Telegram Web Link
🕊

[ † እንኳን ለጥንተ በዓለ ምሴተ ሐሙስ እና ኢዮጰራቅስያ ድንግል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊   †  ምሴተ ሐሙስ  †    🕊

† ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስምንት [1978] ዓመታት በፊት "ምሴተ ሐሙስ" በምትባለው በዚሕች ዕለት :-

፩. በወዳጁ በዓልዓዛር ቤት የዓለማት ፈጣሪ ሲሆን በትሕትና ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል::
፪. ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ ቅዱስ ሥጋውን : ክቡር ደሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥቷል::
፫. በጌቴሴማኒ ላበቱ እንደ ደም እየተንጠፈጠፈ ጸልዮ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ" ሲል አስተምሯል::
፬. ምሽት ፫ (3) ሰዓት አካባቢ ይሁዳ ሊቃነ ካህናቱን አስከትሎ መጥቶ ለ30 ብር አሳልፎ ሰጥቶታል:: [ማቴ.፳፮፥፳፮] (26:26) ዮሐ.፲፫፥፩] (13:1)

ይሕ ሁሉ ለእኛ ድኅነት ተፈጽሟልና ምስጋናና ክብር ለፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን::


🕊 †  ኢዮጰራቅስያ ድንግል †   🕊

† ዳግመኛ በዚህ ዕለት እናታችን ቅድስት ኢዮጰራቅስያ ድንግል አርፋለች::

ቅድስቲቱ በ፭ [ 5 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረች እናት ስትሆን ገና በ9 ዓመቷ ምድራዊ ሐብትን ንቃ መንናለች:: ምክንያቱም ዘመዶቿ የሮም ነገሥታት እነ አኖሬዎስ ነበሩና:: ድንግል ኢዮጰራቅስያ በገዳም : በጾምና በጸሎት : በፍፁም ትሕትናና ታዛዥነት : እንዲሁም በፍቅር ኑራ በዚህች ቀን አርፋለች::

† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላኩዋ ይክፈለን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን ሐዋርያት
፪. ቅድስት ድንግል ኢዮጰራቅስያ
፫. ቅዱስ ፍርፍርዮስ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

† " ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ:: ሥጋዬ እውነተኛ መብል : ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና:: ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም በርሱ እኖራለሁ::"  † [ ዮሐ.፮፥፶፫ ]  (6:53-56)

" እግራቸውን አጥቦ : ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ :: እንዲሕም አላቸው :- 'ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን ? እናንተ መምሕርና ጌታ ትሉኛላችሁ:: እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ:: እንግዲህ እኔ ጌታና መምሕር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባል::' " † [ዮሐ.፲፫፥፲፪-፲፬] (13:12-14)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
                      †                       

[            መድኃኔ  ዓለም             ]

🕊

† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

[ አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ! ]

🕊                       💖                   🕊

" ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት::

ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና:: ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት :: ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ "

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]

🕊

[        መድኃኔ  ዓለም         ]

💖    ድንቅ ትምህርት   💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።" [መዝ.፴፥፫]


🕊                       💖                   🕊
🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ክርስቲያናዊ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ †   🕊

† ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [የመከራ ጊዜ] ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ፵ [40] ዓመታት ዘመቻ አብያተ መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ : ቀርነ ሃይማኖት የቆመው : ብዙ ሥርዓት የተሠራው : ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት : ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት : በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል:: "ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው::

††† ዳግመኛ በዚሕ ቀን የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በሆነው ሞቱ በመቃብር ውስጥ አድሯል::

††† ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: መልካም መሪንም ይስጠን::

🕊

† መጋቢት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ)
፪. ቅድስት እሌኒ ንግስት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

† " እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" † [፩ጢሞ. ፪፥፩-፬

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
#አባ-ጳኲሚስ ዘወትር፣ #አማኑኤል ክርስቶስ፣ የሰው ልጆችን ለማዳን ሲል በዕለተ ዓርብ የተቀበለውን መከራ በማሰብ አብዝቶ ይሰግድ ነበር፤

አንድ ቀን እንዲህ እየሰገደ ከሰውነቱ በሚወጣው ላብ መሬቱን አረጠበው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገለጠለት፤

#አባ_ጳኲሚስም "ጌታዬ እንዲህ የምኾነው አንተን #አገኛለኊ ብዬ ነው" አለው፤

#ጌታችንም በዕለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ታየውና "እኔም አንተን #ለማዳን ብዬ ነው፣ እንደዘህ የተሰቀልኩት" አለው።


[ ታላቁ ቅዱስ ጳኲሚስ - የተጋድሎ ሕይወቱ እና ሥርዐተ ገዳሙ ፤ በወ/ሮ ዘውዴ ገ/እግዚአብሔር ፤ ገጽ፦ ፸፬/74 ፤፳፻፫/


#ሰናይ___ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
🕊

[ † እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †   በዓለ ጽንሰት   †    🕊

† ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች::

በዚሕ ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር:-

፩. ሰማይና ምድርን ፈጠረ:: [ዘፍ.፩፥፩]

፪. በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ [ተጸነሰ]:: በዓሉም "በዓለ ትስብእት" ይባላል:: "አምላክ ሰው : ሰው አምላክ የሆነበት" ማለት ነው:: [ሉቃ.፩፥፳፮]

፫. የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ:: [ማቴ.፳፰፥፩ ፣ ማር.፲፮፥፩ ፣ ሉቃ.፳፬፥፩ ፣ ዮሐ.፳፥፩]

፬.ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚሕች ቀን ይመጣል:: [ማቴ.፳፬፥፩]

††† በነዚሕ ታላላቅና ድርብርብ በዓላት ምክንያት ቀኑ "ርዕሰ በዓላት" [የበዓላት ራስ] : "በኩረ በዓላት" እየተባለም ይጠራል::

† ቸሩ እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ : ከጽንሰቱ : ልደቱና ትንሣኤው በረከትን ይክፈለን:: በጌትነቱም ሲመጣ በርሕራሔው ያስበን::

† ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እልዋሪቆን ገብቷል:: ይህች ሃገር የምድራችን መጨረሻ ናት:: ከዚያ በኋላ ሰውና ሃገር የለም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን የሰበከ ሐዋርያ የለም::

† ከቅዱሱ ሐዋርያ ትጋት : ቅናት : መንፈሳዊነትና ንጽሕና አምላካችን ይክፈለን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]

፩. ጥንተ ዕለተ ፍጥረት [ዓለም የተፈጠረችበት]
፪. በዓለ ትስብእት [የጌታችን ጽንሰቱ]
፫. ጥንተ በዓለ ትንሣኤ
፬. ዳግም ምጽዐት
፭. ቅድስት ማርያም መግደላዊት
፮. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
፯. ቅዱሳት አንስት [ትንሣኤውን የሰበኩ]
፰. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ [ጽንሰታ]
፱. አብርሃ ወአጽብሐ [ጽንሰታቸው]
፲. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ [ጽንሰቱ]
፲፩. ቅዱስ ላሊበላ [ጽንሰቱ]
፲፪. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ [ጽንሰታቸው]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]

" እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል:: ዓይንም ሁሉ : የወጉትም ያዩታል:: የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ:: አዎን አሜን:: ያለውና የነበረው: የሚመጣውም: ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ: አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ይላል::" ††† [ራእይ ፩፥፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2024/09/30 07:27:23
Back to Top
HTML Embed Code: