Telegram Web Link
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የፋሽን ቴክኖሎጂና ዲዛይን ትምህርት ስልጠና በዚህ ዓመት ይሰጣል።

የፋሽን ቴክኖሎጂና ዲዛይን ስልጠና በገበያው ተፈላጊ በመሆኑ በተያዘው ዓመት በደረጃ ስድስት ለመስጠት መወሰኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በደረጃ ስድስት በ21 መስኮች እንዲሁም በደረጃ ሰባትበ19 የስልጠና መስኮች ስልጠና እንደሚሰጥ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በአጭር ጊዜ ስልጠና የሚሰጡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የሮቦቲክስ እና ሌሎች የስልጠና መስኮችን ወደ መደበኛ የስልጠና መስክ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በባዮ-ሜዲካል ቴክኖሎጂ፣ ኤቪዬሽን፣ ማዕድን እና ባቡር ኢንጂነሪንግ መስኮች ስልጠና ለመስጠት የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እየተደረገ መሆኑንም ለኢፕድ ገልፀዋል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በፌዴራል ደረጃ ከደረጃ ስድስት ጀምሮ ስልጠና የሚሰጥ ተቋም ነው።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የፕሮግራሚንግ ክህሎትንና የዲጂታል ዕውቀትን የሚያጎለብት የፕሮግራሚንግ መፅሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ለህትመት በቅቷል።

C++ Programming in Amharic የተሰኘው መፅሐፉ፥ በዘርፉና በሶፍትዌር ማበልፀግ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ዮሐንስ እዘዘው የተፃፈ ነው።

346 ገፆች ያሉት መፅሐፉ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን፣ መምህራንን እና የዘርፉ ተመራማሪዎችን በፕሮግራሚንግ ቋንቋ ዙሪያ እንደሚጠቅም ፀሐፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

መፅሐፉ በነፃ የቀረበ ሲሆን፤ በኦንላይን https://www.tg-me.com/eteldigital ሊያገኙት ይችላሉ ብለዋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
#ማስታወሻ

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ፣ የሦስተኛ እና የአራተኛ ዓመት ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 20 እና 21/2017 ዓ.ም ይካሔዳል።

በቅጣት ምዝገባ፦ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦ ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለምትመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ በቅርቡ ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
"በአምስት ዓመት መመረቅ ሲገባን አንድ ዓመት ተጨምሮብናል" - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኤክስቴንሽን ተማሪዎች

"መውሰድ ያለባቸውን ቀሪ ኮርሶች አጠናቀው ሲጨርሱ ይመረቃሉ" - የዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር


በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ በተለይ የአካውንቲንግ፣ ኢኮኖሚክስ እና ማኔጅመንት የኤክስቴንሽን ተማሪዎች "መማር ካለብን አምስት ዓመት ውጪ አንድ ዓመት ተጨምሮብን የምንመረቅ መሆናችን ተነግሮናል" የሚል ቅሬታ ለቲክቫህ አድርሰዋል።

"ስንጀምር ሰኔ 2017 ዓ.ም እንደምንጨርስ አውቀን ነበር ወደጊቢው የገባነው። በህጉ መሰረት ኤክስቴንሽን ተማሪ አምስት ዓመት ነበር መማር ያለበት። ነገር ግን በዚህ ዓመት አትመረቁም ተብለናል" ብለዋል ተማሪዎቹ።

ያልጨረሱት ኮርስ መኖሩን በዩኒቨርሲቲው የተገለፀላቸው ተማሪዎቹ፤ በኮቪድ-19 ወቅት ሦስት ሴሚስተር መማር ሲኖርባቸው አንድ ሴሚስተር ብቻ መማራቸውን ያነሳሉ።

"ይሁንና ተቋሙ ማካካሻ ትምህርት ሰጥቶ ሊያስመርቀን ሲገባ በወቅቱ ምላሽ ሳናገኝ፥ ቅሬታችንን የሚቀበለን አካል አጥተን ቆይተናል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የጠየቃቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ሀርካን ማሞ፥ በተማሪዎቹ ላይ አንድ ዓመት አለመጨመሩን ገልፀዋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት ተማሪዎቹ ዘግይተው ግንቦት 2013 ዓ.ም ላይ ትምህርት መጀመራቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ "ተማሪዎቹ በዓመት ሦስት ሴሚስተር ነው የሚማሩት፥ በገቡበት ዓመት ደግሞ አንድ ሴሚስተር ብቻ ነው የተማሩት" ብለዋል።

"እነሱ የገቡት ግንቦት ወር ላይ ነው። የዘለሉት ሁለት ሴሚስተር አለ። ምንም የተጨመረ ነገር የለም።" "ኮርሶችን ሳይጨርሱ መመረቅ ስለማይችሉ፥ ቀሪ ኮርሶቻቸውን አጠናቀው ይመረቃሉ" ብለዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር ዘሪሁን ክንፈ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተማሪዎቹ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የዘገየ በመሆኑ ወደ ሰኔ አካባቢ ትምህርት መጀመራቸውን አስታውሰዋል።

በተገለፀው ዓመት መማር የነበረባቸውን ሁለት ሴሚስተር አለመማራቸውንም አስረድተዋል።

ተማሪዎቹ የእረፍት ቀናት እና የማታ መርሐግብር በመሆናቸው በዓመት ውስጥ የክረምት ሴሚስተርን ጨምሮ ሦስት ሴሚስተር ስለሚማሩ፥ የማካካሻ ጊዜ እንዳልነበረ አንስተዋል።

ለተማሪዎቹ በ2017 ዓ.ሞ ጨርሳችሁ ትመረቃላችሁ ብሎ የገለፀ አካል አለመኖሩን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ መውሰድ ያለባቸውን ቀሪ ኮርሶች አጠናቀው ሲጨርሱ ይመረቃሉ ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመልካቾችን በመቀበል ላይ ነው።

ኢንስቲትዩቱ (BDU-EITEX) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎችን ይቀበላል።

የትምህርት መስኮች
- Textile Engineering
- Garment Engineering
- Leather Product Engineering
- Fashion Design
- Textile & Apparel Merchandising
- Visual Art
- Textile Chemical Process Engineering

የማመልከቻ ጊዜ፦
ከጥቅምት 18-27/2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ፦ 0938882020

ለ2017 ዓ.ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች በዝውውር ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

ኦንላይን ለማመልከት 👇
https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#DebreTaborUniversity ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተቋሙ መሔድ ያልቻለችሁና ዊዝድሮዋል…
#Update

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበሩ የተቋሙ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ምዝገባ ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወቃል፡፡

በ2016 ፍሬሽማን አንደኛውን ሴሚስተር መምጣት ሳትችሉ የቀራችሁ ወይንም ዊዝድሮዋል ሞልታችሁ የወጣችሁ (አንደኛውን ሴሚስተር ያልተማራችሁ) ተማሪዎች ጥሪው አይመለከታችሁም፡፡ እናንተ ከ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር ጥሪ ይደረግላችኋል።

በ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ ነገር ግን በ2016 ዓ.ም መምጣት ያልቻላችሁ በዚህ ሰዓት የናንተ ባች ስለሌለ መሔድ የለባችሁም ተብሏል፡፡

በ2015 ዓ.ም ሦስተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ ነገር ግን በ2016 ዓ.ም መምጣት ያልቻላችሁ የመግቢያ ቀን ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#MekelleUniversity

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ያመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በመሆኑም የኅብረተሰብ ጤና ማስተርስ ፕሮግራም (MPH) ለመማር ያመለከታችሁ ከ Epidemiology ትምህርት መስክ በስተቀር በተገለፀው ቀን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠዋት 2፡30 በመገኘት የመግቢያ ፈተናውን እንድትወስዱ ተብሏል፡፡

ተፈታኞች ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ውጤታችሁን መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
💫 ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እይቀረብን ነው! ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት! 👏

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት እና ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
"ሳይ-ገርልስ" (Sci-Girls) የተሰኘና ሴት ተማሪዎች እና መምህራን የሚሳተፉበት ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው ስልጠና፤ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ከ9ኛ-10ኛ ክፍል የሆኑ 40 ሴት ተማሪዎች እና መምህራን እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስልጠናው ሴቶች በሳይንስ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ የሚያግዝ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቤተልሄም ንጉሴ (ኢ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

Akira Interactive የተባለ ተቋም በተለያዩ የሥራ መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

► የሥራ መደብ፦ የሙሉ ጊዜ የግራፊክስ ዲዛይነር (ብዛት 1) እና የማርኬቲንግ ባለሞያ (ብዛት 1) እንዲሁም በኢንተርነት የግራፊክስ ዲዛይነር (ብዛት 1) እና የማርኬቲንግ ባለሞያ (ብዛት 1)
► ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ 12ኛ ክፍል የጨረሰ/ችና ለሙያው ከፍተኛ ዝንባሌ ያለው/ያላት
► የሥራ ቦታ፦ CMC የተባበሩት አደባባይ

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሦስት (3) የሥራ ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የማመልከቻ ቦታ፦
በቴሌግራም ፖርትፎሊዮ እና ሲቪ በመላክ ወይም ስልክ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
ስልክ ቁጥር፦ 0938352532
ቴሌግራም Username: @NSFL100
Tikvah-University
Photo
#Update

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 መሆኑ ተገልጿል፡፡

አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት

@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ኮንሰርቲየም ተመስርቷል፡፡

በተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ መሠረት በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የተለዩ 15 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው የኮንሰርቲየም ምስረታውን ያካሔዱት፡፡

የኮንሰርቲየሙ የመመስረቻ ሰነድ የፀደቀ ሲሆን፤ አምስት አባላት ያሉት የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫም ተካሒዷል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በሥራ አስፈጻሚነት ተመርጠዋል። የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) የኮንሰርቲየሙ ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ኮንሰርቲየሙ ዩኒቨርሲቲዎች ሀብትን በጋራ ለመጠቀም፣ የጥናትና ምርምር፣ ስርዓተ ትምህርት ቀረጻ እና የፕሮግራሞች ልማት ሥራዎችን በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ነጥብ ያሰመዘገባችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ መያዝ የሚኖርባችሁ፦
▪️ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ
▪️ አራት 3x 4 ፎቶግራፍ

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከምፓስ

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ባለፈው ዓመት የሰጡትን የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) የወሰዳችሁ ተፈታኞች የውጤታችሁን ዲጂታል ኮፒ መውሰድ እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ተከታዩን ሊንክ በመጠቀምና የማማልከቻ ቁጥራችሁን በማስገባት የውጤታችሁን ዲጂታል ኮፒ መውሰድ ትችላላችሁ ተብሏል 👇
https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus

@tikvahuniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት በተቋሙ የተከታተሉ ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተከታተላችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዮቹ አማራጮች ማየት ትችላላችሁ፦

በቴሌግራም ቦት፦ @WU_Registrar_bot

በጉግል አድራሻ፦
https://tinyurl.com/wu-remedial-r-2016

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በፖስት ቤዚክ ነርሲንግ በመደበኛ መርሐግብር ለመማር የምትፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ እስከ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በኮምፕሬሄንሲቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአካል በመገኘት ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ ተብሏል።

የትምህርት መስኮች፦
- Surgical Nursing
- Neonatal Nursing
- Pediatric & Child Health Nursing
- Emergency & Critical Care Nursing

@tikvahuniversity
2024/11/05 09:33:34
Back to Top
HTML Embed Code: