Telegram Web Link
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ነገ ግምገማ ሊያካሂድ ነው
ብልፅግና ፓርቲ በአመራሩና አባላቱ ላይ ምንም አይነት ግምገማ አካሂዶ የማያውቅ ሲሆን ነገ ጀምሮ ለግምገማ ስብሰባ ሊቀመጥ መሆኑ ተሰምቷል።

ፓርቲው በመላ ሀገሪቱ ያሉ ግጭቶችን ወጥቶ ወደ ሰላምና ልማት ለመመለስ ግምገማው ይጠቅመዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ብልፅግና በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ አመራሮቹን ከስልጣን የሚያወርድና የሚያወጣ ቢሆንም ምንም አይነት ግምገማ ግን አድርጎ በህግም ሲጠቅ አይታወቅም እየተባለ ይተቻል ።

ፓርቲው በቀጣይ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ስራ አስፈፃሚውን መገምገም ግዴታ ሆኖበታል።

ፓርቲዎ በከፍተኛ ሙስና የደለቡ ንፁሃንን በማሰርና በማሰቃየት በመግደል ስራ የተሰማሩ የፌዴራል ፓሊስና መሰል ተቋማት አመራሮችን ፈትሾ ተጠያቂ ለማድረግ ሊወስን ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🔈 #የመምህራንድምጽ

" አይደለም ያለ ደመወዝ በደመወዝም እንኳን ኑሮን አልቻልነውም ፤ ደመወዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል " -  መምህራን
 
ከየካቲት ወር 2016 ጀምሮ #እየተቆራረጠ 50% ፣ 30% እየተከፈለ ቆይቶ እስከ የሰኔ ወር ሳይጨምር ውዝፍ ደመወዝ ከ70 እስከ 120% አልተከፈለንም ያሉ በጎፋ ዞን የአይዳ ፣ ገዜ ጎፋ እና ደምባ ጎፋ ወረዳ መምህራን ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ያለደሞዝ አይደለም በደሞዝም ኑሮን አልቻልነዉም " የሚሉት መምህራኑ " ስቃያችን መች ነዉ የሚያበቃው ? " ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር፥ " የመምህራኑን ድምጽ በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ሳሳዉቅ ቆይቻለሁ " ብሏል።

መምህራኑም አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው እንደነበርም አስረድቷል።

ነገር ግን የዞኑ አስተዳደር እና የትምህርት መምሪያው ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠቱ መምህራኑ የአመራሩን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሰምኑ እነዚህ መምህራን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሠልፍ ለመጠየቅ ሲሞክሩ  የዞኑ መምህራን ማህበር ከአመራሩ ጋር ውይይት እያደረገ በመሆኑ ሠልፍ እንዳይወጡና በትዕግስት እንዲጠብቁ በማድረግ መመለሱን ማህበሩን አሳውቆናል።

ይሁና መምህራኑ ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ጥያቄ ለማቅረብ ወደተለያዩ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች መሄዳቸውና በዛም " በዚህ ደረጃ መቀጠል አንችልም ደሞዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል !! " በማለት ድምጻቸዉን ማሰማታቸዉ ተገልጿል።

እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ካሁን በፊትም በሌሎች የክልሉ ዞኖች ውስጥም መስተዋላቸውን አንስተን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዉ ዶክተር ታምራት ይገዙ ፤ "  ችግሩን እንደ ክልል ከየካቲት ወር ጀምሮ መቅረፍ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመምህራንን ደሞዝ በተመለከተ አሰራሩ ዲሴንትራላይዝ ተደርጎ ለየዞኖቹ መሰጠቱን የገለጹት ኃላፊዉ " እኛ ቴክኒካል ድጋፍ እያደረግን ብቻ ነው ያለው " በማለት የደመወዝ ጉዳይ ለነሱ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

" ችግሩ በዚህ ደረጃ ከተስተዋለ ግን ገምግመን ድጋፍ የምንሰጥ ይሆናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።(tikvahethiopia)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ባካሄድነው ጥናት 90 በመቶ ተማሪ ኮራጅ መሆኑን ደርሰንበታል"-አለማየሁ ተ/ማሪያም(ዶ/ር)‼️

በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ተናገረዋል፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መል የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡

ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡

ተመራማሪው፤ ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡
በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

@ethio_mereja_news
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆባይደን በትራምፕ ላይ የተሞከረዉን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የፖለቲካዉ ውጥት እንዲቀንስ ጥሪ አቀረቡ ፡፡

ፖለቲካ በፍፁም የዉጊያ  ሜዳ መሆን የለበትም ፈጣሪ የግድያ አዉድማን አጥብቆ ይከላከላል ሲሉ ነዉ  ጆባይደን ጥሪ ያቀረቡት ፡፡

በቅዳሜው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ትራምፕ  የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኃላ  አሜሪካውያን “በአንድነት እንዲቆሙ” ጠይቀዋል።

ባይደን ሀገሪቱ ወዴት እያመራች እንደሆነ እና ማን ይመራታል በሚለው ላይ አለመግባባት ቢኖርም ፖለቲካ "የሰላማዊ የውይይት መድረክ" መሆን እንዳለበት ደጋግመው አሳስበዋል።

የእኛ እምነት የቱንም ያህል ጠንካራ ቢሆን ወደ ሁከት መግባት የለብንም ሲሉ አክለዋል፡፡

ለጥቃቱ ሪፐብሊካኖች ጣታቸዉን በዲሞክራቲኮች ላይ እየቀሰሩ ይገኛል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ምንጭ ኢትዬ ኤፍ ኤም


@ethio_mereja_news
ለጥንቃቄ‼️

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ ማዕከል ከሚደርሱ የወንጀል ጥቆማዎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው አጭበርባሪዎች ከባንክ የተደወለ በማስመሰል ‘'የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን እናስተካክላለን’' በሚል እና ሌሎች አሳሳች መልዕክቶችን በመጠቀም በባንክ ደንበኞች ሂሳብ ላይ የሚፈፀም ስርቆት መሆኑን ፖሊስ በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

በባንኮች አሠራር መሰረት ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል ሳይሄዱ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት እንደለለ ባንኮች ለፖሊስ አሳውቀዋል።

በመሆኑም የባንክ ደንበኞች በስልክ የሚደርሱ ማናቸውንም ዓይነት ጥያቄዎች እንዳያስተናግዱ እና ከአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም መሰል የማጭበርበር ድርጊቶች ሲያጋጥሙ የተደወለበትን ስልክ ቁጥር በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) የፎቶ፣ የቪዲዮ እና የፅሁፍ መረጃ በመላክ ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ጥቆማ እንድትሰጡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአዲሱ በጀት ዓመት የ230 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለከተማዋ ምክር ቤት ማቅረቡን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ረቂቅ በጀቱ፣ የከተማዋ አስተዳደር ተጨማሪውን በጀት ጨምሮ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተጠቀመው አጠቃላይ በጀት የ68 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ጭማሪ እንዳለው ከአስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።

ከአዲሱ ረቂቅ በጀት 62 በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የካፒታል ወጪው እንደኾነና 38 በመቶው ደሞ ለመደበኛ ወጪዎች እንደተመደበ ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼️

በድሬዳዋ አሥተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ ሌሊት 6፡30 ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ድሬዳዋ አሥተዳደር ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ “ዶልፊን” የሚባለው ሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መሥመር ይጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ማመላለሻ “ሲኖትራክ” ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱው  ነው፡፡

የድሬ መንገድ ጠመዝማዛ ነው ደንገጎ አዳጋች ነው ከርቭ ላይ የሰው መስመር ይዘን ከማሽከርከር እንቆጠብ
ለሟቾች ነፍስ ይማር

@ethio_mereja_news
ለማንኛውም ማስታወቂያው ተነስቷል👏

"ካልጠጡ አይንዱ" በማለት ተለጥፎ የነበረው በቴሌ አርማ ላይ የተሰራው ማስታወቂያ ዛሬ ተነስቷል። ማስታወቂያው የተለጠፈው ለጀበና ቡና ቢሆንም አመላካች ነገር ስላልነበረው ዛሬ ቴሌ አስነስቶታል‼️

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ማንኛውም የመንግስት አመራር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ንግድ እና መስል ስራዎችን መስራት የሚከለክል ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን የፌደራል የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

የመንግስት አመራሮች ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከተለዩ ዘርፎች ውስጥ መሆናቸው የሚናገሩት የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ በህዝብ ሃብት ላይ ውሳኔን የሚያሳልፉ አካላት የመንግስትና የህዝብን ስራ ብቻ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ለከፍተኛ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭት መከላከል እና የሥነ-ምግባር ደንብ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክርቤት መላኩን የሚናገሩት ሥራ አስፈፃሚው፤ አመራሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን ሲሰሩ የጥቅም ግጭቶች እንደሚከሰቱ እና አግባብ ባልሆነ መንገድ የህዝብና የመንግስት ሃብትንም ሊመዘብሩ ስለሚችሉ ያንን ለመከላከል ያለመ ረቂቅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የረቂቅ ደንቡ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ የሚኒስትሮች ምክርቤት ቶሎ ምልሽ ሊሰጥበት እንደሚገባ የተናገሩት ሥራ አስፈፃሚው ደንቡ ከፀደቀ ኮሚሽኑም ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ስራን እየሰሩ ባሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የምርመራ ስራን እንደሚጀምር አክለው ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እናት እና ልጅ የ12ኛ ክፍል ፈተና አብረው እየወሰዱ ነው👏

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርታቸውን አብረው ሲከታተሉ የነበሩት እናት እና ልጅ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በጥሩ ውጤት ለማለፍ በጋራ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡

እናት ወ/ሮ ፍሬህይወት ኃይሉ የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ልጇን በመውለና በማኅበራዊ ጫና ትምህርቷን አቋርጣ ነበር። በሒደት ያቋረጠችውን ትምህርት በመቀጠል፣ ከልጇ ተማሪ ሰብሪና ታጅር ጋር ትምህርቷን በመከታተል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በጥሩ ውጤት ለማጠናቀቅ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ገልፃለች።

እናት እና ልጅ እየተደጋገፉ ልጅ ቀን እናት በማታ ትምህርታቸውን እየተማሩ በመደጋገፍ ለፈተናው ሲዘጋጁ እንደነበር ወ/ሮ ፍሬህይወት ጠቁመው፤ ባለቤታቸውም ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ድጋፍ ሲያደርግላቸው እንደነበረ ተናግራለች።

እናት እና ልጅ ፈተናቸውን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ሲሆን፤ ጥሩ ውጤት በማምጣት በቀጣይም አብረው ትምህርታቸውን ለመማር ማቀዳቸውን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ገልፀዋል።

@ethio_mereja_news
ካጋሜ በ99 በመቶ ድምጽ ለአራተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሁለት ዕጩዎች ብቻ ተፎካካሪያቸው ሆነው እንዲቀርቡ በተደረገበት ምርጫ ከፊል ውጤት ከመራጩ ሕዝብ 99 ነጥብ 15 በመቶ የሆነ ድምጽ በማግኘት ያችን አገር ለአራተኛ የሥልጣን ዘመን ለመምራት እየተሰናዱ ነው። ትንሽቱን አፍሪቃዊት ሃገር ለሦስት አስርት ዓመታት በጠንካራ ክንድ በፕሬዚዳንትነት ያስተዳደሩት ካጋሜ በትላንቱ ምርጫ የማሸነፋቸው እጣ ያልተጠበቀ አልነበረም።

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በራሳቸውን ገንዘብ ለመገበያየት ተስማምተዋል ተባለ!

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ለግብይት የራሳቸውን ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ብሔራዊ ባንክ ገዢ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ መፈረማቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በዚህም በሁለቱ ሀገራት ለሚደረግ ግብይት የራሳቸውን ገንዘብ ማለትም ድርሃምና ብር ለመጠቀም ከስምምነት የደረሱ ሲሆን ሁለቱ አካላት ለተግባራዊነቱ ምቹ መደላድል ለመፍጠር ጥረት እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የኢትዮጵያ አንዷ የንግድ አጋርና የውጪ ኢንቨስትመንት ምንጭ መሆኗን ገልጸው ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርገዋል ብለዋል።

በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረት ቀጣይነት ያለው ልማትና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ብሔራዊ ባንክ ገዥ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ በበኩላቸው ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸውን እንደሚያሳይ አመላክተዋል።

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

እንደሚታወቀው ቴሌግራም ብዙዎችን ባለገቢ እያደረገ ይገኛል።

ታድያ አሁን ላይ ታፕ ታፕ ስለሚደረጉት Hamster TapSwap BLUM እና ሌሎችም መረጃዎች ።

በዝርዝር ለማግኘት
ይህን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
...አንዳንድ ሪፖርቶች ጦር መሳሪያው የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የገዛው ስለመሆኑ እየገለጹ ነው።....

የሱማሊያ የጎሳ ሚሊሻዎች ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረና ከኢትዮጵያ የተነሳ ነው በተባለ አንድ ከባድ ካሚዮን ላይ ትናንት በፈጸሙት የደፈጣ ጥቃት በርካታ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ዘርፈዋል።

ጋልሙዱግ ፌደራል ግዛት ውስጥ አቡድዋቅ ከተባለች አነስተኛ ከተማ አቅራቢያ የመሳሪያ ዝርፊያው በተፈጸመበት ወቅት በጎሳ ታጣቂዎቹና በካሚዮኑ አጃቢ ጸጥታ ኃይሎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ፣ በትንሹ አምስት ሰዎች እንደተገደሉ ተሰምቷል።

ካሚዮኑ መትረየሶችን፣ ጸረ-አውሮፕላን መሳሪያዎችንና ቦምቦችን ጭኖ ነበር ተብሏል። የማዕከላዊ ሱማሊያ የጎሳ ታጣቂዎች ለዓመታት አልሸባብን በመውጋት የታወቁ ናቸው።

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት፣ በሱማሊያ ላይ ለ30 ዓመታት ጥሎት የቆየውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ባለፈው ታኅሳስ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ ይታወሳል።

አንዳንድ ሪፖርቶች ጦር መሳሪያው የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት የገዛው ስለመሆኑ እየገለጹ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ታከለ ኡማን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው ሹመዋል።

ታከለ የተሾሙት፣ ከኹለት ዓመታት በላይ አክሲዮን ማኅበሩን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አብዲ ዘነበ በቅርቡ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ነው።

አብዲ ከሃላፊነት ከተነሱ ወዲህ፣ የአክሲዮን ማኅበሩ የቴክኒክ ሃላፊ ዳንኤል ኃ/ሚካዔል በተጠባባቂነት ተሰይመው ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
ህውሀት‼️

#ህወሓት በ50 አመታት ታሪኬ አጋጥሞኝ የማያውቅ ፈተና ውስጥ ነኝ አለ፣ በቀጣይ ሳምንታት የፓርቲ ጉባኤየን ለማካሄድ ወስኛለሁ ብሏል

በሰሞኑ የፓርቲው ስብሰባ ወቅት ስብሰባ ረግጠው የወጡ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር አሉ ተብሏል

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት #ትግራይ (ህወሓት) ለ11 ቀናት ሳካሂደው የነበረው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ስብሰባ እና ግምገማ አጠናቅቂያለሁ ሲል ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሳካሂደው የሰነበትኩት በፓርቲው አመራራ ላይ ያተኮረ የ11 ቀናት ስብሰባ እና ግምገማ “ፓርቲውን ከመበታተን ሊታደግ የሚችል ጉባኤ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታዎችን የፈጠረ ነው” ብሏል።

በያዝነው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ባሉት ቀጣይ ጥቂት ሳምንታት የፓርቲ ጉባኤ ይካሄዳል ሲል የገለጸው የህወሓት መግለጫ “ብሔራዊ ህልውናችንን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተልኳችን ነው” ሲል አስታውቋል።

አሁን “በፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ያጋጠመው ችግር ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ባሉት 50 አመታት አጋጥሞኝ አያውቅም” ያለው ህወሓት ዋነኛ የለየኋቸው ችግሮቼ “ቡድንተኝነት፣ ፀረ ዲሞክራሲያዊነት፣ ጎጠኝነት እና ሙስና ወደ ላቀ ደረጃ አድጎ ፓርቲውን አላፈናፍን ከማለት ባለፈ የመፈራረስ አደጋ ደቅነውብኝ ነበር” ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው”የሚዲያ አዋርድ”የየዘርፉ ምርጥ አስሮች (10) ይፋ ሆኑ
በታጩበት ዘርፍ ከፍተኛ የዳኞች እና የህዝብ ድምፅ ያገኙ የሚዲያ ባለሞያዎች(ጋዜጠኞች) ሁለተኛ ዙርን ተቀላቅለዋል።
በዚህኛዉም ዙር እጩዎች በዳኞች እና በህዝብ ድምፅ የሚመዘኑ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ያገኙት ነጥብ በዚህ ዙር አያገለግልም ፣ ሁሉም እጩዎች ነጥባቸዉ ከዜሮ የሚጀምር ይሆናል
በመጀመሪያ ዙር ላይ ተካተዉ ከነበሩ ዘርፎች መካከል በጥቂቶቹ ላይ በቀጥታ ሚዲያዉን በበላይነት ከሚከታተሉት ተቋማት ጋር በመነጋገር የተወሰኑ ማስተካከያዎችን አድርገናል።
የምርጥ 10 እጩዎች የህዝብ ድምፅ መስጠት ሂደቱ እስከ ሀምሌ 16/2016 ዓ.ም የሚቆይ
በራዲዮ ወንዶች ዜና አንባቢ ተወዳጁን ሄኖክ ወ/ገብርኤልን በመምረጥ ይሳተፉ

ለሁሉም ተወዳዳሪዎች መልካም እድል እንመኛለን
https://ethio-mediaaward.com/
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

መቼስ እንደ ሀገር ነዳጅ ማቅረብ እያዳገተን እንደሆነ እየሰማን ነው። ተጨማሪ መንገዶችን የመስራት አቅማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሟጠጠ እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው። የትራፊክ ማኔጅመንት መስርያ ቤቱ ተቋቋመ እንጂ የትራፊክ ስርዓቱን ለማሳለጥ የሚያስችል አስተማማኝ እውቀትም ሆነ አቅም መፍጠር እንዳልተቻለም እያየን ነው ።

በዚህ ላይ የግል ተሽከርካሪ ፍላጎት ጫፉ አልተነካም። ከ 7 እስከ 8 ሚሊየን ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 350 ሺ የግል ተሽከርካሪ ማለት ኢሚንት ነው። ፍላጎቱ ገና በሚሊየኖች ያድጋል። እንደ መርህ ለዚህ ፍላጎትና እድገት የሚመጥን ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ከማመንጨት ይልቅ እቀባ፣ እገዳ ክልከላና ፈረቃ መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል።

መስርያ ቤት ተቋቁሞ፣ አማራጭ ተፈትሾና እውቀት ተቀምሮ መንገድ በሌለበትና የሕዝብ ትራንስፖርት አስማት በሆነበት ከተማ መፍትሔው በግል ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ላይ ማዕቀብ መጣልና ሌላ ጭንቅንቅ መፍጠር ከሆነ ትርጉም ያለው መፍትሔ ማመንጨት እስኪቻል ትምህርት ቤት፣ የስራ ቀን፣ ከቦታ ቦታ መዘዋወር፣ ተንቀሳቅሶ መስራት፣ በዓል ማክበር፣ ፍጆታን መሸመት፣ ርቆ መጓጓዝና መዝናናት በጥቅሉ ኑሮአችን በፈረቃ ቢደረግ መልካም ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሰሜን ወሎ ውስጥ ሲቪሎች መገደላቸው ተገለፀ።

በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ውድመን በተባለ ስፍራ፣ በመንግስት ሀይልች እና በፋኖ ሀይሎዎች መካከል ባለፈው ሳምንት ዐርብ መካሔዱ በተገለጸው የተኩስ ልውውጥ፣ ስድስት ያልታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን፣ የሟች ቤተሰብ እና የአካባቢው ነዋሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ከሟቾቹ ውስጥ አምስቱ የቅርብ ዝምድና እንዳላቸው አስተያየት ሰጭዎቹ ጠቅሰው፣ ከእነርሱም ሦስቱ አባት እና ልጅ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡

የጉባላፍቶ ወረዳ አስተዳደር፣ የደረሰውን ጉዳት አምኖ መጠኑን ግን በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ ሻለቃ ያሬድ አባተ፣ “ከመንግሥት በተቃራኒ የቆሙ” ሲሉ የጠሯቸው አካላት፣ በሕዝቡ መሀል ሳሉ የተኩስ ልውውጥ ስለሚደረግ ባልታጠቁ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/06 02:01:53
Back to Top
HTML Embed Code: