Telegram Web Link
#ተራዝሟል

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ለሚጀምረው የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በአራት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል፡፡

የሚሰጡ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች፦

► MSc & PhD in Remote Sensing
► MSc & PhD in Space Science
► PhD in Geodesy
► MSc & PhD in Astronomy and Astrophysics

አመልካቾች የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለማስተርስ ዲግሪ ለማመልከት የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.00 እንዲሁም ለፒኤችዲ ፕሮግራም ለማመልከት የማስተርስ ዲግሪ CGPA 3.00 እና የመመረቂያ ፅሁፍ 'በጣም ጥሩ' ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የድኅረ ምረቃ ቢሮ 2ኛ ፍሉር በመገኘት ወይም የትምህርት ሰነዶችን በPDF ፎርማት በማዘጋጀት በ [email protected] የኢ-ሜይል አድራሻ ማመልከት ይቻላል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል 👇

https://result.ethernet.edu.et/

@tikvahuniversity
🌼 አዲስ ቅመም ለአዲስ ዓመት!

ለምንወዳቸው የበዓል ስጦታ Itel Proን ዛሬውኑ ገዝተን በሽ በሽ እናድርጋቸው! ዛሬውኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት ለ90 ቀናት በሚቆይ 5ጊባ ወር​ሃዊ ጥቅል እና በ1000 የሳፋሪኮም ደቂቃ ስጦታ እንንበሽበሽ!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#SPHMMC

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ የ Hematology and Oncology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አስጀምሯል።

ይህ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ሠልጣኞች ዘመናዊና ጥራት ያለው የካንሰር ህክምና፣ ትምህርት እና ምርምር እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ፕሮግራሙ የሁለት ዓመት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን፤ ኮሌጁ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ የሚሆኑ ሦስት ፌሎውስ በዚህ ወር እንደሚቀበል ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
የቻይናው First Highway Engineering Company (CFHEC) ለ102 ወጣት ኢትዮጵያውያን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የግዙፉ CCCC ኩባንያ እህት ተቋም የሆነው CFHEC፤ ስልጠናውን ለአንድ ወር የሚሰጥ ሲሆን፤ ሰልጣኞቹ ከCCCC የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ሳይቶች የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ግንባታ፣ ሰርቬዪንግ፣ የግንባታ ቁሳቁስ ፍተሻ እና የቻይንኛ ቋንቋ በስልጠናው የተካተቱ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።

Seagull Talent Nurturing Project በሚል የሚሰጠው ስልጠና፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት፣ በሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ እና በ CFHEC በጋራ የተዘጋጀ ነው። #Xinhua

@tikvahuniversity
#DebreBerhanUniversity

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከ2ኛ-6ኛ ዓመት ያሉ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምሯል፡፡

ካምፓሱ ለ2017 ትምህርት ዘመን በመደበኛው ፕሮግራም ከ 1,200 በላይ ነባር እና አዲስ ገቢ የህክምናና የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ትምህርት ዘመን ጥሪ የተደረገላቸው ነባር ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 09 እና 10/2017 እንደሚከናወን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#STEMpower

በስድስት የስቴም ፓወር ስልጠና ማዕከላት ትምህርታቸውን ተከታትለው በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን STEMpower ገልጿል።

ቓላሚኖ ስቴም ማዕከል፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል፣ ወላይታ ሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት እና ኦልማ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ካሳለፉ የስቴም ማዕከላት መካከል ይጠቀሳሉ።

STEMpower በኢትዮጵያ 61 የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ የስልጠና ማዕከላት አሉት።

@tikvahuniversity
የናይጄርያ መንግሥት በሐሰተኛ የትምህርት ሰነድ ላይ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ጀምሯል።

የሀገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ፌደሬሽን የሀሰት ሰርተፊኬት የያዘ የትኛውንም ግለሰብ ከሥራ እንዲያባርር ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ቀጣሪ ተቋማት ከሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሊጠበቁና የብቃት ማረጋገጫዎች ትክክለኛነትን ሊያረጋግጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።

ለሀገሪቱ የአካዳሚ ትምህርት መረጃዎች የሚሰጡ የመንግሥት ድርጅቶች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ ዘገባ ያሳያል።

የናይጀሪያ ትምህርት ሚኒስትር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ፕሬዝዳንት ቲኑቡ የሀገሪቱ የሲቪል ሰርቪስ ፌደሬሽን ኃላፊ የሀሰት ሰርተፊኬት የያዘ ማንኛውንም ገልሰብ እንዲያባርሩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

የናይጄርያ መንግሥት ከባለፈው ጥር ጀምሮ በ107 የግል ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ይህም የሀሰት ዲግሪዎችን መስፋፋት ለመከላከል ተጨማሪ ጥረት ነው ተብሏል። #VOA

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #በሜዲካል_ራዲዮሎጅ_ቴክኖሎጅ ፖስት ቤሲክ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የሚከታተሉ 20 ተማሪዎችን በ2017 ዓ.ም ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ከመስከረም 10-20/2017 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

አመልካቾች ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ በመንግሥት እና/ወይም በግል የህክምና ተቋማት ያገለገሉ እንዲሁም በራሳቸው ስፖንሰርነት ወይም ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርነት ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
http://www.dmu.edu.et/Online-Application-form/

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የህክምና ትምህርት ለመማር ለምትፈልጉና የተቀመጡ መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾችን መቀበል እንደሚፈልግ ኮሌጁ አሳውቋል።

መስፈርቶች፤

➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል አማካይ የትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ የሆነ
➧ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች
➧ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከ600 ተፈትነው ለወንድ 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው፤ ለሴት 475 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
➧ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከ700 ተፈትነው ለወንድ 580 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው፤ ለሴት 555 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
➧ ለአፋር ክልል፣ ለቦረና ዞን (ኦሮሚያ ክልል)፣ ለደቡብ ኦሞ ዞን (ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል)፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ለጋምቤላ ክልል፣ ለሱማሌ ክልል፣ ለዋግህምራ ዞን (አማራ ክልል) እና ለምእራብ ኦሞ ዞን (ደቡብ ም/ኢ/ክልል) ለወንድ 450 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው፤ ለሴት 425  እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት

► ማመልከት የሚቻለው በኦንላይን ብቻ ነው።

► የማመልከቻ ጊዜ፦
ከመስከረም 11-18/2017 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃ፦
- www.sphmmc.edu.et/
- ስልክ ቁ. - 0118965125

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ መሆኑ ይታወቃል።

የሪሚዲያል ፕሮግራም የማለፊያ ውጤት ስንት ነው የሚሉ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ደረሰዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰላ (70%) እና በተማሩበት ተቋም የሚሰላ (30%) በድምሩ 50% እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ነጥብ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ሰምተናል።

በተማሩበት ተቋም 30% ውጤት ያልተሞላላቸው ተማሪዎችን ውጤት ለመሙላት ባለሙያዎች እየሠሩ መሆኑንና በቅርቡ እንደሚለቀቅላቸው ሚኒስቴሩ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

@tikvahuniversity
በM-PESA ነው መቀበል!
የሱፉ ይላክልን እንጂ ፤ የከረባቱ በእኛ ነው!
ከአሜሪካ፣ ከካናዳ፣ ከእንግሊዝ፣ ከአውሮፓ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከሊቢያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኬንያ፣ ከናይጄሪያ፣ ከእስራኤል ወይም ከቻይና ገንዘብ ስንቀበል በመላ በM-PESA ነው መቀበል! ለምን? 5% ካሽባክ እና ጉርሻ እናገኛለን!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
2024/09/30 17:18:02
Back to Top
HTML Embed Code: