Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የመቁረጫ ነጥቡ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
የ2017 ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና የመቁረጫ ነጥብ:

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 141 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 137 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 138 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 134 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፡፡

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 142 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 138 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 139 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 135 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፡፡

የስልጠና ደረጀ 5
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 179 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 167 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 170 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 154 እና ከዚያ በላይ፡፡


የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 135 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 134 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 124 እና ከዚያ በታች፡፡

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 140 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 136 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 135 እና እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 125 እና ከዚያ በላይ፡፡

የስልጠና ደረጀ 5
▪️ ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 172 ከዚያ በላይ፣
▪️ ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 164 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥብ 165 እና እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥብ 160 እና ከዚያ በላይ፣
▪️ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 154 እና ከዚያ በላይ፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለፅ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ ምደባው ይፋ እስከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 71
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከ2ኛ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ አይጠይቅም
➤ የሥራ ቦታ፦ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት

የምዝገባ ቦታ፦
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ (በሁሉም ግቢዎች) የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ

ለበለጠ መረጃ፦ 0471350151 / 0473360159

(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
💫 ከዳር እስከ ዳር በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት! እንገናኝ! የተመቸንን ሼር እናድርግ! 👍 ከወደድነው ጋር እንደልብ እንገናኝ!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2016 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተቋሙ መሔድ ያልቻለችሁና ዊዝድሮዋል መሙላት ሳትችሉ የቀራችሁ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ትምህርታችሁን ከቀጣይ ባች ጋር መቀጠል እንድትችሉ ዩኒቨርሲቲው ስለፈቀደ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የምትቀላቀሉ (2016 ዓ.ም ሪሚዲያል የነበራችሁ እና አዲስ የምትመደቡ) ተማሪዎች በሌላ ማስታዎቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መመዝገብ ጀምሯል፡፡

መስፈርቶች
▪️የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነ/የሆነች፣
▪️በ2015/16 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት (50%) ያለው/ያላት፣
▪️በ2014/15 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትለው ያጠናቀቁ

ስልጠናው በአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ የሚሰጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቻይንኛ እና ኮሪያኛ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የምግብ እና የዶርም አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ጥቅምት 11-15/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦
ኅዳር 2/2017 ዓ.ም

አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት

@tikvahuniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በተቋሙ የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ነጥብ ያሰመዘገባችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ መያዝ የሚኖርባችሁ፦
▪️ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ
▪️ አራት 3x 4 ጉርድ ፎቶግራፍ

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከምፓስ

@tikvahuniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለነባር መደበኛ እና የ2016 ሪሚዲያል ተማሪዎቹ ለጥቅምት 11 እና 12/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ጥቅምት 13 እስከ 19/2017 ዓ.ም ያከናውናል፡፡

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (NGAT) ወስደው የማለፊያ ነጥብ በማምጣት ካመለከቱ መካከል፣ በቂ አመልካች ቁጥር የተገኘባቸውና በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ የሚከፈቱ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች፦
▪️ Nutrition (መደበኛ)
▪️ Reproductive Health (መደበኛ)
▪️ MBA (መደበኛ እና ኤክስቴንሽን)

በሌሎች የትምህርት ክፍሎች ያመለከታቸሁ፣ በቂ የአመልካች ቁጥር ባለመገኘቱ የትምህርት ዝግጅታችሁ በሚያሳትፋችሁ በተከፈቱ ትምህርት ክፍሎች ላይ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

በኦንላይን የተመዘገባችሁ ለምዝገባ ስትሔዱ ለማመልከት የተጠየቁትን መረጃዎች ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
2024/11/06 02:59:47
Back to Top
HTML Embed Code: