Telegram Web Link
⚡️

በቅርብ የተዋወኳት ልጅ አለች። ናርዶስ ትባላለች። እድሜዋ ከ14 ብዙም የሚያልፍ አይደለም።

እንዴት ተዋወኳት?

ከትምህርት ቤት ስመለስ የማልፈው በነሱ በር ነው። ሁሌ በራቸው ላይ አያታታለሁ። ስታየኝ ፈገግ ትላለች። ላለማስከፋት ፈገግታዋን በስስ ፈገግታ እመልስላታለሁ። ትስቃለች።

አንድ ቀን በደጃቸው ሳልፍ በዚሁ ፈገግታ እየሮጠች ወደ እኔ መጣችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ። ጨበጥኳት። አመሰግናለሁ አለችኝ። ድምጿን ስሰማ ደነገጥኩ። ድምጿ እና መልኳ አይገናኝም። ጎርነን ያለ ድምጽ ነው ያላት። ያልጠበኩት ድምጽ ስለሆነ ትኩር ብዬ አየኋት። ፈገግ አለች። ፈገግ አልኩላት። ደስ አላት። እየሮጠች ወደ ቤቷ ገባች።

ሌላ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ ጠብቃ በተለመደው ፈገግታዋ ካስቆመቺኝ በኋላ ሂሳብ ብዙም ስለማይገባኝ እንድታስጠናኛ ፈልጋለሁ አለቺኝ። ድፍረቷ ገረመኝ ደስ አለኝም። ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ነገር አልገጠመኝም።

ጊዜ ስለሌለኝ ሰፋ ላለ ጊዜ ማስጠናት እንደማልችል እና ጥያቄዎች ካሏት ጥያቄዎቹን ልሰራላት እንደምችል ነገርኳት። ለተወሰነ ጊዜ በዚህ መንገድ በራቸው ላይ ሳስጠናት ቆየሁ።

የሆነ ቀን በደጃቸው ሳልፍ የነናርዶስ በር ላይ ግርግር አለ። ጠጋ ብዬ አየሁ። ናርዶስ ለያዥ ለገናዥ  አስቸግራለች።

"ሴት አይደለሁም ወንድ ነኝ። ሴት ብላችሁ አትጥሩኝ ናርዶስ አይደለሁም።"

"አጭበርባሪ ነው ይሄ መንፈስ እያታለለ ነው...

"ፀበል የለሞ እንዴት...

"አንድ ሰው ጋር ደውሉ እንጂ...

እኔ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ። ናርዶስ...

ግቢያቸው ውስጥ አጥር ተደግፋ ወደ ቆመች ሴት ተጠጋሁና ናርዶስ ምን ሆና እንደሆን ጠየኳት።

"ያማታል! ጉብዝናዋ ላይ አሰሩባት። ቁንጅናዋ ላይ እንደዚህ አረጉባት ። ይኸው ትምህርቷን ካቆመች 3አመት ሆነ። እሷን ለማዳን ያልዞርንበት ሃኪም ቤት ያልተንከራተትንበት ፀበል የለም። ግን ምንም ለውጥ የለም።" እንባዋን በስሱ አፈሰሰችው። እንባዋን በመዳፏ ጠረገችና...

"ሁልጊዜም ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት ደህና ትሆናለች።  እንጫወታለን እናወራለን ብዙዙ እናወራለን። ድምጿ እንዴት እንደሚያምር። ምን ያደርጋል ደህንነቷ ከ7 ሰዓት አይዘልም። ውስጧ ያለው መንፈስ ይቀሰቀሳል። ድምጿ ይጎረንናል መንፈሱ ማጥመድ ከሚፈልገው ሰው ውጪ ማንንም አትቀርብም አታወራም።" ብላ ትክዝ አለች።

ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ።

እና እስካሁን ሳስጠና የነበረው እሷን ነው ወይስ እሱን ነው
?

ቀጣዩ ክፍል 200 Like በኋላ ይቀጥላል

Inbox የተላከ እውነተኛ ታሪክ ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💘

"ሁልጊዜም ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት ደህና ትሆናለች።  እንጫወታለን እናወራለን ብዙዙ እናወራለን። ድምጿ እንዴት እንደሚያምር። ምን ያደርጋል ደህንነቷ ከ7 ሰዓት አይዘልም። ውስጧ ያለው መንፈስ ይቀሰቀሳል። ድምጿ ይጎረንናል መንፈሱ ማጥመድ ከሚፈልገው ሰው ውጪ ማንንም አትቀርብም አታወራም።" ብላ ትክዝ አለች።

ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ።

እና እስካሁን ሳስጠና የነበረው እሷን ነው ወይስ እሱን ነው?

ውስጤን ደነዘዘኝ። ያልሞቀ አካሌን ላብ ላብ አለኝ። ብዬ ብዬ ደደብ መንፈስ ላስጠና¡ (ይሄን ቃል ውስጤ እንጂ አንደበቴ አላለውም። ምክንያቱም የሚተነፍስ በድን ሆኛለሁ።)

መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ? ወረረኝ። መላ አካሌን ወረረኝ።

ልጅቷን አይዞሽ ብዬ ዞር ስል ከናርዶስ ጋር አይን ለአይን ተፋጠጥን። ስታየኝ(ሲያየኝ) ፈገግ አለች። አለ። ማማተብ ፈለኩ።

ጣቴን መስቀልኛ ላጣምራት ስል እጄን አሰረኝ። እንዳላማትብ ቆለፈኝ። አሁን በቁጥር የማላስታውሰውን መጠን ያህል አማተብኩ ።

አሁንም የናርዶስ አይን አይኔ ላይ እንደተተከለ ነው። ማማተብ አቃተኝ። እጄ እግሬ ላይ የተሰፋ መሰለኝ። እኔን ስታየኝ ሊይዟት አቅም አነሳቸው መሰለኝ ለቀቋት። ፈገግታዋ እየጨመረ ተጠጋችኝ። 

"እየጠበኩህ ስትቆይብኝ እኮ ...

ሰው ሁሉ ተኣምር የሚያይ ይመስል አፉን ከፍቶ ዙርያችንን ከቦ ይመለከተናል።

"ለምን ቆየህ?"

እ...
"መልስልኝ እንጂ! ለምን ዘገየህ? አንተን አይደል ስጠብቅ የነበረው።"

"ት ን ሽ  ስ ራ  በ ዝ ቶ ብ ኝ  ነ ው!" አፌ ተንተባተበ። ፈቅጄ አልነበረም ቃል ከአፌ የወጣው። ማን አስገደደኝ? ማን አፌን ከፈተው? ማን በዚህ መንገድ እንድመላለስ እግሬን አስለመደው?

"ስለምን ትጎዳኛለህ? ላንተ ስል ስንቱን ትቻለሁ። የምረጋጋው ሳይህ ነው። አቅም የማገኘው ሳይህ ነው።"

ጆሮዬ ይጮኻል። ገላዬ ይጮኻል። የሰው አይን ይጮኻል። መንገዱ ይጮኻል። መኪናው ይጮኻል። ህንፃው ይጮካል።

በዚህ ሰዓት ለኔ ጊዜ የሚቆጥር አይመስለኝም። ለምን? ልቤ ቆሟላ። ስለምን ላስብ? ህይወትን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ማለቴን? መኖር የጭቃ ዳገት ሆኖብኝ ወደ ፈኋላ መፈጥፈጤን? መንገድ ልቤን ሲሰብረው ልቤ እስኪድን ላለመቆም በእግር መሄድ መጀመሬን? በሰይጣን መታጨቴን? ለመንፈስ መገበሬን? ስለምን ላስብ?

ህልም ቢሆን የሚባልላቸው ብዙ ሁነቶች አሉ። ይህም ህልም በሆነ...!

በፍጥነት ገፍትሬያት አልፌያት ሄድኩ። አዳሬን እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ። እንዳፈጠጥኩ ዶሮ ጮኸ። እንዳፈጠጥኩ ወፎች ዘመሩ። እንዳፈጠጥኩ...

በተኛሁበት ልብሴ ፊቴን ሳልታጠብ ስራ ገባሁ። ማስተማር አይበለው! ሁኔታዬ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ተለወጠ። እያስተማርኩ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። የተማሪው ፊት ሁሉ የናርዶስ ፊት መሰለኝ። ድምፃቸው ሁሉ ጎረነነብኝ።

"ሰርዬ እንዴ ሰር ምን ሆነህ ነው?"

"አረ ቢሮ ሰው ጥሩ ሰርዬ...

መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ?

የመጨረሻው ክፍል ነገ ማታ 2 ሰአት ይጠብቁን እስከዛ
👍👍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአለም ለይ ካሉ የሴቶች ብዛት አንፃር ሲታይ የወንዶች ብዛት በ570,000 አከባቢ ይበልጣል ይሄም 101 ወንድ ለ100 ሴት ማለት ነው።

መረጃው የ#Wikipedia ነው

@Amazing_Fact_433
ዮቱብና ቲክቶክ  ትሰራላቹ ግን ድምፃቹን ስትቀዱ በስልካቹ ከጎናቹ ያለ ጫጫታ
በቅጂ ውስጥ እየገባ ቮይሱን አበላሽቶባቹሀል
ለሱ አሪፍ መላ አለን #K_9_ዋይርለስ_ማይክ
አቅርበናል #20_ሜትር_ርቀት_ድረስ_ሚሰራ ቮይስ ስቀዱ የናንተን ድምፅ ብቻ መርጦ ሚወስድ ገመድ አልባ ማይክ
👇#in-box
 @Laday_33

ለተጨማሪ መረጃና ለማዘዝ 🤳ይደውሉልን
☎️  0941546755  0777403952
ይህ ብራዚላዊ እሰረኛ ለ5 ዓመታት ያህል ጊዜ የማምለጫ ጉድጓድ(ቀዳዳ) ቆፍሮ የወጣው ግን የእስር ቤቱ ጠባቂዎች የሚቀመጡበት ክፍል ውስጥ ነበር ።
የመጨረሻ እድለቢስ ስቶን😂

@Amazing_Fact_433
💘(የመጨረሻው ክፍል)

በተኛሁበት ልብሴ ፊቴን ሳልታጠብ ስራ ገባሁ። ማስተማር አይበለው! ሁኔታዬ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ተለወጠ። እያስተማርኩ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። የተማሪው ፊት ሁሉ የናርዶስ ፊት መሰለኝ። ድምፃቸው ሁሉ ጎረነነብኝ።

"ሰርዬ እንዴ ሰር ምን ሆነህ ነው?"

"አረ ቢሮ ሰው ጥሩ ሰርዬ...

መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ?

ተንገዳግጄ ወደ ኋላ ስወድቅ ብላክ ቦርዱ የተሰቀለበት ሚስማር አንገቴን የጎን ወጋው። ደሜ ተንዠቀዠቀ። ክላሱ ደም ለበሰ። የተማሪ ድንጋጤ፣ የተማሪ ጩኸት ለቅሶ በሰመመን ውስጥ ይታየኛል፤ ይሰማኛል። ናርዶስ አይኔ ድቅን አለች። በሃሳብ እይታዬን ጋረደችው። ፈገግ አለች። መድማቴ አስደስቷቷል፤ መውደቄ አርክቷቷል።  ለነገሩ የሳቀችው እሷ አይደለችም እሱ ነው። ደም ነው የሚያስፈነጥዘው፤ ማቁሰል ነው የሚያፍነከንከው።

አፋፍሰው ትምህርት ቤቱ አካባቢ ወደሚገኘው ሆስፒታል ወሰዱኝ። ደሜ በቀላሉ የሚቆም አልነበረም። ከብዙ ርብርብ በኋላ ደሙን አስቁመው የተቀደደውን አንገቴን ከሰፉልኝ በኋላ ወደ ቤቴ ገባሁ።

ቶሎ ሊሻለኝ አልቻለም። ቁስሉ በቀላሉ የሚደርቅ አልሆነም። እለት እለት እንደ አዲስ ቁስል ይጠዘጥዘኛል። ሳምንታት ተቆጠሩ። ወራት እንደቀልድ አለፉ። በተደጋጋሚ ወደስራ እንድገባ ብጠየቅም እኔ ግን አቅም አጣሁ። በቦታዬ ሌላ ሰው ተቀጠረ፤ ልቤ ላይ ሃዘን ተተከለ። ከቤት ሳልወጣ 3 ወር ሞላኝ። እያንዳንዱ ቀን የአመት ያህል የረዘመ። እያንዳንዱ እንቅልፍ በቅዠት የተጠቀለለ። ፀሎት መፅሃፍ ታቅፌ ነው የምተኛው። ቅዠቱ ይቀልልኛል ለትንሽም ሰዓት ቢሆን አረፍ እላለሁ።

"አልናፈኩህም ወይ? መች ነው መተህ የምታየኝ?" አይኔን በጨፈንኩ ቁጥር፣ ለሊት መብራት በጠፋ ቁጥር ዙርያዬን የሚያቃጭል ድምጽ ነው።

"አልናፈኩህም ወይ?
መተህ አታየኝም?
በናፍቆትህ ነደድኩ እኮ? ተቃጠልኩ። ኡ ኡ ኡ ኡኡኡ ኡኡ ኡኡ ኡ ኡ ኡ ኡኡ

በጨለመ ቁጥር አይኔን በጨፈንኩ ቁጥር ጆሮዬ ላይ የሚጮህ ድምጽ።

አይኔን አልጨፍንም። ቀኑን ለሊቱን ሙሉ መብራት አላጠፋም። መብራት ሲጠፋ የሚገድሉኝ፤ አይኔን ስጨፍን የምሞት ይመስለኛል።

ፀሎት ላይ እስከዚህም ነኝ። ምን ብዬ እንደምፀልኝ አላውቅም። የሁልጊዜ ፀሎቴ አንተ እንዳልክ ይሁን ነው። ከዚህ የተለየ ፀሎት የለኝም። አልችም። አለመድኩም። ፆም ላይ ግን ብርቱ ነኝ። በምችለውም በማልችለውም የሚያስጨንቀኝን መንፈስ ታገልኩት።

አንድ ቀን አይኔን እንቅልፍ አሸነፈው። ፀሎት መፅሀፌን  ታቅፌ አይኔን ጨፈንኩ። ስጨፍን ግን ያ የሚያስጨንቀኝ መንፈስ አልነበረም። ዝም ፥ እርግት ፥ ስክን ያለ ስፍራ። ዙርያውን በፅድ ዛፎች የተከበበ። አየሩ እጣን እጣን ፥ መኖር መኖር የሚሸት። ተረጋጋሁ።

ከወራት በኋላ ልቤ የሚረጋበት ቦታ አገኘ። ከፅዶቹ መሃል አንድ አባት እጃቸውን ወደ እኔ እየጠቆሙ ና ይሉኛል። ስጠጋቸው ይርቃሉ። ስጠጋቸው ስጠጋቸው የፅድ ጫካ ውስጥ ገብቼ የለበሱትን ልብስ ስነካ ባነንኩ። ይኸውልህ መሌ 12 አመት ሙሉ ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት የክርስቶስን ልብስ ስትነካ ደሟ እንደቆመ ሁሉ እኔም እኚያ አባት የለበሱትን ልብስ ስነካ ጭንቀቴ ከላዬ የረገፈ ያህል ተሰማኝ።

መታደል ነው። ለካ ስትሞክር ነው የምትታገዘው። ለካ ስትጀምር ነው መንገድ የሚሰጥህ። መንገድ ተሰጠኝ። በህልሜ ያየሁትን ቦታ አቀዋለሁ። ከትውልድ መንደሬ አካባቢ ነው።

የዛሬ ወር ጉዞዬን በህልም ወዳየሁት ቦታ አደረኩ። በህልሜ ወደ ሰከንኩበት በአካልም ወዳማርፍበት ቦታ ሄድኩ።  ከሶስት ሰባት በኋላ በአባቶች ብርቱ ፀሎት በፈጣሪም ፍቃድ ነፃ ወጣሁ። ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል። መሌ እዛ ምን እንደተፈጠረ ሌላ ጊዜ እነግርሃለሁ። ለአሁን ግን የነገርኩህን ፃፈው አስነብበው።
_
_
የጓደኛን ታሪክ ጓደኛ ይወርሳል። የመኖርን መንገድ ተጓዥ ይሄድበታል።

በር ዘግቼ፤ ቀልቤን ሰብስቤ ያለኝን ያለፈበትን የሆነበትን  እያንዳንዷን ቃል ስልኬ ላይ አሰፈርኩ። ፃፍኩ። ሻይ ጠጥቼ ስመለስ የፃፍኩት ሁሉ የለም። ጠፍቷል፤  ተደልቷል። ብቻዬን ነኝ ማን ከስልኬ ላይ ፅሁፉን አጠፋው? ሴቭ አላደረኩትም ነበር? ራሴን ተጠራጠርኩ። ድጋሜ ፃፍኩት። ከቆይታ በኋላ የፃኩት ፅሁፍ ጠፋ። ደነገጥኩ። የሚሆነውን ማመን አልቻልኩም። ቃል በቃል ፅሁፉን ደግሜ ፃፍኩት። ድጋሜ ፅሁፉ እያየሁት ጠፋ።

ደነዘዝኩ።
ለቀናት አይኔን መጨፈን አቃተኝ!

ታሪኩ ተጠናቋል እነደዚህ አይነት መሰል ታሪክ እንዲቀጥል ከፈለጉ በ Like አሳዩኝ በቀጣይ በሌሎች ታሪኮች እንገናኛለን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እነዚህ ሰዎች ፊሊፒንሳዊ አባትና ልጅ ናቸው። ልጁን ያለእናት እያሳደገው እያለ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ጊዜ ጣላውቸው የጎዳና ተዳዳሪ ሆኑ። ነገሮች ከቁጥጥሩ ውጭ ቢሆኑበትም አባትዮው በፍፁም ተስፋ አልቆረጠም።
ይልቁንም ተስፋውን ሁሉ በልጁ ላይ አደረገና ያገኘውን ሁሉ የጉልበት ስራ ሳይመርጥ ቀንና ሌሊት እየሰራ ልጁን አሳድጎና አስተምሮ በማኒላ ዩኒቨርስቲ በዶክትሬት ዲግሪ እንዲመረቅ አስቻለው። ልጁም በምረቃው ቀን እንዲገኝለት ሲልክበት አባትዮው ለአንተ ክብር የሚመጥን አልባሳትና ውበት ስለሌለኝ በጓደኞችህ ዘንድ እንዳላሳፍርህ አልመጣም፤ ከእኔ ጋር መታየትም የለብህም የሚል መልስ ስጠው።

ነገር ግን ልጅዮው የእኔ ክብር አንተ አባቴ እንጅ አልባሳትህና ውበትህ አይደለም፤ ደግሞስ ክብርህንና ውበትህን ያጣኸው እኔን የተከበረና ውብ ለማድረግ አይደለም እንዴ? ታዲያ አንተ ምንስ ብትሆን እኔ በአንተ እኮለራሁ እንጅ እንዴት አፍራለሁ? በማለት አሳምኖ እንዲመጣለት አድርጎ በክብርና በደስታ እያቀፈ ፎቶ ሲነሳ ውሏት!

ክብር ዋጋ ከፍለው ለክብር ላበቁን አባቶች!

ቤተሰቤ ድሀ ሆነ ብላችሁ የምታፍሩባቸው፣ የምሸሿቸው ወይም የምትደብቋቸው ሰዎች ሞላጫ ድሆች እናንተ እንጅ እነሱ አይደሉም
!
አንድ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፌሰር አስማሪው ጋር መናፈሻው ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ፡፡

አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደ ጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው፡፡

ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ፅዶችና ሳሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፤ተማሪው የፅዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ቲቸር ዛሬ አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም? ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል፡፡

አስተማሪውም “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ውስጥ ገንዘብ ከተህበት ና፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡

ተማሪው አስተማሪው እንዳለው ቀስ ብሎ በሰውዬው ጫማ ውስጥ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋር ደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ፡፡ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረዋል ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል፡፡ ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው በኋላ የሁለተኛ እግሩንም ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል፤ ሰውዬው አላመነም!! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ፦
- “ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል? ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳን አውቀህ ነው አይደል? የልጆቼ ዳቦ ማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል? ምስጋና ሲያንስህ ነው ጌታዬ” አለ፡፡ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ከልቡ አዘነ አይኖቹም እንባ አቀረሩ፡፡አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትሪክ ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው፤

ተማሪው እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማሩኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም፤ በህይወቴ የማረሳውን ትምህርት ነው ያስተማሩኝ እውነትም ከመቀበል መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው፡፡

"ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና
!!
እርግጠኛ ነሽ ግን አርግዘሻል?

ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች።

በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣

“እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?

ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል ፡፡

ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅና፣ እምነትህም አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጥ፣ ምክንያቱም የአንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል! የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የእርስዎን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አያነፃፅሩ
!
ይህንን ያውቃሉ ??

በዘመናዊ እግር ኳስ ታሪክ ለ32 የተለያዩ ክለቦች በ11 የአለም ሀገራት በመሄድ በመጫወት ሪኮርድ ይዞ የሚገኘው የቀድሞ የኡራጋይ ብሔራዊ ተጫዋች የነበረው በ 44 አመቱ እግር ኳስ በቃኝ በማለት ጫማ የሰቀለው Sebastian Abreu ነው ።
አንድ ሰው በሰዓት ውስጥ በአማካኝ 15.7 ጊዜ ፊቱን ይነካል

@Amazing_fact_433
ይህን ሰው ተዋወቁት ኢድሪስ ዴቢ ይባላል የቀድሞ የቻድ ፕሬዚዳንት የነበረ ሲሆን እንደ ዋዛ ስልጣን ላይ ከወጣ ሰላሳ አመት አስቆጥሮ ነበር !

እንደ ማንኛውም አፍሪካዊ መሪ ስድስት ግዜ ምርጫ አጨበርብሮ ተመርጧል።ለድስተኛ ግዜ ምርጫ ካሸነፈ በኃላ የተሰማውን ደስታ ከመግለፁ በፊት ወጥረው ከያዙት አማፂያን ጋ የሚዋጋውን ወታደር ለመጎብኘት ወደ ግንባር ሄደ። ነገር ግን አማፂያኑ ግምባር ላይ ግምባሩን ብለው ገደሉት።
አንድን ወረቀት 42 ጊዜ ብታጥፉት የታጠፈው የወረቀት ቁመት ከመሬት ጨረቃ ይደርሳል። እውነታው ግን ከ7 ጊዜ በላይ ማጠፍ አትችሉም!

@Amazing_fact_433
እንግሊዝኛን እየተዝናኑ መማር ይፈልጋሉ!

እንግሊዝኛን በጥያቄ መልክ እና በተለያዩ አይነት ትምህርቶች መልክ ለመማር ከሺዎች በላይ ተከታይ ያለውን ቻናላችንን በመቀላቀል በጥያቄዎች ዘና ይበሉ! 👇

https://www.tg-me.com/+zyNM7Bj-YUAyZmM0
https://www.tg-me.com/+zyNM7Bj-YUAyZmM0
#News ወይም ዜና የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ምህፃረ ቃል ሲሆን የአራቱን አቅጣጫዎች ማለትም "North" "East" "West" እና "South" የመጀመሪያ ፊደላት በማቀናጀት የተፈጠረ ቃል ነው ።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
አንድን ወረቀት 42 ጊዜ ብታጥፉት የታጠፈው የወረቀት ቁመት ከመሬት ጨረቃ ይደርሳል። እውነታው ግን ከ7 ጊዜ በላይ ማጠፍ አትችሉም! @Amazing_fact_433
አልገባንም ላላችሁ እና ለምትሳደቡ😁 ሌላም ልጨምርላችሁ

ወረቀቱን 103 ጊዜ ብታጥፉት ከመላው observable universe (አጥናፍ አለም) diameter ይበልጣል

👉 የአንድ የወረቀት thickness ወይም ውፍረት በአማካይ 0.088 mm ወይም 0.000088m ይሆናል። ታዲያ አንድ ጊዜ አጠፋችሁት ማለት ውፍረቱን በ 2 አባዛችሁት ማለት ነው። ድጋሜ ስታጥፉት ደግሞ በ2 ያባዛችሁትን ውፍረት ድጋሜ በ2 አባዛችሁት ወይም ደብል እያደረጋችሁት ነው። ይህም ማለት 42 ጊዜ ስታጥፉት 42 ጊዜ ውፍረቱን ደብል እያደረጋችሁ ወይም በ2 እያባዛችሁት ነው

አጠቃላይ ያለው የወረቀቱ ውፍረት (thickness) 2^(42)*0.000088 m = 387,028,092.97715 ወይም 387,028 km ይሆናል።

በመሬትና በጨረቃ መካከል ያለው ርቀት ደግሞ 384,400 km ነው ስለዚህ የወረቀቱ thickness በመሬትና ጨረቃ መካከል ካለው ርቀት በለጠ ማለት ነው
የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?
ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?

‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ ኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት፡፡

በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አወቅከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት፡፡

ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ
እኔም ለምን አልኩት
እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡

ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው፡፡
ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም
፡፡
ታይሰን በአንድ ወቅት ዶናልድ ትራምፕን ቀጥሯቸው ነበር ፨
...
ከአመታት በፊት ፡ ላስቬጋስ ውስጥ በሚገኝ ሆቴል ፡ አንድ ክፍል ውስጥ ውድ የሆነ LV ( ሉዊ' ቪቶን ) ብራንድ ቦርሳ ተገኘ ።

የሆቴሉ ሃላፊዎች በክፍሉ ውስጥ የተገኘውን ቦርሳ ሲከፍቱት በውስጡ አንድ ሚሊየን ዶላር ነበረበት ።
......
ወዲያው በክፍሉ ውስጥ አድሮ ፡ አንድ ሚሊየን ዶላር ፡ የሚያህል ገንዘብ እንደቀልድ ረስቶ ወደሄደው ሰው ተደወለ ።

" ሃሎ ማይክ ፡ ያደርክበት ሆቴል ክፍል ውስጥ እቃ ሳትረሳ አልቀረህም "

ታይሰን ልክ ይህን ሲሰማ እንዲህ አለ ....

ኦው ፡ ልክ ናችሁ ገንዘብ ረስቻለሁ ።
.....
ታይሰን ማለት እንዲህ ነው ። ሚሊየን ዶላር ረስቶ እስኪያስታውሱት የሚጠብቅ ።
...........
በ1990 ዎቹ በስፖርቱ ዘርፍ የምድራችን ከፍተኛ ተከፋይ የሆነውና በአንድ ወቅት ሚስቱ ለነበረችው ሴት ፡ 2.2 ሚሊየን ዶላር አውጥቶ ከወርቅ የተሰራ የመታጠቢያ ገንዳ በመግዛት ስጦታ የሰጠው. ....
እጅግ ዘናጭ እና መርጦ ለባሽ በመሆኑ ፡ በዛን ወቅት በየወሩ ከመቶሺህ ዶላር በላይ ፡ ለልብስና ለጌጣጌጥ ያወጣ የነበረው ታይሰን ...... በቤቱ ውስጥ እንደውሻና ድመት እየደባበሰ የሚያሳድጋቸው ሶስት ነብሮች የነበሩት ሲሆን ለነዚህ እንስሳትም ወጭ ከፍተኛ በጀት መድቦ ነበር ።
........
እንግዲህ ...... ገንዘብ ራሱ ፡ ታይሰንን እያሳደደ በሚይዝበት በዚህ ወቅት ነበር ፡ ሀይለኛ የቢዝነስ ማይንድ የነበራቸውን ሚሊየነሩን ነጋዴ ዶናልድ ትራንፕን የፋይናንስ አማካሪ አድርጎ የቀጠረው ።

ኋላ ላይ የአሜሪካን ፕሬዝደንት የሆኑት ትራምፕ ፡ በዚህ ከታይሰን ጋር በሚሰሩበት ወቅት ፡ የተለያዩ ውሎችን እና ስራዎችን ታይሰንን ወክለው ከመፈረም ጀምሮ ፡ አጠቃላይ የፋይናንስ ጉዳዮችን ያማክሩት ነበር

........

Viva wassuhun tesfaye
ጃፓኖቹ ጥንዶቸ ተጋብተው በሞቀ የትዳር አለም እየኖሩ ነበረ።

በሁለተኛው አለም ጦርነት ምክንያት ባል እና ሚስት ይጠፋፋሉ።

ሚስት ከባሌ ሌላ ማንንም ወንድ አላይም ፣አላገባም በማለት ለ54 አመት ባሏን በመፈለግና በመጠበቅ ትቆያለች።

ሚስት ብቻዋን እየኖረች ተስፋ ሳትቆርጥ ባሏን ፈልጋ አፈላልጋ ከተለያዩ ከ54 አመት በኋላ ባሏን ታገኘዋለች።

እቺ ታማኝ ሚስት ባሏን ለሀምሳ አራት አመት በትዕግሥት ፣በናፍቆት ስትጠብቀው ቆይታ፤ ባሏ ግን ሌላ ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ እና አያት ሆኖ አገኘችው።

የትዳር ቃል ኪዳን አክባሪ፣ለባሏ ታማኝ፣ትእግስተኛና አሳዛኝ የፍቅር ንግስት ነች!!
2024/11/17 07:38:04
Back to Top
HTML Embed Code: