Telegram Web Link
5_UAT_23_09_2024_Morning_Schedule.xlsx
77.4 KB
#AAU #UAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (UAT) መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ሰኞ መስከረም 13/2017 ዓ.ም ጠዋት ለሚሰጠው ፈተና የተፈታኞች ኮድና ስም ዝርዝር እንዲሁም የመፈተኛ ካምፓስና ክፍል ከላይ ከተያያዘው ኤክሴል ይመልከቱ፡፡

@tikvahuniversity
#AAU #UAT #ተጨማሪ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ምዝገባ ያደረጋችሁና የዩኒቨርሲቲውን መግቢያ ፈተና (UAT) ለመውሰድ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ካምፓስ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲእና እና
- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የመፈተኛ ቦታ አድርጋችሁ የመረጣችሁ ፈተናው መስከረም 11 እና 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የመፈተኛ ቦታ የመረጣችሁ
- አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፈተናችሁ ሰኞ መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይሆናል።

የመፈተኛ Password ትኬት እንዴት ያገኛሉ?

የመፈተኛ ቀን፣ ሰዓት፣ የመፈተኛ Username፣ የመፈተኛ Passward ትኬት ለማግኘት፤ ለማመልከት የተጠቀማችሁበትን የኢሜል አድራሻ እና Passward https://portal.aau.edu.et ላይ በመግባት ከዚያ Apply for admission በመምረጥ Login የሚለውን በመክፈት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Note:
ስምዎ አሁን ባለው ሊስት ውስጥ ካልተካተተ፣ በሚቀጥሉት የፈተና ሊስት ውስጥ እንደሚካተቱ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#AdigratUniversity

ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት መስከረም 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ የሁሉም የአንደኛ ዓመት እንዲሁም የመጨረሻ ዓመት የቅድመ ምረቃ አና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ምዝገባ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#AASTU #ASTU

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ለመማር በዩኒቨርሲቲዎቹ የተዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ፈተናው መስከረም 14/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናው ማክሰኞ መስከረም 14/2017 ዓ.ም በሁለት ክፍለ ጊዜ ማለትም ጠዋት ከ 2፡30-5፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 -10፡30 ይሰጣል።

ከካልኩሌተር እና ለማሰቢያ ከሚሆን ወረቀት ውጭ ማንኛውንም ዓይነት ሞባይል ስልክ ወይም ስማርት ፎን ይዞ ወደ መፈተኛ ማዕከላት አይቻልም ተብሏል።

@tikvahuniversity
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ እና ነባር የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች መስከረም 29 እና 30/2017 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው ይገባሉ።

የ3ኛ ዓመት፣ የ2ኛ ዓመት፣ የ1ኛ ዓመት ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
#HawassaUniversity

የኖርዌይ ሳውዝ-ኢስተርን ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚተገብረውን የ NURTURE Project በተመለከት ውይይት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካሒዷል።

የኖርዌይ ሳውዝ ኢስተርን ዩኒቨርሲቲ ከአምስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመማር ማስተማር፣ ዲጅታላይዜሽን-ሽግግር፣ ትምህርት መሳሪያዎች ድጋፍ፣ እኩልነትና የሴቶች ተሳትፎ እንዲሁም መሰል የአቅም ግንባታዎች ላይ በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል።

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ Nurture Project እየተገበሩ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ መሠጠት የተጀመረው የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT)፣ በነርቸር ፕሮጀክት አማካኝነት በስታፍ ኤክስቼንጅ መምህራንና ሠልጣኞችን ለማስተማር ትልቅ ፈተና መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

እ.አ.አ. በ2023 አንድም የማስተርስ ተማሪ ፈተናውን አልፎ ፕሮጀክቱን ሊቀላቀል እንዳልቻለ ከሳውዝ ኢስተርን ዩኒቨርሲቲ የመጡት የነርቸር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ፕ/ር ሸጋው አናጋው ገልፀዋል።

በርካታ የፒ.ኤች.ዲ. እና የማስተርስ ተማሪዎችን ለፕሮጀክቱ ለመቀበል ፍላጎት ቢኖርም፣ የGAT ፈተናን የሚያልፉ ስታፍ ተማሪዎች ማግኘት መቸገራቸውን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ ዩኒቨርሲቲዎች የስታፍ ተማሪ አቅርቦታቸው ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተካሔደው መድረክ፣ ፕሮጀክቱ የገጠሙት ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጎ የመፍትሔ ሀሳቦች ቀርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahuniversity
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።

የብቃት ምዘና ፈተናው በ13 የጤና ሙያ መስኮች ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተሰጥቷል።

ምስል፦ አክሱም ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
#SPHMMC

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ እንክብካቤ ህክምና የሰለጠኑ ሦስት ፌሎውስ Intensive Care Medicine Fellows (Intensivists) አስመርቋል።

የከፍተኛ እንክብካቤ ህክምና ፌሎውሺፕ ፕሮግራም መጀመር በሀገሪቱ የሚታየውን የዘርፉ ባለሙያዎች ፍላጎት ለማሟላት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

የፕሮግራሙ የመጀመሪያ ዙር ሦስት ተመራቂዎቹ በከፍተኛ እንክብካቤ ህክምና ትልቅ አበርክቶ ይኖራቸዋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#ESSS

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይስን ሶሳይቲ በሥነ-ፈለክ፣ የሕዋ ምህንድስና እና የኤሮስፔስ ምህንድስና ዘርፍ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና አጠናቋል።

ለዘጠኝ ቀናት በተሰጠው ስልጠና ከ250 በላይ ሠልጣኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።

ሠልጣኞች የተማሩትን ቀድሞ ከነበራቸው የሳይንስ ዕውቀት ጋር በማጣመር በሥነ-ፈለክ፣ በሕዋ እና በኤሮስፔስ ምህንድስና የትምህርት ዓይነቶች ያዘጋጇቸውን ይዘቶች አቅርበዋል።

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ፕሮግራሞች ተማሪዎች መግቢያ እሑድ መስከረም 19/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በዕለቱ በየካምፓሶቻችሁ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በቅጣት ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም ብቻ ሲሆን፤ ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የ2015 እና የ2016 ባቾች እንዲሁም የሕክምናና ጤና ሳይንስ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎችን በቅርቡ መቀበሉ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት በተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል። ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል።

አዲስ ገቢ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የ NGAT ውጤት ከተገለፀ በኋላ ይከናወናል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#AksumUniversity

ባሳለፍነውሳለፍነው ሳምንት መደበኛ ነባር ተማሪዎቹን የተቀበለው አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣ በርካታ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በአካል ያልተመዘገቡ ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ ሰጥቷል።

በዚህም በቅጣት ምዝገባ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ገልጿል።

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚድያል ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 19:24:21
Back to Top
HTML Embed Code: