#WolaitaSodoUniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መርሐግብር መግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፉ አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር የአመልካቾች የምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም አራዝሟል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የዶርም አገልግሎት ለሚፈልጉ መደበኛ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በተመጣጣኝ ክፍያ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ገልጿል።
@tikvahuniversity

#DebreMarkosUniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለነባር አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ተራዝሞ የነበረው የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 14 እና 15/2017 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑን አሳውቋል፡፡
በዚህም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች በተጠቀሰው ጊዜ በየነበራችሁበት ካምፓስ በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎችም በተጠቀሰው ጊዜ መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

#AAU
ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ #በአዲስ_አበባ_የምትኖሩ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አራት ጉርድ ፎቶግራፎች መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡
ስለምዝገባ ሒደቶች በተመለከተና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 👇
https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome

በአማራ ክልል ለ2017 ትምህርት ዘመን እስካሁን ምዝገባ ያደረጉ ተማሪዎች 31 በመቶ መሆናቸው ተገለፀ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2017 መጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሒዷል።
በክልሉ በ2017 ዓ.ም ምዝገባ የሚያደርጉ ተማሪዎች ቁጥርን ለማሳደግ ከማኅበረሰቡ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች ቢደረጉም የሚጠበቀውን ያህል ተማሪዎች አለመመዝገባቸው ተገልጿል።
ከ 7.1 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እስካሁን ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተመዘገቡት 2.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ መኳንንት አደመ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከተመዘገቡት ያነሰ መሆኑንም ኃላፊው አብራርተዋል።
ማንኛውም ለክልሉ እድገት የሚያስብ አካል ለትምህርት ቅድሚያ እንዲሰጥ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል። #አሚኮ

የባህር ዳር ሕግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ7ኛው ሀገር አቀፍ ምስለ ችሎት ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል።
ውድድሩ በዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቡድን በፅሁፍ እና በቃል የውድድሩ ክፍሎች የላቀ አፈፃፀም በማሳየት አሸናፊ ሆኗል።
የቡድኑ አባላት ተማሪ ዮናስ መጬ፣ ተማሪ ሮዛ ይመር እና ተማሪ የአብስራ በለጠ በውድድሩ ፍፃሜ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ብርቱ ፉክክር ቢገጥማቸውም በአሸናፊነት አጠናቀዋል።
በመምህር መካሻው ጫኔ የሚመሩት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቡድን አባላት፥ በቀጣይ በናይሮቢ ኬንያ በሚካሔደው የመላው አፍሪካ "ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ" የምስለ ችሎት ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፉ ይሆናል።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በድኅረ እና በቅድመ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,224 ተማሪዎች በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ግቢ ዛሬ አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በክረምት፣ በርቀት እና በተከታታይ መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
በዋናው ደሴ ግቢ 1,980 ተማሪዎች፣ በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት 199 ተማሪዎች እና በልዕለ ህክምና ግቢ 45 ተማሪዎች በድምሩ 2,224 ተማሪዎች መመረቃቸው ተገልጿል።
በማዕረግ ለተመረቁ ተማሪዎች ልዩ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፤ ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ተማሪ አብዮት አሸብር ከኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

Tikvah-University
#AAU ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ #በአዲስ_አበባ_የምትኖሩ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አራት ጉርድ ፎቶግራፎች መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ የ2017…
#Update
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ #በአዲስ_አበባና_አካባቢዋ የምትኖሩ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የዶርም አገልግሎት ልታገኙ የምትችሉበት ዕድል ሊኖር እንደሚችል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
"በሚተርፉን ውስን የመኝታ ቦታዎች ላይ እንደየርቀታቸሁ ሁኔታ አይተን የመኝታ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል" ለትምህርት በየተመደባችሁበት ግቢ ትራንስክሪፕታችሁንና ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን በመያዝ ከጥቅምት 12 እስከ 15/2017 ዓ.ም ድረስ በየኮሌጃችሁ በግንባር በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርስቲው አሳስቧል።
የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት ምዝገባው #የግል አመልካቾችንም (Self-sponsored) እንደሚመለከት ተገልጿል፡፡

Photo
#Update
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለነባር አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ በ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያገኛችሁና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ31 ሺህ በላይ ዜጎች የኮደርስ ስልጠና ወስደው ብቃታቸው ተረጋግጦ ሰርተፍኬት አጊኝተዋል።
ከ246 ሺህ በላይ ዜጎች ተመዝግበው የኮደርስ ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጿል።
ከእነዚህ ውስጥ ከ31 ሺህ በላይ የሚሆኑት ብቃታቸው ተረጋግጦ ሰርተፍኬት መውሰዳቸውን ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
የስልጠና ዘርፎች፦
► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።
ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

#ጥቆማ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡
ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ኅዳር 21/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ጀምሯል።
የፈተና ቦታ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ
ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts
በአካል ለመመዝገብ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ ቁ. 130፣ ቢሮ ቁ. 408
ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

#MoE
የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤት ይፋ ሆኗል።
ተከታዩን ሊንክ ተጠቅማችሁ የምዝገባ ቁጥር ወይም Username በማስገባት ውጤቶቻችሁን ማየት ትችላላችሁ 👇
https://result.ethernet.edu.et
ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና፣ ከ49 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን ለመቀበል ለጥቅምት 14 እና 15/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።
ይህ ጥሪ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎችን የማይጨምር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎቹ ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሼርድ ካምፓስ በ2016 ዓ.ም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ ማሳለፍ መቻሉ ይታወቃል፡፡ 62.4 በመቶ ተማሪዎች ደግሞ ከ600 ከታረመው ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡
በሽልማት መርሐግብሩ ለሁሉም ተማሪዎች ሽልማትና ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት ተማሪዎች የታብሌት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
@tikvahuniversity
የዩኒቨርሲቲው ሼርድ ካምፓስ በ2016 ዓ.ም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ ማሳለፍ መቻሉ ይታወቃል፡፡ 62.4 በመቶ ተማሪዎች ደግሞ ከ600 ከታረመው ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡
በሽልማት መርሐግብሩ ለሁሉም ተማሪዎች ሽልማትና ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት ተማሪዎች የታብሌት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
@tikvahuniversity
Tikvah-University
#MoE የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤት ይፋ ሆኗል። ተከታዩን ሊንክ ተጠቅማችሁ የምዝገባ ቁጥር ወይም Username በማስገባት ውጤቶቻችሁን ማየት ትችላላችሁ 👇 https://result.ethernet.edu.et ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና፣ ከ49 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት…
#Update
የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤትዎን ይመልከቱ!
ውጤት ለመመልከት 👇
https://result.ethernet.edu.et
ሊንኩን በመጫን ከሚመጡት አማራጮች 'TDP' የሚለውን ይምረጡና የምዝገባ ቁጥር ወይም Username በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡
70 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሰልጣኞች ብቻ የተረጋገጠ ሰርተፊኬት እንደሚሰጣቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

#DebarkUniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለነባር አንደኛ፣ ሦስተኛ እና አራተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡
በዚህም የነባር አንደኛ፣ ሦስተኛ እና አራተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
በቅጣት ምዝገባ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ብቻ ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አዲስ አንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ፕሮግራም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል፡፡