Telegram Web Link
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር ልዩ መመሪያ አወጣ፡፡

በጎንደር ከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ባለ ሦስት እግር የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በግራ በኩል ያለውን ሸራ እና በቀኝ በኩል የሚገኘውን መጋረጃ ሳያነሱ ማሽከርከር እንደማይችሉ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ እንደገለጹት በከተማው አገልግሎት የሚሰጡ የባለ ሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ለእይታ ግልጽ እንዲኾኑ የግራ ሽራና በቀኝ በኩል መጋረጃዎችን ከሰኔ 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት አድርገው እንዲያሽከረክሩ ታዟል።

ከአሁን በፊት በተደረገው የባጃጅ የስዓት ገደብ እገታ እና የተለያዩ ወንጀሎችን ማስቆም እንደተቻለ የገለጹት ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ በሕገወጥ መንገድ ያለ ታርጋ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ፣ የከተማ ፍቃድ የሌላቸው እና በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ 56 ባጃጆች መያዛቸውን ገልጸዋል።

ለቁጥጥር እንዲያመች፣ በወንጀል የሚጠየቁ እንዲታዩ እና ለተገልጋዩ ግልጽ እንዲኾኑ የግራ ሸራ እና የቀኝ መጋረጃ ክፍት አድርገው አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚገባ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

ተግባራዊ በማያደርጉ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ የሚወሰድ መኾኑንም ገልጸዋል።

ታርጋው በቅጣት የተፈታበት፣ የከተማ ፍቃድ የሌላቸው ባጃጆችን በከተማው ማሽከርከር እንደማይቻል እና ይህን ተላልፈው በሚገኙት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መኾኑን ኮሚሸነሩ አሳስበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ እንደሚያሳየው በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከ5 ሺህ በላይ የከተማ ፍቃድ ያላቸው ባጃጆች ያሉ ሲኾን ከ500 በላይ የከተማ ፍቃድ የሌላቸው ባጃጆች ደግሞ ወደ ወረዳ መውጣታቸው ነው የተገለጸው። (አሚኮ)

@ethio_mereja_news
የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በመዘመር ስራዉን እንደሚጀምር አስታወቀ

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ከሰኞ ጀምሮ ዘውትር በስራ ቀናት ለ 5 ደቂቃ የሚቆይ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር የቀኑ የስራ ውሎን ያስጀምራል መባሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ከሰኞ ጀምሮ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 2:05 ለ5 ደቂቃ የሚቆይ ዘውትር በስራ ቀናት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህዝብ መዝሙር በመዘመር የስራ ውሎን የሚያስጀምር መሆኑን ገልጿል።

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል የቡታጅራና አካባቢዋ ማህበረሰብ ድንገት ከመንገድ ሲያልፍ የሀገር ክብር፣ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና ጀግንነት የሆነውን የብሄራዊ መዝሙር ሲሰማ በሀገር ወዳድነት ስሜት ባለበት በመቆም አብሮ እንደሚዘምር ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መዝሙር መጀመር የስራ ተነሳሽነት ከማጠናከርም በላይ የሀገር ፍቅርን፣ህብረ ብሄራዊነትን፣አንድነትን፣ጀግንነትንና መሰዋዕትነትን የምንገልፅበት ነው ብለዋል።

@ethio_mereja_news
Netflix እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ብሎ መስራት ያለበት ፊልም አልያም ምርጥ እና አስተማሪ ዶክመንትሪ የሚወጣው ታሪክ በሀገራችን እግርኳስ ተመዝግቧል!

በፀሎት ልዑልሰገድ 2014 ኢትዮጵያ መድንን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ዋናው ሊግ ቢያሳድገውም ለፕሪምየር ሊግ ልምድ የለክም አትመጥንም ብሎ አሰናበተው። በጊዜውም በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ እና በሚዲያዎች ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ አለፈ....

ከመድን የተሰናበተው አሰልጣኝ በፀሎት በ2015 አዲስ የቤት ስራ ተሰጠው። ንግድ ባንክን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሜር ሊግ ማሳደግ። እሱም አላሳፈራቸውም ከምድቡ 1ኛ በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ አስገባቸው።

በመቀጠልም እንደ ቀድሞው ክለቡ ሊያሰናብቱት አልፈለጉም ይልቁኑም የሚፈልጋቸውን በርካታ ተጫዋቾች አስፈርሞ በሊጉ አስተማማኝ እና ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ እንዲቆይ ሀላፊነት ተሰጠው። እሱ ግን ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን ክለቡን ባደገበት ዓመት በ2016 የዋንጫ ባለቤት ማድረግ ቻለ።

ከምንም በላይ ድሉን ደግሞ ጣፋጭ የሚያደርገው በመጨረሻ ጨዋታ ለሊጉ ልምድ የለክም ብሎ ያባረረውን ክለብ ገጥሞ አሸንፎ ዋንጫውን መውሰዱ ነው።{✍️አማኑኤል አስራት}
ልጆች ከትምህርት ዉጪ በሚኖራቸው ጊዜ በቂ እረፍት አለማድረጋቸው የስነ-ልቦና ጫና ሊያስከትልባቸው ይችላል ተባለ‼️
መደበኛ የትምህርት ጊዜ እየተገባደደ መምጣቱን ተከትሎ ልጆች የሚኖራቸውን የእረፍት ጊዜ ማህበራዊ መስተጋብራቸውን የሚያጎለብቱበትን ክንውኖች በማድረግ ማሳለፍ እንደሚገባቸው የትምህርት ባለሙያ  ዶ/ር መክበብ ጣሰው ገልጸው በሃገራችን በትምህርት ስርአት ዉስጥ ያለው የእረፍት ጊዜ ለልጆች አመቺ አለመሆኑንም ይናገራሉ፡፡

በእረፍት ጊዜ የሚሰጡና ከመደበኛ ትምህርት  ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ትምህርቶች በልጆች ስነ ልቦና ላይ የሚያሳድረውን ጫና የሚናገሩት የስነ ልቦና ባለሙያው ልኡል አብርሃም ናቸው ፡፡

ባለሙያው ከመደበኛ ትምህርት ጊዜ ዉጪ ያለውን የእረፍት ጊዜ ክህሎቶች በሚያዳብሩና በሚያዝናኑ ተግባራት እንዲያከናውኑ በማደርግ የልጆችን ስነ ልቦና የማነቃቃትና ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
                   
በሃገራችን የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ከመስከረም እስከ ሰኔ ያለው የት/ት ጊዜ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የዘንድሮው አመትም ተጠናቆ የእረፍት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ምርጫ ቦርድ፣ በአራት ክልሎች ሰኔ 16 የድጋሚና ቀሪ ምርጫዎች ባካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በከፍተኛ ድምጽ አብዛኞቹን ወንበሮች ማሸነፉን ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ይፋ ባደረገው ውጤት፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አራት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ሲያገኝ፣ ተቃዋሚዎቹ ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) እያንዳንዳቸው አንድ መቀመጫ አሸንፈዋል።

ከክልሉ ምክር ቤት መቀመጫዎች ደሞ፣ ብልጽግና ፓርቲ 60 መቀመጫዎችን ሲያሸንፍ፣ ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሦስት እንዲኹም ጉሕዴን ስምንት መቀመጫዎችን አሸንፈዋል።

ብልጽግና ፓርቲ፣ በአፋር ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኹለት፣ ለክልል ምክር ቤት 27፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሦስት የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችን እንዲኹም በሱማሌ ክልል ሰባት የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችን እንዳሸነፈ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
ሼኸ ሙሐመድ አላሙዲን ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው!

ሼኸ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው። ከሰባት አመት በኋላ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ የሚመጡት ባለሀብቱ እሳቸውን ለመቀበል በቅርቡ የተመረተችው የሮልስ ሮይስ ቅንጡ መኪና በ650 ሺህ ዶላር ተገዝታ አዲስ አበባ መግባቷን ፋስት መረጃ ከኢትዮጲካሊንክ ሰምቷል።

ሼኸ ሙሐመድ አላሙዲን በሳኡዲ አረቢያ ለ14 ወራት ታስረው መቆየታቸው ይታወሳል፣ ከሰባት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሳኡዲ አረቢያ የሚወጡት ባለሀብቱ መስከረም 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሌላም ሰው በጥይት ተገደለ

ከትናንት በስተያ አማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በትላንትናው እለት ደዋ ጨፋ ወረዳ ሶዬ በተባለ ቀበሌ አንድ የግብርና ባለሙያ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ሲያልፍ አብረውት የነበሩና አቶ ኑሩ የተባሉ የደዋ ጨፋ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ኃላፊ በጥይት ቆስለው ህክምና ላይ እንደሚገኙ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
(wasu)

@sheger_press
@sheger_press
የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የኦንላይን ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃም ፍጹም ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ ነው ብሏል።

በመሆኑም ተማሪዎች ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
ለምን ክስ መሰረተብን በማለት ከእናታቸው ጋር በመተባባር ወንድማቸውን ደብድበዉ የገደሉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ድሬ ጅቦ ቀበሌ አዳነች ታደሉ የተባሉ የ62 ዓመት እናት እና ፍቅሬ ታፈሰ ፣ ለማ ታፈሰ ፣ መንግስቱ ታፈሰ የተባሉ ወንድማማቾች  የገዛ ወንድማቸዉን መለሰ ታፈሰን ለምን ክስ መሰረትክብን በማለት የወንጀል ድርጊቱን መፈጸማቸው ተገልጿል ።

መለሰ ታፈሰ  አግብቶ ከቤት ወጥቶ የሚኖር ሲሆን እናታቸው  ያላቸው ሀብት እና ንብረት በሙሉ ለሶስቱ ልጆች ብቻ  እንዳወረሱ ይሰማል።   በዚህም እንዴት አንተ የመጀመሪያ ልጅ  አንተ እያለህ ታናናሾችህ  ብቻቸውን ይወርሳሉ በሚል ባለቤቱ  ትናገራዋለች፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ከቤተሰቦቹ ጋር ግጭት የተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል ፡፡ በመሆኑም ከውርስ በመነሳቱ ለምን በማለት እናቱን ላይ ክስ ይመሰርታል።

ፖሊስም  ጉዳዩን በመመልከት  በሽምግልና እንዲፈትቱ የሚል ምላሽ ሰጥቷቸው እንደነበር የሰሜን ሸዋ ዞን ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ዓቃቢ ህግ የሆኑት አዲሱ አሰፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ።ይሁን እና እናት እና ሶስት ልጆች ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ቤት ሲመለሱ  የከሰሳቸውን  ልጃቸውን ከባለቤቱ ጋር ያገኙታል እናም እንዴት  እናታችን ላይ ክስ ትመሰርታለገህ ፤ እናታችንን እየጦርን ያለነው  እኛ ነን  በሚል በመካከላቸው ግጭት ይፈጠራል ።

በመካከላቸው የተፈጠረው አለመግባባት  ወደ ጸብ  አምርቶ በዱላ ይደበድቡታል ፡፡እናትም በድንጋይ ልጇን ጭንላቱ ላይ ትመታዋለች  ። በወቅቱ  ባላቤቷ ጉዳት ሲደርስበት የተመለከተችው ሚስት በአካባቢው ያለ ሰው በመጥራት እርዳታ ትጠይቃለች ። ጉዳት የደረሰበት መሰለታፈሰ በደረሰበት ድብደባ ከፍተኛ ደም የፈሰሰዉ በመሆኑ ህይወቱ ያልፋል። ፖሊስ ጉዳዩን  ከሟች ሚስት እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን እና የአስከሬን ምርመራ በማድረግ  የምርመራ መዝገቡን አጣርቶ ለዓቃቢ ህግ ልኳል።

ዓቃቢ ህግ ጥር 5 ቀን 2015ዓ.ም  የተፈጸመውን  ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ሶስቱን ልጆች እና እናታቸው ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል ። ፍርድ ቤቱም  ሶስቱ ወንድማማቿች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው  በ18 ዓመት እስራት እና ወላጅ  እናት ደግሞ ከእድሜያቸው  አንጻር የቅጣት ማቅለያ ተደርጎላቸው  በ1 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ዓቃቢ ህግ የሆኑት አዲሱ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።dagu
Telegram‼️

ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት እያደረገ ነው 🤩

ቴሌግራም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ቴሌግራምም ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገር መጥቷል ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል።

1 ሰው invite ስታደርጉ 15 star ታገኛላቹ

ስራውን ለመጀመር ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን start በሉት 👇🏻👇🏻

https://www.tg-me.com/major/start?startapp=769729488

https://www.tg-me.com/major/start?startapp=769729488
“ማናቸውም አይነት ተጽእኖ ደርሶብን አያውቅም፤ ቢደርስብንም አንቀበልም” – ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

የሰብአዊ መብት ተቋማት ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወይም አጋር ሀገራት ገንዘብ ማሰባሰባቸው፤ “ነጻነታቸውን የሚቃረን” ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናገሩ። እርሳቸው የሚመሩት ተቋም ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ገንዘብ ቢያሰባስብም፤ “ማናቸውም አይነት ተጽእኖ” ደርሶበት እንደማያውቅም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሐሙስ ሰኔ 27 በተካሄደ የፓርላማ ስብሰባ ላይ የሰብአዊ መብት ተቋማትን እና አሰራራቸውን “መፈተሽ” እንደሚያስፈልግ ተናግረው ነበር።

ይህን መሰሉ ትችት “በመንግስት በጀት የማይተዳደሩ” የሰብአዊ መብት ተቋማት ላይ “ብዙ ጊዜ ይቀርባል” ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ ጉዳዩ በሌሎች ሀገራትምም “የተለመደ እና በተደጋጋሚ የሚሰማ” እንደሆነ አመልክተዋል።

እንደ ኢሰመኮ ሁሉ ሌሎችም የሰብአዊ መብት ተቋማት “ሃብት ማሰባሰባቸው በራሱ ስህተት አይደለም” ሲሉም ዶ/ር ዳንኤል ከትናንት በስቲያ አርብ በመስሪያ ቤታቸው በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

“የተወሰኑ መንግስታዊ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ መንግስትም፣ ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ሀብት ያሰባስባል። ስለዚህ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ወይም አጋር ሀገራት፤ ሀብት እና ገንዘብ ማሰባሰብ በራሱ የተቋምን ነጻነት የሚቃረን ነገር አይደለም” ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ አክለዋል።
Via Ethiopia Insider

@ethio_mereja_news
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መርሃግብር

ለተፈታኞች በሙሉ መልካም እድል

@sheger_press
“ለገንዘብ ሲባል በተማሪዎች እና በንጹሃን ላይ የሚፈጸም እገታ ሊቆም ይገባዋል" አሜሪካ

አሜሪካ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የእገታ ተግባር አወገዘች፣ የህግ የበላይነት እየተሸረሸረ ነው ስትል አሳስባለች

“ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ #በኦሮምያ እና #አማራ ክልሎች እየተፈጸሙ ያሉ የንጹሃን እገታዎች፣ የተራዘመ ግጭት ወንጀለኞች እንዲበረታቱ እና የህግ የበላይነትን እንደሚሸረሽር እንደሚያደርግ ማሳያ ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤሪቪን ማሲንጋ ገለጹ።

“ለገንዘብ ሲባል በተማሪዎች እና በንጹሃን ላይ የሚፈጸም እገታ ሊቆም ይገባዋል” ሲሉ አምባሳደሩ በኤምባሲው ይፋዊ የኤክስ ገጽ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አሳስበዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ከ100 በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታገታቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።

ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በአውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች መታገታቸው መዘገቡ ይታወሳል።

እገታው የተፈፀመባቸው በዋናነት #የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ ኢላማ የተደረገባቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ መሆኑም በዘገባው ተካቷል።

ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው

@ethio_mereja_news
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
2024/09/30 23:35:45
Back to Top
HTML Embed Code: