#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 18
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት
➤ የሥራ ቦታ፦ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከጥቅምት 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት
አመልካቾች ሙሉ የህይወት ታሪካችሁን (CV) እና ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ በዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳዳርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ. ዐ3 በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0463299124
(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity

በጦርነት ምክንያት ሥራ ያቆሙ መምህራንን ማዘዋወር ካልተቻለ ወደ ሥራቸው እስኪመለሱ ባሉበት ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ጠየቀ፡፡
"መምህራን የኑሮ ውድነት በከፍተኛ መጠን እየፈተናቸው እንደሚገኙ፣ የረዥም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ ዕድገት ወይም ዕርከን እያገኙ አለመሆናቸው፣ በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በጊዜ አለመከፈልና በፐርሰንት መቆራረጥ፣ ያለ መምህራን ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደመወዝ መቆረጥና ይህንን ድርጊት የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት እንዳለ" 37ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቅርቡ ያካሔደው ማኅበሩ አሳውቋል፡፡
በተጨማሪም ከዓመታት በፊት የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ አለመሆኑን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩን፣ በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጥ፣ የመጻሕፍትና ሌሎች ግብዓቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ሥልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ማኅበሩ ባወጣው መግለጫ ተዳሰዋል፡፡
"መምህራን ክፍል ውስጥ ገብተው ማስተማር ባልቻሉበት ወቅት፣ አላሰተማሩም ተብሎ ደመወዛቸው ሊቆረጥባቸው አይገባም" ሲሉ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል።
ከወራት በፊት የ18 ወራት ውዝፍ ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ለችግር መጋለጣቸውን የትግራይ ክልል መምህራን መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም በቅርቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአምስት ወራት ደመወዝ ለመምህራኑ እንደሚከፍል ቢናገርም፣ የቀሪው የአንድ ዓመት ውዝፍ ክፍያ ግን አሁንም መፍትሔ እንደሚፈልግ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ገልፀዋል፡፡
በጦርነት ምክንያት ሥራ ያቆሙ መምህራንን ማዘዋወር ካልተቻለ ወደ ሥራቸው እስኪመለሱ ባሉበት ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው የጠየቁት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት፤ መንግሥትም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የመምህራኑን ችግር ሊረዱና መፍትሔ ሊሰጡት ይገባል ብለዋል፡፡
ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች ክልሎች እስከ ሦስት ወራት ደመወዝ ያልተለከፈላቸው በተለይም በቀድሞው ደቡብ ክልል ውስጥ የነበሩ ትምህርት ተቋማትም እንደሚገኙ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ በአማራ ክልል በሚካሄደው ጦርነት ደመወዝ ያልተከፈላቸውና ሥራ ያቆሙ መምህራን መረጃ ተጠናቅሮ አልደረሰም ብለዋል። #ሪፖርተር

ኢንዲያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና አንድነት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የማስተማር ፈቃዳቸው እንዳልታደሰላቸው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል፡፡
በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ፈቃድ ያላቸው፣ የሌላቸው እና የፈቃድ ዕድሳት ጥያቂያቸው በሒደት ላይ የሆኑ ዓለም አቀፍ እና የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ዝርዝርን ባለሥልጣኑ ይፋ አድረጓል፡፡
በዚህም ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩት ኢንዲያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና አንድነት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የማስተማር ፈቃዳቸው ያልታደሰላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ አቅርበው በሒደት ላይ የሚገኙ ተቋማት፦
▪️ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት
▪️ላየን ኸርት አካዳሚ
▪️ሄለኒክ ግሪክ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት
የፈቃድ ጥያቄ አቅርበው በሒደት ላይ የሚገኙ ተቋማት፦
▪️ትራንሴንድ አካዳሚ
▪️ማህሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት
ሌሎች 23 ዓለም አቀፍ እና የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ የተሰጣቸው እና ፈቃዳቸው የተሰጣቸው መሆኑንም የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል፡፡
(ባለሥልጣኑ ያወጣው ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የ2017 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ በተለያዩ ዞኖች በአግባቡ አለመጀመሩ ተገለፀ፡፡
በክልሉ የተለያዩ ዞኖች የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የተነሳ እስካሁን በአንዳንድ ትምህር ቤቶች ትምህርት አለመጀመሩ ተሰምቷል፡፡
ከግል እና ከጥቂት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውጪ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች እንዳልተከፈቱ፣ ቢከፈቱም ከሁለት በላይ መመህራን ስለማይገቡ ትምህርት አለመጀመሩን አስተያየታቸውን ለቮኦኤ የሰጡ ወላጆች ስጋታቸውን ገልፀዋል።
በወላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን፣ በኮንሶ ዞን እና በጎፋ ዞን በሚገኙ 28 ወረዳዎች የሚያስተምሩ በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ደመወዝ በወቅቱ እንደማይከፈል የክልሉ መምህራን ማኅበር ገልጿል።
በዞኖቹ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን መኖራቸውን የገለፁት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ፤ መምህራኑ በጣም በመቸገራቸው ኑሯቸውን ለመደጎም የቀን ሥራ ጭምር እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
መምህራኑ የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ ሲያቀርቡ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና እስራት እየተፈፀመባቸው እንደሆነም ወላጆች እና መምህራን ገልፀዋል፡፡
በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣ ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደመወዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ መግለፁ ይታወሳል፡፡
የቪኦኤን ዘለግ ያለ ዘገባ ያድምጡ 👇
https://amharic.voanews.com/a/south-ethiopia-school-disruption/7836277.html

#UniversityOfGondar
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ-ምረቃ እና ድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡
በዚህም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
በተመሳሳይ የነባር እና አዲስ ገቢ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች ጥቅምት 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡
በ2017 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የምትመደቡ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል መርሐግብር ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

Safaricom Talent Cloud: Becoming a Competent Young Professional for the 21st Century
📯 Professionals Talk | የሙያ ወግ 📯
🔍 Topic: Becoming a Competent Young Professional for the 21st Century
📅 October 26, 2024
🕰 2:00 PM - 4:00 PM EAT
📍 Vamdas Cinema
Calling all aspiring young professionals! Join us for an exclusive panel discussion featuring industry experts from youth entrepreneurship and employment professionals ecosystem.
Gain valuable insights on navigating the evolving job market, developing essential skills, and unlocking opportunities in the 21st century.
This event offers:
🌟 Open Panel Discussion
🌟 Training Scholarship Opportunities
🌟 Networking with Professionals & various organizations
Don't miss your chance to elevate your career and connect with like-minded entrepreneurs and professionals.
🎟 FREE ENTRANCE
📝 Register now: https://forms.gle/8MyMssm5qiq2h9wQA
For more info, contact @Stenarcustomerservice
See you there!

#MoE
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።
ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦
በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://www.tg-me.com/moestudentbot
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

#አቢሲንያ_ባንክ
ቅዳሜ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 በአቢሲንያ ፌስቡክ ፔጅ ላይ ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር ይደረጋል፡፡ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ፔጅን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የአቢሲንያ ባንክ ፌስቡክ ፔጅን በመቀላቀል ይሸለሙ!
ሊንኩን በመጠቀም ይቀላቀሉ፦
https://www.facebook.com/BoAeth
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

#ማስታወሻ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የሰልጣኞች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡
መስፈርቶች
▪️የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑ፣
▪️በ2015/16 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት (50%) ያላቸው፣
▪️በ2014/15 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትለው ያጠናቀቁ
ስልጠናው በአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ የሚሰጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቻይንኛ እና ኮሪያኛ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የምግብ እና የዶርም አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡
የምዝገባ ጊዜ፦
ጥቅምት 11-15/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦
ኅዳር 2/2017 ዓ.ም
አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት

ትምህርት ሚኒስቴር በአቅም ማካካሻ (Remedial) ፕሮግራም ውጤት አያያዝ ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ50 በመቶ በታች ውጤት ካገኙ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች መካከል የተሻለ ውጤት ያላቸውን በመምረጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማካካሻ (Remedial)) ፕሮግራም ተመድበው የማካካሻ ትምህርት እንዲከታተሉ መደረጉ ይታወቃል።
በዚህ መሠረት ተማሪዎቹ 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ተፈትነው ሲያልፉ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ሆነው እንዲቀጥሉ እየተደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ከ30% በተቋማት የሚሰጠው ውጤት አሰጣጥ ላይ ወጥነት የሌለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፉት ሰርኩላር ገልፀዋል፡፡
በዚህም ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% የሚሰጠው ከማዕከል እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በአንድ ጠቅ ብቻ የመብራት ክፍያችንን በ M-PESA እንክፈል! 10% ተመላሽ ገንዘባችንን እናግኝ! የ M-PESA ተመላሽ እና ሽልማቶች እንደቀጠሉ ናቸው !
የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👇
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለሚገቡ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል።
የኦንላይን ምዝገባው ከዛሬ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት ይካሔዳል።
ሰልጣኞች በከተማዋ በሚገኙ 14 የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተዘጋጀው ሊንክ በመግባት ምዝገባ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡
በከተማዋ በዚህ ዓመት ከ23 ሺህ በላይ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከደረጃ 5 እስከ ደረጃ 2 ስልጠናዎችን እንደሚከታተሉ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ገልጿል።