Telegram Web Link
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡

የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ለፈተናው በድጋሜ የሚቀመጡ ተማሪዎች ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና ይወስዳሉ፡፡

ተፈታኞች የማኔጅመንት፣ የጂኦሎጂ እና የሕዝብ አስተዳደርና ዴቨሎፕመንት ማኔጅመንት ፈተናዎችን ዛሬ ሙሉ ቀን የሚወስዱ ይሆናል፡፡

ተሻሽሎ የወጣው የመውጫ ፈተና መርሐግብር፤ ሀገር አቀፍ ፈተናው እስከ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል፡፡

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

በተለያየ ምክንያት ዛሬ የተሰጡትን የ Management, Business Administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship ፈተና ያልወሰዳችሁ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደየተመደባችሁበት ተቋም በመሔድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሁሉም ተፈታኞች User Name Password በመያዝ ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣቢያ መገኘት እንዳለባችሁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል ላለፉት ሁለት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተጠናቋል፡፡

በክልሉ ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መጠናቀቁን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከ170 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ከዚህ ቀደም ያሳወቀው ቢሮው፤ ምን ያህሉ ፈተናው እንደወሰዱ አልገለፀም።

በክልሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ለፈተናው ምዝገባ አለማድረጋቸው ይታወቃል።

@tikvahuniversity
አዲስ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ወደ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ።

አዋጁ የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርትን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በፍትሐዊነት ለማዳረስ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር እና የትምህርትን ጥራት፣ ተደራሽነት እና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁ የትምህርት አግባብነትን፣ ስርዓተ ትምህርትን፣ የትምህርት ተቋማት አደረጃጀትን እና መምህራንን የሚመለከቱ ሙያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የያዘ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የትምህርት ተቋማት ደረጃ ማውጣትን እና ከመንግሥት ውጭ ባሉ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚደረግ ቁጥጥርን በተመለከተ ድንጋጌዎችን አካቶ የቀረበ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑ የሚኒስትሮች ም/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ምክር ቤቱ በቀረበው አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 5ኛ አመት ተመራቂ ተማሪዎች " ከሁለት አመት በፊት Add አድርገን መጨረስ የምንችላቸውን ኮርሶች በዩኒቨርሲቲው ምክንያት ባለመውሰዳችን የመውጫ ፈተና ላይም መቀመጥም ሆነ የመመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንዳንገኝ ዩኒቨርሲቲው ወስኖብናል " በማለት ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አቅርበዋል።

" ከሁለት አመት በፊት ከ በግዜው በኮቪድ ምክንያት በክረምት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ ተማሪዎች ጋር አድ አድርገን መጨረስ እንችል ነበር " ያሉት ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ከመደበኛ ተማሪዎቹ ጋር መማር አትችሉም የሚል ህግ አውጥቶ እንዳይማሩ እንዳገዳቸው አሳውቀዋል።

በክረምት መማር አትችሉም የተባሉት ተማሪዎች በቀጣዩ አመት ነገሮች እንዲመቻች ይደረግላችሁኋል በማለት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕ/ት ቃል ገብተውላቸው እንደነበር አስረድተዋል።

ከዛ በኋላ መስከረም ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕ/ት ሂዱና የትምህርት ክፍላችሁን አናግሩ በማለት መፍትሄ እንዳልሰጧቸው እና በድጋሚ የቀሩትን ኮርሶች በቀጣዩ ክረምት ትወስዳላችሁ ተብሎ ቃል ቢገባላቸውም ቃሉ እንዳልተጠበቀላቸው ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎም ኮርሶቹን ባለመጨረሳቸው ለመውጫ ፈተናም መቀመጥ እንዳይችሉ እንደተደረጉ የገለፁት ተማሪዎቹ በተጨማሪም የምረቃ ስነስርዓት ላይ እንዳይገኙ እንደተወሰነ ጠቁመዋል።

ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መፈተን እንዳይችሉ ከመደረጋቸው ባሻገር "ቤተሰብ ይመረቃሉ ብሎ ቢጠብቀንም መመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንኳን እንዳንገባ ወስነውብናል" የሚል ቅሬታቸውን በማቅረብ ዩኒቨርሲቲው ይህንን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ በሚገኙ 183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከሰኔ 12-14/2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠው ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈተናቸውን በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ገልፀዋል፡፡

በአማርኛ ስርዓተ ትምህርት ለሚማሩ ተማሪዎች በአምስት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
#ማስታወሻ

ትናንት የተሰጡትን የ Management, Business Administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship የመውጫ ፈተና በተለያየ ምክንያት ያልወሰዳችሁ ተፈታኞች ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደየተመደባችሁበት ተቋም በመሔድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች User Name Password በመያዝ ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣቢያ መገኘት አለባችሁ ተብሏል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ማዕከል የመጀመሪያ ዙር 60 ሰልጣኞችን መቀበል ጀምሯል።

ምዝገባው የሚያበቃው፦
ሰኔ 19/2016 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
CSSH ህንጻ 1ኛ ፍሉር R-10

ለተጨማሪ መረጃ፦

0977945129 / 0916159720
Email: [email protected]

@tikvahuniversity
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተናዎች እየተሰጡ ነው፡፡

የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እና በድጋሜ ተፈታኞች ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

የአካውንቲንግ እና ሕግ ፈተናዎችን ጨምሮ የሰባት ትምህርት አይነት ፈተናዎች ዛሬ ሙሉ ቀን እየተሰጡ ነው፡፡ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው እስከ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ምስል፦ ቦረና፣ አዲግራት እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲኖሩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑ ተሠማ።

የዩኒቨርስቲው መምህራን በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል። 

ለመምህራን ሳይከፈል የቀረው የ17 ወር ደመወዝ ዘንድሮ “ይከፈላል ተብሎ እየተጠበቀ” መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ውዝፍ ክፍያው ከተፈጸመ በኋላ ወደ ተማሪዎች መኖሪያ እንዲገቡ የተደረጉት መምህራን፤ ዶርሞቹን ሊለቁ እንደሚችሉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዝርዝር ዘገባን ያንብቡ፦
https://ethiopiainsider.com/2024/13369/

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ለ Fulbright African Research Scholars Program (FARSP) ያመልክቱ!

የዩኒቨርሲቲ መምህር ነዎት? ምርምርዎትን በዩናይትድ ስቴትስ ማከናወን ይፈልጋሉ?

ዓመታዊው የፉልብራይት አፍሪካ የምርምር ምሁራን ፕሮግራም (FARSP) 2025/26 ለአመልካቾች ክፍት ነው፡፡

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም

ለማመልከት 👇
https://apply.iie.org/fvsp2025

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 👇 [email protected]

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
2024/09/28 20:55:51
Back to Top
HTML Embed Code: