Telegram Web Link
በስልጤ ዞን የአዕምሮ እድገት ውስንነት ባለባት ህፃን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

በስልጤ  ዞን የዳሎቻ ወረዳ ዐቃቤ ህግ እንዳስታወቀው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወንጀል ህግ አንቀፅ 27/1/ እና 620/2/ሐ/ ላይ የተደነገገውን በመጥቀስ ተከሳሽ ጀማል ሰይድ የድርጊቱን ምንነት ለይታ በማታውቅ እና መከላከል በማትችል ህፃን አምሪያ ጀማል ላይ ድርጊቱም ለመፈፀም ሞክሯል።

ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በዕለተ ሀሙስ ከቀኑ 10:00 በእንቃት አጋም ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆሮ ቆሻሜ ተብሎ በሚታወቀው መንደር የግል ተበዳይ ከተቀመጠችበት በኃይል  የወንጀል ድርጊቱን ሊፈፅም ሲል የግል ተበዳይ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል መፈፀሙን ክሱ አመላክቷል።

የወንጀል ክስ የቀረበለት የዳሎቻ ወረዳ ፍርድ ቤቱም ክሱን ሲያከራክር ቆይቶ  በዋለው የወንጀል ችሎቱ ተካሳሽን ያርማል ሌሎችም መሰል ድርጊት እንዳይፈፅሙ ያስተምራል በማለት ተከሳሽን በ5 ዓመት ከ6 ወራት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ማሳለፉን የዳሎቻ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።

#ዳጉ_ጆርናል
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ስርዓት ወደ ፕሬዝዳንታዊ ስርዓት ሊቀየር ነው - ኤልያስ መሰረት

በኢትዮጵያ የስራ አስፈፃሚውን በጠ/ሚር ከሚመራ (parliamentarian) ወደ ፕሬዝደንታዊ (presidential) ስርዐት የመለወጥ ሂደት መጀመሩ ተሰምቷል።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡ ሰሞን በስፋት ይነሳ የነበረው ይህ የፕሬዝደንታዊ ስርዐትን የመዘርጋት ሂደት አሁን ከታሰበው የህገ መንግስት ማሻሻያ ጋር አያይዞ በስፋት ስለተሄደበት በቅርብ ግዜያት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

በፓርላመንታዊ ስርዐት ዜጎች የመረጧቸው የህዝብ ተወካዮች ጠ/ሚሩን ሲመርጡ በፕሬዘደንታዊ ስርዐት ደግሞ ዜጎች በቀጥታ ፕሬዝደንት የሚሆነውን ይመርጣሉ።


- የፕሬዝዳንታዊ እና ፓርላመንተሪ ስርዓት ልዩነት በፎቶ አያይዘናል።

Via:- EliasMeseret

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የቤተሰብ አባላቱ ለጉብኝት ከውጭ ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ።

ትንሽ እንዝናና ብለው ከአዲስ አበባ ወጣ እንዳሉ እገታ ይፈፀምባቸዋል። 10 ሚልየን ብር ክፈሉ ተባሉ፣ ከፈሉ፣ ጥቂት ሰው ተለቀቀ።

የመክፈል አቅም አላቸው ብለው ሳይጠረጥሩ ያልቀሩት አጋቾች ተጨማሪ 10 ሚልዮን አምጡ ይሏቸዋል፣ አሁንም ይህ ብር ይከፈላል፣ ጥቂት ሰዎች ይለቀቃሉ።

ለሶስተኛ ግዜ ሲጠየቅ ግን ያላቸውን ንብረት ሸጠው እና ተበድረው የጨረሱት ሰዎቹ "ያለንን በሙሉ ሰጠን፣ ምንም የለንም" ይላሉ።

አሁን ድረስ ቀሪው የቤተሰቡ አባላት በእገታ ላይ ይገኛሉ፣ አጋቾቹም ስልክ መመለስ አቁመው ጭንቅ ላይ ይገኛሉ።

እንዲህ አይነት ወንጀሎች የማይነገርበት፣ እንደ ሿሿ ያለ ተራ ወንጀል ግን በየቀኑ የሚለፈፍበት ግዜ ላይ መድረሳችን ብዙዎችን እያሳዘነ እና እያስገረመ ይገኛል። 😭

(ገና እገታ ላይ ያሉ የቤተሱ አባላት ስላሉ ዝርዝር መረጃውን ትቼዋለሁ)
በ Elias Meseret

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በደላንታ ወረዳ ማዕድን በማዉጣት ላይ የነበሩ ከ 20 በላይ የሆኑ ወጣቶች ባጋጠማቸው አደጋ በፍርስራሽ ዉስጥ ተዉጠዋል ተባለ

በደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆቅ ዉሃ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በባህላዊ መንገድ የኦፓል ማዕድንን በማዉጣት ስራ ላይ የነበሩ ወጣቶች ሀሙስ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ገደማ ላይ ባጋጠማቸዉ የመሬት መደርመስ አደጋ በፍርስራሽ ዉስጥ ተዉጠዉ እንደሚገኙ የደላንታ ወረዳ ማዕድን ልማት ጽ/ት ቤት ሀላፊ አ/ቶ ተስፋ ሰማሁ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

እስከ 200 ሜትር ጥልቀት ድረስ የተቆፈረዉ ጉድዷድ ወጣቶቹ በድንገት በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት በመደርመሱ በፍርስራሽ ዉስጥ ሊዋጡ መቻላቸዉን ነግረዉናል። ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቁ ወጣቶች አደጋዉ ያጋጠማቸዉ ሲሆን ከቤተሰቦቻቸው በመጣ ሪፖርት መሰረት ግን ከ 20 በላይ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል ብለዋል።

ወጣቶቹ በህይወት ስለመኖራቸዉ የሚታወቅ ነገር የለም ያሉት ሃላፊዉ ከአርብ ንጋት ጀምሮ ቁፋሮ እየረከናወነ መሆኑን ለብስራት ተናግረዋል።

ገደሉ ጥልቅ በመሆኑ በዘመናዊ ማሽነሪዎች የታገዘ ቁፋሮን ለማከናወን አልተቻለም ያሉን አቶ ተስፋ ህብረተሰቡን በማስተባበር በሰዉ ሀይል የነፍስ አድን ስራዉ እየተከናወነ መሆኑን አክለዋል። እስከአሁን ድረስም 25 ሜትር ጥልቀት አካባቢ ቁፋሮ በሰዉ ሀይል መከወኑን ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በነፍስ አድን ስራ ላይ ላሉ ሰዎች ምግብ በማቅረብ ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነም አክለዋል።

ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው የኦፓል ማዕድንን የማዉጣት ስራ የተጀመረ ሲሆን ወጣቶች በባህላዊ መንገድ ማዕድኑን ሲያወጡ ቆይተዋል። ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከዚህ ቀደም ፤ በወረዳው የኦፓል ማዕድን በስፋት የሚገኝ መሆኑን እና ከ5 ሺ በላይ ወጣቶች በዘረፉ ተሰማርተው የዕለት ከዕለት ህይወታቸውን እየገፉበት እንደሚገኙ ዘገባ ሰርቷል፡፡ ወረዳው ሀብቱን በአግባቡ ለመጠቀም ዘመናዊ መሳሪያ ባለመኖሩ በወጣቶች በግምት እየተቆፈረ እንደሚገኝ የደላንታ ወረዳ ማዕድን ልማት  ጽ/ቤት አስታውቆ ነበር።
ጥብቅ መረጃ‼️

ትልቁ አደጋ እየመጣብን ነው ዶ/ር ዐብይ
ፋኖ የትግራይን ህዝብ ልብ ማርኳል ጠ/ዩ👇👇

ሙሉውን በዚ ሊንክ ያድምጡ👇👇
https://youtu.be/yuADIkpv4kQ
https://youtu.be/yuADIkpv4kQ
ወላይታ ሶዶ እያነባች ነው!😭😭

ትናንት ወላይታ ሶዶ ከተማ ዘግናኝ የመኪና አደጋ አስተናግዳለች ። በህይወት እና በንብረት ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል። እስካሁን 4 ሰው የሞተ ሲሆን ከ25 በላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የዓይን እማኞች ...
[ ወደ ኦቶና እና ክርስቲያን ሆስፒታሎች ተወስደዋል ሲሉ ተናግረዋል ]

አንድ ሃይሉክስ መኪና፣
2 ቪቲዝ፣
3 ባለ3 እግር ባጃጅ እና
ባለ2 እግር ሞተር ሳይክል ከጥቅም ውጭ ሆኗል !!😭😭

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት መካከል እጅግ በጣም ትሁት፤ ታዛዥ የሞተር አከራይ፤ ሰርቶ አዳሪው ኦኮቻ በመሆኑን ተንገብግበዋል።

ነፍስ ይማር!! 😭

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥብቅ መረጃ‼️

ሾልኮ የወጣው የነ ዶ/ር ዐብይ ፋኖ ላይ ያነጣጠረው ሚስጥራዊ ስብሰባ እነሆ እጃችን ገብቷል👇👇

እነሆ በዝርዝር ይመልከቱ👇👇
https://youtu.be/3TKDbSShGA8
https://youtu.be/3TKDbSShGA8
አጫጭር መረጃዎች ስለ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ "

- በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ  5 ወለል እና 8 በሮች አሉት።
- 8ቱ በሮች ፦
* የምሥራቅ ጀግኖች በር፣
* የምዕራብ ጀግኖች በር፣
* የሰሜን ጀግኖች በር፣
* የደቡብ ጀግኖች በር፣
* የፈረሰኞች በር፣
* የአርበኞች በር፣
* የፓንአፍሪካኒዝም በር ተብለው ተሰይመዋል።

- በመታሰቢያው ነጋሪትን ጨምሮ የኢትዮጵያውያን የተለያዩ (ባህላዊዎችን ጨምሮ) የጦር መሳሪያዎች ተቀምጠዋል።
- በዓድዋ ድል መታሰቢያው የአፄ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ፣ የ12ቱን የጦር መሪዎች ሀውልት፤ በጦርነቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ፈረሶች መታሰቢያ የአርት ሥራዎችም ሰፍረዋል።
- አንድ መቶ ሃያ ሺህ ጀግኖችን የሚዘክር  ማስታወሻ፣ የዓድዋ ድል ለፓንአፍሪካኒዝም ንቅናቄ ማሳያነቱንም ይዟል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፋውንቴንም ተሰርቶለታል።
- በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 500 ሰዎችን መያዝ የሚችል የፓንአፍሪካኒዝም አዳራሽ አለው።
- በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 300 ሰዎችን መያዝ የሚችል ዘመናዊ ሁለገብ አዳራሽ አለው።
- አራት ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል የቤት ውስጥ የስፖርት ሜዳ እና አዳራሽ አለው።
- የህፃናት መጫወቻ፣ የንግድ ሱቆች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎችና የአርት ጋላሪ አለው።
-ከአንድ ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ አለው።
- እያንዳንዳቸው 280 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ 2 ሲኒማ ቤቶች አሉት።
- በቅርቡ ወደ ሀገር የገባችው " ፀሀይ አውሮፕላን "በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንድትቀመጥ ተደርጓል።
-አጠቃላይ ስራው 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

🛣️ 00 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው።

Via:EPA
@ethio_mereja_news
ቴዲ አፍሮ በመኪና አደጋ ይሞታል፡ያለው ፓስተር ራሱ በመኪና አደጋ ሞተ።

በዲላ ከተማ ሰፊ የሆነ የህዝብ አመኔታን ያተረፈው ፓስተር ጆ ፡ቴዲ አፍሮ በ2016 ዓ.ም ይሞታል ብሎ የተናገረ ቢሆንም ፤በዛሬው ዕለት ከዲላ ወደ አዲስ አበባ በገዛ መኪናው በመጓዝ ላይ ሳለ በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።

ፓስተር ጆ የ 34 ዓመት ወጣት'የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው።

Via - Roha Media

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባህርዳር ገቡ
ምክትል ጠ/ሚኒስቴር አቶ ተመስገን ጥሩን ዛሬ ማለዳ ባህርዳር ገብተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በደቡብ ወሎ ማዕድን ሲያወጡ ናዳ የተጫናቸውን በርካታ ሰዎች የማውጣት ጥረት አራተኛ ቀኑን ያዘ!

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት አራተኛ ቀኑን ያዘ።የአካባቢው ባለሥልጣን እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር ሊቀመንበር ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም።

የወገል ጤና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዓለምነው ፍለጋውን በማሽን ለማገዝ የአካባቢው መልከዓ ምድር ምቹ ባለመሆኑ ጥረቱን አዳጋች አድርጎታል ብለዋል።በሕጋዊ መንገድ ተሰማርተው በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ናዳ የተጫናቸው ከአራት ቀናት በፊት ነበር። ሌሎች የአካባቢው ወጣቶችም አብረው ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተነግሯል።

ትናንት እሁድ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ባለፉት ቀናት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከአስር ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥረታቸው አዝጋሚ መሆኑን ተናግረዋል።

ስምንቱ የማኅበሩ አባላት በናዳው ተይዘው እንደሚገኙ የገለጸው ወርቅ ዋሻ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ሊቀመንበር ተስፋዬ አጋዥ በበኩሉ እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።ሐሙስ ጥር 30/2016 ዓ.ም. ምሽት 3፡00 አካባቢ ናዳው እንደተከሰተ ከአካባቢው ሰው መስማቱን የገለጸው ሊቀመንበሩ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአካባቢው ሕዝብ ሌት ተቀን ርብርብ እያደረገ ነው ብሏል።በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም አሁን ላይ በክልሉ የሚካሄደውን ግጭት ተከትሎ ሕገ ወጥ የማዕድን አውጪዎች በአካባቢው ተሰማርተው እንደነበር የገለጸው ተስፋዬ፣ ይህ ለዋሻው መደርመስ አንዱ ምክንያት መሆኑን ተናግሯል።

ይህ አደጋ ከተከሰተ በኋላ በመንግሥት በኩል የተቀበሩትን ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅም ሆነ ከዋሻው ለማውጣት የተደረገላቸው ድጋፍ እንደሌለም ገልጿል።የወገል ጤና ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ግን እርሳቸውን ጨምሮ የወረዳውም ሆነ የከተማው አመራር በሥፍራው እንደሚገኝ ገልጸው፣ በቂ ድጋፍ ማድረግ ያልተቻለው አማራጭ ስለሌለ መሆኑን አስረድተዋል።“ጥረቱን በማሽን ለማገዝ አልተቻለም፤ ማዕድን አውጪዎቹም ባህላዊ ማዕድን አምራች ተብለው የተሰማሩት ቦታው ከባህላዊ ቁፋሮ ውጪ የሚቻል ባለመሆኑ ነው። ቦታው ለእግር መንገድ እንኳን ምቹ አይደለም” ብለዋል።

በመሆኑም ለቀናት በዋሻ ውስጥ ተቀብረው የሚገኙትን ግለሰቦች ለማውጣት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሰማርተው በእጅ ቁፋሮ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከንቲባው ገልጸዋል።ከሦስት ዓመታት በፊት በተመሳሳይ አደጋ በዋሻ ውስጥ ተቀብረው አስራ አንድ ቀናት ቆይተው በሕይወት የወጡ ግለሰቦች መኖራቸውን ያስታወሱት ባለሥልጣኑ፣ እነዚህም በሕይወት ይወጡ ይሆናል የሚል የተስፋ ጭላንጭል እንዳላቸው ተናግረዋል።ከ100 ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው ዋሻ መግቢያ ላይ የተደረመሰውን አፈር በማንሳት 30 ሜትር ገደማ መግባት እንደተቻለ እና ይህም ተስፋ እንደሰጣቸው አክለዋል።“ዋሻው ሰፊ በመሆኑ ትንሽ አየር ማግኘት ከቻሉ በሕይወት የመትረፍ ዕድል ሊኖራቸው ይችላል” ብለዋል።

Via BBC
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/05 01:31:24
Back to Top
HTML Embed Code: