Telegram Web Link
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት በወረዳው አስተዳዳር ሕንጻ የመንግሥት ሠራተኞችን ላጭር ጊዜ አግተው እንደነበር ቢቢሲ የዐይን እማኞችንና ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የትናንቱን እገታ ተከትሎ፣ በድባጤ ከተማ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደዋሉ ዘገባው አመልክቷል።

የወረዳው አስተዳደር ሠራተኞችን ያገቱት፣ ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የፈጸመው የቀድሞው አማጺ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ታጣቂዎች እንደኾኑ የዓይን ምስክሮች መስማታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

አጋቾቹ፣ የወረዳው አስተዳደር አመራሮችን ብቻ እንደሚፈልጉ በመግለጽ፣ ከኹለት ሰዓታት በኋላ ቀሪዎቹ ሠራተኞች በቀጣዩ ቀን ሥራ እንዳይገቡ አስጠንቅቀው እንደለቀቋቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ኢትዮ መረጃ NEWS ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች መልካም በዓልን ይመኛል።

@ethio_mereja_news
የ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላው ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ቻናላችን በድጋሚ መልካም በዓልን ይመኛል

ዒድ ሙባረክ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር ዜና‼️

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።

" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው በከተማ ተገድለው ተጥለው ነው  የተገኙት " ተብሏል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር በዋስ ከእስር ተለቀው ነበር። ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይተ ተመተው ተገድለዋል። ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የቀድሞ ድምፃዊ ዘማሪ ሙሉቀን መለስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የቀድሞ ሙዚቀኛ ሙሉቀን መለሰ በጎጃም ክፍለ ሀገር አነደድ ወረዳ ውስጥ ዳማ ኪዳነ ምሕረት በምትባል መንደር በ1946 ዓ.ም እንደተወለደ ግለታሪኩ ያወሳል።

አሥር ዓመት ሲሆነው እናቱ ስለሞቱ፣ አዲስ አበባ ይኖሩ የነበሩ አጐቱ እንዲማር ብለው ያመጡት ሙሉቀን መለስ ኮልፌ ሰፈር ጳውሎስ ትምህርት ቤት ሊገባ ችሏል።

ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር የነበረው ድምፃዊው እርሱ በነበረበት አከባቢ በተከፈተው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብቶ በአቶ ተፈራ አቡነ ወልድ አማካይነት ለስድስት ወራት የዘለቀ የትምህርት እገዛ አግኝቷል።

ገና የ13 ዕድሜ ታዳጊ ሳለ ሙዚቃን የጀመረው ድምፃዊው  በ1958ዓ.ም በፈጣን ኦርኬስትራ ውስጥ ተቀላቅሎ በመግባት ለሁለት ዓመታት ያክል መስራት ችሏል።

ከእዚያ በማስከተል በ1960 ዓ.ም ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል በመግባት ይበልጥ በሙዚቃ ስራው ዝናን ማትረፍ ችሎ ነበር።

በ1972 ዓ.ም ላይ ደግሞ ከዳህላክ ባንድ ጋር ተቀላቅሎ ሰርቷል፣ እስከ 1980ዎቹ ድረስ በነበሩት ዓመታት እጅግ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎችን መስራት ችሏል።

አንጋፋዋ ሁለገብ ከያኒት የአለምፀሐይ ወዳጆችን እና የተስፋዬ ለሜሳን ግጥምና ዜማዎች አቀንቅኗል።

በ1980ዎቹ በኃላ ፊቱን ወደ መንፈሳዊ ስራዎች በማዘር የመዝሙር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ላለፉት አመታት በሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ኑሮውን አድርጎ እስከ ህልፈት ሕይወቱ ድረስ በእዚያው ቆይቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ መጠን ናረ!

ለጋዛው ጦርነት ከተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ፣ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያሳደረው ተስፋ መመናመን እና ሜክሲኮ ለዓለም ገበያ በምታቀርበው ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት መጠን ላይ ተጨማሪ ቅነሳ ለማድረግ የያዘችውን እቅድ ተከትሎ በዛሬው ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ መናሩ ተዘግቧል።

ትናንት ሰኞ ካይሮ ላይ የተካሄደውን አዲስ ዙር የተኩስ አቁም ድርድር ተከትሎ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ የማሽቆልቆል አዝማሚያ ማሳየት ቢጀምርም፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ጦራቸው በጋዛዋ የራፋህ ግዛት ጥቃት የሚፈከፍትበት ‘ቀን ተቆርጧል’ ካሉ በኋላ፣ የአካባቢው ውጥረት ‘ይረግባል’ በሚል አሳድሮት የነበረውን ተስፋ እያመከነ መሆኑን ተንታኞች ተናግረዋል።

የግጭቱ አለማብቃት ሌሎች አገሮችንም ወደ ጦርነት እንዳይስብ፤ በተለይም ደግሞ ዋናዋ የሃማስ ደጋፊ እና በዓለሙ የነዳጅ አምራች አገሮች ድርጅት፣ ለዓለም ገበያ በሚቀርበው የነዳጅ መጠን በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውን ኢራንን ወደ ጦርነቱ እንዳያስገባ ያሳደረው ሥጋት እንዲቀጥል ማድረጉ ተዘግቧል።

በተጨማሪም የሜክስኮው መንግስታዊ የነዳጅ ኩባንያ ‘ፔሜክስ’ በቀኑ ለዓለም ገበያ ከሚያቀርበው 330ሺሕ በርሜል መጠን ያለው ነዳጅ በመቀነስ ተጨማሪ ነዳጅ ለአገር ውስጥ ማጣሪያዎች ለማቅረብ የያዘው ዕቅድ አሳሳቢውን ሁኔታ ይበልጥ እንዳባባሰውም ተመልክቷል። ውሳኔውም ኩባንያው ለዩናይትድ ስቴትስ፣ ለአውሮፓ እና ለእስያ ተቀባዮቹ ያቀርብ የነበረውን ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት መጠን በአንድ ሶስተኛ ይቀንሰዋል ተብሏል።ፔሜክስ አዲሱን ውሳኔውን ይፋ ከማድረጉ አስቀድሞም በያዝነው የሚያዝያ ወር ውስጥ በየቀኑ ከሚያቀርበው የነዳጅ ዘይት መጠን በ436ሺሕ በርሜል ቀንሶ ነበር።

Via VoA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር ዜና‼️

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገድለው፤ አስክሬናቸው ተጥሎ ተገኘ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ የትውልድ ከተማቸው በሆነችው መቂ ከተማ ተገድለው አስክሬናቸው ተጥሎ ተገኘ።ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንገልጸው የአቶ በቴ ኡርጌሳ የቅርብ ጓደኛ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ በቴ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘው መቂ ከተማ የተገደሉት ትናንት ሰኞ ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም. እኩለ ለሊት ላይ ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ የፖለቲካ ኦፊሰሩን ግድያን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም የፓርቲው የሕዝብ ግንኑነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “በቴ የሆነውን ማመን አቅቶኛል” ሲሉ ጽፈዋል።አቶ በቴ የካቲት አጋማሽ ላይ በቁጥጥር ስር ውለው ለሁለት ሳምንታት ያህል በእስር ከቆዩ በኋላ በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና የተለቀቁት ከአንድ ወር ገደማ በፊት የካቲት 30/2016 ዓ.ም. ነበር።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲከኛው የቅርብ ጓደኛ እንደሚሉት፤ አቶ በቴ በመቂ ከተማ አርፈው ከነበረበት የሆቴል ክፍል ውስጥ ተይዘው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል።በአቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ ግድያን ማን እንደፈጸመው እንደማያውቁ የገለጹት ይህ ግለሰብ፤ በአሁኑ ወቅት በመቂ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት በመቋረጡ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አዳጋች እንደሆነባቸው ጨምረው ተናግረዋል።

አቶ በቴ በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት በተደጋጋሚ ለእስር ሲዳረጉ የቆኡ ፖለቲከኛ ሲሆኑ ከጥቂት ሳምንታት በፊትም ከአንድ ፈረንሳይዊ ጋዜጠኛ ጋር በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር።አቶ በቴ ኡርጌሳ ሐሙስ የካቲት 14/2016 ዓ.ም ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ጋር በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ቁጭ ብለው እየተነጋገሩ ሳለ በቁጥጥር ስር ውለው ከሁለት ሳምንታት እስር በኋላ ተለቀዋል።

በወቅቱ መንግሥት የ“አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ጋዜጠኛው እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር በቁጥጥር ስር የዋሉት “ከፋኖ እና ኦነግ ሸኔ ጋር በመተባባር ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት በመንቀሳቀሳቸው ነው” ብሎ ነበር።በኦሮሞ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት እና በፓርቲያቸው ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑት አቶ በቴ ከዚህ ከቀደምም ለተደጋጋሚ እስር ሲዳረጉ ቆይተዋል።

Via BBC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
ሰበር ዜና‼️ የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገድለው፤ አስክሬናቸው ተጥሎ ተገኘ! የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ የትውልድ ከተማቸው በሆነችው መቂ ከተማ ተገድለው አስክሬናቸው ተጥሎ ተገኘ።ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንገልጸው የአቶ በቴ ኡርጌሳ የቅርብ ጓደኛ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ በቴ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘው መቂ ከተማ የተገደሉት…
Update‼️

በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ#ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግስት ለበርካታ አመታት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ እንዲሳተፉበት ተከልሎ የቆየው ቡናን ፣ ጫትን ፣ የቁም እንስሳትን እና ቆዳና ሌጦን ለውጭ ገበያ የመላክ ስራ ለውጭ ባለሀብቶች የሚፈቅድ መመሪያ ማዘጋጀቱ ተሰምቷል።

ከማዳበሪያ እና ነዳጅ ውጪ ሌሎች ምርቶችን ማስገባትንም መመሪያው ለውጭ ባለሀብቶች ይፈቅዳል በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በሚመራው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የተዘጋጀው እና ዋዜማ የተመለከተችው ሰነድ (መመሪያ) መንግስት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ውሳኔን ለመወሰን ያበቃውን ምክንያት ያትታል።

@sheger_press
@sheger_press
ሹመት‼️

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶክተር ፍሬው ተገኝ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።ዶ/ር ፍሬው ተገኝ  ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በእንስሳት እርባታ እና አመጋገብ ከ Humboldt-Universität zu Berlin አጊኝተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸው ሥራ መጀመራቸውም ታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደሌለና ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት መሆኗን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ተናገሩ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት” መሆኗን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር እና ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብም ተናግረዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ሞሐመድ ይህንን ያሉት የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም. ለአገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ነው።

“የኢትዮጵያ መሪዎች ወደ ቀልባቸው መመለስ አለባቸው” ያሉትን ሐሴን ሼህ፤ ግጭት እየፈጠረች ያለችው ኢትዮጵያ እንጂ ሶማሊያ እንዳልሆነች ለዓለም እየተናገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

“እኛ የኢትዮጵያን አካል እንፈልጋለን አላልንም። ለኢትዮጵያን መንግሥት እውቅና አንሰጥም [አላልንም]፤ ከክልል መንግሥት ጋር ስምምነት እንፈጽማለንም አላልንም” ሲሉ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት እየፈጠረች አይደለም የሚለውን ሀሳባቸውን አስረድተዋል።

ሁለቱ ጎረቤት አገራት በጋራ ፍላጎቶቻቸው ላይ መሥራት ያላቸው “ብቸኛ አማራጭ” መሆኑን በንግግራቸው ላይ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ “ሉዓላዊነታችንን፣ አንድነት እና ሙሉዕነታችንን ለድርድር የሚያቀርብ የጋራ ፍላጎት ሊኖረን አይችልም” ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
44 ቢሊየን ዶላር ያጭበረበረችው ቬትናማዊት ቱጃር በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ

44 ቢሊየን ዶላር ያጭበረበረችው ቬትናማዊት ቢሊየነር በሞት እንድትቀጣ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ትሩኦንግ ማይ የተባለችው የ67 ዓመት ቬትናማዊት ቱጃር ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በሀገሪቱ ከሚገኘው ሳይጎን የንግድ ባንክ ለ11 ዓመታት ያህል ዘረፋ ስትፈፅም እንደነበር ተገልጿል፡፡

ግለሰቧ ከመዘበረችው ገንዘብ ውስጥ 27 ቢሊየን ያህል ዶላር ተመላሽ እንድታደርግ ብይን ቢሰጥም፤ ዐቃቤ ህግ ግለሰቧ ገንዘቡን መመለስ እንደማትችል በማረጋገጡ የሞት ቅጣቱ እንደተላለፈባት ተመላክቷል፡፡

ግለሰቧ የፈፀመችው ወንጀል ውስብስብ የወንጀል ድርጊት ሲሆን በአጠቃላይ 44 ቢሊዮን ዶላር ወይም 35 ቢሊዮን ዩሮ በመመዝበር የሞት ፍርድ የተፈረደባት የመጀምሪያዋ ቬትናማዊት ሆናለች ነው የተባለው፡፡

ቢሊየነሯ ትሩኦንግ ማይ በተለያዩ ሚስጢራዊ ኩባንያዎቿ የሸሸገችውን ሀብት በመጠቀም የወሰደችውን ገንዘብ የምትመልስ ከሆነ የሞት ፍርዱ ሊቀርላት እንደሚችል ተነግሯል።

በግለሰቧ የክስ ሂደቱ 10 አቃቤ ህጎች እና 200 ጠበቆች መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን 2 ሺህ 700 ምስክሮች ቃላቸውን እንዲሰጡ የጥሪ ወረቀት እንደደረሳቸውና ከ5 ሺህ 400 ኪሎግራም በላይ የሚመዝኑ የሰነድ ማስረጃዎች በ104 ሳጥኖች መቅረባቸውም ተገልጿል።

በቬትናም ታይቶ አይታወቅም በተባለው ግዙፍ የፍርድ ሂደት ከቢሊየነሯ ጋር 85 ሰዎችም ክስ ቀርቦባቸዋል መባሉን የዘጋርዲያን እና ቢቢሲ ዘገባዎች አመልክተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአቶ በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር በመቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ላይ በትውልድ ከተማው መቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እንደተፈፀመ ፋስት መረጃ ከአዲስ ስታንዳርድ አንብበዋል።

አቶ በቴ ማክሰኞ ለሊት ካረፉተብ ሆቴል ተወስደው በርካታ ጥይት ተተኩሶባቸው የተገደሉ ሲሆን ትላንት ጠዋት ላይ አስክሬናቸውን በመቂ ከተማ መንገድ ላይ ተጥሎ መገኘቱ ተገልጿል።

የአራት ልጆች አባት የሆኑት አቶ በቴ በቅርቡ “ከሸኔ እና ፋኖ ታጣቂዎች ጋር በአዲስ አበባ ሁከት እና በጥብጥ በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ከሁለት ሳምንት እስር በኋላ በ100 ሺህ ብር ዋስ መለቀቃቸው ይታወሳል።

@sheger_press
ዕለታዊ ዜናዎች‼️

1፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ ባስቸጋሪ ኹኔታ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ አገራቸው መመለስ ይጀምራል። ኮሚቴው ከዛሬ ጀምሮ ሪያድ እና ጅዳ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን በሳምንት 12 የአውሮፕላን በረራዎችን በማዘጋጀት መመለስ እንደሚጀምር መናገሩን የዘገቡት የመንግሥት ዜና ምንጮች ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የመሩት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን፣ ተመላሾችን ለመለየት በሪያድ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ እና በጅዳ ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጋር ማዕቀፍ አዘጋጅቷል ተብሏል። ኮሚቴው ከሳዑዲ ዓረቢያ ለመመለስ ያቀደው፣ 70 ሺህ ፍልሰተኞችን ነው።

2፤ ብሪታንያ፣ በኦነግ አመራር አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ "አስቸኳይ"፣ "ገለልተኛ" እና "ሙሉ" ምርመራ እንዲደረግና የድርጊቱ ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲኾኑ ጠይቃለች። በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደር ዳረን ዌልች፣ በግድያው ዙሪያ "ፍትህ እና ተጠያቂነት" እንዲሰፍን አሳስበዋል። በኦሮሚያ ክልል በሲቪሎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንዲያበቃ፣ ፖለቲካዊ ንግግር ማድረግ ቁልፉ ርምጃ እንደኾነም አምባሳደር ዌልች በ"ኤክስ" (ትዊተር) ገጻቸው ገልጸዋል።

3፤ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ በአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ በቅርቡ አምስት ሙስሊሞች"በጥይት እሩምታ" እና "በአሰቃቂ" ኹኔታ መገደላቸው እንዳሳዘነው ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ጉባዔው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የኃይማኖት አባቶችና ምዕመናን ላይ "የግፍ ግድያ"፣ "እገታ" እና "ዝርፊያ" እየተፈጸመባቸው ይገኛል ብሏል። መንግሥት በአምስቱ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አጣርቶ ርምጃ እንዲወስድና ንጹሃንን በማገት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚጠይቁ አካላትን በሕግ እንዲቀጣ ጉባኤው ጠይቋል። ጉባኤው፣ የፖለቲካ ድርጅቶች የሐይማኖት ተቋማትን የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም መጠቀሚቸው ከማድረግ እንዲቆጠቡም አሳስቧል።

4፤ ኬንያ፣ የኢትዮጵያ እና ሱማሊያን ውዝግብ ለመፍታት ኢጋድ ለውቂያኖስ ሃብቶች አጠቃቀም ቀጠናዊ የስምምነት ማዕቀፍ እንዲነደፍ ሃሳብ ማቅረቧን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኬንያ፣ ከጅቡቲና ኢጋድ ጋር በመተባበር ያቀረበችው ሃሳብ፣ ወደብ አልባ አገራት ወደቦችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የሚገልጽ ነው። ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የመፍትሄ ሃሳቡን እያጤኑት እንደኾነ የኬንያ ባለሥልጣናት መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የኬንያ ባለሥልጣናት ይህን የተናገሩት፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሱማሊያው አቻቸው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ጋር ትናንት ናይሮቢ ውስጥ ከተወያዩ በኋላ ነው። [ዋዜማ]
2024/10/01 17:29:37
Back to Top
HTML Embed Code: