Telegram Web Link
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ ሕገወጥ ተግባራት እየተበራከቱ በመሄዳቸው ጊዜያዊ አስተዳደሩን የሚፈታተኑና የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎችን ለማጣራት ኮሚቴዎችን በማቋቋም ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልጧል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የክልሉ ፖሊስ በሕገወጥ የብረት ማዕድን ንግድና ሌሎች ሕገወጥ ድርጊቶችና ወንጀሎች የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ሥር ማዋል ጀምሬያለኹ ብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
"የአዲስ አበባ ሰሞነኛ ድምቀቶች" የሚል ፖስት ላይ መሬት ላይ ከተሰራው ፕሮጀክት ይልቅ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈበረከ ምስልን (ያውም ጎላ፣ ጎላ ባለ መልኩ) እንዲህ ማቅረቡ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው?

ምናልባት ሀሳቡ "ወደፊት እንደዚህ ይሆናል" ወይም "ለመሆን እቅድ አለ" ከሆነም በደፈናው የAI ፎቶ ማስቀመጥ ሳይሆን እሱን በፅሁፉ ውስጥ በግልፅ ማስፈር ያስፈልጋል።

በባለስልጣናት፣ ውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ፖለቲከኞች፣ የቢዝነስ ሰዎች... ወዘተ የሚጋሩ መረጃዎች ትክክለኛ የሆኑ፣ ወቅትን የጠበቁ እንዲሁም ሊያደርሱ የሚችሉትን spill over effeft ያገናዘቡ ሊሆን ይገባል... በተለይ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ ተብለው የተቋቋሙ እንደ ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ያሉ ተቋማት ይህን ሊተገብሩ ይገባል።

EliasMeseret

@sheger_press
@sheger_press
Merkato Media:
በአማራ ክልል ያሉ የአዉደ ዉጊያ ዉሎ መረጃዎችን እየተከታተለ ወደ እናንተ የሚያደርስ ቻናል ልጠቁማችሁ

👇👇👇
https://www.tg-me.com/SNN_merja
https://www.tg-me.com/SNN_merja
<<...መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ...ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ

ሲኖዶሱ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ።


በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል።ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ለእግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው።


"ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ።

እግዚአብሔር  መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣;ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።


በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል።

በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል።


ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ መልዕክት ተላልፏል፡፡
በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም ዓለም አቀፍ ተቋማት የተካተቱበት ኮሚቴ ተቋቋመ-

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን፣ በኢትዮጵያ በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ቁጥር አስመልክቶ የተባበሩት መንግሥታቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ)፣ ከሰሞኑ ያወጣውን ሪፖርት መቃወሙን ዋዜማ ተረድታለች።
ጉድ በል ጎንደር

የፖርቹጋሉ ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ንዋንክዎ ካኑ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ሁለቱ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።
የፌደራል እና የሚመለከታቸው የክልል መንግስታት የግዛት ወሰናቸው ባሉባቸው አካባቢዎች የሚፈጸሙ የእገታና አፍኖ የመሰወር ድርጊቶችን እንዲያስቆሙ፣ የእገታና አፍኖ የመሰወር ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎችን በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና ለዜጎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ ኢሰመጉ ጥሪ አቀረበ።

ኢሰመጉ በተለያዩ ጊዜያት በሚያወጣቸው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫዎች በዜጎች ላይ የሚፈጸመው እገታና አፍኖ የመሰወር ተግባር በሀገራችን በአሳሳቢ ደረጃ እየተስፋፋ ያለ ጉዳይ መሆኑን እና በዚህም የተነሳ የሰዎች በሕይወት የመኖር መብት፣ የአካል ደህንነት መብት እና ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን በመረጃ በማስደገፍ በተደጋጋሚ መግለጫዎችን ማውጣቱን አስታውሷል።

ቢሆንም ግን የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስታት በግዛት ክልልቸው የሚፈጸመውን እገታ እና አስገድዶ መሰወር ለማስቆም በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው ይህ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ምሬት እና እንግልት እየዳረገው ይገኛል፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ ገብረ ጉራቻ አካባቢ በታጠቁ አካላት የታገቱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከታገቱ ተማሪዎችም መካከል የተወሰኑት ተማሪዎች የተጠየቀዉን መክፈል በመቻላቸውና በተለያዩ ምክንያቶች ከአጋቾች ማስለቀቅ መቻሉን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በኢትዮጵያ በመጠለያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ቁጥር በተመለከተ ከቀናት በፊት ያወጣውን ሪፖርት ተቃውሞታል።

ኮሚሽኑ፣ በመጠለያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን እንደኾኑ ለዋዜማ ተናግሯል።

ኮሚሽኑ፣ የቢሮው ሪፖርት "የቆየ እና በትክክለኛ ጥናት ላይ ያልተመሠረተ ነው" በማለት አጣጥሎታል።

የተመድ ቢሮ በሪፖርቱ፣ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተፈናቃዮች በመጠለያዎች እንደሚገኙ ገልጦ ነበር። ኮሚሽኑ፣ ከጥቂት ወራት በኋላ ሌላ ቆጠራ ሲደረግ የተፈናቃዮች ቁጥር መቀነሱ እንደማይቀርም ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትግራይ የታጠቁ ኃይሎችና የውጭ ዜጎች ከሚሳተፉበት የወርቅ ሕገወጥ ቁፋሮና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ከሚያዝያ ወዲህ ብቻ ከ20 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ በምርመራ ማረጋገጡን ሪፖርተር ዘግቧል።

በተለይ እንዳባጉና ወረዳ የሚገኘው የትግራይ ጀኔራሎች የሚቆጣጠሩት "ራህዋ" የወርቅ ማውጫ ከፍተኛ ሕገወጥ የወርቅ ቁፋሮና ኮንትሮባንድ እንደሚካሄድበትና ተዋናዮቹ የቀድሞ የሕወሃት ተዋጊዎች፣ ወጣቶች፣ ስደተኞችና ቻይናዊያን እንደኾኑ ዘገባው ጠቅሷል።

ዘገባው፣ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በ"ሒንጻት" የወርቅ ማውጫ ከኹለት ወራት በፊት በቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎችና በጥበቃዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 22 ሰዎች እንደሞቱ መስማቱን ገልጧል።

ሕገወጡ ወርቅ ወደ አዲስ አበባ፣ አሥመራ፣ ሐርጌሳ፣ ናይሮቢ እና ካምፓላ እንደሚሸጥና ከዚያም መዳረሻው ዱባይ እንደኾነ ምንጮች ስለመናገራቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

@sheger_press
@sheger_press
የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ዶናልድ ትራምፕ ከሆስፒታል ወጡ።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት በኒውጀርሲ ወደሚገኘው የጎልፍ ክለባቸው ማቅናታቸውን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

በፔንሲልቫኒያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ትራምፕ ቀኝ ጆሯቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ፊታቸው በደም ተሸፍኖ ታይቷል።

ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራውን ያደረገው ግለሰብ በአሜሪካ ሚስጢራዊ የደህንነት ባለሙያዎች ወዲያውኑ መገደሉም ተገልጾ ነበር።

የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ከጥቂት ስአት በፊት ባወጣው መግለጫ ትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ቶማስ ማቲው የተባለ የ20 አመት ወጣት ነው ብሏል።

ማቲው ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆኖ ወደ ትራምፕ እና የምርጫ ቅስቀሳው ታዳሚዎች ደጋግሞ ሲተኩስ ሚስጢራዊ ጠባቂዎቹ በፍጥነት ሊያስቆሙት ያለመቻላቸው ጉዳት አነጋጋሪ ሆኗል።(አልአይን)

@ethio_mereja_news
Internet‼️

ከ330 ቀናት እገዳ በኋላ ዛሬ ከንጋት 12:00 ጀምሮ ኢንተርኔት የተለቀቀላቸው የአማራ ክልል ከተሞች
👉ደሴ
👉ኮምቦልቻ
👉ከሚሴ
👉እንጅባራ
👉ፍኖተ ሰላም
👉ቡሬ
👉ባህር ዳር
👉ደብረ ማርቆስ
👉ደጀን
👉 ጎንደር
👉ደብረ ታቦር
👉ሁመራ
👉ገንደውሃ
👉ደብረ ብርሃን
👉ወልዲያ
👉ባቲ
👉ከሰቆጣ ናቸው።
(wasu)

@ethio_mereja_news
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ አሜሪካ መግባቱ ተሰማ

እውቁ ተዋናይ አማኑኤል ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ወደ እስራኤል እየሄደ በፀጥታ አካላት ተይዞ በአዲስ አበባ በእስር መቆየቱ ይታወሳል ።

አርቲስቱ አሁን ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ አሜሪካ ማቅናቱን ከወዳጁ ያሬድ ሹመቴ ፅሁፍ ያመላክታል።

@ethio_mereja_news
አርቲስቱ ታመመ‼️

ተወዳጁና ተጫዋቹ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በፀና ታሞ በህንድ Rela ሆስፒታል ይገኛል

ፈጣሪ በምህረት እጁ ይዳብስህ ነፂ🙏🙏

አርቲስት እና የማስታወቂያ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ለሕክምና ሕንድ ሃገር በሚገኘው Rela Hospital እንደሚገኝ ከቅርብ ወዳጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

በሰላም_ተመለስልን
(ኪንኪንግ ኪያ)

@ethio_mereja_news
መልካም ዜና‼️

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ!!

ተዋናይ፣ ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢው ነፃነት ወርቅነህ ለህክምና ወደ ሀገረ ህንድ መሄዱን የሚገልጽ ማስታወሻ በግል የፌስ ቡክ ገፁ ማጋራቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎች ለአርቲስቱ መልካም ምኞታቸውን ሲገልፁ ነበር።

ገሚሶቹ ደግሞ አርቲስቱ ላይ ያጋጠመው የጤና እክል የከፋ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ጭምር ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል።

ያም ሆኖ ግን አርቲስቱ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተጨማሪም መልካም ምኞታቸውን ለተመኙለት ምስጋናውን በማቅረብ በጥቂት ቀናት ውስጥ የህክምና ክትትሉን አገባዶ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለስ ተናግሯል።

አርቲስቱ በፌስ ቡክ ገፁ ያጋራውን መልዕክት የዝግጅት ክፍላችን ከመረጃው ጋር አያይዞታል፣ ሸገር ፕረስ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ወደ ቀደመ ጤንነቱ እንዲመለስ ይመኛል።

@sheger_press
@sheger_press
በሲም ካርዳችን ወንጀል ከሚሰሩና ከሚዘርፉ አጭበርባሪዎች ራሳችን እንዴት እንጠብቅ?

የሰዎችን የስልክ ቁጥር የራስ በማስመሰል የሚሰሩ የማጭበርበር ወንጀሎች መበራከታቸው ተነግሯል።

ይህን ስራ የሚሰሩት አጭበርባሪዎች ወደ ቴሌኮም ኩባንያ በመደወል ስልካቸው እንደተሰረቀ ወይም እንደተበላሸ በመንገር የሰዎችን ስልክ ቁጥርን ወደራሳቸው በማዞር ነው ገንዘብ እና ግላዊ ሚስጥሮችን የሚመነትፉት።

የስልክ ቁጥሩ ባለቤት ስልኩ እጁ ላይ እያለ የሚደወሉ ስልኮች እና መልዕክቶች በአጭበርባሪዎቹ እጅ የሚገባ ሲሆን ቀጥሎም የባንክ እና ዲጂታል መገበያያ መተግበርያ የይለፍ ቃሎችን በመቀየር አጭበርባሪዎቹ ያሻቸውን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

Via:alain
@ethio_mereja_news
2024/11/05 23:11:07
Back to Top
HTML Embed Code: