Telegram Web Link
ተማሪዎች ሚልየን ብሮች ተጠየቀባቸው

ባለፈው ሳምንት ከ100 በላይ ተማሪዎችንና መንገደኞችን ያገቱት ታጣቂዎች ላንድ ታጋች 1 ሚሊዮን ብር እየጠየቁ እንደሚገኙ መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል። የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አዝመራው ዘገዬ፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መታገታቸውን እንዳረጋገጡና ነገር ግን ዝርዝር መረጃ ከመስጠት እንደተቆጠቡ ዘገባው አመልክቷል።

ከእገታው ያመለጠ አንድ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ ታጣቂዎቹ ኦሮሚኛ ቋንቋ ይናገሩ እንደነበርና በጸጉራቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች እንደሚመስሉ ተናግሯል ተብሏል። ሮይተርስ፣ ፌደራል መንግሥቱ፣ የክልሉ መንግሥት እና የአማጺው ቡድን ቃል አቀባዮች በጉዳዩ ዙሪያ ላነሳው ጥያቄ ምላሽ እንዳልሰጡት ገልጧል።(ዋዜማ)

@sheger_press
call 📞0914280819
ውዴ የባህል መድሀኒት የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
1ለገበያ
2 ለመስተፍቀር
3 ለመፍትሄ ሀብት
4 ለበረከት
5 ለጥይት መከላከያ
7 የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
8 ራዕይ የሚያሳይ
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ስራይ
14 ጋኔን ለያዘው ሰው
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለቁራኛ
17 ለአምፅኦ
18 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
21 ለዓይነ ጥላ
22 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
23 ለሁሉ መስተፋቅር
24 ጸሎተ ዕለታት
25 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
26 ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
📞📞
0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን
የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ደመወዛቸውን 40 በመቶ እንደሚቀንሱ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነት እርምጃ የወሰዱት ተጠያቂ አስተዳደር በመፍጠር አርዓያ ለመሆን እና ከላይቤሪያውን ጋር ያላቸውም አጋርነት ለማሳየት እንደሆነም ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

በኑሮ ውድነት ምሬት የገባቸው ላይቤሪያውያን አንደኛው ቅሬታ የሚያነሱት ጉዳይ የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ነው።

በላይቤሪያ ውስጥ በአማካኝ ከአምስቱ አንዱ ሰው ከ2 ዶላር ባነሰ ዕለታዊ ገቢ ኑሯቸውን ለመግፋት ተገደዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከጥቂት ወራት በፊት ዓመታዊ ደመወዛቸው 13 ሺህ 400 ዶላር እንደሆነ ገልጸው አሁን ባቀረቡት 40 በመቶ ቅነሳ ወደ 8ሺህ ዶላር ያደርሰዋል።

ከሳቸው በፊት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ደመወዛቸውን 25 በመቶ ቀንሰው ነበር ሲል ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል።

አንዳንዶች የፕሬዚዳንቱን እርምጃ ቢያደንቁም ሌሎች ግን እንደ ዕለታዊ አበል እና የህክምና ሽፋን ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ የጠቀሱ በበኩላቸው ይህ በእውነት መስዋዕትነት ነው ወይ ሲሉም ይጠይቃሉ።

የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የዚህ ዓመት በጀት ወደ 3 ሚሊዮን ይጠጋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም)
በአዲስ አበባ ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

የንግድ ሥርዓቶችን ተላልፈው በተገኙ ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመዲናዋ በሚገኙ ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ተደርጓል።

በዚህም ልዩ ልዩ የንግድ ሥርዓቶችን ተላልፈው በተገኙ ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

ከዚህ ውስጥ 21 ሺህ የንግድ ተቋማት እንዲታሸጉ፣ ምርታቸው ከገበያ እንዲሰበሰብና ሌሎች ተመሳሳይ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ኢዜአ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን አማራጭ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ሊያረጋግጡ የሚችሉ መሰረተ ልማቶችን በጋራ ለመገንባት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ሃገራቱ ባደረጉት ውይይት የድንበር አካባቢ ደህንነት እና የሁለትዮሽ ንግድ ለማሻሻል እና አማራጭ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ተስማምተዋል ነው የተባለው።

ስምምነቱ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን የማጠናከርንና በኢንቨስትመንት መስክ አብሮ መስራትን የሚያካትት መሆኑን ሱዳን ትሪቢዩን አስነብቧል።

ባለፈው ወር የደቡብ ሱዳን ምክር ቤት ለኢትዮ ደቡብ ሱዳን የፍጥነት መንገድ ግንባታ 778 ሚሊየን ዶላር ማፅደቁን ዘገባው አስታውሷል።

የመንገዱ መገንባት ደቡብ ሱዳን ነዳጇን ወደ ጅቡቲ ወደብ ለማድረስ እንደሚረዳትም ዘገባው አመላክቷል።

@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ከልብ እንደምትሠራ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ዐቢይ፣ "የወንድም የሱዳን ሕዝብ ችግር የእኛም ችግር፣ ሰላማቸውም ሰላማችን በመኾኑ፣ ለሱዳን ሕዝብ እፎይታና የብልጽግና ጉዞ ዛሬም እንደትናንቱ ከልባችን እንሠራለን" ብለዋል።

ዐቢይ ከሱዳን ወታደራዊ መሪ ጀኔራል ቡርሃን ጋር በዝግ ባካሄዱት ውይይት፣ ጀኔራል ቡርሃን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እየፈጸመ ነው ያሉትን "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል" ለዐቢይ አብራርተውላቸዋል።

ካርቱም በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ቁጥጥር ሥር ከገባች ጀምሮ፣ ሰሜናዊቷ ፖርት ሱዳን የአገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት፣ የዲፕሎማቶች እና የዓለማቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ኾናለች።

@ethio_mereja_news
ዘንባባ መግጨት ከ150ሺህ እስከ 300ሺ ብር ያስቀጣል

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማት የተሰሩ ስራዎችን በአግባቡ ያልተጠቀሙ እና ጉዳት ያደረሱ አካላት መቅጣት ተጀምሯል። በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል::

ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀም እና በመንከባከብ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር አሳስበዋል።

@ethio_mereja_news
ታግተው ከነበሩት 167 ተማሪዎች ውስጥ 160ዎች መለቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ

ባለፈው ሳምንት ከዳባርቅ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደመኖሪያ ቤቶች ሲመለሱ ከነበሩት ‹‹ 167 ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ መለቀቃቸውን ›› የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ለአሻም ቲቪ ተናግሯል።

‹‹ ተማሪዎቹ ከታገቱበት የተለቀቁት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ መሆኑንም ›› ኃላፊው አክለዋል፡፡

ተማሪዎቹ የታገቱት በኦነግ ሸኔ መሆኑን የተናገሩት ኃይሉ አዱኛ ‹‹ ቀሪዎቹን ተማሪዎቹን ለማስፈታት የፀጥታ ኃይሎች ጥረት ›› እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል ሲል አሻም ዘግበዋል።

@ethio_mereja_news
በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

ከዛሬ ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጎል። በዚህም መሰረት

👉 ቤንዚን …………ብር 82.60 በሊትር

👉 ነጭ ናፍጣ..... ብር 83.74 በሊትር

👉 ኬሮሲን ……….. ብር 83.74 በሊትር

👉 የአውሮፕላን ነዳጅ ……... ብር 70.83 በሊትር

👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ……… ብር 65.48 በሊትር

👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ……… ብር 64.22 በሊትር ሆኗል።

የአለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሠረት ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ ላይ የሚውለው የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማሰተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
"በተደረገ ጥብቅ ኦፕሬሽን ከ167 ታጋች ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ ተለቀዋል"--- የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ

"እውነት ይሆን?" ብዬ የታጋቾች ቤተሰቦችን፣ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወንጌላዊያን ህብረትን እና የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንትን ማምሻውን ጠየቅኩ። ምላሹ ይህን ይመስላል:

"አሁንም ልጆቻችን በእገታ ስር ናቸው፣ የማስለቀቂያ ገንዘብ ከህዝብ እየለመንን ነው። በዚህ ግዜ እንዲህ አይነት መረጃ ማውጣት የጭካኔ ስራ ነው"--- የታጋቾች ቤተሰቦች

"ታግተው ያሉ በርካታ ተማሪ አልተለቀቁም፣ ተለቀቁ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከየት እንደመጣ አናውቅም። እንደውም አሁን ተማሪዎቹን ወደ ወለጋ እንደወሰዷቸው እየሰማን ነው"--- የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወንጌላዊያን ህብረት

"አንዴ መረጃ ሰጥቻለሁ፣ እኔ ጋር ለምን ትደውላላችሁ?"--- የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ

Via EliasMeseret

@Merkato_media
ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል ባለሃብቶችንና የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ይጎዳል በማለት እንደተቃወመ ሪፖርተር ዘግቧል።

ኮሚሽኑ ለትራንስፖርት ሚንስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ የሕግ ድንጋጌ ሳይኖርና ግልጽ ሕግ ሳይወጣለት ከበላይ አካል በተሰጠ ትዕዛዝ ብቻ ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ማገድ አግባብነት የለውም በማለት ቅሬታውን እንደገለጠ ዘገባው ጠቅሷል።

ውሳኔው፣ በግብርና፣ በግብርና ምርት ማቀነባበር፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግና ግንባታ በተሠማሩ ባለሃብቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሯል ተብሏል። ኮሚሽኑ፣ ላንዳንድ ኢንቨስትመንቶች ከባሕሪያቸው አንጻር በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዲያስገቡ እንዲፈቀድላቸው መጠየቁን ጋዜጣው አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥይት በፔርሙስ‼️
በፔርሙዝ ዉስጥ ተሸሽጎ ሊዘዋወር የነበረ የዲሽቃ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
በቦረና ዞን ነገሌ ከተማ በፔርሙዝ ዉስጥ በመደበቅ ለማዘዋወር የተሞከረ የዲሽቃ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የነገሌ ቦረና  ከተማ አስተዳደር  ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አስቻለዉ ቡልቻ ተናግረዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ ከነገሌ ከተማ ወደ አዶላ ዋዩ ሲጎዝ ነበረበ ኮድ 3 72685 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ በፔርሙዝ እና በጫማ ዉስጥ ተደብቆ ሊዘዋወር የተሞከረ የዲሽቃ ጥይት መያዙን ገልጸዋል።
ፖሊስ የጦር መሳሪያዉን ለማዘዋወር የሞከረዉን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም  የነገሌ ቦረና  ከተማ አስተዳደር  ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አስቻለዉ ቡልቻ ተናግረዋል።

የኮንትሮባንድ እና የህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በየጊዜዉ ስልታቸዉን እየቀያየሩ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸዉም ተመላክቷል።
#ብስራትሬዲዮ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቡርኪናፋሶ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚከለክል ረቂቅ ህግ አወጣች!!

የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚከለክልና በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ ህግ አወጣ።

በኢብራሂም ትራወሬ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክርቤት ሳምንታዊ ስብሰባውን ሲያደርግ በረቂቅ የቤተሰብ ህግ ላይ መክሯል።

በዚህም የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ወደ ስራ እንዲገባ ወስኗል ነው የተባለው። የሀገሪቱ ጊዜያዊ የፍትህ ሚኒስትር ኢዳሶ ሮድሪክ ባያላ፥ “ከዛሬ ጀምሮ ግብረሰዶማዊነትና ተያያዥ ተግባራት የተከለከሉና በወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው” ማለታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።

የሚኒስትሮች ምክርቤት ያጸደቀው ረቂቅ ህግ ወደ ስራ እንዲገባ በፓርላማ መጽደቅና የሀገሪቱ የሽግግር ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራወሬ ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉት ይገባል።

የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ከ2022 ጀምሮ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን በያዙ መሪዎች እየተመራች ነው።(አል ዐይን)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሄራዊ ባንክ ትናንት 19 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው የሰነዶች ጨረታ ማካሄዱን አስታውቋል።

16 ባንኮች በተካፈሉበትና ትርፍ ገንዘብ ከባንኮች ለመሰብሰብ ባለመው የሰነድ ጨረታ፣ የባንኩ ሰነዶች በ15 በመቶ የወለድ ተመን ተሽጠዋል።

ባንኩ፣ ከባንክ ገበያው ትርፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ወይም ተጨማሪ ገንዘብ ለመልቀቅ በወር ኹለት ጊዜ የገንዘብ ፖሊሲ ነክ ጨረታ እንደሚያካሂድ ያስታወቀው ማክሰኞ'ለት አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ባስተዋወቀበት ወቅት ነበር።

ባንኩ፣ በወለድ ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ መከተል ከጀመረ ወዲህ፣ በ15 በመቶ ወለድ የሰነዶች ጨረታ በማውጣት ትርፍ ገንዘብ ሲሰበስብ የትናንቱ የመጀመሪያው ነው።

@sheger_press
@sheger_press
2024/11/06 01:53:53
Back to Top
HTML Embed Code: