Telegram Web Link
ችግሩ ተፈትዋል…???


ለ ዓመታት የቆየ መፍትሔ ማይገኝለት የመሰለ ችግር ባልተጠበቀ ጊዜ እና ባልታሰበ ሁኔታ መፍትሔ አግኝቷል ከ ሰሞኑን በ ዲ/ን አቤኔዘር ውብሸት በtiktok ቤተሰቦቹ አማካኝነት በጊንጪ ደንዲ ወረዳ የሚገኘው 116 ዐመት ያስቆጠረው የጋሬ ደብረ ሰላም አቡነ ተ/ሀይማኖት ቤ/ክ በአዲስ መልኩ ታድሶ ከተመረቀ የቅርብ ቀን ትውስታ ነው።


ለአመታት ከ 10 የማይበልጡ አባ ወራዎች በአካባቢያቸው ላይ ያለው ባዶ ቦታ ላይ መስቀል በመትከል በየወሩ በ24 በቦታው ላይ ተሰባስበው ተክልዬን ይዘክሩ ነበር ሰው ከሞተም ፍትሐት ሳይፈታ ባዶ ቦታውን እንደ ቤተ ክርስትያን በመጠቀም ይቀብሩ ነበር ይሄም ቤ/ክ ስለሌላቸው ቁጡራቸው በጣም ጥቂት በመሆን ይቸገሩ የነበሩ አባቶች እና እናቶች በብዕፁ አባታችን አቡነ ይስሐቅ በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ መልካም ፍቃድ እና ክትትል እንዲሁም በዲ/ን አቤኔዘር ውብሸት የtiktok ቤተሰቦች ሙሉ የግንባታ ወጪ በመሸፈን ለአመታት የተክልዬ ቤተ ክርስትያን ነው ብለው በባዶ መሬት ላይ ያለ ቤተ መቅደስ ፀሎት ሲያደርጉ የነበሩ 10 የሚሆኑ አባ ወራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተክልዬ ቤ/ክ ተሰርቶ በዛሬው እለት በቀን 08/03/2017 ተመርቋል።


የዚህ ቦታ መገኛውም በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት በሁምቦ ወረዳ የኮይሻ ጎላ ኦቤያ አቡነ ተ/ሀይማኖት ቤ/ክ ነው  ልብ በሉ ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡

ለዝያም ነው ለዘመናት ንፁህ ልብ ይዘው የፈጣሪ ቤት አንድ
ቀን እኛ ጋር ይመጣል ብለው በእምነት ሲፀልዩ የነበሩ 10 ብቻ የሚሆኑ አባ ወራዎች ዛሬ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው  የቤ/ክ ባለቤት የሆኑት::
መረጃ ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ በሚባል አካባቢ የፋኖ ሀይሎች በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ላይ ሰበአዊ ጉዳት መድረሱን ምንጮች አስታዉቀዋል ፡፡

በአካባቢዉ  መንዝ ሞላሌና ይፋት  በሚባል ቀጠና መንግስት ተከታታይ የድሮን ጥቃት ማድረሱ ተሰምቷል ፡፡

በአጣዬ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ወሰድን ባሉት ጥቃት የፋኖ ሃይሎችን ደመሰስን ሲሉ በፎቶ በማስደገፍ  አቅርበዋል ፡፡

በክልሉ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለዉ ዉጊያ የብዙ ንፁሃን ዜጎች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል ፡፡

#አንኳር_መረጃ  


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትናንትናዉ እለት በባሕርዳር ከተማ ሄሊኮፕተር ተከስክሷል ቢባልም "የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው የለም" ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር አስተባበለ

በባሕርዳር የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው ሄሊኮፕተር አለመኖሩን የመከላከያ ሚኒስቴር አስተባብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷የኢፌዴሪ አየር ሃይል ካሉት "ቤዞች" አንደኛው ምድብ የሆነው ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ አየር ምድብ መሆኑን አንስቷል፡፡

በትላንትናው ዕለት በነበረው የአየር ኃይል የምድብ ልምምድ ምክንያት መደበኛ የአየር መንገድ በረራ ለጥቂት ጊዜያት ተቋርጦ የነበር መሆኑን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጅ የአየር መንገድ ተሳፍሪዎች የተወሰነ መጉላላትን አጋጣሚ በመጥቀስ ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል የማደናገሪያ ሃሳብ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ እየተራገበ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡

መደበኛ በረራ ለውስን ጊዜያት ተቋርጦ የነበረው በተገቢው መንገድ ስራ የጀመረ ሲሆን÷ የምዕራብ አየር ምድብም ልምምዱን ስኬታማ በሆነ መንገድ አጠናቅቋል ብሏል።

"የጠላት ሁለንተናዊ አቅምና የፕሮፖጋንዳ መስክ መክሰርና መከስከስ ካልሆነ በስተቀር የተከሰከሰ ሄሊኮፕተር የለም" ሲልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር ይህንን ቢልም በተለያዩ የዲጂታል ሚዲያዎች በኩል ንብረትነቱ የኢፌዴሪ አየርሀይል የሆነ ሄሊኮፕተር መከስከሱን ሲዘግቡ ነበር።
መረጃ ‼️

በ ዶ/ር ደብረፅዬን ገ/ሚካኤል የሚመራዉ የህዉሃት ቡድን በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፀጥታ ሃይሎች ላይ በአክሱም ከተማ ተኩስ ከፍቷል ፡፡

ትላንትናም በተመሳሳይ በከተማዉ ተኩስ እንደነበረ ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡

ሸገር ፕረስ

ለበለጠ መረጃ👇
@Sheger_press
@Sheger_press
“በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ”

ታላቁ ጻድቅ አባት አባ ሣሉሲ ዜና ሕይወታቸው እጅግ ከሚያስገርሙ ገዳማውያን አንዱ ናቸው። መጽሐፈ ስንክሳር እንደሚገልጸው የዘመነ ከዋክብት ፍሬ ከሚባሉት ጻድቃን አንዱ ሲሆኑ በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን 'የማይጾመው፣ የማይጸልየው፣ ሥራ ፈቱ መነኩሴ' በሚል ነበር።


ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን አባ ሣሉሲ ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም። ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ። በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም።

አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ። "አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ቢያንስ ለቁርባን እናብቃቸው።" ሲሉ ወሰኑ። በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው።

አባ ሣሉሲም "ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት?" ሲሉ ተቆጡ። መነኮሳቱ ግን "ሳትቆርብ አንለቅህም።" አሏቸው። በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው "እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው። አንቺ ግን ርኅርኅት ነሽ።" ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ።


እርሳቸውም ሁለት ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ። ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ ሦስት መቶ ጊዜ "እግዚኦ....." አሉ። በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ። በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ።

አባ ሣሉሲ ግን ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በተመስጦ በልባቸው ስለሚጸልዩና ይህ ቅድስናቸው እንዳይታወቅ ነበር የሚጥሩት፡፡ በጧት ተነስተው የሚያኝኩትም ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረም። ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው።


ስንቶቻችን ጥቂቷን በጎነታችን ሰው ሁሉ እንዲያውቅልን ስንጥር ገዳማውያን አባቶቻችን ግን ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ጸብአ አራዊቱን ታግሰው ሀገርንና ሕዝብን ሌት ተቀን በጸሎት ሊያስምሩ እየተጉ መንፈሳዊ ጸጋና ክብር ሲያገኙ ትሕትናቸው ይበልጥ ከፍ ይላል፡፡

የጸሎታቸው ረድኤት አብሮን እንዲሆን ገዳማትን ማገዝ ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው፡፡ የገዳማውያኑን በረከትና ጸሎት አይለየን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም
                        ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                        1000442598391

                        አቢሲኒያ ባንክ
                        141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
የትግራይ ዉጥረት ወዴት እያመራ ነዉ⁉️

የፀጥታ ኃይሉ በደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ሕወሓት ላይ ዕርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ቀረበ

 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር 14ኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ያካሄደው ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ሕወሓት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥራዎች ከማደናቀፍ አልፎ ግልጽ በሆነ መንገድ መፈንቅለ መንግሥት ማካሄዱን በመቀጠሉ የፀጥታ ኃይሉ ዕርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ፡፡ 
ቡድኑ ወደ ለየለት ሥርዓት አልበኝነት ተሸጋግሯል በማለት የገለጸው የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤቱ፣ ‹‹በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በሚገኙ መንግሥታዊ መዋቅሮች ላይ ሕገወጥ ምደባዎችን በማካሄድና ጫና በመፍጠር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥራዎች በማደናቀፍ ላይ ተጠምዷል፤›› ብሏል፡፡
ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ መንግሥታዊ ኃላፊነት ላይ ተመድበው ሕዝቡን ለማስተዳደር ወንበሩን የተቆናጠጡ አካላት፣ የሚያስተዳድሩት ሕዝብም ሆነ ሀብት እንደማይኖርም ነው ጽሕፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡ 
ሁኔታው ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መሰል ሥርዓቱ አልበኝነት ከአቅሙ በላይ በመሆኑ የትግራይ ፀጥታ ኃይል፣ የፍትሕ አካላትና ባንኮች እየታየ ያለውን ሕገ መንግሥቱን የጣሰ አካሄድ ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡
በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ሕወሓት ከሁለት ወራት በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚደረገውን ሹም ሽር በተደጋጋሚ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ በታችኛው መዋቅር የሚገኙ ምክር ቤቶች ስብሰባ በማካሄድ አዳዲስ ምደባዎችን እንደማይቀበልና አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በካቢኔያቸው ውስጥ ያሉት አምስት ሰዎች በድርጅቱ መባረራቸውን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ጽሕፈት ቤት ግን ‹‹በግላጭ መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደብኝ ነው፤›› በማለት በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው መግለጫዎች እየገለጸ ነው፡፡      
የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት በማከልም፣ በእያንዳንዱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ውስጥ የሚገኙና በክልሉ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላትና ተቋማት፣ የፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) በሚመራው ሕወሓት በሕገወጥ መንገድ ተመድበው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አካላት፣ መንግሥታዊ ኃላፊነት ይዘው በየትኛውም መድረክ ላይ መሳተፍ እንደማይችሉ በመገንዘብ ፈቃድ ሊሰጡ እንደማይገባ አሳስቧል፡፡

በክልሉ ባሉ የሃይማኖት አባቶች አሸማጋይነት በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) እና በአቶ ጌታቸው በሚመሩት ቡድኖች መካከል ውይይት ተደርጎ ዕርቅ ይወርዳል የሚል ተስፋ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም፣ በአቶ ጌታቸው የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር ኅዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ‹‹መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደብኝ ነው፤›› ብሎ ነበር፡፡

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህንን ያለው ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የድርጅቱ ሌላኛው ክንፍ ሥራ አስፈጻሚ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ተወያይቶ፣ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታና በሕዝቡ ላይ የተጋረጡ በግልጽ የሚታዩ ሥጋቶች ዙሪያ ሙሉ በሙሉ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን የተመለከተ አጭር መግለጫ ባወጣ ጥቂት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ 
ስምምነት ተደርጎበታል የተባለውን ውይይት በተመለከተ ከሕወሓት በኩል ዝርዝር መረጃ አልወጣም፡፡ የፀጥታ ኃይሉም ውይይት ስለመደረጉም ሆነ ስምምነት ላይ ተደርሶባቸዋል ስለተባሉት ጉዳዮች ያለው ነገር የለም፡፡   
 የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በአራት ቀናት ልዩነት ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ቢያወጣም፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) በሚመራው ሕወሓት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ 
ሪፖርተርም ከድርጅቱ ኃላፊዎች መረጃ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡    

@ሪፖርተር
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
መረጃ ‼️


ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ስንዴ አምራች ሆናለች

የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር  ለገሰ ቱሉ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ስንዴ አምራች ሆናለች ሲሉ ተናግራዋል፡፡

በዘንድሮዉ አመት 5.3ሚሊዬን ሄክታር በሰብል ምርት መሸፈኑን የተናገሩት ሚነስትሩ መንግስታቸዉ በሙሉ አቅም በመስራቱ የሚፈለገዉ ዉጤት ማምጣት እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡

ሃገሪቱ በስንዴ ምርት እራሶን በመቻል ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ስንዴ አምራች  እንደሆነች አቶ ለገሰ ቱሉ አስታዉቀዋል፡፡

ሚኒስተሩ ይሄን ይበሉ እንጂ በቅርቡ ሩሲያ እየተጠናቀቀ ባለዉ የፈረንጆቹ አመት ስንዴ የላከችላቸዉን ሃገራት ይፋ ስታደር ኢትዬጲያ በዝርዝር ዉስጥ እንደተካተተች የሚታወስ ነዉ ፡፡

via- አንኳር_መረጃ  

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሙትአንሳ  ማር  ቅዱስ ሚካኤል አንድነት  ገዳም በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ይገኛል።


በዚህ ታሪካዊ ገዳም ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት ትልቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡
አከባቢው በከፍተኛ ድርቅ ምክንያት ምንም ዓይነት አዝርእት አልበቀለበትም፣ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆናል።


በተጨማሪም መነኮሳቱ በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ተከበው ይገኛሉ።
የሚቀምሱት እህል ፣ የሚለብሱት ልብስ፣ ጋደም የሚሉበት ቦታም የላቸውም።


ውድ ኢትዮጵያዊያን ይህን እያየንና እየሰማን እኛ በተሸለሙ ቤቶቻችን ዝም ብለን ለመቀመጥ ጊዜው አይደለምና እነዚህን ገዳማውያ ልንጎበኛቸው አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል።


ድጋፍ ለማድረግ:-
                        ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                        1000 44 25 98 3 91
                        አቢሲኒያ ባንክ
                        14 10 29 4 44
ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-09 18 07 79 57     
                         ወይም 09 38 64 44 44 በመደወል ማነጋገር ይቻላል፡፡
የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው‼️

በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ማዓሾ ለስራ ከአክሱም ወደ መቐለ እየተጓዙ እያለ ተሽከርካሪያቸው በተለያዩ ቦታዎች በጥይት
መመታቱን ተዘግቧል ።

via አንኳር_መረጃ  

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሚኖሩ ሱዳናዊያን ስደተኞችን እንደገና የቪዛ  ክፍያ ማስከፈል መጀመራቸው ስደተኞቹን አጣብቂኝ ላይ እንደጣላቸው የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

መንግሥት ለሱዳናዊያን ስደተኞች የቪዛ ክፍያ ማስከፈል ያቆመው፣ ባለፈው ዓመት የካቲት ነበር። ኾኖም መንግሥት ቪዛቸውን በጊዜው በማያሳድሱ ስደተኞች ላይ የ30 ዶላር ቅጣት በቅርቡ ጥሏል ተብሏል።

የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን፣ ከመጠለያ ውጭ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሱዳናዊያን ስደተኞችን በስደተኝነት አልመዘገበም።

አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ አንድ የሱዳን ሲቪክ ድርጅት፣ ለጉዳዩ መፍትሄ ፍለጋ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አቤቱታ ማስገባቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርካቶ‼️

ዛሬ በመርካቶ አድማ መደረጉ የሸገር ፕረስ ምንጮች ገልፀዋል።

ነጋዴዎቹ ለዚህም እንደምክንያትነት ያስቀመጡት ገቢዎች አላሰራም ስላሉን አድማ አድርገናል ነው ያሉት።

መንግስት ከነጋዴው ጋር ያለው አለመስማማት በንግግር እንዲፈታ በትህትና እንጠይቃለን።

ሰላም ለሀገራችን

ምንጭ ( ሸገር ፕረስ)

ለተጨማሪ መረጃ ሁለተኛው ቻናላችን ይቀላቀሉ👇
@Sheger_press
@Sheger_press
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
2024/11/18 15:47:41
Back to Top
HTML Embed Code: