Telegram Web Link
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ይፋ ሆኗል‼️
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች የምዝገባ ሂደትን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡

በመደበኛ እና በማታ መርሐ ግብር ከ872ሺህ በላይ ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ብቻ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ይኾናል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10 ዓመት 🤔

የ13 ዓመት ልጃቸውን አስገድደው የደፈሩት አባት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን (በቀድሞው አማሮ ልዩ ወረዳ) ኬሌ 01 ቀበሌ በተለምዶ " ማክሰኞ ሰፈር " ተብሎ በሚጠራዎ አካባቢ አንድ አባት በመጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ልጃቸውን አስገድደው የደፈሩት አባትበእስራት እንደተቀጡ የዞኑ ፎትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ስንታየሁ ከተማ መኮንን የተባሉ የ42 ዓመት አባት የአብራካቸው ክፋይ የ13 ዓመት 8ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸው ላይ ነበር።

በለበሰችው ሻርፕ አፏን አስሮ ኃይል ተጠቅሞ ደፍሯታል።

ልጅቷ በተደረገባት ድርጊት ማሕጸኗን ሕመም ሲሰማትና መቋቋም ባለመቻሏ የዐቃቢ ሕግ 2ኛ ምስክር ለሆነች ጎረቤቷ እያለቀሰችና እያነከሰች ሂዳ የተፈጸመባትን በዝርዝር ተናግራ ጎረቤቷም ወደ ሕክምና ተቋም አብረዋት ሂደው አስመርምረዋታል።

በምርመራውም በሕፃኗ ላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የመደፈር ወንጀል መፈጸሙንና የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ መገኘቱን በሕክምናው ተረጋግጧል።

የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን ሰምተውት የወንጀል ምርመራ አድርገዋል።

የኮሬ ዞን ከፍተኛ አቃቢ ሕግ ክስ በመመስረት ጉዳዩን በወቅቱ ለነበረው የአማሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ወንጀል ስለመፈጸማቸው በችሎት ተጠይቀው ‘አልፈጸምኩም’ ብለው ክደው ተከራክረዋል።

በክርክሩ ልጅቷ የ13 ዓመት ታዳጊ በመሆኗ ከ5-20 ዓመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑና በልጅቷ ላይ ዛቻና እንግልት በመፈጸማቸው አባት ዋስትናቸው ተነፍጎ በፓሊስ እጅ ሆነው እንዲከራከሩ ተደርገዋል።

ፍርድ ቤት የልጅቷን፣ የዐቃቢ ሕግ ቃል ሰምቶ ምክሮችም እንደ ዐቃቢ ሕግ ክስ በዝርዝር ወንጀል ስለመፈጸሙ አስረድተው፣ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችም አባት ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ ለማስተባበል ቢሞክሩም በግልጽ ያስረዱት ነገር እንደሌለ ተመላክቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝ የምስክር አመሰካከር፣ የቀረቡ የሕክምና ሰነዶች ከተገቢ ሕጎች ጋር አይቶ ግለሰቡም ጥፋተኛ ብሎ በሙሉ ድምፅ ፍርድ ሰጥቷል።

ዐቃቢ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሲጠየቅ በሕጉ በራሱ ከብዶ የተዘረዘረ ስለሆነ የለኝም ያለ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቃ ፤ ቀደም ሲል ደንበኛቸው በወንጀል ተፈርዶበት የማያውቅ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ፣ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ስለሆነ ለፍርድ ቤቱ 3 ማቅለያዎችን አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኝ ተመልክቶ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወስነበት የዞኑ ፍትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

Via - Tikvahethiopia
 

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰው መግደል ማፈናቀል አስርቦ መፍጀት ነው እንዴ የብልፅግና ስኬት‼️

እንግዲ የብልፅግና እንዳለው በስልጣን ላይ ባለሁበት በእስካሁኑ ሂደቶቼ ስኬታማ ነኝ ብሏል፡፡

የ21ኛው ክፍለዘመን ውዱ ጦርነት በማረግ
ብሎም ደግሞ
የራሱን ህዝብ ለመግደል ከኤርትራ ድረስ ወታደር ያመጣ
ሚሊዮኖች ያፈናቀለ
ሚሊዮኖችን የገደለ
ሚሊዮኖችን ቤት አልባ ያደረገ
ሚሊዮኖችን አስርቦ የፈጀው የብልፅግና ፓርቲ ስኬታማ ነኝ እያለን ይገኛል።

ያሳዝናል

ማህበረሰቡ የኑሮ ዉድነቱ ፤የፖለቲካ ጡዘቱ በሰላም ወቶ በማይገባበት ፥ስራ አጥነት ተደማምሮ መንግስት ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች እንደተጋረጡበት በተለያዩ ወቅቶች በምክር ቤት ጭምር ሲነሳ ተሰምቷል፡፡

ገዥዉ የብልፅግና ፓርቲም በበኩሉ ግምገማዉን በሚያደርግበት ወቅት መሰረታዊ የሆነ ለዉጥ ማምጣት እንደቻለ እየተናገረ ይገኛል።

ብልፅግና ባወጠው መግለጫ ከመሰረተ ልማት ግንባታ እስከ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ማስፈፀም ድረስ በያዘዉ የጊዜ ሰሌዳ እያከናወነ እንዳለ አንስቷል፡፡

አሀዱ ኤፌኤም ፓርቲዉ ስልጣን ላይ ባሳለፋቸዉ አመታቶች ለዉጥ አምጥቷል ወይ ብሎ የፓርቲዉን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ ፈዲላ ቢያን ጠይቋል፡፡

እሳቸዉም ብልፅግና ፓርቲ መሬት ላይ የሚታይ ስራ እየሰራ ነዉ ይህም ዜጎችን ተጠቃሚ አድርጓል ስኬታማም ነዉ ቃል የገባቸዉንም እየፈፀመ ነዉ ሲሉ መልሰዋል(ሸገር ፕረስ)።

@sheger_press
@sheger_press
በክፍያ መንገድ ላይ የደረሰ የትራፊክ አደጋ።

የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ በኪ.ሜ 3 ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ ሲጓዝ የነበረው ሲኖትራክ ተሽከርካሪ በክፍያ መንገዱ ውስጥ ለደንበኞች የጉዞ ደህንነትን መልዕክት ማስተላለፊያ ስክሪን (Variable Message Sign) እና የመንገድ መቆጣጠሪያ ካሜራ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ችሏል።

ጉዳት ሊደርስ የቻለው አሽከርካሪው የተሽከርካሪውን ገልባጭ ከፍ አድርጎ በማሽከርከር መሆኑን ታውቋል።

ኢንተርፕራይዙ የመንገድ ደህንነት ባለሙያዎችን በማስተባበር ሌላ አደጋ ሳይከሰት በፍጥነት መንገዱ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖረው ማድረግ ተችሏል።
Wasu

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የነፍስ አድን ስራው ድጋሜ ተጀመረ‼️

በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት  ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራው ዳግም ተጀመረ።

የደቡብ ወሎ ኮሙንኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ እያሱ ዮሀንስ እንዳሉት የወጣቶቹን ህይወት ለመታደግ የወረዳው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሌት ተቀን በፈረቃ እየቆፈረ እንደነበር ነገር ግን መልክዓ ምድሩ ለቁፋሮ አመቺ አለመሆኑን ተከትሎ ተጨማሪ ሰው ላለማጣት በሚል ቁፋሮው ከአቅም በላይ ነው ተብሎ ቆሞ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ዳግም እንደተጀመረ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ ማዕድኑን ለማውጣት እየቆፈሩ እያሉ መውጫቸው በዓለት የተዘጋባቸው ሲሆን በአካባቢው በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀን ጀምሮም ወጣቶቹን ለመታደግ የደላንታ ወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዘመቻ እየቆፈረ ነው የተባለ ሲሆን ወጣቶቹ ያሉት በግምት 750 ሜትር ርቀት ላይ ይሆናልም ተብሏል፡፡

እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ50 ሜትር በላይ ርቀት ቁፋሮ እንደተቆፈረ የተናገሩት ሀላፊው ቦታው አለታማ እና የቁፋሮ ማሽን ለማስገባት አመቺ አለመሆኑ ጥረቱን ፈታኝ አድርጎታል ሲሉም አክለዋል፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ ኦፓል ማዕድን በማውጣት ስራ ላይ የነበሩ ወጣቶች ተማሳሳይ አደጋ አጋጥሟቸው ነበር ያሉት አቶ እያሱ በተደረገው ርብርብ ከ11 ቀናት እልህ አስጨራሽ ቁፋሮ በኋላ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ማግኘት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

አቶ እያሱ አክለውም ወጣቶቹን በህይወት ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረው በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ለመታደግ ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡
ዘገባው የአል አይን ነው
በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ድርቅ እና ርሃብ ያስከተለው አደጋ መቀጠሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለስልጣናት እየገለፁ ነው።

ከትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አበርገለ የጭላ ወረዳ በሶስት ወራት ብቻ 120 ህፃናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን የአበርገለ የጭላ ወረዳ አስተዳደር ገልጿል።

ካለፈው ከመስከረም ወር ጀምሮም በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ 83 ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።
በአማራ ክልልም በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው ድርቅ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ተጠቂ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ ከ380ሺህ በላይ ህፃናትና እናቶች ለከፍተኛ የአልሚ ምግብ እጥረት የተጋለጡ መሆናቸውን የአማራ ክልላዊ መንግስት ከሰሞኑ አስታውቋል።

በክልሉ በሰሜን ጎንደር ጃንአሞራ ወረዳ እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ የሚገኙ በድርቅ የተፈናቀሉ ወገኖች “ተገቢ እርዳታ እያገኘኙ ባለመሆናቸው ለከፋ ችግር መዳረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡

መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው ኦክስፋም የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ከሦስት ሰዎች አንዱ ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጡን አመልክቷል።እንደ ረድኤት ድርጅቱ በትግራይ እና አማራ ክልሎች በድምሩ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ለረሀብ ተዳርጓል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ፤በኢትዮጵያ በግጭቶች፣ በድርቅ እና በጎርፍ ሰበብ ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል።(ዶቸቬለ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:52 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ ጀርባ ለህንጻ ግንባታ የመሰረት ብረት እያሰሩ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋስት መረጃ ባደረሱት መረጃ አደጋዉ የደረሰዉ ሰራተኞቹ ለመሰረት በተቆፈረዉ አስር ሜትር ጥልቀት ባለው ቦታ በስራ ላይ እንዳሉ ድንጋይ ተንዶባቸዉ ነዉ።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወቱ ያለፈዉን ሰዉ አስከሬን የአወጡ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ህክምና አየተደረገላቸዉ ይገኛል።

ዛሬ አደጋ የደረሰበት ቦታ አሁንም ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የሚመለከታቸዉ አካላት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ በግንባታ የስራ ላይ አደጋ በ20 ቀናት ዉስጥ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን አቶ ንጋቱ ለፋስት መረጃ ተናግሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“400 የኢቢሲ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳላቸው” ያጋለጠው ግለስብ ከሥራ “ተባረረ”

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኢቢሲ) ለዘጠኝ ዓመታት ያገለገለው ወገን አበበ የተባለ ግልሰብ በኢቢሲ የተለያየ የሥራ ዘርፍ ላይ ያሉ “400 የሚሆኑ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ” እንዳላቸው አጋልጠሃል በሚል ከስራ መባረሩን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በወገን አበበ ላይ “ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” ወንጀል ክስ የመሰረተበት ሲሆን፤ ወገን አበበ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው ሠዎችን ሥም ዝርዝር በማቅረብ ተከራክሮ ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 7 ቀን 2016 በዋለ ችሎት ወገን አበበ በነጻ እንዲለቀቅ ወስኗል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መራዊ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ፈጽመውታል የተባለውን የንጹሃን ሰዎች ግድያ ሊመረምር መዘጋጀቱን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ነጃት ግርማ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቦርዱ፣ ክስተቱን በከተማዋ በአካል ተገኝቶ መቼ እንደሚመረምር ግን ምክትል ሰብሳቢዋ አለመግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ምክትል ሰብሳቢዋ፣ ባካባቢው ያለው የጸጥታ ኹኔታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሂደቱን እንደሚወስነው ገልጸዋል ተብሏል።

ቦርዱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተፈጸሙባቸው የክልሉ አንደንድ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ሳቢያ ምርመራ ለማድረግ መቸገሩንን ምክትል ሰብሳቢው ስለመጠቆማቸው ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።(Wazema)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ ነው!

የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን የስድስት ወራት አፈፃፀም ሰሞኑን ገምግሟል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራው ከታሰበው በላይ ቁጥሩ የሰፋ እና ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ የሚገኝ ነው።

ለትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሂደቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰብሳቢነት የሚሳተፍበትና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የትምህርትና ሥልጠና እና የትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ዲግሪና ከዲግሪ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽነር ኃይሌ (ዶ/ር) አስታውቀው፤ ከዲግሪ በታች የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሠራተኞች ማስረጃ የማረጋገጡ ሥራ በቀጣይ የትግበራ አካል እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ሥራው በአምስት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተሠራ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነር መኩሪያ (ዶ/ር) የፌዴራል ተቋማትን፣ የሚኒስትሮችና የተጠሪ ተቋማትን ማስረጃ ማጥራት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሆኖ ቢሠራ የተሻለ እንደሚሆን በማመን ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሠራ ነው ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሕክምና ዶክትሬት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ መንትዮቹ ዶክተሮች

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት 271 የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥም በሕክምና ዶክትሬት የተመረቁ መንትዮቹ ዶክተር ቸርነት ተስፋሁን እና ዶክተር ብሩክ ተስፋሁን ይገኙበታል፡፡

መንትዮቹ  ዶክተሮች  በከፍተኛ ማዕረግ እንደተመረቁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲሰቲ መረጃ ያመላክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ምን አሉ?

አፍሪካ በድሮ ጊዜ የማይካድ ሁሉን አቀፍ ስልጣኔ ነበራት  ነገር ግን ቀኝ አገዛዝ ብዙ ነገሯን አበላሽቷል። በአለም ስልጣን እና ኢኮኖሚ ላይ  አፍሪካ ትርጉም ያለው ድርሻ ሊኖራት ይገባል።

ከአለም አቀፍ የሚገኙ ብድሮች ፍትሃዊ  እና በአነስተኛ ወለድ የሚሰጡ መሆን አለባቸው። ሆኖም ግን አፈሪካ ለማደግ ሁሉን አቀፍ እድገት የሚያመጣው ላይ ትምህርት  ላይ ትኩረት  ሰጥታ መስራት አለባት። ኢትዮጵያ ለትምህርት  ቅድሚያ በመስጠት ባለፉት አምስት አመታት ከ 30,000 በላይ መዋዕለ ህፃናት ከፍታለች።

የአለም ቴክኖሎጂያዊ እድገት ጥቅም እንዳለው ሁሉ የአፍሪካን እድገት ላይም ፈተና የደቀነበት ነገር አለ።በግብርና ፣ በሳይንስ ፣ በቴክኖሎጂ  በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ ከድህነት ለመውጣት ብዙ ነገር መስራት ይጠበቅበናል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር መረጃ … ከአዲስ አበባ

የሱማሊያ መንግስት ልዑካን ቡድን ያልተፈቀደ የጦር መሣሪያ ይዘው ወደ አፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመግባት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።ይህንን ተከትሎ  ከሞቃድሾ መግለጫ ወጥቷል። መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ወደሚካሄድበት ስፍራ “እንዳልገባ ለመከልከል ሞክረዋል” በማለት ከሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
ሰበር መረጃ … ከአዲስ አበባ የሱማሊያ መንግስት ልዑካን ቡድን ያልተፈቀደ የጦር መሣሪያ ይዘው ወደ አፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመግባት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።ይህንን ተከትሎ  ከሞቃድሾ መግለጫ ወጥቷል። መግለጫው ከላይ ተያይዟል። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ወደሚካሄድበት ስፍራ “እንዳልገባ ለመከልከል ሞክረዋል”…
#Update

ለሶማሊያ ፕሬዝዳንት ክስ ኢትዮጵያ ምን ምላሽ ሰጠች!

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ በራሳቸው እና በልኡካቸው ላይ ደርሷል ስላሉት መጉላላት ላይ የኢትዮያ መንግስት ምለሽ ሰጠ።

37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፤ የሶማያሊው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃድ ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ የመከልከል ሙከራ እንደተደረገባቸው አስተውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከስብሰባው መክፈቻ በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ በዝግ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በሚሞክሩበት ጊዜ የኢትዮያ የጽታ ኃይሎች ካረፉበት ሆቴል እንዳይወጡ መንገድ ዘግተው እንደከለከሏቸው ገልጸዋል።“በሌላ ፕሬዝዳንት መኪና ከሆቴል በመውጣት የስብሰባው ስፍራ ብደርስም፤ የፀጥታ አካት እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብን ነበር ብለዋል” ፕሬዝዳቱ በመግለጫቸው።

በኋላ ላይ ግን ፕሬዝዳነቱ ወደ ስብሰባው መግታቸው እና በስብሰባው መክፈቻ እንዲሁም የቤተሰብ ፎቶ ላይም ታይተዋል።የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ላይ በሰጠው መግለጫውም፤ “የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ልኡካቸው ወደ 2024 የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንዳይገቡ ያደረገውን ሙከራ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስ በጽኑ ያወግዛል” ብሏል።የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ደንብን የሚጥቀስ ነው ያለው የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የአፍሪካ ኅብረትን የቆየ ባህል የሚቃረን በመሆኑ ህብረቱ ጉዳዩን በገለልተኛ ሆኖ እንደሚረምርም ጠይቋል።

አል ዐይ ኒውስ በጉዳዩ ላይ ከምንግስት ኮሙዩኒኬሽን ባገኘው ምላሽ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታ መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ማድረጉን አስታውቋል።እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታው ደህንነታውን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበትም አስታውቋል።ነገር ግን የሶማሊያ ፕሬዝዳት ልኡካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም ማለታቸውን ነው አል ዐይን ኒውስ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ያገኘው መግለጫ ያመለክታል።

ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደህንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት መከልከላቸውን ገልጿል።በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማያው ፕሬዝዳንት እና የልኡካቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ እንዳላደናቀፈ እንዲሁም ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊዜ እንዳይገቡ እንዳልከለከለ አሳውቋል።ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም ነው የመንስት ኮሙዩኒኬሽን መግለጫ የሚያመላክተው።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለው የፈረንጆቹ ጥር አንድ ቀን በፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ ምክንያት ቁጣቸውን ያሰሙት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ ትናንት አዲስ አበባ መግታቸው ይታወሳል።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ የፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሰጥታ በምላሹ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባህር ጠረፍ በ50 አመት የሊዝ ኪራይ እንድታገኝ የሚያስችል መሆኑ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አካል አድርጋ የምታያት ሶማሊያ በስምምነቱ ከፍተኛ ቁጣ በማሰማት ከአምባሳደሯን ከኢትዮጵያ መጥራቷም አይታወሳል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ከተማ ከሰሞኑን የሽንኩርት ዋጋ  መጠነኛ ቅናሽ አሳየ

👉 ቲማቲም በኪሎ 15 ብር በአንዳንድ ገበያዎች እየተሸጠ ይገኛል

ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን በተለያዪ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ባደረገው የገበያ ቅኝት መሰረት ባለፉት ሳምንታት ሽንኩርት በኪሎ ከ130 እስከ ከ140 ብር ይሸጥባት ከነበረው ዋጋ ቅናሽ በማሳየት ከ80 እስከ 100 ብር እየተሸጠ መሆኑን ያነጋገርናቸው ሸማቾሽ እና ነጋዴዎች ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ቲማቲም ዋጋ ተተምኖለት ይሸጥበት ከነበረው ከ40 እስከ 60 ብር ወደ 20 እና 15 ብር በመቀነስ ሸማቾች ሲገበያዩ በቅኝታችን አረጋግጠናል።

በሌላ በኩልም ድንች በኪሎ 20 ብር እንዲሁም ካሮት ከ30 እሰከ 45 ብር በተለያዩ ገበያዎች እየተሸጠ ይገኛል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የቀንዱ ሀገራት ችግራቸውን በንግግር እንዲፈቱ የአፍሪካ ኅብረት አሳሰበ

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያና ሰሜናዊቷ ሶማሊላንድ በተፈራረሙት የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ፣ በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትና ውጥረቱ በቀጠናው ሰላም፣ ጸጥታና መረጋጋት ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ "በጥልቅ እንዳሳሰበው" አስታውቋል።

ኅብረቱ፣ ኢትዮጵያና ሱማሊያ ውጥረቱን እንዲያረግቡትና ችግሩን በንግግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጠይቋል። ኅብረቱ፣ ለሱማሊያና ኢትዮጵያ ብሎም ለኹሉም አባል አገራት ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት፣ ነጻነትና አንድነት ያለውን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጧል።

ዋዜማ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አብዛኛዎቹ የአብን አባላት ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም በሒደት ላይ መሆናቸው ተነገረ

ከገዥ ፓርቲ ጋር የካቢኔ አባል ሆነው በሚሠሩትና በሌሎችም ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች የተነሳ፣ የፓርቲው ህልውና አደጋ ውስጥ በመግባቱ፣ አብዛኛዎቹ አባላት ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም በሒደት ላይ መሆናቸውን፣ ፓርቲውን ወክለው ለፓርላማ የተመረጡት የፓርላማ አባል ተናገሩ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ አበባው ደሳለው ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፣ ፓርቲው (አብን) ስለታሰሩ አባላቱም ሆነ በአገር ላይ እየተከሰተ ስላለው ሁኔታ ምንም እያለ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፓርቲው አባላት (አመራሮች) የፌዴራልና የክልል የካቢኔ አባል በመሆናቸው፣ ካቢኔ ውስጥ ወስነው በፓርቲ ደረጃ መቃወም ስለሚከብዳቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዚህም ከገዥው ፓርቲ ተነጥለው የማታዩበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አክለዋል፡፡

‹‹የምናደርገው ቸግሮን ነው ያለነው›› የሚሉት የፓርላማ አባሉ፣ በአብን ምርጫ ተወዳድሮ የፓርላማ አባል ከተሆነ በኋላ፣ ሌላ ፓርቲ ማቋቋቋም ስለመቻሉም ሆነ ስለመከልከሉ ሕገ መንግሥቱ የሚለው ባለመኖሩ፣ የሕግ ባለሙያዎችን በማነጋገር ከልካይ ሁኔታ እንደሌለ መረዳታቸውን አስረድተዋል፡፡

Via ሪፖርተር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 21:21:52
Back to Top
HTML Embed Code: