Telegram Web Link
ከ18 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎችን ከሀገር ተባረዋል

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሐሰተኛ የመኖሪያ ፍቃድ በአገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ18 ሺህ በላይ የውጭ አገር ዜጎችን ከአገር ማባረሩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባቀረበው ሪፖርት ገልጧል።

ከአገር ከተባረሩት መካከል፣ ለሌሎች የውጭ ዜጎች ሐሰተኛ የመኖሪያ ፍቃድ አዘጋጅተው በገንዘብ ሲሸጡ የነበሩ እንደሚገኙበት ተቋሙ ገልጧል።

በኢንቨስትመንት ፍቃድ ወደ አገሪቱ የገቡ የውጭ ዜጎች ለበርካታ ዓመታት በሕገወጥ ሥራዎች ላይ ተሳታፊ ኾነው እንደተገኙም ተቋሙ ጠቅሷል።(ዋዜማ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መልካምነት ለእራስ ነው 🥰

በአጋጣሚ ከማያቁት ሰው በርከት ያለ ገንዘብ በባንክ አካውንቱ ቢላክሎ ምን ያደርጋሉ ??? 🤔

ነገሩ እንዲህ ነው በአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ እንዲሁም በድለላ ስራ ቤተሰቡን የሚያስተዳደር የባቱ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ቱፋ ሰለሞን የተለመደውን ስራ ለመስራት የእለት እንጀራውን ለማግኝት በስራው ለይ እያለ ባጋጣሚ ወደ ባንክ አካውንቱ 2,000,000 ብር ይገባል።

የዚን ጊዜ ከየት የመጣ በረከት ነው ብሎ ብሩን አውጥቶ ለመጠቀም አይደልም ያሰበው ከየት እንደመጣ ለማውቅ ነው የቸኩለው በስህተትም ይሆናል ብሎ አስቦ ነበር።

ፈላጊው እስኪገኝ ድረስ ለ1 ወር ያክል ገንዘቡን ሳይነካ ባለቤቱ እስኪመጣ ሲጠባበቅ ነበር። በመጨረሻም ከ1 ወር ቁይታ በዋላ አብነት ግርማ የተባለች የአዲስ አበባ ነዋሪ በስህተት ወደ ቱፋ ሰለሞን አካውንት ማስገባቷ ከተረጋገጠ በዋላ አቶ ቱፋ ሰለሞን ገንዘቡን ለባለቤቷ በመመለስ ታማኝነታቸውን አሳይተዋል።

ለፍቶ አዳሪው አቶ ቱፋ ለታማኝነታቸው ምስጋና ይገባቸዋል 🙏🙏🙏

@ethio_mereja_news
የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በመጋቢት ወር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በቀዎት፣ ኢፍራታና ጊደም እና አንጾቂያ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ 18 ሺህ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉና 290 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጠሉ አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

በክልሉ ኦሮሞ ልዩ ዞን በግጭት የተጎዱ 36 ሺህ 450 በላይ ሰዎች አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚፈልጉም ቢሮው ገልጧል።

በክልሉ በቀጠለው ግጭት ሳቢያ፣ 4 ሺህ 178 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉም ቢሮው የጠቀሰ ሲኾን፣ በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም እንዲኹም በደቡብ ጎንደር ዞኖች ብቻ 89 በመቶዎቹ ትምህርት ቤቶች በግጭቱ ሳቢያ ዝግ ናቸው ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በአገሪቱ የሚዘረጋቸውን የቴሌኮም ታዎሩች ብዛት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በሦስት እጥፍ ለማሳደግ ማቀዱን እንደገለጠ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ኩባንያው ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 2 ሺህ 500 የቴሌኮም ታዎሮች ያሉት ሲኾን፣ 1 ሺህ 500ዎቹ ታዎሮች ከኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የተከራያቸው ናቸው። ኾኖም መላ አገሪቱን ለመሸፈን 7 ሺህ ታዎሮች እንደሚያስፈልጉት የኩባንያው ሃላፊዎች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል።

ዘገባው፣ በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ግን በኩባንያው እቅዶች ላይ ትልቅ እንቅፋት ደቅነውብኛል ማለቱንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ ባይቶና፣ አፍሪካ ኅብረት እና አጋር አገራት፣ የትግራይን ግዛቶችና የትግራይን ነባራዊ ኹኔታ "በተሳሳተ አኳኋን" ገልጠውታል በማለት ወቅሷል።

የሰባት አጋር አገራት ኢምባሲዎች ከሳምንት በፊት እንዲኹም አፍሪካ ኅብረት ትናንት ባወጧቸው መግለጫዎች፣ የተወሰኑ የትግራይ ግዛቶችን "አወዛጋቢ" ብለው በመጥራት የፈጠሩትን "ስህተት ያርሙ" በማለት ጠይቋል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ በመግለጫቸው፣ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላ ወረዳዎችን ጨምሮ "በአወዛጋቢ አካባቢዎች ማኅበረሰቦች መካከል ሰሞኑን የተፈጠረው ውጥረት" እንዳሳሰባቸው ገልጠው ነበር።

አፍሪካ ኅብረት በሕገ-መንግስቱ የታወቁ የትግራይ ግዛቶችን "አወዛጋቢ" ብሎ መግለጡ፣ "ለፌደራሉ መንግሥት ያለውን ወገንተኝነት ያሳያል" በማለትም ፓርቲው ከሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል ተብሏል

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መከላከያ ሠራዊት ምዕራብ ኦሮሚያን "ከበባ ውስጥ በማስገባት ሕዝቡን በጅምላ እየቀጣ ነው" በማለት ከሷል።

ኦሮሚያ ክልል የአገሪቱ አብዛኛው ሃብት ምንጭ ናት ያለው አማጺው ቡድን፣ ኾኖም የፌደራሉ መንግሥት "ኦሮሚያን ለረጅም ጊዜ ሙሉ ከበባ ውስጥ ማስገባት አይችልም፤ አይፈልግምም" ብሏል።

መንግሥት ከምዕራብ ሸዋ ዞን ጀምሮ በመላው ምዕራብ ኦሮሚያ ባኹኑ ወቅት እየወሰደ ያለው ርምጃ፣ "የአማጺው ቡድን ተዋጊዎች ቤተሰቦችና ቡድኑን ይደግፋሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በመንግሥት የሕክምና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፍርድ ቤቶችና የቀብር ቦታዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ" እንደኾነ ቡድኑ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሆሳዕና በአርያም 🌴

እንኳን አደረሳችሁ

የ “ሆሳዕና በአርያም” በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ሆሳዕና በአርያም ከፋሲካ በፊት ያለው እና የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሣምንት ሲሆን÷ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው” የሚሉ ትርጉሞችም እንዳሉት የዕምነቶቹ አባቶች ያስተምራሉ።

የዕምነቶቹ ተከታዮች በሆሳዕና በአርያም በዓል መሪው ተመሪውን ዝቅ ማለትን ያስተማረበት እና ተመሪውም የሚመራውን ጨርቁን እያነጠፈ እና ዘንባባ እየጎዘጎዘ ያከበረበት የትህትና እና የፍቅር በዓል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡

ሆሳዕና በአርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በተለይም÷ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወጣቶች እና ሕጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ ሆሳዕና በዓርያም” በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም፤ መተግበር አለበት።

በኢትዮጵያ መናናቅ እና የት ይደርሳል ማለት ችግር ሲፈጥር እየታየ መሆኑንም መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም።ውጤቱ መተግበር ይኖርበታል።

እንደ ሀገር የመወያየት ችግር ባይኖርም መሠረታዊ ችግሩ አፈፆፀም ላይ ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መስራት ያስፈልጋል።ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው  እንወያይ እንጋገር ከማለት የዘለለ አይደለም>>

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳፎ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት የተወሰደ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ አቀባበል ተደረገለት

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በሆሳዕና እለት ወደ ሀገሩ ሲገባ በቤተሰቡ፣ በወዳጆቹ ቀነኒሳ ሆቴል አቀባበል ተደረገለት።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፈታኙ ሎንዶን ማራቶን 2.04.15 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቁ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትግራይ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በዋሉ የራያ እና አላማጣ አካባቢዎች ህይወት ምን ይመስላል?

ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል።

የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል።

የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል።

የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።


ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል።

የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል።

የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል።

የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤፍ ቢ ሲበመዲናዋ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአውሮፓ ህብረት #ለኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ፈቃድ መከከሉን አስታወቀ‼️

ለዚህ ውሳኔ መነሻው ከመንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው ብሏል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ፈቃድ መስጠት የሚከልክል ውሳኔ አሳለፈ።

ለክልከላው የሰጠው ምክንያት ከኢትዮጵያ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው ብሏል።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን እዚህ ውሳኔ ላይ ያደረሰው በህብረቱ ሀገራት በህገወጥነት በሚቆዩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዙሪያ ከሀገሪቱ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው ብሏል።
በዚህም የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ
- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ ተጠቁሟል።
ውሳኔው ለምን ያክል ግዜ እንደሚቆይ ያለው ነገር የለም፤ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን አራዝሞታል።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው የህብረቱ ምክር ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት የሚቆዩ ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።(Alain)
2024/11/05 23:14:34
Back to Top
HTML Embed Code: