Telegram Web Link
ኢራን በእስራኤል ላይ ከ 240 በላይ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷ ተዘገበ

ምሽቱን ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሚሳኤል ድብደባን ፈጽማለች። ኢራን ከ 240 እስከ 250 የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ተኩሳለች የተባለ ሲሆን ብዙዎቹ ቢከሽፉም በእስራኤል ምድር ላይ የወደቁ ሚሳኤሎች መኖራቸዉን ግን ዳጉ ጆርናል ከስፍራው የቀጥታ ስርጭት ዘገባ ከሚሰሩ የዜና አዉታሮች ታዝቧል።

አሁ ላይም ኢራን ሌላ ዙር ጥቃት በእስራኤል ላይ ካልፈጸመች የአየር ጥቃቱ ቆሟል የተባለ ሲሆን በጥቃቱ የደረሰዉ ጉዳት ግን እስካሁን አልታወቀም። ኢራን ጥቃቱን በእስራል ላይ ያደረገችዉ በሁለት አቅጣጫዎች ነዉ ተብሏል።

ቴልአቪቭ ፤ ለቴርሃን ጥቃት ምን አይነት ምላሽ ትሰጣለች የሚለዉ አሳሳቢዉ ጉዳይ ሲሆን ጦርነቱን ሀያላኑ ሀገራት እንዳይቀላቀሉት አስግቷል። የእስራኤል መከላከያ ሀይል በበኩሉ ከ 180 በላይ ሚሳኤሎች መተኮሳቸዉን እንዳረጋገጠ ኤቢሲ ኒዉስ ዘግቧል።

እስራኤል የኢራን የአየር ጥቃት መቆሙን ተከትሎ ዜጎች ከሚሳኤል መሸሸጊያዎች እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፋለችም ተብሏል። እስራኤል ሶስት የአየር ጥቃት መከላከያ ያላት ሲሆን ሶስቱን የጸረ ሚሳኤል መከላከያን የጣሱ የኢራን ሚሳኤሎች ግን በእስራል ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት እንደሚያደርሱ ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

@sheger_press
@sheger_press
በእስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ በተከፈተ የጅምላ ተኩስ ስድስት ሰዎች ተገደሉ

ኢራን በእስራኤል ላይ ከፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በተለየ ሁኔታ፣ በቴል አቪቭ የጅምላ ተኩስ ተከስቷል።

ዛሬ ማምሻውን ታጣቂዎች በከተማው ጎዳና ላይ በሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል ሲል ፖሊስ የገለፀ ሲሆን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ቢይንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ዘግበዋል። ቢያንስ ሰባት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን አንዳዳዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለጠፉት ምስሎች እንዳሳዩት ታጣቂው በጃፋ አካባቢ በሚገኝ የባቡር ጣቢያ ላይ መሬት ላይ ተኝተው በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ሲተኩስ ታይቷል። ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት “ሽብር” ሲል ገልጾታል።
መስማት የተሳናትን የ ስምንት አመት ልጅ እና የአእምሮ ውስንነት ያለባትን የ አስራ ስድስት አመት ልጅ ላይ የአገድዶ መድፈር ጥቃት የፈፀሙ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዋ ወረዳ ውስጥ መስማት የተሳናትን የስምንት አመት ልጅ እና በጎሮ ወረዳ የአስራ ስድስት አመቷን የአእምሮ ውስንነት ያለባትን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ ላይ የእስራት ቅጣት መተላለፉን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

እንደ ደቡቡ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ገለፃ ተከሳሽ ፈይሳ ከበደ የተባለው ግለሰብ ሰኔ 1ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ላይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዋ ወረዳ ቡሳ 01 ቀበሌ የስምንት አመቷን መስማት የተሳናትን ልጅ አባብሎ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ተገልጿል። ተከሳሹ መስማት የተሳናት የስምንት አመት ልጅ ላይ የመድፈር ጥቃት ከፈፀመ በኋላ የስምንት አመቷ መስማት የተሳናት ልጅ የተፈፀመባት ድርጊት መቋቋም አቅቷት ስትጮህ የአካባቢው ሰዎች ደርሰው ድርጊቱን ለማስጣል ሲሞክሩ የመድፈር ጥቃት ፈፃሚው ሮጦ ለማምለጥ ቢሞክርም በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ፖሊስም በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለውን ተከሳሽ ላይ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ተጎጂዋን የስምንት አመት ልጅ ወደ ጤና ጣቢያ በመላክ በማስመርመር የህክምና እርዳታ እንድታገኝ አድርጓል። በህክምና ማስረጃ መሰረት በታዳጊዋ ላይ የመደፈር ጥቃት ሙከራ መከናወኑን የሚገልፅ በመሆኑ እና በአይን እማኝ ምስክርነት የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለአቃቤ ህግ መላኩን ገልፀዋል።አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ 627 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ለአቅመ ሄዋን ባልደረሱ እንስቶች ላይ የሚፈፀም የመድፈር ጥቃትን በመጥቀስ ክስ መስርቷል። በአቃቤ ህግ የተመሰረተውን ክስ ሲመለከት የነበረው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን በ6 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ  ሸዋ ዞን ጋልዮ ሞጆ ቀበሌ ውስጥ በአስራ ስድስት አመቷ የአይምሮ ውስንነት ባለባት ልጅ ላይ የመድፈር ጥቃት በመፈፀም ክብረ ንፅህናዋን የወሰደው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልፆል።ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ላይ ተከሳሽ ጌታቸው ታደሰ የተባለው ግለሰብ የ አስራ ስድስት ዓመቷን የአይምሮ ውስንነት ያለባትን ልጅ በጉልበት እጇን በመጠምዘዝ ወደ ሰዋራ ስፍራ ወስዶ የመድፈር ጥቃት እንንዳደረሰባት በማስረጃ መረጋገጡን ገልፆል። ተጎጂዋ የደረሰባትን ጥቃት መቋቋም አቅቷት ስትጮህ የሰሙ የአካባቢው ሰዎች ደርሰው ተከሳሹን ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለፖሊስ ማስረከባቸውን ተገልጿል። ፖሊስም የድርጊቱ ፈፃሚ በመያዝ ጥቃት የደረሰባት ታዳጊ የአይምሮ ውስንነት ያለባት ልጅ የክብረ ንፅህናዋ እንደተወሰደ በማረጋገጥ ማስረጃውን ለአቃቤ ህግ መላኩን የፖሊስ መምሪያው ገልፆል። 

አቃቤ ህግ ከፖሊስ የተላከለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ 620 ንሁስ አንቀፅ 2 ቸአይምሮ ውስንነት ባለባቸው ሰዎች ላይ በሚፈፀም የመድፈር ጥቃት መሠረት በማድረግ ክስ ይመሰርታል። በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ተከሳሽ ጌታቸው ታደሰ በአቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ ዘጠኝ አመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ገልፆል።
በእነ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የተሰጠው እግድ እንዲጸና ትዕዛዝ ተሰጠ

👉የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በመስከረም 08 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ሊነሳ #አይገባም በማለት የእነ ዶር #አሸብር ወልደ ጊዮርጊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እግዱ እንዲፀና ትእዛዝ ሰጠ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙሉ ትዕዛዝ ከላይ ተያይዟል።

@sheger_press
@sheger_press
ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ

ኢራን በእስራኤል ላይ የባልስቲክ ሚሳኤሎችን ከተተኮሰች በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል ፣ይህም በመካከለኛው ምስራቅ የነዳጅ አቅርቦትን ሊያስተጓጉል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል ።

ብሬንት ክሩድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለነዳጅ ዘይት ዋጋ ቁልፍ መለኪያ ሲሆን አንድ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል ከ1 በመቶ በላይ ጨምሮ ወደ 74.40 ዶላር ከፍ ብሏል። ማክሰኞ በግብይት ወቅት ከ 5 በመቶ በላይ ጨምሯል። እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ኢነርጂ አስተዳደር መረጃ ኢራን ከአለም ሰባተኛዋ የነዳጅ አምራች ሀገር ስትሆን በኦፔክ የነዳጅ ዘይት አምራቾች ውስጥ ደግሞ ሶስተኛዋ ትልቋ አባል ነች።

ነጋዴዎችም በክልሉ ውስጥ የሚፈጠር ማንኛውም ወታደራዊ ሃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ የባህር ዳርቻ የመርከብ ጉዞ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። በኦማን እና በኢራን መካከል ያለው የመርከብ ማጓጓዣ መንገድ  20 በመቶ የሚሆነው የዓለም አቅርቦቶች የሚጓጓዙበት አለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ ቁልፍ መስመር ነው።

ሌሎች የኦፔክ አባላት ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኩዌት እና ኢራቅ ወደ ውጭ የሚላኩትን ዘይት በብዛት በባህር ሰርጡ በኩል ይልካሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ምናለ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ” እላለሁ

“ከሰው አልጨመርም። አብዝቼ እተክዛለሁ። ፊደል ያልቆጠረ ብዙ የማውቀው ሰው ቤት ንብረት አለው። የተሻለ ሕይወት ይመራል። እኔ ለምን ተማርኩ እላለሁ - አንዳንዴ። እንደሱ አይባልም - አውቃለሁ። ግን ምን ላድርግ? ወደ አእምሮዬ የሚመጣውን ነው የምነግርህ።

ውስጤ ጠንካራ ሆኖ ነው ከራሴ ያለሁት እንጂ ጭንቅላቴ እኮ ልክ አይደለም።

እንደ ባይተዋር ነው የምኖረው።

አንዳንዴ ለብቻዬ እያወራሁ ራሴን አገኘዋለሁ።

ጓደኛ የለኝ፣ ምን የለኝ። ሰው ሆነህ ከሰው ጋ መጨመር ካልቻልክ ማበድ ማለት አይደለም?

ከወር-ወር ኪሴ ባዶ ነው።ከቤት የማልወጣውም ለዚያ ነው። ታክሲ ውስጥ ሰው ባገኝስ ብዬ እሳቀቃለሁ። ከዚህ ሁሉ ለምን ቤት አልቀመጥም ብዬ ነው ያለሁ።

በቀደም ትዝ ሲለኝ ለባለቤቴ የተጋባን ቀን ከገዛሁላት ስጦታ ውጭ ገዝቼላት አላውቅም።

ባትነግረኝም ሞራሏ መጎዳቱ አይቀርም። ለልጄም እንደዚያው። ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር አለ?

እኔ መምህር በመሆኔ እና እነሱ የመምህር ቤተሰብ በመሆናቸወ ተጎድተዋል። ምንም ጥያቄ የለውም። አንዳንዴ ‘ምናለ ድሮ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ’ የምለውም ለዚያ ነው።

ዘገባው የBBC አማርኛ ነው

@sheger_press
@sheger_press
ሰበር : መንገድ ተዘጋ ከባዱ ውጊያ ተጀምሯል | ዘመነ ካሴ ከባዱን ትእዛዝ ሰጠ | የብልፅግና ሰራዊት ተደመ-ሰሰ የመጨረሻው ጦርነት ተጀመረ ሙሉ ዜናውን አሁኑኑ ከስር ባለው ሊንክ አድምጡ! 👇👇👇
https://youtu.be/bdq-QobRnvU?si=unkgwFq8dtjw_mkE
ኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች ማህበራት ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን (FIATA) የ2027 ዓለም አቀፍ ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች

ሀገሪቱ ይህን አለም አቀፍ ጉባኤ ለማካሄድ መመረጧ በአፍሪካ አህጉር በሎጂስቲክስ ዘርፍ እየጎለበተ የመጣውን ሚናዋን በጉልህ የሚያመላክት ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊና የመርከብ አገልግሎት ወኪሎች ማህበር ይህን ጉባኤ በሀገሪቱ እንዲያሰናዳ መታጨቱ ለኢትዮጵያ ብሎም ለመላ አህጉሪቱ ጠቀሜታው የግላ መሆኑም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ከ800 በላይ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች፣ የዘርፉ ታላላቅ አመራሮችና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉበት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮቴሌኮም በሲም ካርድ ዋጋ ላይ  ጭማሪ አደረገ‼️

ኢትዮቴሌኮም ከዚህ ቀደም የጠፋ ሲም ካርድን ለማዉጣት 15 ብር የሚጠይቅ ቢሆንም አሁን ግን  በአዲሱ ማሻሻያ 85 ብር እንዲሆን አድርጓል።

በተመሳሳይ አዲስ ሲም ካርድ ለማዉጣት ይጠየቅ የነበረዉ 30 ብር አሁን ግን 85 ብር መሆኑ ተሰምቷል።

ተቋሙ ከሚሰጣቸው አገልግሎት ዝቅተኛ ዋጋ የሚጠይቁት ማለትም በ 3 እና በ 5 ብር የሚገዙ ፓኬጆች ላይ ምንም አይነት ዋጋ ጭማሪ አለመደረጉ ተገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press
"ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።" ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ ሰጡ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የሙስናና ብልሹ አሰራር በዝርዝር በማጥናት የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የሠራቸውን ሥራዎች ሪፓርት በማቅረብ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ በመወያየት የሥራ መመሪያ ተቀብሏል።

ኮሚቴው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከውስጥ አልፎ በአደባባይ መነጋገርያ በመሆኑ በጥናት ላይ በተመሠረተ አግባብ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችልና የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲደራጅ የሚያደርግ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶር) እና ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርኩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት አባታዊ የሥራ መመሪያ "ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም” ያሉ ሲሆን ስለሆነም ሕግና ሥርዓትን አክብራችሁ፣ በእውነተኝነት ለቤተክርስቲያን፣ለእግዚአብሔርና ለራሳችሁ ብላችሁ ሳታፍሩና ሳትፈሩ ሥራችሁን ሥሩ። ሥራው ታማኝነት"ጥብዓት" ያስፈልጋል ብለዋል።

ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ሆናችሁ በጋራ ሥሩ ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ጠንከር ያለ መድኅኒት ሊሆን የሚችል ጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደምታቀርቡ እምነቴ የጸና ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም የተላካችሁበት ሥራ ያለ ውጤት የሚቀር መሆን የለበትም።

ቤተክርስቲያን የተዋረደችበት ጊዜ ማብቃት አለበት ያሉት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያናችን ራሷን አንጽታ ለሌሎች መልካም አብነት መሆን አለባት ካሉ በኋላ ዓለማዊያን የሚሰሩት ሥህተት እንዳይኖር በተግባር የምታስተምር ተቋም እንጂ በሙስና የምትታማ መሆን የለበትም ብለዋል ሲል የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል፡፡

ልጆቼ እውነቱን ለማውጣት ታጥቃችሁ ሥሩ በሙስና ህመም ለምትሰቃየው ቤተክርስቲያን መድኃኒት ፈልጉላት በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንመረመርም ማለት ራሱን ችሎ ወንጀል ነው ካሉ በኋላ ይህ ሥራ ለእናንተም ታሪክ ነው።

እውነትን መሰረት አድርጋችሁ በመሥራት ታሪክ አስመዝግቡ ብለዋል። በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይም ወደ እዚህ ተቋም የሚገቡ ሁሉ ይህን ያህል ጊዜ ቆይተን ይህን ያህል ይዘን እንውጣ የሚሉ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩና የሚያስቡ እንዳልሆኑ ይታወቃል ካሉ በኋላ የተሰጣችሁን ኋላፊነት በትጋት ፈጽሙ ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press
አሳዛኝ ዜና‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ 015 ቀበሌ ደቦት ልዩ ቦታው እቧዮች ኪዳነምህረት መስከረም 22/2017 ዓ/ም ምሽት ላይ ከባህር ዳር ወደ ወልድያ መስመር ወደ መቅደላ ዩኒቨርስቲ የሚሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጭኖ  ሲጓዝ የነበረ አባዱላ መኪና ተገልብጦ ከጫነው 21 ሰው 7 የሞተ ሲሆን 14 ተማሪዎች ቆስለው ወደ ጤና ጣቢያና ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ!

ከኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
 
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 25/ 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል ፤ ይህን ተከትሎ የሚከተሉት መንገዶች ይዘጋሉ።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፤

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፤

- ከአጎና  ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ  አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፤

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፤

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም  ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፤

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፤

- ከሃራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ፤

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ  ቤተ መንግስት አጠገብ፤

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ ሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፤

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ፤


ከመስከረም 24/ 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያና በአካባቢ በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

    #AddisAbabaPolice

@sheger_press
@sheger_press
እስራኤል በሊባኖስ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ፈፀመች

እስራኤል ዛሬ ጠዋት በሊባኖስ ላይ አዲስ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተገለፀ፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የዳሂየህ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ከፍተኛ ፍንዳታ መከሰቱ ተነግሯል።

የሂዝቦላህ ጠንካራ ምሽግ እንደሆነ የሚነገርለት የዳሂየህ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ከአየር ጥቃቱ በኋላ ዛሬ ጠዋት በእሳት ተያይዞ ነበር ተብሏል፡፡

ጥቃቱ በቅርቡ በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደሉትን የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ ይተካሉ የተባሉትን የአጎታቸውን ልጅ ሀሽም ሳፊዲንን ኢላማ ያደረገ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

የሊባኖስ የህዝብ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ ባለፉት 24 ሰአት ውስጥ በተፈፀመው የምድር እና የአየር ጥቃት 37 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 151 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

እንደሊባኖስ ባለስልጣናት መረጃ ደግሞ እስራኤል ላለፉት ሁለት ሳምንታት ባካሄደችው ዘመቻ ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ1 ሚሊዮን በላይ ደግሞ አካባቢያቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡

እስራኤል ባለፉት ሶስት ቀናት በደቡባዊ ሊባኖስ እያካሄደች ባለችው ዘመቻ ከተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች ዘጠኝ ወታደሮች እንደሞቱባት የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጆ ባይደን እስራኤል የኢራንን የነዳጅ ማውጫዎች ልትመታ እንደምትችል ፍንጭ ሰጡ

ፕሬዘዳንቱ ጥቃቱ መቼ እና እንዴት እነደሚፈጸም ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት በዚህ ወቅት የፕሬዘዳንቱ አስተያዬት የዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመርን አስከትሏል፡፡ ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን መጠነ ሰፊ የሚሳኤል ጥቃት ተከትሎ ብሬንት የተሰኘው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል የ10 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ጆ ባይደን በኢራን የነዳጅ ማውጫዎች ላይ ጥቃት ማድረስን በተመለከተ ውይይት አድርገናል ካሉ ጀምሮ ብቻ የዓለም የነዳጅ ዋጋ 5 በመቶ ጭማሪ ማሳዬቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የአሜሪካ እና የእስራኤል ባለስልጣናት ማክሰኞ ዕለት ኢራን ላስወነጨፈቻቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች ተገቢ ምላሽ እንደሚሰጡ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ የሚሳኤል ጥቃቱ በእስራኤል ለተገደሉት የሀማስ የሄዝቦላህ እና የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ ምላሽ ነው ስትል ተናግራለች።

@sheger_press
@sheger_press
በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኞ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

ዛሬ ከ6 ሠዓት ጀምሮ እስከ የፊታችን ሰኞ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከልሉን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ክልከላው የተላለፈው ለኢሬቻ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደኅንነትን ለማስጠበቅ መሆኑን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም የትራፊክ ፖሊሶችም አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአፋር ክልል አዋሽ 40 ወረዳ ቀበና .ሳቡሪ ወረዳዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል እና ህዝዙ ቀዬውን ለቆ እየተፈናቀሉ ይገኛል እባካችሁ ለሚመለከተው አካል አድርሱልን:: ( ሸገር ፕረስ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቤይሩት እና ወደ ቴልአቪቭ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን አስታወቀ!

በከተሞቹ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቤይሩት እና ወደ ቴልአቪቭ የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ፥ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስከሚያወጣ ድረስ ወደ ቤይሩት የሚያደርጋቸውን ሁሉንም በረራዎች ማቋረጡን ገልጿል።

ወደ ቴልአቪቭ ደግሞ እስከ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በረራ የማያደርግ መሆኑን ነው አየር መንገዱ የገለጸው።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የጠቀሰው አየር መንገዱ፤ ስለጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ እየተለዋወጠ ስለመሆኑም ጠቁሟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/05 01:31:25
Back to Top
HTML Embed Code: