Telegram Web Link
#ደብረ_ዘይት_የዐብይ_ጾም_አምስተኛ_ሳምንት

#ደብረ_ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል።

#ባጠቃላይ_ደብረ_ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።

#የደብረ_ዘይት_ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩

ከዚሁ ተራራ ላይ ነው #ፈጣሪያችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።

#መልካም_ዕለተ__ሰንበት 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
                         †                         


†      [      ደብረ ዘይት      ]        †

🕊                       💖                   🕊



" እኔ በሕይወቴ ሦስት ነገሮችን ሳስብ እፈራለሁ:: ነፍሴ ከሥጋዬ የምትለይበት ሰዓት ፤ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንድቀርብ መላእክት በሚወስዱኝ ሰዓት ፤ ከፈጣሪም አንደበት የፍርድ ቃል ለመስማት በፊቱ የምትቆምባትን ሰዓት::"

[ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ]

አመ ይመጽእ ወልድኪ መንፈቀ ሌሊት በሥልጣን ፥ አሜሃ ይበክዩ ኃጥአን ፥ ወይትፌሥሑ ጻድቃን ፥ ትብሕም አፍ ወትትዓሠር ልሳን ፤ አሜሃ ዕለተ ያቊመነ በየማን ፤ ምስለ አባግዒሁ ቡሩካን ፥ በደብረ ጽዮን መካን።

†   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †

💖

🕊                       💖                   🕊
🕊

[ ✞ እንኩዋን ከተባረከ ወር "ሚያዝያ" እና ከጻድቁ አባታችን "ቅዱስ ስልዋኖስ" "ወቅዱስ አሮን ካህን" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

🕊    አባ ስልዋኖስ    🕊

ጻድቁ አባ ስልዋኖስ ግብፃዊ ሲሆኑ ከታላቁ መቃርስ መንፈሳዊ ልጆች አንዱ ናቸው:: ገና በሕጻንነታቸው ወደ ገዳም ገብተው ጾምን : ጸሎትን : ትሕርምትን ገንዘብ በማድረግ ታላቅ  የንጽሕና ሰው ሁነዋል::

ከመካከለኛ እድሜአቸው ጀምረው ደግሞ የገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በመልካም እረኝነት አገልግለዋል:: ጻድቁን ለየት የሚያደርጉዋቸው አንዳንድ ተግባራት ነበሩ::

እርሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ገዳማዊ ከጾምና ከጸሎት ባሻገር ሥራ ሠርቶ ማታ መመጽወት አለበት:: ያ ማለት ያለ ምጽዋት ውሎ ማደር አይፈቀድም ነበር:: ይሕም መነኮሳቱን ከጽድቅ ባለፈ ታታሪና ባተሌ አድርጉዋቸዋል::

አባ ስልዋኖስ በተሰጣቸው ጸጋ መላእክትን : ገነትና ሲዖልን ያዩ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ስለ ኃጥአን ከማልቀስ ዐይናቸው ቦዝኖ አያውቅም:: የዚሕን ዓለም ብርሃን አላይም ብለው ቆባቸውን ዓይናቸው ላይ ጥለው በመልካም ሽምግልና በዚሕች ቀን አርፈዋል::

አምላካችን ከጻድቁ በረከት ያሳትፈን::


🕊    ቅዱስ አሮን ካህን   🕊

†  ቅዱስ አሮን ፦
- የሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ወንድም::
- የነቢዪት ማርያም ታናሽ::
- የዮካብድና ዕንበረም ልጅ::
- የእግዚአብሔር ካህን እና
- የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ነው::

† እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የነበረው የክህነት አገልግሎት ከእርሱ ዘር እንዳይወጣ ምሎለታል:: ዳታን : አቤሮንና ቆሬ ይህንን ቢቃወሙ ከነ ሕይወታቸው መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች:: በድፍረት "እናጥናለን" ብለው ወደ ደብተራ ኦሪት የገቡትንም እሳት ከሰማይ ወርዶ በልቷቸዋል::

ቅዱስ አሮንም በጌታ ትእዛዝ በትሩ ለምልማ : አብባና አፍርታ ተገኝታለች:: ይህም ለጊዜው ክህነት ከሱ ልጆች እንዳይወጣ ሲያደርግ በፍጻሜው ለድንግል ማርያም ምሳሌ ሆኗል::

የአሮን በትር ሳይተክሏት : ሳይደክሙባትና ውሃ ሳያጠጣት አብባና አፍርታ እንደተገኘች ድንግል ማርያምም የወንድ ዘር ምክንያት ሳይሆናት ፍሬ አፍርታለች [ክርስቶስን ወልዳለችና]::

አባ ሕርያቆስ "ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን:: ወዓዲ በትር እንተ ሠረጸት : ወጸገየት : ወፈረየት" እንዳለ:: [ቅዳሴ ማርያም]

ቅዱስ አሮን በማዕጠንቱና በመስዋዕቱ ፈጣሪውን አገልግሎ : ድውያንንም ፈውሶ : እስራኤል በበርሃ ሳሉ አርፎ ተቀብሯል:: [ዘኁ.፳፥፳፭]

[ ለተጨማሪ ንባብ ፫ [3] ቱን ብሔረ ኦሪት [ከኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፬ ጀምረው እስከ ኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ ፳ ድረስ] ያንብቡ]

ክብሩ : በረከቱ ይደርብን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አሮን ካህን [የሊቀ ነቢያት ሙሴ ወንድም]
፪. አባ ስልዋኖስ ጻድቅ
፫. ቅዱሳን መነኮሳት
፬. ቅድስት መጥሮንያ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

" ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል:: እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም::" [ዕብ.፭፥፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🕊

[ † እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  ቅዱስ ክርስቶፎሮስ  †    🕊

† ክርስቶፎሮስ ትርጉሙ "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ መሆኑ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ይጠሩ ነበር:: ከነዚህ አንዱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ሃገሩ በላዕተ ሰብእ [ሰውን የሚበሉ] ውስጥ ነበር::

ይህች ሃገር አሁን የት እንዳለች በውል ባይታወቅም የቅዱስ ማትያስ ሃገረ ስብከት በመሆኗ አውሮፓና እስያ ድንበር አካባቢ እንደሆነች ይገመታል::

የአካባቢው ሰዎች ከሰው ሥጋ ውጪ እህልን አይቀምሱም ነበር:: ቅዱስ ማትያስ በነርሱ ያደረውን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ አሳምኗቸዋል::

ከሃገሩ ሰዎችም አንዳንዱ ገጻተ ከለባት [የውሻ መልክ ያላቸው] ነበሩ:: ክርስቶፎሮስም ከነርሱ አንዱ ነበር:: በክርስቶስ አምኖ ከተጠመቀ በሁዋላ በስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ : ስለ ሃይማኖትም ብዙ ጸዋትወ መከራ ተቀብሎ በዚህች ቀን በሰማዕትነት አርፏል::

† ከሰማዕቱ በረከት አምላኩ ያድለን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ክርስቶፎሮስ [ሐዋርያና ሰማዕት]
፪. አባ ስምዖን ዘሃገረ ሐሊባ
፫. ቅዱስ መላልኤል [የያሬድ አባት - ከአዳም ፭ኛ ትውልድ]
፬. እግዚአብሔር ፀሐይን : ጨረቃን : ከዋክብትን ፈጠረ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፬. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፭. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፮. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፯. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

" ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" † [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🕊

[ እንኩዋን ለጻድቁ አባታችን "ቅዱስ መርቄ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ]


🕊    ጻድቁ ቅዱስ መርቄ    🕊

ቅዱስ መርቄ በሁለት ዓለም የተሳካለት ደግ ሰው ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው :-

ቅዱሱ በዓለም የሚኖር ታዋቂ ነጋዴ ነው:: ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንደ አስቸጋሪ ከሚታዩ የሥራ ዘርፎች አንዱ የንግድ ሥራ ቢሆንም እርሱ ግን "ቅዱሱ ነጋዴ" ለመባል በቅቷል::

ለዚህም ምክንያቱ ፪ ነገሮች ናቸው :-

፩. በንግድ ሕይወቱ ማንንም ሳያጭበረብር ከመኖሩ ባለፈ ፍጹም ጸሎትን ጾምንና ምጽዋትን ያዘወትር ነበር::
፪. ለንግድ በተዘዋወረባቸው ሃገራት ሁሉ ስለ ክርስቶስ ያለማቁዋረጥ የሚሰብክ በመሆኑ በርካቶችን አሳምኖ ሐዋርያዊ ክብርን አግኝቷል::

ቅዱስ መርቄ በሕይወቱ ይሕንን ከፈጸመ በሁዋላ አንድ አረማዊ ጉዋደኛ ነበረውና : ሐብት ንብረቱን ሰብስቦ "ጌታችን ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለ ለርሱ ስጥልኝ" ብሎ ላከው::

አረማዊው ጉዋደኛውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ግርማ አግኝቶ ንብረቱን ከእጁ ተቀብሎታል::

አረማዊውም በዚህ ምክንያት ከ፸፭ ቤተሰቦቹ ጋር አምኖ ተጠምቁዋል:: ቅዱስ መርቄ በርሃ ውስጥ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዳዊት ከሰማይ ወርዶ ዘምሮለታል:: መላዕክት በምስጋና ገንዘውት አንበሶች ቀብረውታል::

አምላክ ከቅዱሱ በረከትን ያድለን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቄ ጻድቅ [ክርስቲያናዊ ነጋዴ]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
፫. አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
፬. እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

" እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ::" [ማቴ.፭፥፲፬-፲፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2024/09/30 05:14:42
Back to Top
HTML Embed Code: