Telegram Web Link
በሙሉ ስሟ Tyla Laura Seethal በመባል ትታወቃለች ። ደቡብ አፍሪካዊት የአፍሮቢት አርቲስት ነች ።
...
የ22 አመቷ ፡ ታይላ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙዚቃዎቿ ፡ ከአህጉረ አፍሪካ አልፎ ፡ በመላው አለም ተወዳጅ ሆኖላት ግራሚ አዋርድን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን ትናንት ምሽት ተካሂዶ በነበረው የ MTV አዋርድ ላይም Best African Music Performance በሚል ዘርፍ ተሸልማለች ።
......
ታይላ በሙዚቃው ይህን ያህል ስኬታማ ሆና የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ከማግኘቷ በፊት በነበሩት ጊዜያት አንድ የፍቅር ጓደኛ ነበራት ።
እና ጥሩ የፍቅር ጓደኛ ለመሆን በቻለችው መጠን ትሞክር ነበር ። በተቃራኒው የወንድ ጓደኛዋ ደግሞ እያደር ከሷ መሸሽ ጀመረ ። ምንም እንዳላጠፋች ታውቃለች ። ፍቅረኛዋ ለምን እየሸሻት እንደሆነ ገብቷታል ።
.....
ታይላ እንግዲህ እንደምታዩዋት ውብ ነች ፡ ግን ለፍቅረኛዋ ይህ ብቻ በቂ አልነበረም ። እሱ ጥሎበት ተለቅ ያለ መቀመጫና ሞላ ያለ ዳሌ ወዳጅ ነው ።
አንዴ እንደውም አፍ አውጥቶ ፡ ዳሌሽ ሞላ ቢል እኮ ምንም የማይወጣልሽ ልጅ እኮ ነሽ ብሏት ያውቃል ።
......
እና በዚህ ምክንያት እያደር ሸሻት ።
...
ተፈጥሮ በሰጣት ቁመና ምክንያት የምትወደው ሰው ራቃት ።
....
ወራት አለፉ ታይላም ይህንን ሰው ረስታ ስራዋ ላይ ማተኮር ያዘች ።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተለይ Water የሚል ርእስ ያለውን ሙዚቃዋን ከለቀቀች በኋላ ታዋቂነቷ ጨመረ ። ከአፍሪካ አልፎ በአሜሪካና አውሮፓ ሙዚቃዎቿ መደመጥ ጀመሩ ።
....
እና የግራሚ አዋርድ ሰወች በዚህ ሙዚቃዋ አፍሪካን ወክላ እንድትሸለም መረጧት ።
...
የግራሚ አዋርድ መሸለሟን ተከትሎ ወዳጅ ዘመድ እየደወለ እና ቴክስት እያደረገ እንኳን ደስ ያለሽ አላት ። እና ከነዚህ ሰወች መሀከል የአንድ ሰው ቴክስት ይገኝበታል ።
ይህ ሰው የቀድሞ የታይላ ቦይፍሬንድ ነው ። እና በጻፈላት ቴክስት ባገኘችው ስኬትና ሽልማት መደሰቱን ገልጾ ፡ ሪሌሽናቸውን በተመለከተ ማውራት እንዳለባቸው ፡ ዳግም አብረው እንዲሆኑ እንደሚፈልግ ነገራት ። ይህን በተመለከተ ታይላ ስትናገር
.......
ቀጠን ባለው ሰውነቴ ምክንያት የራቀኝ ቦይፍሬንዴ ፡ ከግራሚ በኋላ ይህን ቴክስት ሲልክ ....
ያደገው ዝናዬ እንጂ. ..ሰውነቴ አሁንም እንደምታውቀው ነው. . አንተ ደግሞ ትንሽ ዳሌ አትወድም የሚል ምላሽ ሰጥታው ዳግም አብራው መሆን እንደማታስብ ነግራዋለች ።
....
ከግራሚ በኋላ ይህን ቴክስት ያደረገላት ቦይፍሬንዷ ፡ የትናንት ምሽቱን የ MTV ሽልማት ከሰማ በኋላም ሌላ ቴክስት አርጎላት ይሆናል
ኢቫንጋዲ
ፍቅረማርቆስ ደስታ

ለመግዛት - @Alpha6249
ደራሲ ፍቅረማርቆስ ከተወዳጅ ስራው ከቡስካ በስተጀርባ በመቀጠል ለተደራሲያን ያቀረበው ስራው ነው።ሐመርን ይወቁበት ያንብቡ !
Share

https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
የ ሳውዲው አልጋወራሽ ልዑል ቤተሰብ
80 ለሚሆኑ ጭልፊቶቹ 1(አንደኛ )ደረጃ መዓረግ የአውሮፕላን ቲኬት በመግዛትና በማጓጓዝ የዓለምን ህዝብ አጃኢብ አሰኝቷል


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የአለማችን በእድሜ ትንሹ አባት እንግሊዛዊው Sean Stuart ይባላል። በ 11 አመቱ የልጅ አባት መሆን ችልዋል።

ልጁን የወለደውም ከጎረቤታቸው ልጅ ነዉ


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
በዛን እለት. . አሜሪካዊው ራፐር ቱፓክ ሻኩርና ፡  ገርልፍሬንዱ Kidada Jones ላስቬጋስ ኔቫዳ ውስጥ በሚገኝና ለወራት አብረው በቆዩበት ሆቴል ውስጥ   አንድ ላይ ነበሩ ። እና የሆነ ሰአት ላይ ቱፓክ ሊወጣ ሲነሳ. ..
ወቅቱ ጥቁር ራፐሮች ጎራ ለይተው እርስ በርስ የሚታኮሱበት ስለሆነ. ..ገርልፍሬንዱ  Kidada  ..
" ቱፓክ እባክህ የጥይት መከላከያ ጃኬትህን ልበስ " አለችው. .
ቱፓክ የገርልፍሬንዱ ስጋት ብዙም አልተሰማውምና  ሞቆኛል  በማለት ሳይለብስ ወጣ ።
.....
ከተወሰኑ ሰአታት በኋላም ፡  ቱፓክ የማይክ ታይሰንን የቦክስ ውድድር አይቶ ሲወጣ. .  ባልታወቁ ሰወች ተኩስ ተከፍቶበት. . አራት ቦታ ተመቶ ሆስፒታል መግባቱን  ገርልፍሬንዱ  Kidada .. ሰማች ።
.....
ከስድስት ቀናት የሆስፒታል ቆይታ በኋላም ከዚህ አለም በሞት ተለየ ።
  ቱፓክ በህይወት ዘመኑ 713 ሙዚቃዎችን ሰርቷል .  . በሰባት ፊልሞች ላይ ተውኗል እንዲሁም . . 75 ሚሊየን ቅጂ መሸጥ የቻለ ዝናው በአለም ላይ የታወቀ ራፐር  ሲሆን ፡ አስገራሚው ነገር እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሰራው ፡ በምድር ላይ በቆየባቸው 25 አመታት ነበር ።
......
በዚህ እድሜ ነው እንግዲህ. .. ይህ ሁሉ ስራ !
.....
በአለም ዙሪያ በሚሊየን የሚቆጠሩ የምር አድናቂዎቹ ፡ ቱፓክ  ከዚህ አለም በሞት የተለየበትን ቀን ትናንት አስበውት ውለዋል ።
አንዳንድ ወዳጆቹ ደግሞ. .. ቱፓክ ገርልፍሬንዱ እንዳለችው የጥይት መከላከያ ለብሶ ቢወጣኮ ምናልባት ላይሞት ይችል ነበር እያሉ  ያንን እለት. . በቁጭት ያስታውሱታል ።

ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው  አድናቂዎቹ ደግሞ. እስከዛሬም ድረስ  . የቱፓክን መሞት ማመን አይፈልጉም ።
........
በነገራችን ላይ ይህንን  በወጣትነቱ የተቀጨ ራፐር ብዙዎች ፡ ከዘፋኝም በላይ  የጥቁሮች መብት ተሟጋች እና የሰብአዊ መብት ጠበቃ እንደሆነ ሙዚቃዎቹን እየጠቀሱ ይናገሩለታል ።
.....
RIP LEGEND
ይህንን ያውቃሉ ⁉️

ቁጥሮችን 0 , 1 , 2 , 3 .... ወይም ደግሞ One , Two , Three ... እያላችሁ እስከ 999 ድረስ ብትፅፉ በቁጥሮቹ ስም ውስጥ አንድም የ " A " ፊደል አታገኙም 🤤

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
በጃፓን 90% የሞባይል ስልኮች ውሃ የማይገባባቸው ናቸው ምክንያቱም ወጣቶች ገላቸውን ሲታጠቡም ጭምር ስልኳቸውን ስለሚጠቀሙ ነው !

አጃኢብ ነው ! 😂
Hardcopy ወይንም Pdf ሁለቱንም እኛ ጋር ያገኛሉ !
የመረጡትን መጽሐፍ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ካሉበት ቦታ እንልካለን !
የጊዜ እና የገንዘብ ወጪዎን ያማከለ ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን !

Inbox - @Alpha6249
Call - +251916167999
Share
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
ይህ ሰው ሲግመንድ ፍሩድ ይባላል  ....

ይህ ኦስትሪያዊ ቤተ እስራኤል በስነ ልቦና (psychology ) መስክ ዓለምን ከቀደመ አስተሳሰቧ የቀየረ ነው ሰው ነው .... ይህ ኒውሮሎጂስት ፣ ሳይኮ አናሊስስት  የሆነ ሰው የሰው ልጆችን ጠባያት  በማጥናትና  የአእምሮ ሕክምና በማስተዋወቁ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ያበረከተ ሰው ነው !

ሲግመንድ ፍሩድ ሴቶችን ለሰላሳ አመታት አጥንቶ እንዲ አለ

ሴትን ልጅ ለ30 አመት አጠናሗት ግንምን እንደምትፈልግ ለማወቅ አልቻልኩም ነው ያለው !

እውነት ሴቶች የሚታወቁ ፍጥረቶች አይደሉም ? ሀሳባቹን እስቲ 😁

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
📷በጉግል መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ለየት ያሉ መቀመጫዎች

@Amazing_fact_433
ብታምኑም ባታምኑም

አለም ላይ ካሉት የአንበሶች ቁጥር በላይ ያሉት የአንበሶች ሀውልቶች ይበዛሉ፤ ምን ያህል እንደተመናመኑና የሰው ልጅ ምን ያህል ራስ ወዳድ እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው

@Amazing_fact_433
እጅግ አስፈሪ ስለሆነው #ቤርሙዳ #ትሪግል ምን ያሀሎቻቹ ታቃላቹ? ይህ አስፈሪ የሆነውን ስፍራ እንሆ በጥቂቱ

ሊገለፅ የማይችል እጅግ አሰፈሪ ስፍራ ከ300 በላይ መርከቦች ገብተው የጠፉበት ከ75 በላይ አውሎፕራኖች ደብዛቸው የጠፋበት ቤርሙዳ ትሪያግል ይባላል::

በርካቶች እሚስማሙበት ነገር ቢኖር የሴጣን ምድር ነው በማለት ነው የትኛውም ሳይንቲስት መርከቦቹና አውሎፕራኖቹ ሰምጠው እሚቀሩበትን ምክንያት ማወቅ አልቻለም::

በአትላንቲክ ውቅያኖስ መሀል በአሜሪካዋ ግዛት ፍሎሪዳ አልባድሪ ይገኛል ይህ አከባቢ የ3 ማእዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን ስፋቱም ወደ ሁለት መቶ 70 ሺ እስኩር ማይልስ ይጠጋል;;

አንድ አንድ ሰወች ይህን ሚረጉት የባህር ለይ ጭራቆች ናቸው ሲሉ አንድ አንዶች ደሞ ከሌላ ፕላኔት የመጡ ፍጥረታት ናቸው ይላሉ አንድ አንድ አጥኚዎች ግን በውሀ ውስጥ እሚፈጠር ከባድ አውሎ ንፋስ ነው ይላሉ::

5 ቶፔዶ ቦንብ ጣይ አውሎፕራኖችናአነስተኛ ጀቶች በ1945 የእቃ ማጓጓዣ መርከብ በ1943 al faro የተባለ የእቃ ማጓጓዣ መርከብ በ2015 እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር እነዚና ሌሎች በዚ ሶስማዘን በሚመስል በውሀ በተከበበ ክፍል ጠፍተዋል::

ቦታው እንዳለው ዝና ግን በርካቶች ሊጉበኙት አልቻሉም ሆኖም ግን በየቀኑ ቁጥራቸው የበዛ የንግድ አውሎፕራኖች ሲበሩ ይውላሉ::

ይህ በውሀ የተከበበ ስፍራ ውስጥ ብቻ የሚገኙ እጅግ በጣም አስፈሪ የሆኑ ፍጥረታት ይገኛሉ ከነሱም ውስጥ ድራጎን ፊሽ ባምፓዬር አስኮዴት ጎብልን ሻርክና ባምፓየር ሻርክ በጥቂቱ ናቸው:: ከዚ ቡሀላስ የቤርሙዳ ሚስጥር ይገኝለት ይሆን?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Geelong, Australia የሚገኘው FRANKIE የተባለው የ10 ሳምንታት ዕድሜ ያለው ድመት ባልተለመደ መልኩ 4 ጆሮና 1 ዓይን ይዞ ሊወለድ ችሏል፡፡

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
እውቁ ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ነፍስ ይማር

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ፓፒዮ
ጌታቸው ገብሬ ( ተርጓሚ )
ለመግዛት - @Alpha6249
ሄንሪ ሻሪየ (ፓፒዮ) ባልሰራው ወንጀል ተከሶ እጅግ ስቃይ በበዛበት ወህኒ ይታሰራል። በተደጋጋሚ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ከእስር ለማምለት ሞክሯል። ሄንሪ በህይወቱ እጅግ የተፈተነ ለብዙዎች የፅናት ተምሳሌት መሆን የቻለ ፈረንሳዊ ነው። ይህ የመጀመሪያው ከእስር በፊትና በእስስ ላይ የነበረውን ህይወት የሚዳስስ መጽሐፉ ነው።በፊልምም ያገኙታል። በሕይወት ጎዳና ላይ የሚገጥሙ ሳንካዎችን አልፎ ተስፋ ሳይቆርጡ ውጤታማ ህይወትን ለመኖር የሄንሪን ታሪክ ያንብቡ !
Share

https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
2024/09/28 17:25:54
Back to Top
HTML Embed Code: