Telegram Web Link
ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ በመጠቀም ወንድማችን ታሟል በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ እና በ በተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ታማሚ በማስመሰል የማጨበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ  ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን ፖሊስ አስታዉቋል።

በማጨበርበር ድርጊቱ የተሰማሩት ተጠርጣሪዎች አብዛኛዎቹ ወጣቶች ሲሆኑ  ከተለያዩ አከባቢዎች በመምጣት ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ በማዘጋጀት  ወንድማችን በህመም እየተሰቃየብን ነው በማለት መኪና በመከራየት ሲያጭበረብሩ መገኘታቸዉ ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ  ከአስራ ዘጠኝ ሺህ ብር በላይ ከህብረተሰቡ በማጨበርበር መሰብሰባቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከሰሞኑ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ሲተኩስ የታየዉን የፌዴራል ፖሊስ አባል ተከትሎ ኮሚሽኑ ከመተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ ነዉ ሲል ኮነነ

የፖሊስ አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ዉሏል
ተብሏል

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ካሰራጨዉ መግለጫ ሸገር እንደተመለከተው ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ  ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን  በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው ወቅሷል።

አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ   በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።

ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት እንደሚያቀርበው በመግለጫው መጥቀሱን ሸገር ፕረስ ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት ተንዶ በሌላ ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳረገ‼️

ዛሬ ሚያዝያ 16 ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12፣ ጠሮ መስጂድ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት በአቅራቢያው ባለ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳርጓል።

የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አውጥተው ለፖሊስ ማስረከባቸው ተገልጿል።

@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት ተንዶ በሌላ ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳረገ‼️ ዛሬ ሚያዝያ 16 ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12፣ ጠሮ መስጂድ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት በአቅራቢያው ባለ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳርጓል። የሟቾቹን አስከሬን…
#Update

የግለሰብ መኖሪያ ተደርምሶ ከሞቱ 7 ሰዎች  መካከል የአራት አመት ህፃን መኖሩ ተነገረ

በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራ አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት ቢተርፉም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን አጥተዋል


በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራም አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት እንዲተርፉ ቢያደርጋቸውም በቤት ውስጥ ተኝተው ትተዋቸው በሄዱበት አጋጣሚ ሚስታቸውን እና ቤተሰባቸው የግንባታው እቃ ተደርምሶ እንደሞቱባቸው አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ጠሮ መስኪድ አካባቢ ለሊት 11:00 ሰዓት ላይ እየተገነባ ያለ የግለሰብ ቤት የግንባታ እቃ ተደርምሶ የ7ሰዎች ህይወት ማለፉን ብስራት መዘገቡ ይታወሳል።

በአደጋው ከሞቱት ሰባት ሰዎች ውስጥ አራቱ ሴቶች ሲሆኑ የ28 ፤የ25 ፤የ12 አና የ11 ዓመት መሆናቸው አቶ ንጋቱ የተናገሩ ሲሆን ከሞቱት መሀከል የ30 የ12 እና የአራት አመት እድሜ ያላቸው ወንዶች ህይወታቸውን አተዋል።

@ethio_mereja_news
በልዩ ቅናሽ ኦርጅናል ስልኮች ይሸምቱ

Brand #Samsung

A15- 4 ram 128 GB - 16,500

A05 -4 ram 64 GB - 11,500

A34- 6ram 128 GB - 28,000

A54- 8ram 256GB - 38,000

S24 Ultra -12 ram - 512 GB -126,000

ይደውሉልን 👉 0913366506

Telegram @Birukepromo

ተጨማሪ እቃዎችን ለመሸመት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/bura_collection
" ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ " - ቀሲስ በላይ መኮንን

የቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ስለ ዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ ደንበኛቸው ቀሲስ በላይ መኮንን በሐሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የተገኙት " ሰዎች አታልለዋቸው " እንደሆነ ለፍ/ቤት መናገራቸውን ገልጸዋል።

ጠበቃ ቱሊ ፤ " እሳቸው በቦታው ከመገኘት ውጪ ደብዳቤውን በማዘጋጀት፣ በመቀበል በዚህ ወንጀል ውስጥ ተሳትፎ የላቸውም " ያሉ ሲሆን " ደብዳቤው ላይ የእሳቸው ስም፣ የባንክ ቁጥር የለም። የቤተ ክርስቲያን የሂሳብ ቁጥር የለም " ብለዋል።

" ከመጀመሪያውም ወንጀሉ በሌሎች ሰዎች የተሞከረ ቢሆንም እሳቸውን አይመለከትም " ሲሉ ገልጸዋል።

በችሎቱ ላይ ለመናገር ዕድል ያገኙት ቀሲስ በላይ የአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገኙት " ሰዎች ወስደዋቸው " እና " #ተታልለው " እንደሆነ ተናግረዋል።

" በዚያ ቦታ ላይ ከመገኘት ውጪ ምንም የፈጸሙት ድርጊት እንደሌለ " ገልጸዋል።

ቀሲስ በላይ ፦

" ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ። እኔ ወደዚያ የሄድኩት ለመተባበር፣ ይህ ሰነድ ‘ትክክለኛ ሰነድ ነው አይደለም’ የሚለውን የባንክ ማናጀሮችን ለመጠየቅ ነው እንጂ በምንም ሁኔታ በሰነዱ ለመገልገል አስቤ አይደለም። ጉዳዩ ዞሮ እኔ ታሳሪ ሆንኩኝ እንጂ፤ ሰነዱ ‘ትክክል አይደለም’ የሚል የባንክ ማናጀሩ ሲገልጹልኝ ወዲያው ፖሊስ ያስጠራሁት እኔ ነኝ " ማለታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

ቀሲስ በላይ ሰነዱን አዘጋጅተዋል የተባሉ ሰዎች " ማምለጣቸውን " እንዲሁም ስለ ሰነዶቹ " የሚያውቁት እና መመርመር ያላባቸው " እነሱ እንደሆኑም ለፍርድ ቤቱ አንስተዋል ተብሏል።

በዛሬው የፍ/ ቤት ውሎ የቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ለመርማሪ ፖሊስ ስምንት ተጨማሪ ቀን መሰጠቱ ይታወቃል።

የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
M13 Samsung 128/6
Slightly used
fixed coast 14000etb

አናግሩን👇
@ethio_sellerr
ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@sheger_press
@sheger_press
ኢትዮጵያ ፤ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።

Via ዋልታ
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል።

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡

እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6 በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል።

ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል።
የችሎት ዘገባው የፋና ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኬንያ እና ኢትዮጵያ የንግድ ማነቆዎችን ለማስወገድ አዲስ ጥረት እንደጀመሩ ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።

አዲሱ ጥረት የተገለጠው፣ የኬንያና ኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቡድን ሰሞኑን በአዲስ አበባ የጋራ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ነው።

በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2022 ኬንያ 95 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ሸቀጦችን ወደ ኢትዮጵያ የላከች ሲኾን፣ ኢትዮጵያ ጥራጥሬና አትክልቶችን ጨምሮ በተጠቀሰው ዓመት ወደ ኬንያ የላከችው ግን 26 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

በኹለቱ አገሮች ድንበር ዘለል ንግድ ውስጥ ሊወገዱ ከሚገባቸው ማነቆዎች መካከል፣ ታሪፍ ነክ ያልሆኑ ማነቆዎችና ባንዱ አገር ጥራቱ የተረጋገጠለት ምርት በሌላኛው አገር በድጋሚ ጥራቱ እንዲረጋገጥ የማድረግ አሠራር እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዐቃቤ ሕግ የሽብር ተከሳሾችን ክስ እንዲያሻሽል በተሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አቀረበ!

ዐቃቤ ሕግ፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን የእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ዛሬ ኀሙስ በሰጠው ብይን ላይ፣ “ምስክሮቼን ያጋልጥብኛል” በማለት አቤቱታ አቅርቧል፤ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ክሱ ካልተሸሻለ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡በተከሳሶቹ የወንጀል ድርጊት “ተገድለዋል” የተባሉ ሰዎች፣ በክሱ ላይ በስም እንዲጠቀሱ ብይን ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፣ በዛሬው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በእነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ዛሬ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ለመመልከት ነበር፡፡

የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት የሽብር ወንጀል፣ የ217 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መጎዳታቸውንና ከፍተኛ ንብረትም መውደሙን ሲያስረዳ፣ በተከሳሽ ጠበቆች ጥያቄ መሠረት፣ ሟቾቹ በስም ተጠቅሰው፣ ሌሎች ጉዳቶችም በዝርዝር ተገልጸው ክሱ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ኅዳር 12 ቀን በይኖ ነበር፡፡

ኾኖም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ክሱ እንዲሻሻል የተሰጠው ብይን እንዲሻር በደብዳቤ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ለዚኽም በምክንያትነት ያቀረበው፣ እንደ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሟቾቹን ስም መጥቀስ “ምስክሮቹን ለጉዳት የሚዳርግ ነው፤” የሚል እንደኾነ፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው፣ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ብያኔ አክብሮ ክሱን የማያሻሽል ከኾነ ክሱ እንዲነሣ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ፣ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን መቅጠሩን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡

በክስ መዝገቡ ላይ ከተጠቀሱ 51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎችን ጨምሮ 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ለሕክምና እንደወጡ ማምለጣቸውን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወካዮች ከዚኽ ቀደም ለፍርድ ቤት ማሳወቃቸውን ጠበቆቹ ገልጸዋል፡፡ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾችን፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ውጤቱ ለቀጣዩ ችሎት እንዲቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡
(VoA)

@sheger_press
@sheger_press
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 244 የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ ሰራተኞቹን መቅጣቱን እና በህግ ተጠያቂ ማደረጉን ገለፀ

👉 አገልግሎቱ አመራሮቹ እና ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ሰራተኞቹ ሀብታቸዉን እንዲያስመዘግቡ አድርጓል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትከዚህ በፊት ይነሳበት የነበረዉን የሙስና ተግባር ለመከላከል የተለያዩ ለዉጦችን እየከወንኩኝ እገኛለሁ ማለቱን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ለዚህም በማሳያነት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከወናቸዉን ተግባራት በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል።

በተመሳሳይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 244 ሰራተኞቹን ከስራ እንዲታገዱ ፣ ከሀላፊነት እንዲነሱ እና በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉንም አሳዉቋል።

አገልግሎቱ ይህንን ያለዉ በዛሬዉ እለት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸምን በገመገመበት ወቅት ነዉ።

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ - ፓስፖርት (E-passport) ለመቀየር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየከወነ መሆኑንም ብስራት ከሪፖርቱ ሰምቷል። በተመሳሳይ በዉጪ የሚታተመዉን ፓስፖርት በሀገር ዉስጥ ለማድረግ የዲዛይን ስራዎች ተጠናቅቀዋል የተባለም ሲሆን ህትመቱን ከሚሰራዉ ተቋም ጋር ዉል መታሰሩን እና ህትመቱን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ለመጀመር ማቀዱንም ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ስራዎቹን ለመከወን እንዳልቻለ የገለጸ ሲሆን በአንጻሩ በትግራይ ክልክ ተቋርጦ የነበረዉን አገልግሎት ለማስጀመር የዳሰሳ ጥናት መስራቱን አስታዉቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኤርትራ ጦር ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ

የዛላአንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል ብለዋል፡፡

ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች ፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮብ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮ ኤፍኤም ዘገባ ተመልክቷል።

አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡

የኤርትራ ጦር የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ተነግሯል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል።

በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ 30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ  አቶ ብርሀነ ገልፀዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በወላይታ ዞን የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ትምህርት መቋረጡ ተገለጸ!!

ላለፉት ሁለት ወራት ገደማ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን መምህራን፣ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን አስታወቁ፡፡

ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች መጋለጣቸውን የተናገሩት መምህራኑ፣ አብዛኞቹም ኑሯቸውን ለመምራትና ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ እንደተሳናቸው አመልክተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐማኑኤል ጳውሎስ፣ በዞኑ ከሚገኙ ስድስት የከተማ አስተዳደሮች እና 17 ወረዳዎች ውስጥ፣ የአንድ ከተማ አስተዳደር እና የ20 ወረዳዎች መምህራን ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ገልፀውልኛል።
2024/12/26 07:03:10
Back to Top
HTML Embed Code: