Telegram Web Link
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች 20 መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

መስፈርቶች
- ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም በዲግሪ የተመረቀ/ች፣
- የመምህርነትን ሙያዊ ክብር የሚጠብቁ፣
- በሚመደቡበት ቦታ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆኑ፣
- ከዚህ በፊት በክልሉ ቅጥር ያልፈፀሙ፣
- ደመወዝ በክሉሉ የደመወዝ ስኬል መሰረት፣
- የመምህርነት ሙያ ክህሎት ስልጠና ለወሰዱ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ከጥቅምት 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ በአካል ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0577752063

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጥበባት ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም እና በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና በሙዚቃ እና በትያትር ጥበባት የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት ያላችሁን በመደበኛ ፕሮግራም ማሰልጠን ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉና ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ ይዛችሁ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከጥቅምት 21 እስከ ህዳር 6/2017 ዓ.ም

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪ የነበራችሁና ለፍሬሽማን ፕሮግራም የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁፋችሁ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ

🔔 የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ጀምሯል❗️

BSc fields of study:
→ Doctor of Medicine
→ Doctor of Dental Medicine
→ Bachelor of Dental Science
→ Nursing
TVET Programs:
→ Dental Therapy
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Radiography

የ CPD ማዕከል አገልግሎት!

☎️ 0913398780 / 0911596059

አድራሻ፦
CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ

Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege
#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በኤክስቴንሽን መርሐግብር የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (UAT) አርብ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የመፈተኛ ቦታ፣ የፈተና ማዕከል እና የተፈታኞች ዝርዝር በተቋሙ ድረ-ገፅ እና በይፋዊ የማኅበራዊ ገፆፁ ተለጥፈዋል፡፡

@tikvahuniversity
#UniversityOfKabridahar

በ2016 ዓ.ም በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተር ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል በመሙላት ትምህርታችሁን ያቋረጣችሁ ተማሪዎች የሞላችሁትን ቀሪ ፎርም በመያዝ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቂ አመልካች በተገኘባቸው የድኅረ-ምረቃ አመልካቾች የ2ዐ17 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ ከጥቅምት 25-27/2017 ዓ.ም ብቻ እንደሚከናወን አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ #አለማድረጉን አሳውቋል፡፡

በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር የተመለከትነው ዩኒቨርሲቲው ከላይ ለተገለፁት ተማሪዎች "ለጥቅምት 27 እና 28/2017 ዓ.ም ጥሪ እንዳደረገ" የሚገልፅ ማስታወቂያ እውነተኛ ነው ወይ ስንል የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራር ጠይቀናል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት ጥሪ አለማድረጉንና በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወረው የጥሪ ማስታወቂያ ሐሰተኛ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ላመጡ እና በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ጥሪ እንደሚያደርግ የገለፁት ኃላፊው፤ እስከዛ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡

@tikvahuniversity
ጥራትን ከሚገርም ዋጋ ጋር ይዞ የመጣውን አዲሱን Kimem Itel Pro እናስተዋውቅዎ!  በአቅራቢያችን ወደ የሚገኝ የሳፋሪኮም ሱቅ ጎራ ብለን ዛሬውኑ እንግዛ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity
ቀጣይ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 በፌስቡክ ገፃችን ላይ ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ!

ዛሬውኑ የፌስቡክ ገፃችንን በመቀላቀል እና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ! 👇
https://www.facebook.com/BoAeth
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ጥቆማ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማኅበረሰብ፣ የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ #ነጻ የኮሪያ ቋንቋ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናው በዲላ ዩኒቨርሲቲ እና በኮሪያ መንግሥት ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ስልጠናውን ተከታትለው ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣል።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከጥቅምት 25 እስከ ኅዳር 3/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦ ኦዳያኣ ግቢ

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እንዲሁም በተከትታይ እና በርቀት ትምህርት በቂ አመልካች በተገኘባቸው ፕሮግራሞች የድኅረ-ምረቃ አመልካቾች የ2ዐ17 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ ከጥቅምት 25-27/2017 ዓ.ም ብቻ እንደሚከናወን አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
#AAUAlumniNetwork

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂ ከሆኑ የዩኒቨርሲቲውን የቀድሞ ምሩቃን ኔትወርክ (AAU’s Alumni Network) እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል፡፡

ኔትወርኩ የቀድሞ ተማሪዎች አብረዋቸው ከተማሩ ጋር በቀላሉ ለመገናኘትና በኅብረት ለመስራት፣ ሙያዊ አበርክቶ ለማስፋት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የለውጥ ተግባራት ለማገዝ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ተከታዩን ሊንክ በመጫንና የራስዎን ፕሮፋይል በመሙላት አባል ይሁኑ 👉 https://alumni.aau.edu.et

@tikvahuniversity
የሀገር ውስጥ የበረራ ቲኬታችንን በ M-PESA ስንቆርጥ 5% ተመላሽ ብር ከጉዞ ሳንወርድ እጃችን ይገባል! በ M-PESA ይከፈላል! ቅናሽ ይታፈሳል! Bon Voyage!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
ለዕድገት ቁልፉ ምንድን ነው?
ኢንቨስትመንትን ከንግድ ግቦች ጋር ማጣጣም የሚቻለው እንዴት ነው?

ለስልጠናው አሁኑኑ ይመዝገቡ 👇
https://forms.gle/UW9zXcPzEwnciHYL9

"የኢንቨስትመንት እቅድ – የእድገት ስትራቴጂ" ስልጠናን በነፃ ይሳተፉና ውጤታማ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂዎችን ያግኙ!

🗓 ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00-11:00 ሰዓት

#ዕድገት #ኢንቨስትመንት #መስራት
#Y12HMC

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በኤክስቴንሽን መርሐግብር በ General Public Health, Reproductive Health, Epidemiology and Health Care Quality የትምህርት መስኮች ለመማር ላመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ቅዳሜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:30 እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ የፈተና ቀን ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
#TTI

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዲስ የመደበኛ (የቀን) መርሐግብር ተመዝጋቢ ተማሪዎች የቃል ፈተና (Interview) ሰኞ ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30 ላይ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተጠቀሰው ቀን ለመደበኛ መርሐግብር ያመለከታችሁ በሙሉ በመፈተኛ ቦታ እንድትገኙ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም አይኖርም በሚል በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች እየተዘዋወረ የሚገኘው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሆነው የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም "በዚህ ዓመት በበጀት እጥረት ምክንያት ተቋርጧል" በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቹ ባጋራው መረጃ አረጋግጧል፡፡

@tikvahuniversity
2024/11/05 11:37:14
Back to Top
HTML Embed Code: