Tikvah-University
Photo
#ETQRA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2017 የትምህርት ዘመን በከተማዋ ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

በአዲስ አበባ ለ2017 የትምህርት ዘመን የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው 125 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል።

(የትምህርት ቤቶቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ
#EthiopianAviationUniversity

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ዘርፍ የአቪዬሺን መስክ ስልጠና ለግል አመልካቾች ይሰጣል።

ለግል አመልካቾች የሚሰጡ ስልጠናዎች፦

➧ የኤርፖርት መንገደኞች አገልግሎት የኤጀንትነት ስልጠና
➧ የአየር መንገድ የስልክ ማዕከልና የቲኬት አገልግሎት የኤጀንትነት ስልጠና
➧ የካርጎ አገልግሎት የኤጀንትነት ስልጠና

ስልጠናዎቹ ዕውቅና ያላቸው፣ እጅግ ዘመናዊ በሆነ የተግባር መለማመጃ እና ልምድ ባላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሰጡ መሆኑ ተገልጿል።

ለማመልከት 👇
https://eau.edu.et/admission/applyonline

ለበለጠ መረጃ 👇
- [email protected]
- [email protected]
- ስልክ ቁ. 0115174600 / 0115178598

@tikvahuniversity
* አፋልጉኝ

" ማክሰኞ (11/10/2016) ከሰዓት በኋላ ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ መንገድ ላይ በርካታ ዶክመንቶች ጠፍተውብኛል።

- የትምህርት ማስረጃዎች
-የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪና
- የድሮ ፖስፖርት
- student copy
- የዩንቨርስቲ acceptance እና
ሌሎች ማስረጃዎች ጋር ካኪ ፖስታ ውስጥ አብሮ ጠፍቶበብኝ።

ያገኘ ሰው ካለ ይተባበረኝ።

የትምህርት መረጃው ላይ ያለው ስም ሻሎም ንጉሤ ተክሌ (Shalom Nigussie Teklie)

ስልክ ቁ፡ 0921787893 ወይም 0912665211

አመሠግናለሁ። "

(ሻሎም ንጉሴ)

@tikvahethmagazine
በሀረሪ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

76 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 5,350 ተማሪዎች ለፈተናው መቀመጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ነገዎ ገልፀዋል።

ፈተናው በ29 የፈተና ጣቢያዎች ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

ለፈተናው የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከባለድረሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች እና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ተብሏል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
20% ቅናሽ 4 ቀናት ቀሩት

የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ (Computer Programming) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!

👉 100 % በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርትን አካቶ የሚሰጥ
👉 C++, Java እና Python ፕሮግራሞች ከፍ ባለ ደረጃ (Advanced Level) በጋራ የሚሰጡበት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1 ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Welcome to Courageous Conversations!

Join us for a youth-led discussion series that tackles workforce development issues head-on. This session focuses on upskilling and reskilling for future job markets, exploring key areas like:

- Identifying in-demand jobs
- Accessing training and education
- Tech skills and digital literacy
- Entrepreneurial mindset

Date: Saturday June 29, 2024
Time: 8:30 AM-1:00 PM EAT, 2:30 PM-7:00 PM LT
Location: In person, at Ramada Hotel
Registration link: https://forms.gle/ZjRzHcXju4EoiLhYA

Let's address youth unemployment challenges and find solutions together. See you there! Women and Persons with disability and vulnerability are highly encouraged to attend! Your voices matter!

#CourageousConversations #YouthLed #WorkforceDevelopment #Employment #Upskilling #DigitalLiteracy #Entrepreneurship
Tikvah-University
መንገሻ አየነ (ዶ/ር) የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ፡፡ መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ከሰኔ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን ሰኔ 10/2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል፡፡ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን…
አዲስ የተመደቡት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች በተገኙበት ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የሴኔት አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ራስ ገዝ ማድረግ፣ አዲሱን ተቋማዊ የሰራተኞች የሥራ ምደባ ማስፈጸም እንዲሁም የተቋሙን የምርምር ዩኒቨርሲቲነት እውን ሊያደርጉ የሚችሉ ተግባራትን ማከናወን ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

የነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 2 እና 3/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

አዲስ የPGDT ኮርስ ተመዝጋቢዎች ምዝገባ ከሰኔ 25-30/2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የክረምት ትምህርት ከሐምሌ 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አድርሰውናል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ሲሉ መልሰውልናል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተና ለወሰዱ ተፈታኞች ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡

በዚህም ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ላይ እንደሚሰጥ ተፈታኞች እና ፈታኞች እንዲያውቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ዛሬ ከሰዓት ፈተናውን እንደሚወስዱ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MekelleUniversity

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የተሰጡት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተናዎች ከተዘጋጀው ብሉ ሪንት ውጪ በመሆናቸው ፈተናዎቹ በድጋሜ እንዲሰጡ ተፈታኞቹ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ተወካይ በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ አመራሮች ጋር የተወያየ ሲሆን፤ ፈተናዎቹ ከብሉ ፕሪንት ውጪ እንደተዘጋጁ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ Management የመውጫ ፈተና በተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት መሰረት የተዘጋጀ እንዳልነበር በርካታ ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ለ74ኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

@tikvahuniversity
2024/06/26 00:15:59
Back to Top
HTML Embed Code: