Telegram Web Link
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ተመን ይፋ አደረገ
በፓስተር ማቲዎስ ያቆብ በሚመራው በዘፀአት የለውጥ ሪል-እስቴት ማህበር ተጭበርብረናል ሲሉ ቤት ገዢዎች እና የቦርድ አባላት አስታወቁ

በቢልየን የሚቆጠር ገንዘብ ተጭበርብረናል ሲሉ የተናገሩት በማህበሩ የተወሰኑ የቦርድ አባላት እና ዋና ኃላፊው ፓስተር ማቲዎስ ያቆብ መሆናቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል።በዘፀአት  የለውጥ ሪል-እስቴት ማህበር ስም የተሰበሰበው ቢልየን የሚቆጠር ብር መጭበርበሩ  የማህበሩ ቦርድ አባል የሆኑት መጋቢ አጥናፉ አመያ የተናገሩ ሲሆን ይህን ገንዘብ በ37 ሰዎች ስም ተሸንሽኖ ተላልፎ ገንዘቡ የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ተናግረዋል።

ከ4ሺ እስከ 5ሺ  የሚሆኑ ሰዎች ለዚሁ ዘፀአት  የለውጥ ሪል-እስቴት ማህበር የቤት ባለቤት ያደርገናል ብለው ገንዘባቸውን ቢከፍሉም እስካሁን ተጨባጭ ነገር እንዳላገኙ አስረድተዋል።አስቀድሞ ማህበሩ የብድር እና ቁጠባ ተቋም የነበረ ቢሆንም ወደ ሪል -ስቴት ማህበርነት ተቀይሮ በአነስተኛ ገቢ ቤት ለማግኘት ህብረተሰቡን ለመጥቀም በሚል መለወጡ ተነግሯል።

ሆኖም የቤት ባለቤት እሆናለው ብለው የኃይማኖት አባቶች ናቸው በማለት አምኖ ገንዘቡን ቢከፍልም የኃይማኖት አባቶች በተባሉ ሰዎች በመጭበርበር ወደ ግለሰብ አካውንት መግባቱን የማህበሩ አባላት ሲያረጋግጡ ለፀረሙስና ኮሚሽን ሪፖርት አድርገዋል።

በፍርድ ቤት ትዕዛዝ  የባንክ አካውንታቸውን ተንቀሳቃሽ ንብረት እና ከሀገር እንዳይወጡ እግድ ሲጣልባቸው ወደእርቅ እንመለስ ህዝቡን በድለናል በማለት ሽማግሌ ልከው በደብዳቤም አቅርበዋል። ሆኖም እርቁ እግዱ እንዲነሳላቸው ከሀገር ለመውጣት እና የባንክ ገዘብን ለማሸሽ የታቀደበት እንጂ የተጭበረበርነውን ገንዘብ ለመመለስ የታሰበበት አለመሆኑን መንግስትም እና ህብረተሰቡን ተረድቶ ከጎናችን ይቁሙ ሲሉ ተጎጂዎች እና የማህበሩ የቦርድ አባል መጋቢ አጥናፉ ተናግረዋል።

ለዘፀአት የለውጥ ሪል-እስቴት ማህበር ገንዘብ የከፈሉ ግለሰቦችም በመግለጫው ተገኝተው ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
103 ሚሊዮን ብር መንግስት ገቢ ማግኘቱ ተሰምቷል

በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ደንብ ከተላለፉ አካላት ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡

ከደንብ ተላላፊዎች ተገኝቷል የተባለው ይህ ቅጣት ከመንግስታዊ ተቋማት ጭምር የተሰበሰበ መሆኑን የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል።

የተሰበሰበው ገንዘብም ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ሆኗል ብሏል::

@Sheger_press
@Sheger_press
#ግማሽ ክፍለ ዘመን እንቅልፍ ያላዩ ዓይኖች


ስምንት መቶ ሰባት ዓመታትን ወደኋላ ስንመለስ “ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን” “የአእላፍ ቅዱሳን አባት” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ጻድቅ የተወለዱበት ዓመት 1210 ዓ.ም ላይ እንገኛለን፡፡

ጎንደር ስማዳ ዳሕና ሚካኤል የተወለዱት አባት ገና በጉብዝናቸው ወራት በ30 ዓመታቸው ዓለምና አምሮቷን ንቀው ወደ ትግራይ “ደብረ ዳህምሞ” የአባታችን አቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ በመግባት ከጻድቁ አምስተኛ የቆብ ልጅ አባ ዮሐኒ ካልዕ ደቀ መዝሙር ሆኑ፡፡


በደብረ ዳሞም ቀኑን ለመነኮሳት በመታዘዝ፣ በመፍጨትና ውሃ በመቅዳት ሌሊቱን ደግሞ እኩሉን በጸሎት እኩሉን ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ ያሳልፉት ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በ37 ዓመታቸው ምንኩስና ተሰጣቸው፡፡


በዚው ዓመትም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብዙ ተአምራትና አገልግሎት የምትሰራበት ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶልሀልና ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ደብረ ዳሞና ሐይቅ እስጢፋኖስ እጅግ የተራራቁ ቢሆኑም መልአኩ ነጥቆ የተፈቀደላቸው ስፍራ ላይ አደረሳቸው፡፡


በዚም ለሰባት ዓመታት ከሐይቁ በስተሰሜን በሚገኘው የጴጥሮስ ወጳውሎስ ገዳም በማስተማርና በማገልገል ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ሌሊቱን በሐይቁ ውስጥ ገብተው በመጸለይ ያሰዳልፉ ነበር፡፡ በኋላም ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበው በብዙ ትግል አበምኔት አደርገው ሾሟቸው፡፡ ይህም የታላቁ ስራቸው መጀመሪያ ሆነ፡፡


አባታችን አቡነ ኢየሱስ ሞአ ከደሴ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም 800 ደቀ መዛሙርትን በመሰብሰብና በማስተማር ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ያፈረሰቻትን ቤተ ክርስቲያን ይገነቡ ጀመር፡፡


ታላላቅ መጻሕፍትን በማሰባሰብ የመገልበጥና የማባዛት ስራ ያሰሩ ሲሆን ደቀ መዛሙርቶቻቸውንም በማስተማር በመላው ሀገሪቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት አሰማርተው ቃለ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ፣ ትምህርት ወንጌል እንዲሰርጽ አድርገዋል፡፡


ለ45 ዓመታት በዘለቀው የገዳሙ አበምኔትነት አገልግሎታቸው አይናቸው ከእንቅልፍ ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ይህን ተጋድሏቸውን ለፍሬ አድርጎላቸው ታላላቅ ጻድቃን አባቶችን አፍርተዋል፡፡


ከእነዚህም መካከል የደብረ ሊባኖስ ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አባ ኂሩተ አምላክ ዘጣና ሐይቅ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን ዘደብረ ዳሬት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንጉሱ አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸው ለክብር ያበቋቸው እርሳቸው ናቸው፡፡ የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስም ጌታችን ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

በተወለዱ በ82 ዓመታቸው በ1292 ዓ.ም ሕዳር 26 ቀን ወደ ማያልፈው ክብር ጌታችን ጠርቷቸዋል፡፡ አስገራሚው ነገር አበምኔት ከመሆናቸው በፊት ለሰባት ዓመታት በገዳሙ አስተዳዳሪነት ደግሞ ለ45 ዓመታት በጠቅላላው ለ52 ዓመታት በቆየው ተጋድሏቸው እንቅልፍ የሚባል በአይናቸው አልዞረም፡፡


ገዳማውያን ዓለምንና አምሮቷን ትተው ሲመንኑ የበለጠውን ክብር ሽተው፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ሰፊ ጊዜ ለማሳለፍ ፈልገው እንጂ ተሞኝተው አይደለም፡፡ መስቀሉን ተሸክመው ሲከተሉት ዓለም እንደ ሞኝነት ይቆጥርባቸዋል፡፡

በረከታቸው ግን ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ ድንቅ ይሰራል፡፡ አሁን በዘመናችን ያሉትን ገዳማትና መናንያን ስንደግፍም ይህ ቃል ኪዳንና በረከት ከኛ ጋር ይሆናል፡፡     
       


ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ግብፅ‼️
ግብፅ በሶማሊያ እንደተካደችና ሞቃዲሾ ካይሮን ከጀርባ እንደወጋቻት በመቁጠር መበሳጨቷ ተገለፀ‼️
የሶማሊያ የስለላ ተቋም መሪ የነበሩት አብዲሳላን ጉሌድ የግብፅ መንግስት ሃሰን ሼክ በአንካራ ከኢትዮጵያ ጋር መፈራረማቸው በጣም እንዳሳዘናት ባደረጉት ቃለ መጠይቃቸው ይፋ አድርገዋል።

የካይሮ ቤተመንግስት ታማኝ የባለስልጣናት ምንጮችን ዋቢ ያደረጉት ሰውየው፣ የግብፅ አገዛዝ ይህን የሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ድርጊት ከጀርባ እንደተወጋ በመቁጠር ክህደት እንደተፈፀመባት አድርጋ እንደምትመለከተው እወቁት ብለዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ጊዝያዊ ምክር ቤት ማቋቋሙን አስታወቀ

ታህሳስ 4 ምሽት ይፋ የተደረገው መግለጫ እንደሚያሳየው ከሆነ የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላማዊ ትግልና ውይይት እንጂ በጦርነት አይደለም ብሎ የሚያምነው በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ፓርቲው መደበኛ 14 ጉባኤውን እስኪያካሂድ ድረስ ፓርቲውን የሚመራ ጊዝያዊ ምክር ቤት ማቋቋሙን ከመግለጫው ተመልክተናል።

የምክር ቤቱ አባላት ደግሞ ከኃላ ቀሩና ከወንጀል ቡድኑ ጋር አንሰለፍም ያሉ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን መግለጫው ይገልፃል።

@Sheger_press
@Sheger_press
#ለድንቅ ስራ የተመረጠ እጅ፣ የተቀባ ራስ


በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገድለ ላሊበላን የጻፉት የውቅር አቢያተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ቅርጽና አሰራር ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡፡ “በላሊበላ እጅ እኒህ አብያተ ክርስቲያናት ከምድር ልብ ወጥተው የሚሠሩበት ጊዜ ደረሰ… ምድርን ከፈጠረ ጀምሮ ተሠውሮ የነበረውን ሕንጻ እንዲገልጥ እግዚአብሔር ወዷልና።” የልዩ ጥበባዊ መገለጥ፣ የድንቅ አእምሯዊ ሀሳብ፣ የመጠቀ የስነ ሕንጻ ጥበብን የመረዳት አቅም ውጤት የሆኑት እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት እውን ለመሆናቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳለበት ይህ አገላለጽ ማሳያ ነው፡፡


ይህን መነሻ አድርገው ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ሲወቅር የመላዕክት እገዛ እንዳለበት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያብራራሉ፣ አንድም እነዚህ የጥበብ ውጤቶች ልዩና የማይደገሙ ተደርገው ቢሰሩም በሰው እጅ መሰራታቸውን መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ያም ሰው እግዚአብሔር ስራውን ሊገልጽበት ፈልጎ ይህን እውቀት በአእምሮው ያኖረለት እጁንም የባረከለት ንጉሱ ቅዱስ ላሊበላ ነው ይላሉ፡፡


ቅዱስ ላሊበላ ገድሉ በንግስና ስሙ ጠቅሶ ስራውን ሲያብራራ “ገብረ መስቀልም ልዩ ልዩ የሆኑ የብረት መሣሪያዎችን አሠራ። ለመጥረብም የተሠራ አለ። ለመፈንቀልም የተበጀ ብረት አለ። ለመፈልፈልም የተሠራ አለ። እነዚህን ቋጥኝ ድንጊያ የመቅደስ ሕንጻ የሚፈጸምባቸውን አሠራ። ገብረ መስቀልም ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምድራዊ ሐሳብን፣ ሚስቱንም ደስ ለማሰኘት ፈቃድ ቢሆንም አላሰበም። ሁሉንም በሙሉ መንፈስ ስለ እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት አሰበ እንጂ።” ይላል፡፡ መጽሐፉ ከዚህ ጋር አያይዞ በንጉሥ ላሊበላ አዛዥነት በሀገሬው ሰዎችና በመላእክት እገዛ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ እንደተሰሩ ይነግረናል፡፡


“ንጉሱ ሕዝቡን ሁሉ ወደ እርሱ ሰብስቦ በአብያተ ክርስቲያናቱ ሕንጻ ሥራ የምትረዱኝ ሁላችሁም የምትቀበሉትን ደሞዛችሁን ተናገሩ አላቸው፣ እግዚአብሔር እንድሠራ አዞኛልና። እናንተም በአንደበታችሁ ደመወዛችሁን እንዴት እንደምትቀበሉ ተናገሩ። በጠራቢነትም ሥራ የሚረዳ፣ ጥራቢውንም በማውጣት የሚረዳ ሁላችሁም በአንደበታችሁ ተናገሩ። እንደ አላችሁኝ እሰጣችኋለሁ” ሲልም አወጀ፡፡


ያለ ፈቃዳችን አስገደደን እንዳትሉኝ። በአጉረመረማችሁ ጊዜ ድካማችሁ ብላሽ እንዳይሆን። “ሁላቸውም ልባቸው እንዳሳሰባቸው ነገሩት። እርሱም ስጦታቸውን ሳያጓድል እንዳሉት ሰጣቸው። የአብያተ ክርስቲያናቱን ሕንጻ ሥራ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ፈጸመ ድረስ ለሚፈለፍልም ሆነ ለሚጠርብ የቤተ ክርስቲያኑን ጥራቢ ለሚያወጣም ሆነ ደሞዛቸውን በጊዜው ይሠጣቸው ነበር።” ይላል ገድለ ቅዱስ ላልይበላ፡፡

ይህን ድንቅ ስፍራ መጎብኘት በተለይ በልደቱ ቀን ታሕሣስ 29 በስፍራው መገኘት ልዩ እድል ታላቅ በረከትም ነው፡፡ ይህን ልዩ ቀን ላስታ ላይ ለማሳለፍ ለምትፈልጉም ልዩ የጉዞ መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡

 
ለአረጋውያን፣  ለነፍሰጡሮች፣ ለህፃናትና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ምቹ ማረፊያም አዘጋጅተናል፤ ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17 ዓ.ም

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17 ዓ.ም

የጉዞ ዋጋ ምግብን ፣ ማረፊያንና መስተንግዶን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ

የኡጋንዳ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙሆዚ ካኒሩግባ አዲስ አበባ ናቸው።ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መምከራቸውን ሰምተናል።

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ከስደተኞች ጋር መሽገው ወንጀል የሚፈፅሙትን በጋራ ለመከላከልና ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውም ተሰምቷል።ዚህም ሁለቱ ሀገራት የፀጥታ መረጃ መቀያየር፣ ሁሉን አቀፍ ስልጠና እንዲሁም ለቀጣናው ሰላም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ተዘግቧል።
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Video
“እነሆ ይህ የእሳት ፍም ከንፈሮችህን ስለ ነካ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ይቅር ተብሎልሃል”

በቤተ ክርስቲያናችን አበይት ነቢያት ለሚባሉት አንዱ ቅዱስ ኢሳይያስ ነው፡፡ በዘመኑ የነበረው ንጉስ ዖዝያን ኃጢአት ሲሰራ እያው ዝም አለው፡፡ በዚህም ምክንያት ከንፈሩ በለምጽ ተመታ፡፡ በኋላም ንጉሱ በሞተበት ዓመት “ቅዱስ እግዚአብሔር ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት” ለነቢዩ ታየው፡፡ አንተ ትፈራው የነበረው ንጉስ ሞተ እኔ ግን ሕያው ነኝ ሲል፡፡ እርሱም ይሕን በማየቱ ፈርቶ የሚሞት መስሎት ወዮልኝ አለ፡፡

እኛ ግን ድንቅ ምስጢር በሚፈጸምባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደስታ ገብተን ጸጋውን ተቀብለን ሕይወትም አግኝተን በሰላም እንወጣለን፡፡

ነቢዩ ስለዚህ ነገር በትንቢተ ኢሳያስ 6፣1-7 ሲናገር “ከእነዚያም መላእክት አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ ከመሠዊያው የወሰደው የእሳት ፍም የያዘበት ጒጠት በእጁ ነበር። በእሳቱም ፍም ከንፈሮቼን ነክቶ እነሆ ይህ የእሳት ፍም ከንፈሮችህን ስለ ነካ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ይቅር ተብሎልሃል አለኝ።” ይላል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶችም መልአኩ በጉጠት የያዘው ፍም የቅዱስ ስጋውና የደሙ ምሳሌ ነው ይሉናል፡፡ መልአኩ ስልጣነ ክህነት ስለሌለው በጉጠት የያዘውን እሳት ካሕናት አባቶች ዛሬ በእጃቸው ፈትተው ያቆርቡናል፡፡ የካሕናት ስልጣን ትልቅ ነው፡፡

ታዲያ ይህን መንፈሳዊ ስራ የሚያከናውኑባት ቤተ ክርስቲያን ደሳሳ ጎጆ ሆና፣ ዝናብ እያፈሰሰች  ዝም ማለት እንደምን ይቻለናል???   
  
በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘው ሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ለሚገኙ መነኮሳት  እጃችንን እንዘርጋ፡፡


ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጺ ወያነ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ጉዳይ የሃሳብ ልዩነት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡

ነገር ግን " የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡

በአዲስ አበባው ውይይት በደብረፅዮን (ዶ/ር) ይሁን በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በወቅቱ " የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም " በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

" የፌደራል መንግስት ' ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል ' በማለት መልሶልናል " ሲሉ አብራርተዋል።

ሌተናል ጄነራሉ ፥ " በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል " ብለዋል።

የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው " በማለትም አስረግጠዋል።

" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት ዓለምአቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅ እና የማስከበር ስልጣን አለው፤ ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ በቦታው የሚገኙ የውጭ ሃይሎች አውጥቶ የግዛት አንድነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት ጠይቀናል " ብለዋል።

በዚህ ምክንያት " ' ከሃዲዎች ' በሚል ስማችንን ማጠልሸት ተገቢ አይደለም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን  ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።

#Tigray #TPLF
(tikvahethiopia)

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
#የምሰራው ቤት ታላቅ ነው

ንጉስ ሰሎሞን የሰራው ቤተ መቅደስ ምድራችን ካየቻቸው ድንቅ ነገሮች አንዱ አንደሆነ የታሪክ ጸሐፍት ያትታሉ፡፡ በመጽሐፈ ነገስት ካልዕ ምዕራፍ 2 ቤተ መቅደሱን ለመስራት ሲያስብ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ለማሰባሰብ ከነገስታት ጋር ተጻጽፏል ባሕር ተሻግረው ከሊባኖስ በታላላቅ መርከቦች የመጡ እንጨቶች እንደነበሩ ተጽፏል፡፡ ወደ ጢሮስ ንጉስ ወደ ኪራም በላከው መልዕክትም፡- 
“ደግሞም ባሪያዎችህ ከሊባኖስ እንጨት መቍረጥ እንዲያውቁ እኔ አውቃለሁና ከሊባኖስ የዝግባና የጥድ የሰንደልም እንጨት ስደድልኝ።” የሚል ዓረፍተ ነገር ቁጥር ስምንት ላይ ይገኛል፡፡


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሰራ በዚህ መልኩ ግብአቶችን በአይነት ማቅረብ ጥንታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ ነው፡፡ በዘመናችንም አብያተ ክርስቲያናት ሲገነቡ እንድናደርግ ከምንጠየቀው ገንዘብ እገዛ ውጪ በአይነት እንጠየቃለን፡፡ ሲሚንቶ፣ ጠጠር፣ አሸዋ፣ ብረት ወዘተ ይህን ያህል እንፈልጋለን ተብሎ ይነገረናል፡፡


ጠቢቡ ንጉስ ሰሎሞን ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም በላከው መልእክት “እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘላለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ለማጠን፣ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፣ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራና እቀድስ ዘንድ አሰብሁ። አምላካችንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ነውና የምሠራው ቤት ታላቅ ነው።” ባለው ጊዜ በደስታ ነበር ተባሉትን የተመረጡ እንጨቶች የላከለት፡፡

እነሆ በዘመናችንም ጥሪ እየቀረበልን ነው፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያለውን ቤተ ክርስቲያንና ገዳማውያን አባቶችን ለመርዳት፣ በዓታቸውንም ለመስራት ድንጋይ፣ ሲሞንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠርና ብረት በአይነት ማገዝ የምትችሉ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች ደውላችሁ ብትነግሩን ያላችሁበት ድረስ በራሳችን ትራንስፖርት መጥተን ለመውሰድ ዝግጁዎች ነን፡፡ የምንሰራው ቤት ታላቅ ነውና ከታላቁ በረከት ተሳተፉ፡፡ የገዳማውያኑ በረከትና ረድኤት አይለየን!!! 

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
"‘ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለሁሉአቀፍ የማህበረሰብ ጤንነት!’ በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አከናውነዋል።

የከተማችን ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል በማድረግ ሁሉም በየአካባቢው እና በየመስሪያ ቤቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንዲያደርግ መስራት ይኖርብናል።

ጎዳናዎቻችን ጽዱ እና ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው የተገነቡ ሲሆን፣ ሁላችንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረግን እንንከባከባቸው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

@Sheger_press
@Sheger_press
በደብረ ማርቆስ

አማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መንቆረር ክ/ከተማ የቦ አርጀና ቀበሌ በተሰበሰበ የአርሶ አደር የስንዴ ክምር ላይ ጉዳት መድረሱን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
 
አርሶ አደሮች አመት የደከሙበት 9 የስንዴ ክምርና የተሰበሰበ የከብቶች መኖ ጭምር ታህሳስ 5ቀን 2017 ዓ.ም ሆን ተብሎ እንዲወድም እንደተደረገ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን በገፁ ላይ አስፍሮ ተመለክተናል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2025/01/03 21:36:59
Back to Top
HTML Embed Code: