካለው በውይይቱ ለመሳተፍ ሀገራቸው ፈቃደኛ መሆኗን ለመንግሥት መግለፃቸውን ኢትዮጵያን የጎበኙት ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

በአማራ ክልል ለቀጠለው ግጭት ወታደራዊ መፍትሔ ስለሌለው ዩናይትድ ስቴትስ ሰላምን ለማስፈን የምትሞክርበትን ዕድል ካለ በደስታ እንደምትቀበለውም አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ትናንት በበይነ መረብ በጋራ በሰጡት መግለጫ መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር ለዳግም ውይይት እንዲቀመጥ አሜሪካ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ድጋፍ እንደምታደርግም ገልፀዋል። ሁለቱ ባለሥልጣናት የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆንም አሜሪካ ድጋፏን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተጋጋሚ እየተገኙ ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት እያደረጉ ያሉት ዩናይትድ ስቴትስየአፍሪካቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ባለፈው ሳምንትም አዲስ አበባ እና መቀሌ ተገኝተው በኢትዮጵያ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ትናንት ከሀገራቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር በበይነ መረብ በጋራ በሰጡት መግለጫ መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር ዳግም መነጋገር ከፈለገ ለማመቻቸት፣ ከፋኖ ጋር ለመወያየት የሚችልበት ዕድል ካለ በደስታ እንደምትቀበል የመንግሥታቸውን አቋም መግለፃቸውን ተናግረዋል።

«ባለፈው ኅዳር በዳሬሰላም ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በተደረገው ድርድር በቀጥታ ተሳትፈናል። ለሁለቱም ወገኖች ባቀረብነው ጥሪ መሰረት ለዚያ ግጭት ሰላማዊ መፍትሔን ለማመቻቸት ዝግጁ ነን። ከፋኖ ጋር የመገናኘት ዕድል ካለም፣ ሰላምን ለማስፈን የምንሞክርበትን ዕድል በደስታ እንቀበላለን። በተደጋጋሚ እንደተናገርነው ለእነዚህ ግጭቶች ከዉጊያ መፍትሔ አይኖርም። እንደ እውነቱ ከሆነ አሁን ትኩረት መደረግ ያለበት ስለ ውይይት እንዲሁም በእርግጥም የዜጎችን ጥበቃ በማረጋገጥ ላይ ነው።» 

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉትና ከማይክል ሀመር ጋር ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከተለየ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ነግረውናል ያሉትንም አቋም አብራርተዋል።

«ብዙ የመንግሥት አካላትን እንዲሁም የማኅበረሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን አግኝተናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እያጋጠሟት ያለውን ፈተና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ ነኝ ብለዋል። በዚህ ቁርጠኝነት ላይ ጠንክረው እንዲሠሩ እናበረታታለን። የፀጥታ አካላት ለሚኑሱ ተቃውሞዎችም ሆነ  ጥቃቶች ምላሽ በሚሰጡበት ጊዜ የሚወስዱት እረምጃ የሚያሳስበን መሆኑን በይፋም በግልም ገልጸናል። የተወሳሰበ የደህንነት ፈተና እንደሆነ እናውቃለን፣ ነገር ግን የሲቪሎችን መብት ለማክበር ብዙ መደረግ አለበት። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሁለቱም ክልሎች መረጋጋት እንዲሰፍን በሚያደርጉት ጥረት በየክልሉ ባሉ አምባሳደሮቻችን በኩል ቆመናል።» ብለዋል ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ።(ዘገባ፣ዶቼ ቬሌ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ንፁሐን ተገድለዋል ተባለ

ባለፈው ሰኞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰላ ድንጋይ ከተማ አቅራቢያ ሰላ መገንጠያ በተባለ ቦታ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ንፁሐን መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ ህፃንን ክርስትና አስነስተው ሲመለሱ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል የህፃኑ እናትም ህይወቷ ማለፉ ተነግሯል፣ በተመታው መኪና ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል 2 ልጆቻቸው እንደተገደሉባቸው አንድ አባት ገልጠዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ  ልዩ ስሙ “ሰላ መገንጠያ” በተባለ አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ የነበሩና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሰላ ደንጋይ ነዋሪ በሰጡን አስተያት  ሳሊት ከተባለ ከተማ የህፃን ልጅ የክርስትና ጥምቀት ፈፅመው በአይሲዙ የጭነት መኪና ተሳፍረው በመመለስ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ የድሮን ጥቃት ደርሶ እስከ 10 ዓመት አድሜ ያላቸው ህፃናትና ሌሎች ንፁሀን ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል፡፡

“ክርስትና ነበር፣ የተሰበሰቡ እናት፣ እህት፣ ወንድም አክስት፣ የዘመድ ልጆች ነበሩ፡፡ የክርስትናውን ድግስ በልተውና ጠጥተው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ነበሩ፣ አይሱዙ መኪና ነበረች፣ በዚያች መኪና ወላዷና ሌሎችም ሰዎች ተጭነው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የድሮን ድምፅ ተሰማ፣ ከተማው ላይ ነበርን እኛም ሰማን፣ በመኪናው ውስጥ የነበሩ ንፁሀን ናቸው፣ ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም፣ ከ10 ዓመት በታች ሁሉ ህፃናት ነበሩበት፡፡” ነው ያሉት፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪው “በጥቃቱ ክርስትና አስነስታ ስትመለስ የነበረች እናት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ህጻኑ ደግሞ በተዓምር ከሞት አምልጧል” ብለዋል፡፡ ሌሎች 40 ያክል ሰዎች ደግሞ በጥቃቱ መገደላቸውን መስማታቸውን መልክተዋል፡፡

“የሞቱትን አንድ ሁለት ብለን ባንቆጥርም ባለው መረጃ ፣ 40 ነው የተባለው፣ እናት ሞታለች፣ አባት ቤት ይጠብቁ ስለነበር ወደ ቦታው ባለመሄዳቸው ተርፈዋል፣ በእለቱ ክርስትና የተነሳው ህፃኑ ሁለቱም አያቶች፣ አክስት አጎት፣ ሞተዋል፣ ህፃኑ አልሞተም ተርፏል፡፡” ብለዋል፡፡

ሌላ የሰላ ድንጋይ ከተማ አስተያት ሰጪ በበኩላቸው በጥቃቱ የሞቱትን ቁጥር በትክክል መናገር ባይችሉም ከአንድ ቤተሰብ እስከ 7 ሰዎች መገደላቸውን በስልክ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

“ጉዳት የደረሰው ከእኛ አካባቢ ከክርስትና ሲመለሱ ሰኞ እለት አይሱዙ ተሳፍረው በነበሩ ሰዎች ላይ ሰላ መገንጠያ ላይ ነው፡፡ ክርስትና ሲያስነሱ የነበሩ ቤተሰቦች እንዳለቁ ነው ያለው መረጃ፣ ምን ያክል ሰው እንደሞተ ባይታወቅም በጣም ብዙ ሰው እንደተጎዳ ነው መረጃ ያለው፣ ከአንድ ቤተሰብ እስከ ሰባት ሰዎች እንደሞቱ ከባለክርስትናው ቤተሰብ ተነግሯል፣ (በእለቱ)ጦርነት የነበረው ከእኛ ከሳሲት ከተማ ጋውና ወርዶ ፊላ ገነት ነው፣ ይህም ወደ 15 ኪሎሜትር ይርቃል፡፡”

የክርስትና ስነርዓቱ ተካፋይ ያልነበሩ ነገር ግን “ፊላ ገነት” በተባለው አካባቢ ጦርነት ስለነበረና ጦርነቱ ሊደርስባቸው ይችላል በሚል  ከሳሲት ከተማ ልጆቻቸውን  የትራንስፖርት ገንዘብ ከፍለው በክርስትና ስነስዓት ላይ የነበሩ ሰዎችን አሳፍሮ በነበረው የጭነት መኪና እንዲሳፈሩ ያደረጉ አንድ አርሶ አደር አባት ሁለት ህፃናት ልጆቻቸው በእለቱ በጥቃቱ እንደተገደሉባቸውና ቀብራቸው እንደተፈፀመ ገልጠዋል፡፡

“ ... ተማሪዎች ናቸው፣ ተኩስ ስለነበር (ፊላ ገነት) እነሱን አሸሻለሁ ብየ ነው፣ ንፁሀን ናቸው፣ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም (ጥቃቱ) የ10 ዓመትና የ8 ዓመት ተማሪዎች ናቸው፣ ሴትና ወንድ ናቸው፣ ቀብር ተከናውኗል፣ ብዙ ሰው ደግሞ ቆስሏል፡፡”

ጥቃቱ ከተፈፀመበት ሰላ መገንጠያ በግምት ከ15 እስከ 20 ኪሎሜትር  ቦታ ላይ በእለቱ በፋኖና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ጦርነት እንደነበርም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክተን ተጨማሪ አስተያት ለማካተት ለአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታና ለክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊዎች ብንደውልም ስልካቸው አይነሳም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገርም የለም ።

Via ዶቼቬሌ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ለስድስተኛ ክፍል 86 ሺህ 691 ተማሪዎች እንዲሁም ለስምንተኛ ክፍል 88 ሺህ 28 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ በሥነ-ልቦና የማዘጋጀት፣ ከኩረጃ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲይዙ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል። ተማሪዎች በስልክና በመሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲቀነሱና ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ::

ነፍስ ይማር::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኦሮምያ ባለስልጣናት የተደራጀ ህቡዕ ኮሚቴ ከፍተኛ ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ ይሰጥ ነበር” - የሮይተርስ ምርመራ ሪፖርት!!

ሮይተርስ የዜና ወኪል አካሄድኩት ባለው ለወራት የዘለቀ ምርመራ በኦሮምያ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተቋቋመ እና በህቡዕ የተደራጀ ኮሚቴ፣ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ወንጀሎችን እንዲፈጸሙ፣ ተቃማሚዎችን እንዲያጠፉ ትዕዛዝ ይሰጥ ነበር ሲል አስታወቀ።

የህቡዕ አደረጃጀት አለው የተባለው ኮሚቴው ስያሜው “ኮሬ ነገኛ” ወይንም የጸጥታ ኮሚቴ መሆኑን እና ዶ/ር አብይ አህመድ ጠ/ሚኒስትር ሁነው በተሾሙ ወራት ውስጥ የተቋቋመ መሆኑን የዜና አውታሩ በሪፖርቱ ጠቁሟል።

ኮሚቴው የሚመራው በኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ መሆኑን እና በአባልነት የክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ እና የፖለቲካ ባለስልጣናት እንደሚገኙበት ጠቁሟል።

በ2014 ዓ.ም በከረዩ አባገዳዎች ላይ የተፈጸመው ግድያ ጋር በተያያዘ ሮይተርስ በምርመራ ማለትም ከሚስጥራዊ ሰነዶች እና ቃለምልልሶች አገኘሁት ባለው መረጃ ከህቡዕ አደረጃጃቱ በተላለፈ ትእዛዝ እንዲገደሉ ተደርገዋል ብሏል።
ሙሉ ሪፖርቱን ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ👇👇👇👇👇
https://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-violence-committee/?fbclid=IwAR3jwt6lqBxTqwaC9ki4waWcOtNkUFJSycWY4lUdRF3h0CxE_q60mfSHE5I

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን የመነኮሳት ግድያ አስመልክቶ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት ከመንግሥት አካላት ጋር ውይይት መካሄዱ ተሰምቷል።

በቢሾፍቱ ከተማ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ግቢ ተካሂዷል የተባለው ሰፊ ውይይት ዐራት ሰዓታትን እንደፈጀ ተነግሯል።

ውይይቱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ መሪነት ነው የተካሄደው ተብሏል። በውይይቱ የምሥራቅ ሸዋ ዞን የጸጥታ ክፍል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮነን የተመራ ልዑክ ጨምሮ  የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አበምኔትና የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች መገኛቸው ተዘግቧል።

በውይይቱ ላይ በመንግሥት የፀጥታ አካላት አማካኝነት የሰማዕታቱን አስክሬን ከወደቁበት አንስቶ በክብር ወደ ገዳሙ በማምጣት ሥርዓተ ቀብር እንዲፈፀምላቸው፤በቋሚነት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊትና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጸጥታ መዋቅር ገዳሙንና ገዳማውያንን በዘላቂነት መጠበቅ እንዲቻል እና  በመንግሥትና በሀገረ ስብከቱ እንዲሁም በቤተክርስቲያን አባቶች ልባቸው የተሠበረና የተጎዱ የገዳሙ አባቶችና እናቶችን በጋራ ማጽናናት የሚቻልባቸውን መፍትሔዎች ተቀምጧል ።

በስተመጨረሻም ግብረ ኃይሉ  ከሀዘኑ በኋላ ዳግም ተገናኝቶ በተሠሩ ሥራዎችና ወደ ፊት አስተማማኝ ሰላም በሚሠፍንበት ጉዳይ ላይ ለመመካከር ቀጠሮ ተይዞ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዕለቱ ውይይት በጸሎት ተዘግቷል ሲል መረጃውን የሀገረ ስብከቱ ሐመር ተዋሕዶ ሚዲያ አውጥቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሰመኮ፣ በኦሮሚያ ክልል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና ኢመደበኛ የአማራ ታጣቂዎች በውጊያና ከውጊያ ዐውድ ውጭ በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን ማረጋገጡን አዲስ ባወጣው የኹለት ዓመታት የክትትል ሪፖርት አስታውቋል።

ኢሰመኮ ይህን ያለው፣ በቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሲቪሎች ላይ ተፈጽመዋል ያላቸውን ከሕግ ውጭ የኾኑ ግድያዎች በማስመልከት ባወጣው ሪፖርት ነው።

ኮሚሽኑ፣ ድርጊቶቹ “እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች” እና "የጦር ወንጀልን" እና "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀልን" ሊያቋቁሙ እንደሚችሉ ገልጧል።

በጥሰቶቹ ላይ "ፈጣን፣ ገለልተኛና የተሟላ" ምርመራ ሊደረግ፣ ተጠያቂነት ሊረጋገጥና ተጎጂዎች ሊካሱ እንደሚገባም ኢሰመኮ አሳስቧል።
#NewsAlert‼️

በአማራ ከልል ሶስት ከተሞች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አንዲቆም ተደረገ

በአማራ ከልል ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት፣ ከሸዋሮቢት ወደ ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ/ብረሀን -ሸዋሮቢት - ደሴ የትኛውም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከዛሬ የካቲት 16 ቀን ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ።

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት የትራንስፖርት አንቅስቃሴ እንዲቆም የወሰነው፤ በቀጠናው “ፅንፈኛ ሀይሎች” ላይ እርምጃ እየወሰደ በመሆኑ “ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው” እና አካባቢውን በአጭር ቀናት “ከፅንፈኛ” ሀይሉ ነፃ ለማድረግ ኦፕሬሽን ስራ የተጀመረ በመሆኑ ነው ሲል ገልጿል። ኮማንድ ፖስት አክሎም “ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የፀጥታ ሀይሉም ውሳኔው ይፈፀም ዘንድ ክትትል እንዲያደርግ” በሚል የተወሰነ መሆኑን አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዶ/ር ካሳ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት አነሳ!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 16፤ 2016 ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ፤ የየካ ምርጫ ክልል ተወካይ የሆኑትን የዶ/ር ካሳ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት አነሳ። የዶ/ር ካሳ የህግ ከለላ የተነሳው፤ “በአማራ ክልል ተደራጅቶ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ይንቀሳቀሳል” ከተባለ “ጸረ ሰላም ኃይል” ጋር “ትስስር ያላቸው” እና “ለቡድኑ መመሪያ ይሰጡ የነበረ በመሆኑ ነው” ተብሏል።

VIa:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ፣ ኢትዮጵያ ከሰሜን ሶማሌላንድ ጋር በተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት መሠረት የባሕር ኃይል ጣቢያ ለማቋቋም ከተንቀሳቀሰችና ምናልባትም ለሶማሊላንድ እውቅና ከሰጠች፣ "ሱማሊያ ራሷን ለመከላከል ማንኛውንም ርምጃ ትወስዳለች" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሱማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ውጥረት ውስጥ በገባች ማግስት፣ የውቂያኖስ የግዛት ወሰኗን ከጣልቃ ገብነትና ከ"ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች" ለመከላከል ከቱርክ ጋር የተፈራረመችውን የመከላከያ ስምምነት ዝርዝር ይዘት እስካኹን ይፋ አላደረገችም።

ኾኖም ፕሬዝዳንት ሞሃመድ፣ ከቱርክ ጋር የተፈራረምነው የባሕር መከላከያ ስምምነት በየትኛውም አገር ላይ ያነጣጠረ አይደለም በማለት ከጥቂት ቀናት በፊት ተናግረው ነበር።

ሱማሊያ ሉዓላዊ የባሕር ወሰኔ የምትለው የውቂያኖስ ዳርቻ፣ የራስ ገዟን ሶማሊላንድን የባሕር ወሰን ያካትታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የሱማሊያ ሉዓላዊነት መከበር አለበት" ኤርትራ እና ግብፅ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በምን ጉዳዮች ላይ ተወያዩ?

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዛሬዉ እለት ወደ ግብፅ እንዳመሩ ዳጉ ጆርናል መዘገቡ አይዘነጋም። የግብፁ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ለኤርትራዉ አቻቸዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ባቀረቡላቸው ግብዣ ጉዞ ማድረጋቸዉን የኤርትራ መረጃ ሚኒሰቴር አስታዉቋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ካይሮ ሲደርሱም የግብጹ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ በጽ/ቤታቸዉ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

ዛሬ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ካይሮ ውስጥ ባካሄዱት ውይይት የሱማሊያን ሉዓላዊነት የማክበርን አስፈላጊነት አጽንዖት እንደሰጡበት ተሰምቷል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለሦስት ቀናት በግብፅ በሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳለህን የተካተቱበትን ልዑክ ይዘዉ ነው ካይሮ የደረሱት። የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገብረ መስቀልም ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ፕሬዝዳንት ሲሲ በኹለትዮሽ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ በ"ኤክስ" ገጻቸው አስታውቀዋል።

ሆኖም የግብፅ መገናኛ ብዙሃን የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል ተፈርሞ ሶማሊያ ሉዓላዊነቴን ይጥሳል ስትል ቅሬታ ላነሳችበት ጉዳይ በሚመስል መልኩ የሶማሊያን ሊዓላዊነት የማክበርን አስፈላጊነት አጽንዖት እንደሰጡበት ተሰምቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጥቂቱ 30 ንጹሃን መገደላቸው ተነገረ።

በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ሳሲት በተባለችው ከተማ አቅራቢያ 50 ሰዎችን ያሳፈረ አይሱዙ ተሽከርካሪ መንገደኞችን ለማውረድ በቆመበት ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት 18 ሰዎች መቁሰላቸውንም ነው የአይን እማኞችን የጠቀሰው የሪሊፍ ዌብ ዘገባ የሚያሳየው።

የድሮን ጥቃቱ ሲፈጸም በአካባቢው በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት እንዳልነበር የተናገሩት ነዋሪዎች፥ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላም ድሮኖች በአካባቢው ሲሽከርከሩ እንደነበር ገልጸዋል። ሬውተርስ በበኩሉ ባለፈው ሰኞ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት በጥቂቱ 15 ንጹሃን ህይወት ማለፉንና ጥቃቱ መከላከያና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ ከሚያደርጉበት አካባቢ በ24 ኪሎሜትር ርቀት ላይ መፈጸሙን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
 
“መጀመሪያ ከባድ ፍንዳታ ሰማን ከዚያም አካባቢው በጭስ እና አቧራ ተሸፈነ፤ የ15 ሰዎችን አስከሬን ሰብስበናል፤ እጅና እግራቸው እዚያም እዚህም የተበታተኑ ሟቾችን አስከሬን መሰብሰብ ዘግናኝ ነበር” ብለዋል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ቄስ ለሬውተርስ በሰጡት ቃል።

በጥቃቱ 10 የቤተሰብ አባላቱን እንዳጣ የሚገልጽ ሌላ የሳሲት ነዋሪም በጥቃቱ ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ከባድ ፍንዳታ ከመሰማቱ በፊት ትንሽ ድሮን መመልከቱን ገልጿል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልሉ ግጭት ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል። ኮሚሽኑ እስካሁን በጥቂቱ 81 ንጹሃን በድሮን ጥቃት እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መንገድ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው መግለጹም አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴና ማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን የሕወሃት ጠቅላላ ጉባዔ በኹለት ወራት ውስጥ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

ፓርቲው፣ የኹለቱ አካላት የጋራ መድረክ የጉባዔውን አጀንዳ መምረጣቸውንም ገልጧል። ፓርቲው ጨምሮም፣ በመጪው ሳምንት በክልል ደረጃ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባና ከዚያም በዞን፣ ወረዳና ጣቢያ ደረጃ የአመራር፣ የአባላትና የሕዝብ ተወካዮች መድረክ ለማካሄድ ከውሳኔ ተደርሷል ብሏል። ምርጫ ቦርድ ሕወሃትን ከሕጋዊ ፓርቲነት የሰረዘበት ውሳኔ ግን እስካኹን እንደጸና ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዘን በሸዋሮቢት ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ጥቃቱ ተከትሎ በአካባቢው የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ትላንት የካቲት 15/ 2016 ከአዲስ አበባ ወደ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከሚሴ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበስሩ ስምንት ሰዎች፤ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በታጣቂ ኃይሎች ተገደሉ።

ክስተቱን ያሳወቀ ምንጫችን እንደገለጸው ከተገደሉት ስምንት ሰዎች ውስጥ አምስቱ መምህራን ናቸው ብለዋል።
ምንጩ አክሎ እንደገለጸው ሰዎቹ እየተጓዙበት የነበረውን ተሽከርካሪ ታጣቆዎቹ በማስቆም “መታወቂያቸውን በማየት የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን ካረጋጋጡ በኋላ ገደሏቸው” ሲል ገልጿል።

ቶሎሳ ኩሩ፣ ኤፍሬም እንዳለው፣ ኢድሪስ ሞሀመድ እና ገመቹ ካሳሁን የሚባሉ ገለሰቦች ከተገደሉስ ሰዎች መካከል ናቸው።
አዲስ ስታንዳርድ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከህወሓት አባልነታቸዉ ለመሰናበታቸዉ "የሐቅ የበላይነት በሌለበት ጊዜ እውነት ሊያሸንፍ አይችልም" ሲሉ ተናገሩ

ሰሞኑን ህወሓት አደረኩት ካለው ግምገማ በኃላ "ለጠላት ሚስጢር አሳልፈው ሰጥተዋል" ያላቸውን ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ሙሉ ገብረእግዚአብሔር ከፓርቲው እንዲባረሩ ማድረጉ ይታወሳል።  

ታድያ ከተባረሩት የህወሓት አባላት መካከል አንደኛዋ የሆኑት የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋና የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም በተሰጣቸው ውሳኔ ዙርያ ከVOA ትግርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም፤ "የተደረገው ግምገማና የተሰጠው ውሳኔ ሚዛናዊነት ትተን ካሳለፍኩት ስቃይና መከራ ወጥቼ በፓርቲየ ተገምግሜ የትግሉ አካል ሆኜ እዚህ በመድረሴ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል።

አያይዘውም ስለተፈጠረው ነገር ሲያብራሩ "እኔ ወቅታዊ ችግር እንጂ የፖለቲካ ችግር ትላንትም አልነበረኝም ዛሬም የለኝም" ያሉ ሲሆን ስላጋጠማቸው ወቅታዊ ችግር ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

ቀጠል አድርገውም "በዚህ የሓቅ የበላይነት በሌለበት ሰዓት እውነት ሊያሸንፍ ስለማይችል፣ ሓቅና ፅንስ ግን ጌዜውን ጠብቆ መውጣቱ ስለማይቀር በጊዜ ሂደት እውነታውን ሁሉም ያየዋል" ሲሉም ተደምጠዋል።

የህወሓት ፅሕፈት ቤት ፕሮፓጋንዳ ክፍል ሀላፊው አቶ አያሱ ተስፋይ በኩላቸው በሁለቱ የህወሓት አመራሮች  ላይ የተወሰደው እርምጃ፣ የህወሓት አመራሮች በጦርነቱ ወቅት የነበራቸውን አሰላለፍ ከገመገመ በኃላ ነው ማለታቸውም ዳጉ ጆርናል VOA ትግርኛ ካሰራጨው ዘገባ ተመልክቷል።

ህወሓት በጦርነቱ ወቅት “በጠላት እጅ ወድቀው ነበር” ያላቸውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በተመለከተ “ለረጅም ጊዜ ሲንጓተት” የቆየውን ያስተላለፈው ውሳኔ ፤ የነበሩትን ሁኔታዎች በመገምገም እና የፓርቲውን ህገ ደንብ በመከተል መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ መጥቀሱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

በሌላ በኩል  ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲቀጥሉ  ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፣ አፅብሃ አረጋዊ፣ ወይዘሮ ኪሮስ ሀጎስ እና ዶ/ር ረዳኢ በርሄ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ይቀጥላሉ ማለቱን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ አይዘነጋም። ህወሓት በምርጫ ቦርድ ህጋዊ የፓርቲነት እዉቅናዉን ያጣ ቢሆንም በክልሉ ግን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ይገልጻል።

በቅርቡም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ንግግር የፓርቲዉን እዉቅና ለመመለስ መግባባት ላይ መድረሳቸዉን መናገራቸው አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 21:24:38
Back to Top
HTML Embed Code: