Telegram Web Link
"የኑሮ ዉድነቱ ቀንሷል" ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ‼️

የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ በተያዘው በጀት ዓመት የኑሮ ዉድነቱ እንደቀነሰ ተናግረዋል። መንግስት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ በርካታ እቅዶችን ይዞ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሰብል ምርትም አምና እንደሀገር 395 ሚሊዮን ኩንታል ተመርቷል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ዘንድሮ 507 ሚሊዮን ኩንታል መመረቱን ገልጸዋል።ይህንን ዉጤት በርካታ የአለማቀፍ ተቋማት እያደነቁት መሆኑንም ገልጸዋል። የኑሮ ዉድነቱ በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የተከሰተ አለመሆኑንና አለምአቀፋዊ የሆኑ ጫናዎች መኖራቸውንም ለማስረዳት ሞክረዋል።

በዚህ ዓመት ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰው በላይ ስራ አስይዘናል ከእንዚህም ውስጥ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑትን በሃገር ውስጥ ስራ የተቀጠሩ ናቸው፡፡
በውጭ ሃገር 332 ሺሕ ሰው በህጋዊ መንገድ ሰልጥነው ተቀጥረዋል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ታሳሪዎች ምን አሉ ?

" 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ'  ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦

" እስረኛ መፍታት ላይ እኛ እንታማለን ? ' እንዴት እስረኛ ትፈታለህ ? ' ተብለን ስንገመገም እና ስንወቀስ እንዳልነበረ።

ያልፈታነው ጉድ አለ እንዴ ? እስር ቤቱን በሩን ከፍተን ነው የለቀቅነው። በዚህ እንኳን አንታማም።

ከዚህ ፓርላማ የታሰሩት ወንድማችንን በተመለከተ (አቶ ክርስቲያንን ማለታቸው ነው) ሁሉም ተቃዋሚ የሚታሰር ከሆነ ጠያቂዬ (አቶ አበባውን ማለታቸው ነው) ለምን አልታሰሩም ?

ጠያቂዬ ተቀምጠው እየጠየቁ ነው እዚህ።

እርሶን የሚያስቀምጥ እሳቸውን የሚያሳስር ነገር ካለ ልዩነት አለ ማለት ነው። ልዩነቱን ግን እኔ ዳኛ አይደለሁም። ወንጀለኛ ናቸው ፣ ጥፋተኛ ናቸው ልል አልችልም። የፍትሕ ስርዓቱ አይቶ መርምሮ ፈትሾ ፍርድ ይስጥ።

የግል ምኞትህ ያሉኝ እንደሆነ እርሶም እርሳቸውም ከእርሶ ጎን ተቀምጠው ባያቸው ደስታውንም አልችለውም።

በሰላማዊ መንገድ 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ'  ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም።

የግል ጥላቻ የለኝም። የግል መግፋትም የለብኝም።

ህግ ከፈታቸውና ከኛ መካከል ቢሆኑ ደስታውን አልችለውም። ነገር ግን ሁላችንም ማወቅ ያለብን ፦
- የፓርላማ አባል መሆን
- ጋዜጠኛ መሆን
- ሚኒስትር መሆን
- ማዕከላዊ ኮሚቴ መሆን ከወንጀል እና ከጥፋት አይታደገንም። አለማጥፋት ነው።

የኔ ዋስትና አለማጥፋት ነው። ካጠፋው እመጣለሁ ያለመከሰስ መብቴ ይነሳል እጠየቃለሁ።

እዚህ አካባቢ ላይ መቀመጥ ለማንኛውም ጥፋት ዋስትና አድርገው ፤ ዝም ብሎ መንገደኛ ይነሳና ዩትዩብ ከፍቶ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው እንደዛ ትክክል አይደለም።

ጋዜጠኛም ህግ አለው ፣ ወታደርም ቢሆን ህግ አለው መጠየቅ አለበት ፣ ሚኒስትርም ህግ አለው።

በዚህ አግባብ ማየት ካልቻልን ስራችንን ቆርጠን ጥለነው በኋላ የማንጠግነው ነገር ይፈጠራል። "#TikvahEthiopia

@sheger_press
" የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ወታደር ዜጎችን በጅምላ አይገድልም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን በወታደራዊ ፍርድ ቤት ስርዓት እስር ቤት እንደሚገቡ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ መከላከያ ከ ' Code of conduct ' ውጭ በማይገባ መንገድ ኦፕሬሽን ሰርታችኋል በሚል በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን እስር ቤት እንዳስገባ አሳውቀዋል።

የጅምላ ግድያን በተመለከተ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ወታደር ዜጎችን በጅምላ አይገድልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በጅምላ ለማሸነፍ ይነሳና ሲሞት ነው በጅምላ ሞትኩኝ የሚለው እንጂ መንግሥት አይገድልም " ሲሉ ገልጸዋል።

@sheger_press
#FactCheck

"6ቱ ጎረቤቶቻችን ተደምረው ሊኖራቸው የማይችለውን GDP አስመዝግበናል"--- ጠ/ሚር አብይ አህመድ በፓርላማ ከተናገሩት

መንግስት ደጋግሞ የሚጠቀምበትን የ IMF ዳታ ስንመለከት የዘንድሮ የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (Gross Domestic Product- GDP) 205 ቢልዮን ዶላር እንደሚሆን መረጃ አስቀምጧል።

የሌሎቹን ስንመለከት የኬንያ GDP 104 ቢልዮን ዶላር፣ የጅቡቲ 4 ቢልዮን ዶላር፣ የሶማልያ 12 ቢልዮን ዶላር፣ የሱዳን 26 ቢልዮን ዶላር፣ የደቡብ ሱዳን 6 ቢልዮን ዶላር ሲሆን ይህ በድምሩ 152 ቢልዮን ዶላር ይሆናል። ስለ ኤርትራ GDP መረጃ እንደሌለው IMF ያስቀምጣል፣ በርካታ ግምቶች ግን 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይጠቁማሉ።

ስለዚህ የስድስቱ ጎረቤት ሀገራቶች GDP ድምር 154 ቢልዮን ዶላር ገደማ ሲሆን ይህም ከኢትዮጵያ 205 ቢልዮን ዶላር GDP ያነሰ መሆኑን መመልከት ይቻላል፣ ስለዚህ በፓርላማ የቀረበው መረጃ ትክክለኛ ነው።

ይህንን እንዲሁም የዜጎችን ኑሮን/የመግዛት አቅም በተሻለ ያሳያል የሚባለውን የነፍስ ወከፍ አመታዊ ገቢን (per capita income) ዝርዝር ለመመልከት ሊንኩን ይከተሉ: https://www.imf.org/external/datamapper/NGDPD@WEO/DZA/ZAF/MAR/NGA/EGY/AFQ

ይህ መረጃ እንዲጣራ ታግ በማድረግ እና በኢንቦክስ ለጠየቃችሁ እነሆ...
Elias Meseret

@ethio_mereja_news
የትግራይ ኃይሎች በቅርብ ወራት መልሰው ከተቆጣጠሯቸው ራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም፣ ዛታ፣ ዋጃ እና ጥሙጋ እስከ ሰኔ 30 እንዲወጡ ፌደራል መንግሥት ማዘዙን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች፡፡

በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ፣ መከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ የትግራይ ታጣቂዎች በቀነ ገደቡ እንዲወጡ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በትዕዛዙ መሠረት፣ ከሰኔ 25 ጀምሮ የትግራይ ኃይሎች ከዋጃ እና ጥሙጋ አንዳንድ አካባቢዎች መውጣት መጀመራቸውንና በአላማጣ ከተማ ግን እስከ ሰኔ 26 ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ዋዜማ ከነዋሪዎች ሰምታለች፡፡

በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፎች የታገዱ ሲኾን፣ የባጃጅ እንቅስቃሴም ከቀኑ 12 ስዓት በኋላ እንዲኹም ከምሽቱ ኹለት ሰዓት ጀምሮ የሰዎች እንቅስቃሴና የምግብ ቤቶችና መዝናኛ ቤቶች አገልግሎት አንዳይኖር ገደብ እንደተጣለ ታውቋል፡፡ (wazema

@sheger_press
በቦታ ርቀት ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በደስታ ቀናቸው መገኘት ያልቻሉ ተመራቂ ተማሪዎች።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። በዛሬ እለት በተካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ይህ ሆነ፣

ቤተሰቦቻቸው በርቀት ምክንያት የልጆቻቸው ምርቃት ላይ መገኘት አልቻሉም፣ ተመራቂዎቹ ደግሞ ከምርቃት በኋላ ከነ ጋወናቸው ስታዲየም ቁጭ ብለው ኳስ እያዩ ነው፣ ተቀይሮ ለመግባት እያሟሟቀ የነበረው አማኑኤል ኤርቦ ተመራቂዎቹን ያያቸዋል የሆነ ነገርም ማድረግ እንዳለበት ያሰበ ይመስላል፣ ተቀይሮ እንደገባ ጎል አስቆጠረ ደስታውን ግን በምርቃታቸው ቀን ወላጆቻቸው ሊገኙ ያልቻሉ ተመራቂዎች ጋር በመሄድ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታውን አብሯቸው ገልጿል። የጎሉንም ማስታወሻ ለተመራቂዎቹ አደረገ።

እኔም ጠጋ ብዬ ስጠይቃቸው ቤተሰቦቻቸው በርቀት ምክንያት ምርቃታቸው ላይ መገኘት ስላልቻሉ ከምርቃት ፕሮግራም በኋላ ጨዋታ በማየት ጊዜያቸውን ለማሳለፍ እንደወሰኑ ነገሩኝ።
ተፃፈ በAku Images
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ለቀጣዩ በጀት ዓመት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት አጽድቋል።

መንግሥት ከበጀቱ 451 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ያህሉን የመደበው ለመደበኛ ወጪዎች እንዲኹም 283 ነጥብ 2 ቢሊዮኑን ለካፒታል ወጪዎች ሲኾን፣ 236 ነጥብ 7 ቢሊዮኑ ደሞ ለክልሎች ድጎማ የተመደበ ነው። ከበጀቱ 139 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የአገሪቱን ዕዳ ለመክፈል ተመድቧል።

በጀቱ ከዘንድሮው ዓመት በጀት በ21 ነጥብ 1 በመቶ ብልጫ አለው።

የ2017 ዓ፣ም በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል በኾነው ከ2016 እስከ 2018 በሚቆየው የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና ከ2017 እስከ 2021 ዓ፣ም የሚቆየውን የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍ ለማስፈጸም የተዘጋጀ ነው።

@sheger_press
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
ከቀያቸው የተፈናቀሉ #ኢትዮጵያውያን ቁጥር 4 ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሚገመት ተገለጸ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እና ገጠራማ አከባቢዎች ተጠልለው የሚገኙ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ባወጣው ሪፖርት አብዘሃኛዎቹ ተፈናቃዮች የሚገኙት በሶስት ክልል ነው ብሏል፤ #በሶማሊያ#ኦሮምያ እና #ትግራይ

አብዘሃኛዎቹ ቀያቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ ያደረጋቸው በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች መሆናቸውንም ቢሮው አመላክቷል።

ቀያቸውን ጥለው ከተፈናቀሉ የሀገሪቱ ዜጎች ውስጥ 56 በመቶ የሚሆኑት ቤታቸውን ጥለው ከወጡ ሶስት አመት ሞልቷቸዋል ሲል የገለጸው ቢሮው 23 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከሁለት እስከ አራት አመት የሆናቸው ናቸው ብሏል፤ 11 በመቶ የሚሆናቸው ደግሞ ከቀያቸው ከተፈናቀሉ አምስት እና ከዚያ በላይ አመታት ማስቆጠራቸውን ጠቁሟል።

ከጥር 2014 ዓ.ም ወዲህ 3 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚሆኑ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ያስታወቀው ማስተባበሪያ ቢሮው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቀያቸውን ጥለው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በሀገሪቱ የተፈናቃዮች ቁጥር 4 ነጥብ 5 ሚሊየን መድረሱን አስታውቋል።

በርካታ ተፈናቃዮች በተለይም ደግሞ ለተራዘመ ግዜ ከቀያቸው ተፈናቅለው የቆዮ ዜጎችን የተወሰነ ድጋፍ ተደርጎላቸው እንዲመለሱ ወይንም ደግሞ አሁን ተጠልለውባቸው በሚገኙባቸው አከባቢዎች ከሚኖሩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ኑሮ መስርተው እንዲኖሩ ማድረግ አለያም ደግሞ ወደ ሌላ አከባቢ እንዲዛወሩ ማድረግ እንደሚቻል ያካሄደውን ጥናት ዋቢ በማድረግ ቢሮው አመላክቷል።(አዲስ )

@sheger_press
አመራሩ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ‼️
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ ከጁመዓ በኋላ ከመስጊድ ሲወጣ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የአዩዘበሀሻ ምንጮች ገልጸዋል።
በዚህ የተነሳ በከሚሴ ከተማ የባጃጅ እንቅስቃሴ ታግዷል ሲሉ ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ተናግረዋል።
#አዩዘሀበሻ

@sheger_press
በኢትዮጵያ “ቀዳሚ” እና “አሳሳቢው” የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርስ ሞት እና የአካል ጉዳት መሆኑን ኢሰመኮ አስታወቀ

በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ከተከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ በቀዳሚነት አሳሳቢ የሆነው፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰው የሞት እና የአካል ጉዳት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። በርካታ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት የተዳረጉት፤ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች በተወሰዱ እርምጃዎች መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

▶️ ብሔራዊው የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ይህን የገለጸው፤ “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ” የዳሰሰ ዓመታዊ ሪፖርት ዛሬ ሰኔ 28፤ 2016 በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

▶️ ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት፤ አሳሳቢ እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ  ጉዳዮችን፣ መልካም እምርታዎችን እና ምክረ ሀሳቦችን የያዘ ነው። 

▶️ በሶስት ክፍሎች የተሰናዳው ባለ 132 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ “ጠቅለል ባለ መልኩ የሚያሳይ” መሆኑን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል። 

▶️ ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ “የተከሰቱ የሁሉም ክስተቶች እና የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ሙሉ ስብስብ” አለመሆኑን አስገንዝበዋል። 

▶️ ዶ/ር ዳንኤል “በሪፖርት ዘመኑ አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ ጉዳዮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው በህይወት የመኖር መብት ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

🔴 ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2024/13525/

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
የኛ ብድርና ቁጠባ ሀላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ለ20 አባላቱ ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ 20 ተሽከርካሪዎችን በብድር አስረከበ።

ተሽከርካሪዎቹ የከተማዋን ገጽታ ሊያጎሉና የትራንስፖርት አገልግሎቱን ከማሳለጥ አንጻር ሚናቸው የማይናቅ መሆኑ ተጥቁሟል።

በ2015 ዓ.ም በአነስተኛ ካፒታል የተመሰረተው የኛ ብድርና ቁጠባ ሀላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ አባላትን በማፍራት ካፒሉን ማሳደግ የቻለ የፋይናንሥ ተቋም ነው።

ተቋሙ ከ47 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ካፒታል በብድር የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ ከፍተኛ አመራሮችና የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም አባላቶቹና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ቁልፍ አስረክቧል።

የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በወቅቱ ንግግራቸው፤ በአስተዳደሩ የቁጠባ ባህል እንዲጎለብትና ስራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲበራከቱ በማድረግ የስራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተቋሙ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸው፣ በታማኝነት ህብረተሰቡን በማገልገል ተልዕኮውን በሚገባ እንዲያሳካ አሳስበዋል።

የማህበሩ ሊቀመንበር እና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ታደሰ በበኩላቸው ተቋሙ ለአባላቱ የብድር አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የከተማዋን ገጽታ የሚያጎሉ የዘመነ የታክሲ አገልግሎት መኖር ወሳኝ በመሆኑ የበኩላቸውን ለማበርከት አላማ ያለው የብድር ምችችት ያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም በቀጣይ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ የከተማዋን ገጽታ የሚያጎለብቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን የማበረታታት ሥራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ ሰሞኑን በአሸዋ የንግድ ማዕከል በደረሰው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የህብረት ስራ ማህበሩ የመቶ ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።(ድሬቱብ)
"የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲፈርደኝ እፈልጋለሁ " ፍሬወይኒ ሀይሉ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ያለአግባብ በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ሳልካተት ቀርቻለሁ ስትል ቅሬታዋን ህዝብ ይወቅልኝ በማለት ገልፃለች።

በ1500 እና 5000 ሜትር ተወዳዳሪ መሆኗን ያስታወሰችው አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ በአመቱ ውስጥ በሁለቱም ርቀቶች ከሌሎች አትሌቶች የተሻለ ውጤት አስመዝግቤ ነበር ትላለች።

አትሌቷ በ2024 የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ1500ሜ ወርቅ እና የተሻለ ሰዓት እንዲሁም በ5000ሜ የ2024 የአለም ምርጥ 3ኛ ሰዓት ባስመዘግብም ከሁለቱም ርቀቶች ከኦሎምፒክ ውጪ ሆኛለሁ ብላለች።

አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ቀጥላም " እኔ በዚህ አመት የተሻለ ሰዓት ባስመዘግብም ከአመት በፊት ጥሩ ውጤት ያላቸው አትሌቶች ተመርጠው እኔ ቀርቻለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ።

በ2024 ምንም ውድድር ሳይወዳደሩ የ2023 አላቸው ተብሎ መምረጥ አግባብ አይደለም ለምን በሀቀኝነት አይመረጥም ምንም ሳይሮጡ እየተመረጡ ነው እኛ ግን ደክመንም እየቀረን ነው።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለምንድን ነው የእኛን ማየት የማይችለው በዚህ ላይ ማብራሪያም እፈልጋለሁ።"ስትል ተናግራለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶችን ይፋ ሲያደርግ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ የ5000ሜ ተጠባባቂ ሆና ተመርጣለች።

ምንጭ - ሀገሬ ቴሌቪዥን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 21:30:50
Back to Top
HTML Embed Code: