Telegram Web Link
ኢንዲያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና አንድነት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የማስተማር ፈቃዳቸው እንዳልታደሰላቸው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል፡፡

በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ፈቃድ ያላቸው፣ የሌላቸው እና የፈቃድ ዕድሳት ጥያቂያቸው በሒደት ላይ የሆኑ ዓለም አቀፍ እና የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ዝርዝርን ባለሥልጣኑ ይፋ አድረጓል፡፡

በዚህም ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩት ኢንዲያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና አንድነት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የማስተማር ፈቃዳቸው ያልታደሰላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ አቅርበው በሒደት ላይ የሚገኙ ተቋማት፦
▪️ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት
▪️ላየን ኸርት አካዳሚ
▪️ሄለኒክ ግሪክ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት

የፈቃድ ጥያቄ አቅርበው በሒደት ላይ የሚገኙ ተቋማት፦
▪️ትራንሴንድ አካዳሚ
▪️ማህሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት

ሌሎች 23 ዓለም አቀፍ እና የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ የተሰጣቸው እና ፈቃዳቸው የተሰጣቸው መሆኑንም የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል፡፡

(ባለሥልጣኑ ያወጣው ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የ2017 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ በተለያዩ ዞኖች በአግባቡ አለመጀመሩ ተገለፀ፡፡

በክልሉ የተለያዩ ዞኖች የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የተነሳ እስካሁን በአንዳንድ ትምህር ቤቶች ትምህርት አለመጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ከግል እና ከጥቂት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውጪ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች እንዳልተከፈቱ፣ ቢከፈቱም ከሁለት በላይ መመህራን ስለማይገቡ ትምህርት አለመጀመሩን አስተያየታቸውን ለቮኦኤ የሰጡ ወላጆች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በወላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን፣ በኮንሶ ዞን እና በጎፋ ዞን በሚገኙ 28 ወረዳዎች የሚያስተምሩ በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ደመወዝ በወቅቱ እንደማይከፈል የክልሉ መምህራን ማኅበር ገልጿል።

በዞኖቹ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን መኖራቸውን የገለፁት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ፤ መምህራኑ በጣም በመቸገራቸው ኑሯቸውን ለመደጎም የቀን ሥራ ጭምር እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

መምህራኑ የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ ሲያቀርቡ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና እስራት እየተፈፀመባቸው እንደሆነም ወላጆች እና መምህራን ገልፀዋል፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣ ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደመወዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ መግለፁ ይታወሳል፡፡

የቪኦኤን ዘለግ ያለ ዘገባ ያድምጡ  👇
https://amharic.voanews.com/a/south-ethiopia-school-disruption/7836277.html

@tikvahuniversity
#UniversityOfGondar

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ-ምረቃ እና ድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በተመሳሳይ የነባር እና አዲስ ገቢ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በ2017 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የምትመደቡ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል መርሐግብር ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
Safaricom Talent Cloud: Becoming a Competent Young Professional for the 21st Century

📯 Professionals Talk | የሙያ ወግ 📯

🔍 Topic: Becoming a Competent Young Professional for the 21st Century

📅 October 26, 2024
🕰 2:00 PM - 4:00 PM EAT
📍 Vamdas Cinema

Calling all aspiring young professionals! Join us for an exclusive panel discussion featuring industry experts from youth entrepreneurship and employment professionals ecosystem.

Gain valuable insights on navigating the evolving job market, developing essential skills, and unlocking opportunities in the 21st century.

This event offers:

🌟 Open Panel Discussion
🌟 Training Scholarship Opportunities
🌟 Networking with Professionals & various organizations

Don't miss your chance to elevate your career and connect with like-minded entrepreneurs and professionals.

🎟 FREE ENTRANCE
📝 Register now: https://forms.gle/8MyMssm5qiq2h9wQA

For more info, contact @Stenarcustomerservice

See you there!
#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://www.tg-me.com/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#አቢሲንያ_ባንክ

ቅዳሜ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 በአቢሲንያ ፌስቡክ ፔጅ ላይ ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር ይደረጋል፡፡  የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ፔጅን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የአቢሲንያ ባንክ ፌስቡክ ፔጅን በመቀላቀል ይሸለሙ!

ሊንኩን በመጠቀም ይቀላቀሉ፦ 
https://www.facebook.com/BoAeth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ማስታወሻ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የሰልጣኞች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

መስፈርቶች
▪️የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑ፣
▪️በ2015/16 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት (50%) ያላቸው፣
▪️በ2014/15 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትለው ያጠናቀቁ

ስልጠናው በአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ የሚሰጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቻይንኛ እና ኮሪያኛ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የምግብ እና የዶርም አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ጥቅምት 11-15/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦
ኅዳር 2/2017 ዓ.ም

አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በአቅም ማካካሻ (Remedial) ፕሮግራም ውጤት አያያዝ ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡

ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ50 በመቶ በታች ውጤት ካገኙ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች መካከል የተሻለ ውጤት ያላቸውን በመምረጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማካካሻ (Remedial)) ፕሮግራም ተመድበው የማካካሻ ትምህርት እንዲከታተሉ መደረጉ ይታወቃል።

በዚህ መሠረት ተማሪዎቹ 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ተፈትነው ሲያልፉ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ሆነው እንዲቀጥሉ እየተደረገ ይገኛል።

ይሁን እንጂ ከ30% በተቋማት የሚሰጠው ውጤት አሰጣጥ ላይ ወጥነት የሌለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፉት ሰርኩላር ገልፀዋል፡፡

በዚህም ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% የሚሰጠው ከማዕከል እንዲሆን ተወስኗል፡፡

@tikvahuniversity
በአንድ ጠቅ ብቻ የመብራት ክፍያችንን በ M-PESA እንክፈል! 10% ተመላሽ ገንዘባችንን እናግኝ! የ M-PESA ተመላሽ እና ሽልማቶች እንደቀጠሉ ናቸው !

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👇
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለሚገቡ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል።

የኦንላይን ምዝገባው ከዛሬ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት ይካሔዳል።

ሰልጣኞች በከተማዋ በሚገኙ 14 የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተዘጋጀው ሊንክ በመግባት ምዝገባ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡

በከተማዋ በዚህ ዓመት ከ23 ሺህ በላይ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከደረጃ 5 እስከ ደረጃ 2 ስልጠናዎችን እንደሚከታተሉ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MoH

ሰኔ 19/2016 ዓ.ም የፅሁፍ ፈተና እና መስከረም 30/2017 ዓ.ም የተግባር ፈተና (OSCE) የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች ከዛሬ ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ ተብሏል።

http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁ. 952 / 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#BoranaUniversity

በቦረና ዩኒቨርሲቲ በ Disaster Risk Management የማስተርስ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ የመጀመሪያ ዓመት አንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ጥቅምት 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በፕሮግራም ደረጃ የመግቢያ ፈተና ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም አዲስ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም ጠዋት የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል፡፡

የፈተና ቦታ፦
ከጤናና ህክምና ኮሌጅ አመልካቾች ውጪ በዋናው ግቢ ሲሆን፤ የጤናና ህክምና ኮሌጅ አመልካቾች ሐረር ካምፓስ፡፡

አመልካቾች ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ፣ የትምህርት ሰነዶች፣ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ እና የክፍያ ደረሰኝ ሜዝ ይኖርባችኋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0255530405 / 0255530332

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሰው ሠራሽ አስተውሎት(Artificial Intelligence) የድኅረ-ምረቃ መርሐግብር ሊከፍት ነው።

ዩኒቨርሲቲው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በቢግ ዳታ እና በሳይበር ሴኪዩሪቲ መስኮች የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር እየሠራ መሆኑን በተቋሙ የምርምርና ልህቀት ማዕከላት ዳይሬክተር ጌታቸው አዳም (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ባሉት ስምንት የልህቀት ማዕከላት የተለያዩ የድኅረ-ምረቃ መርሐግብሮችን በመክፈት ላይ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት በዩኒቨርሲቲው የተከፈተው የኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የድኅረ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከላቱን ታሳቢ ያደረገ የህንፃ ግንባታ እያካሕደ ሲሆን፤ እስካሁን የአራት ልህቀት ማዕከላት ግንባታ መጠናቀቃቸው ታውቋል።

@tikvahuniversity
2024/11/05 11:31:45
Back to Top
HTML Embed Code: