Telegram Web Link
በአማራ ክልል ከሰባት መቶ ሺህ በላይ ህፃናት ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠዋል ተባለ

በአማራ ክልል ከሰባት መቶ ሺህ በላይ ህፃናት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን የክልሉ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው የህፃናት ክፍል ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘየደ ቢሮው በክልሉ በስድስት ወራት ውስጥ በፀጥታ ችግር እና በሌሎች ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለችግር የተዳረጉ ህፃናትን በተመለከተ ግምገማ አድርጓል ብለዋል፡፡ በዚህም ከሰባት መቶ ሺህ በላይ ህፃናት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ህፃናት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለረሃብ የተዳረጉ፤በጎዳና ላይ የሚገኙና በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙም ጭምር ናቸው የተባለ ሲሆን እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከሆነ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ነው፡፡

በክልሉ ለችግር የተዳረጉ ህፃናት ለማገዝ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አኳያ አብዛኛዎቹን መድረስ እንዳልተቻለ አቶ አሻግሬ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተ ድርቅ በርካታ ህፃናት ተጎጂ መሆናቸውን የተለያዩ አካላት ሲገልፁ ይሰማል ፡፡ይህን በተመለከተ ለቢሮው ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ)
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

ዛሬ ከአማራ ክልል ከአውደ ውግያ የተሰሙ ሰበር መረጃዎች እነሆ👇

በዚ ሊንክ በዝርዝር ይመልከቱ👇👇
https://youtu.be/ssrrJNL4tQ4
https://youtu.be/ssrrJNL4tQ4
ተመሳሳይ ፆታን በሚመለከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ተቃውሞውውን በመግለጫ አሳውቋል።ሲኖዶሱ:—
“ይህ ግብረ ርኵሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች፣ ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በአገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ”
"ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሂደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ እንጠይቃለን"
<በስምምነቱ ሰነድ ጤናማ መስለው የሠረፁ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ በጾታና ሥርዓተ ጾታ መብት፣ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት ጋር በማያያዝ ጾታን በቀዶ ጥገና የመቀየር ውርጃ ልቅ የሆነ የተመሳሳይና ተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን መፍቀድ፣ግለሰቦችን እና ማኅበረሰብን መረን በማድረግ ውስብስብ ለሆነ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ችግሮች የሚዳርጉ ናቸው።>
<<ይህን አስመልክቶ የሚደረጉ ስምምነቶች የሀገሪቷን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴት የሚጥሱ መሆኑ ታውቆ ሁሉም ዜጎች እንዲቃወሙት፤ የፈዴራል መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው እየጠየቅን ግብረ ሰዶምን እና ተያያዥ የጾታ ሥርዓትን የሚበርዙ ተግባራት በሙሉ ሀገሪቷ በሃይማኖት፣ በሕግ፤ በማኅበራዊ ዕሴቶቿና በሥነ ምግባር መመሪያዎቿ የማትቀበላቸው ጉዳዮችና ልምምዶች ስለሆኑ በማናቸውም ይፋዊ ግንኙነቶች አንቀበላቸውም>>ብሏል።
(ቀሪው ከላይ ተያይዟል)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የመረጃ ቻናል ጥቆማ‼️#SHEWA_NEWS_NETWORK
ስለ ወቅታዊ የሸዋ አማራ ከቦታው መረጃ የሚሰጣችሁ የመረጃ ቻናል ልጠቁማችሁ የትላንትና እና የዛሬ የአዉደ ዉጊያ ዉሎ እና አንድ ሰበር የጥንቃቄ መረጃ join በማለት ሙሉውን ይከታተሉ👇👇👇
https://www.tg-me.com/+0j24gRc38Gg2OGVk
https://www.tg-me.com/+0j24gRc38Gg2OGVk
የአራት አመት ህጻን ልጅ በጅብ ተነክሶ ህይወቱ አለፈ

👉እናት የልጇን ህይወት ለማዳን ስትል በጅቡ ተነክሳ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ወረዳ ጀንጀቃ ቀበሌ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሸቱ 3 :00 ሰዓት ከጫካ ወደ መኖሪያ የዘለቀዉ ጅብ የአራት አመት ህፃን በጅብ ጭንቅላቱን ተነክሶ ህይወቱ ሲያልፍ ህፃኑን ለማዳን የጣረች እናት በጅቡ ከባድ ጉዳት ደርሶባት ሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ ቲችንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።

በጅብ የተነከሱትን ሰዎች ጩኸት የሰማዉ ግለሰብ ጅቡን ሲከላከል በግራና ቀኝ እጅ ላይ ተነክሶ ቀላል ጉዳት ደርሶበት ሸኮ ወረዳ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተረገለት መሆኑን መረጃዉ አመላክቷል።

ህፃኑን ለሞት እና በሁለት ሰዎችን ላይ ጉዳት ያደረሰው ጅብ መሠወሩን የገለፀዉ ፖሊስ በወረዳዉ ጅብ ለተደጋጋሚ ጊዜ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ እንዲያበጅና ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህወሃት ሊመለስ ነው‼️

የሕወሓት ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ጌታቸው ረዳ ተናገሩ‼️

የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ የተናገሩት ትላንት ሰኞ የካቲት 4፣ 2016 ነው፡፡

ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ለመመለስ ከመንግሥት ጋር ከስምምነት የተደረሰው፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ዐርብ የካቲት 1፣ 2016 ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረገው ግምገማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሕጋዊ ሰውነቱ ይመለሳል የተባለው ሕወሓት፤ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ጦርነት በገጠመበት ወቅት በአመጻ ተግባር ተሳትፏል በሚል ሕጋዊ ሰውነቱ የተሰረዘው ጥር 10፣ 2013 ነበር፡፡

ሆኖም ሕወሓት ከመንግሥት ጋር የገጠመው ጦርነት ጥቅምት 2015 በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መቋጨቱን ተከትሎ ሚያዝያ 28፣ 2015 ለምርጫ ቦርድ የሕጋዊ ሰውነቴ ይመለሰልኝ ጥያቄ ቢያቀርብም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ነበር፡፡ ምርጫ ቦርድ በወቅቱ የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ለማስመለስ ጉዳዩን በሕግ የተደገፈ ሆኖ አላገኘሁትም ብሏል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል መራዊ ከተማ ቢያንስ 45 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች  “ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን “ከህግ ውጭ መግደላቸውን” ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለጊዜው ብዛታቸውን ማረጋገጥ ያልቻላቸው ሰዎች “የፋኖ አባላት ናቸው” በሚል ተጠርጥረው ከተያዙ በኋላ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተመሳሳይ ሁኔታ መገደላቸውንም ገልጿል።

ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው “የትጥቅ ግጭት” በሲቪል ሰዎች ላይ “ከህግ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎችን” (extrajudicial killings) በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

ኮሚሽኑ “የትጥቅ ግጭቱ” በሰብአዊ መብቶች እና በማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ እያስከተለ ያለውን ጉዳት እና አሉታዊ ተጽዕኖ፥ የመንግስት አካላትን እና የተለያዩ ወገኖችን በማነጋገር እየተከታተለ እንደሚገኝ በመግለጫው ጠቅሷል።

በዚህ መሰረት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በተለምዶ “ፋኖ” ተብለው በሚጠሩት “የታጠቁ ኃይሎች” መካከል፥ በመራዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ኮሚሽኑ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን አመላክቷል።

ኢሰመኮ የምርመራ ሥራውን በተለያዩ ምክንያቶች ማጠናቀቅ ባይችልም እስካሁን ድረስ ባደረገው ክትትል የደረሰበትን ግኝት በዛሬው መግለጫው ይፋ አድርጓል።

በመራዊ ከተማ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በ”ፋኖ ታጣቂዎች” መካከል ውጊያ የተካሄደው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንደነበርም ኮሚሽኑ አስታውሷል።

ኮሚሽኑ ከምስክሮች ባሰባሰበው መረጃ በውጊያው ዕለት ለቀን ሥራ በጠዋት ከቤታቸው ወጥተው ድንገት ተኩስ ሲከፈት “በአንድ ቦታ ተጠልለው የነበሩ 18 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን” መረዳቱን ነው የገለጸው።

በከተማዋ ቀበሌ 02 አካባቢ በተለምዶ ሚሊኒየም ተብሎ በሚጠራ ሰፈር ስምንት ሲቪል ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ የጤና ተቋማት ከ13 ሚሊዮን በላይ ኮንዶም መሰራጨቱ ተነገረ

👉በዛሬዉ እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮንዶም ቀን እየታሰበ ይገኛል


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተደረጉ ስራዎችን በሚመለከት ባለፉት 6 ወራት ያከናወነውን ተግባር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።ቢሮው በተያዘው በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ እንዲያገኙና  ተመርምረው ራሳቸውን እንዲያውቁ መደረጉን ገልጿል።

የቢሮው የኤች አይ ቪ ዘርፈ - ብዙ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በኤች አይ ቪ ኤድስ አዲስ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ቀንሷል።ነገር ግን  በቫይረሱ የተያዙ በርካታ ዜጎች በመኖራቸው  በጤና ተቋማት   ባለፉት 6 ወራት 13 ሚሊዮን አንድ መቶ 99 ሺህ የኮንዶም ስርጭት መከናወኑ በግምገማው ተነግሯል ብለዋል።

በዚህም ተጋላጭ ለሚባሉና አጠቃላይ የማህበረሰብ ክፍሎች በበጎ አድራጊ ድርጅቶች አማካኝነት እንዲሰራጭ ተደርጓልም።ኮንዶም በግዢ በሚከናወንበት ወቅት ዋጋው ውድ በመሆኑ ማንኛውም ዜጋ በቀላሉ እና በነጻ በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስት  የጤና ተቋማት በመሄድ አገልግሎቱን እንዲጠቀምና እራሱን ከኤች አይቪ ቫይረስ እንዲጠብቅ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ሲስተር ፈለቀች ጨምረው ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

ከኮንዶም ስርጭት ባለፈ የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት እ.ኤ.አ በ2030 ኤድስን ለመግታት በሚደረገው ሂደት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የጣይቱ ትምህርት እና ባህል ማእከል  ወደ አገልግሎቱ ሊመለስ ነው‼️


የጣይቱ ትምህርት እና ባህል ማእከል ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተረክቦት የነበረዉን  120 አመት ያስቆጠረን የቅርስ ቤት የእድሳት ስራ 95% ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ዉስጥ የሚገኘዉ የቢትወደድ ሀይለጊርጊስ ወ/ሚካኤል መኖሪያ ቤት የነበረዉ እና የመጀመሪያ ማዘጋጃ ቤት በመሆን ያገለገለው  ጥንታዊ ቤት እድሳት 95 በመቶ የሚሆነዉን ስራ ማጠናቀቁን ማእከሉ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልፆል።

ከፍተኛ የቅርፅ ባለሙያዎች ጥናት  እና ከቦታዉ ጋር የሚመጥን የማስፋፊያ ዲዛይን  ተደርጎበታል የተባለው ባህል ማእከልን   ለማጠናቀቅ ሁለት አመት እንደፈጀ ለማወቅ ተችሏል።

ምንም አይነት እድሳት ሳይደረግለት በመቆየቱ  የእድሳት   ሂደቱን አስቸጋሪ  አድርጎታል  የተባለ   ሲሆን የቅርስ ይዘቱን ሳይለቅ ለማደስ ሲባል የጥሬ እቃዎችን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር ግንባታዉን የመሩት አቶ ተስፋዬ አዶላ ለኢትዩ  ኤፍኤም    ገልፀዋል።

በአርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ሀሳብ አመንጪነት ቦታዉን ወደ ባህል ማእከልነት ለመቀየር በማሰብ  በ 2011 ዓ.ም ከ/ከተማ መስተዳድር  ቦታዉን መረከቡ የሚታወስ ነዉ፡፡

ቀሪ ለማእከሉ የሚያስፈልጉ የመብራት ገጠማ እና ሌሎች ስራዎችን በመጨረስ በቅርብ ጊዜ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ እና ለከተማውም አማራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንደሚሆን ተጠብቋል።
‹‹የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይፈጸም ሠራዊታችን ትጥቅ ፈትቶ እንደማይበተን ለመንግሥት አሳውቀናል›› - አቶ ጌታቸው ረዳ

የፕሪቶሪያው ስምምነት ተሟልቶ ሳይፈጸም ‹‹የትግራይ ሠራዊት›› ትጥቅ ፈትቶ እንደማይበተን ለፌዴራል መንግሥት ማሳወቃቸውን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። 

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በአዲስ አበባ ተገናኝተው የገመገሙ ሲሆን፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በግምገማው ወቅት ከሁለቱም አካላት የተነሱ ጉዳዮችን አብራርተዋል።

‹‹የፕሪቶሪያው ስምምነት አልተፈጸመም፣ ሕወሓት ሕጋዊ ሰውነቱን መልሶ አላገኘም፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው አልተመለሱም፣ የአማራና የኤርትራይ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ አልተደረገም፤›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህንንም ለፌዴራል መንግሥት በዝርዝር ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ በሕወሓትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ ካነሳቸው ቅሬታዎች መካከል፣ ‹የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለጊዜ መግዣ እየተጠቀማችሁበት ነው፣ ትጥቃችሁን ለመፍታት ፍላጎት የላችሁም፣ ሠራዊታችሁን ማጠናከር ነው የምትፈልጉት፣ ከኤርትራና ከሌሎች የውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር መንግሥትን ለመጣል እየሠራችሁ ነው› የሚሉት እንደሚገኙበት፣ አቶ ጌታቸው በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

‹‹የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሳይሆን ይህንን ሠራዊት ተበተን የምንልበት ምክንያት የለም። ይህ ሠራዊት መስዋዕትነት የከፈለ፣ ለትግራይ ህልውና የቆመ ሠራዊት ነው፤›› ብለዋል።

Via ሪፖርተር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ ተፈጸመ የተባለውን የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ትናንት ማምሻውን በቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤቱ በኩል አስተባብሏል።

የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ፣ በመራዊ ከተማ ጥር 20 በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ መካከል ግጭት መካሄዱን አረጋግጠው፣ የመንግሥት ወታደሮች ግን በሲቪሎች ላይ ጥቃት አልፈጸሙም በማለት ለዶይቸቨለ ተናግረዋል።

ለገሠ፣ ኾኖም ጉዳዩ በክልሉ የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሰብዓዊ መብት ኹኔታ የሚከታተለው መርማሪ ቦርድ ሃላፊነት እንደኾነ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመራዊ ከተማ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች 45 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል ማለቱ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወገልጤና ከተማ አቅራቢያ ኦፓል ማዕድን ሲቆፍሩ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በአፈር መደርመስ ሳቢያ የተቀበሩ በ20 በላይ ማዕድን አውጪዎችን እስከ ትናንት ድረስ ከጉድጓዱ ማውጣት እንዳልተቻለ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ የነፍስ አድን ሥራው እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ሌላ የአፈር መደርመስ መከሰቱንና ጥረቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን እንደገለጡ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

የማዕድን ቆፋሪዎቹን ነፍስ ለማዳን የዘመናዊ ማሽን እገዛ እንዲያደርግለት የአካባቢው አስተዳደር ጠይቋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከ 20 በላይ የሆኑ የማዕድን አዉጪዎች ከተዋጡበት ፍርስራሽ ለማዳን ሲደረግ የነበረዉ የነፍስአድን ጥረት ከአቅሜ በላይ ሆኗል ሲል የደላንታ ወረዳ አስታወቀ

ባሳለፍነዉ ሀሙስ ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ገደማ ላይ በደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆቅ ዉሃ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በባህላዊ መንገድ የኦፓል ማዕድንን በማዉጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች ባጋጠማቸዉ የመሬት መደርመስ አደጋ በፍርስራሽ ዉስጥ እንደሚገኙ የደላንታ ወረዳ ማዕድን ልማት ጽ/ት ቤት ሀላፊ አ/ቶ ተስፋ ሰማሁን ዋቢ በማድረግ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ወጣቶቹ ላለፉት ሰባት ቀናት በፍርስራሽ ዉስጥ ተዉጠዉ የቆዩ ሲሆን የነፍስ አድን ቁፋሮዉ በማህበረሰቡ ትብብር ሲከናወን ቆይቶ ነበር። ሆኖም አሁንም በቁፋሮዉ ወቅት የመሬት መደርመስ እና መንሸራተት እያጋጠመ ስራዉን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር ብስራት በትናንትናው እለት ዘግቦ ነበር።

ይሁንና የደላንታ ወረዳ ማዕድን ልማት ጽ/ት ቤት ሀላፊ አ/ቶ ተስፋ ሰማሁ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት አሁን ላይ በሰዉ ሀይል ሲከናወን የነበረው ቁፋሮ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ነዉ።

"በነፍስ አድን ስራዉ ወቅት ተጨማሪ የሰዉ ህይወት እንዳናጣ በሚል ስራዉን አቋርጠናል" ሲሉ ገልጸዋል። ወረዳዉም ሆነ የደቡብ ወሎ ዞን ጉዳዩን ለክልሉ እና የፌዴራል መንግስት ማሳወቃቸዉንም ነግረዉናል።

አቶ ተስፋ " ቁፋሮዉ ከሰዉ አቅም በላይ በመሆኑ ከህብረተሰቡ በድማሚት እና ከባድ መሳሪያ ፈንጂዎች ቢመታ የሚል ጥያቄ እያቀረበ ነዉ" ያሉን ሲሆን ይህንንም ለማከናወን ቦታዉ በጂኦሎጂስት ባለሙያ መታየት ያለበት በመሆኑ የክልሉ መንግስት ባለሙያዉን ለመላክ መስማማቱን አስታዉቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጉዳዩ ከአቅም በላይ መሆኑን ሪፖርት በማድረግ ለማዕድን ሚኒስቴር ያሳወቁ ሲሆን ተጨማሪ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸውንም ጠቅሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በመራዊ ከተማ “የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም” ዶክተር ለገሰ ቱሉ

የኢትዮጵያ መንግሥት በመራዊ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን የ45 ሰላማዊ ሰዎች ግድያ አስተባበለ። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ “የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥር 20 ቀን 2016 በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተደረገ በኋላ “በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት” ምርመራ እያካሔደ መሆኑን ትላንት ማክሰኞ አስታውቋል።

መንግሥታዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመራዊ ከተማ “ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ‘ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል’ በሚል ምክንያት ከሕግ ውጭ መግደላቸውን” እንዳረጋገጠ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን  የካቲት 5 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ “‘የፋኖ አባላት ናቸው’ በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል” ብሏል። 

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።

ታጣቂዎቹ “በተለያዩ አቅጣጫዎች መከላከያ ሠራዊቱ የሰፈረበትን ካምፕ በአራት አቅጣጫ በማፈን መሣሪያ እና ሎጂስቲኩን ለመዝረፍ በመንቀሳቀሳቸው ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ ነው እርምጃ የወሰደው” ሲሉ ተናግረዋል።  

መከላከያ ሠራዊት ”ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ እርምጃ ሲወስድ እነዚህ ኃይሎች ተመልሰው ወደ ግለሰቦች ቤት ነው የገቡት” ያሉት ዶክተር ለገሰ “ወደ ግለሰቦች ቤት በሚገቡበት ጊዜ በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አሰሳ ሲያደርግ መልሰው ተኩስ ከፈቱበት” ሲሉ አብራርተዋል።

መከላከያ ሠራዊት “ራሱን ነው የተከላከለው” ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ “የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም” ሲሉ አስተባብለዋል። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች በጉዳዩ ላይ መግለጫ ያወጡ የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰዎች መካከል ከቤት እየተወሰዱ የተገደሉ መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ይህንን በተመለከተ የተጠየቁት ሚኒስትሩ "እንደዚያ አይነት እርምጃ ስለመወሰዱ ተረጋግጦ የመጣ መረጃ የለም" ብለዋል። አክለውም "ሲቪል ይቅርና ታጣቂ እንኳን ለማጥቃት ሄዶ እጅ እስከሰጠ ድረስ የሚገደልበት ሥርዓት የለም። ሊሆንም አይችልም" ብለዋል። "እንዲህ ሆኖ ከሆነም ራሱ መከላከያ ተቋሙ እርምጃ ይወስዳል" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

Via ዶይቼ ቬለ
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 23:20:14
Back to Top
HTML Embed Code: