Telegram Web Link
#MoE

ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሔድ የቆየው 33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ተጠናቋል።

ጉባኤው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ስኬታማ እንዲሆን አበርክቶ ለነበራቸው የፌደራል እና የክልል ባለድርሻ አካላት ዕውቅና በመስጠት እና ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

የትምህርት ጥራትና የፍትሃዊነት ችግሮችን ለመፍታት እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች በቅንጅት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አላደረኩም ብሏል።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ ያላደረገ መሆኑን አረጋግጧል።

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ጥሪ በቅርቡ እንደሚያደርግ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ እስከዛ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
#MoE

ለቀናት ተራዝሞ የነበረው በ2017 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ዛሬ ተጠናቋል።

ፈተናው ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ወደየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል ለፈተና ስትሔዱ የተሰጣችሁን User Name and Password እንዲሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቃባችኋል።

@tikvahuniversity
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አለማድረጉን አሳውቋል።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አለማድረጉን አረጋግጧል።

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ጥሪ በቅርቡ እንደሚያደርግ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
በተለያዩ ክልሎች የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል።

የኦሮሚያ ክልል፣ ሀረሪ ክልል እና የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

በእነዚህ ክልሎች የተማሪዎች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ይካሔዳል።

ወላጆች፣ መምህራን እና ሌሎች ዜጎችም ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያደርጉ ልናበረታታ ይገባል።

@tikhavuniversity
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል (STEM Center) ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ 10ኛ ክፍል ከተዛወሩ ተማሪዎች መካከል አወዳድሮ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በ2017 ዓ.ም በማዕከሉ 10ኛ ክፍል ገብታችሁ ለመማር ፍላጎቱ ያላችሁና የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና ኮፒውን በመያዝ በማዕከሉ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

መስፈርቶች፦

► በ2016 ዓ.ም የ9ኛ ክፍል የእንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ እና ፊዚክስ ትምህርቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት በአማካኝ 90% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ፡፡

► መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ያላት እና ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የላቀ ዝንባሌ ያለው/ያላት፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ከነሐሴ 27/2016 እስከ ጳጉሜን 01/2016 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና መስከረም 03/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:30 በማዕከሉ ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን አስተዋወቀ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫው ተከታትሏል።

ዩኒቨርስቲው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል በዚሁ መግለጫ አስታውቋል።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕረዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፥ ራስ-ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ የተቋቋመው ዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ነጻነት፤ አስተዳዳሪዊ ነጻነት፤ የፋይናንስ ነጻነት እና አካዳሚክ ነጻነት ማግኘቱን ገልጸዋል።

" ይህም መምህራኑን ሆነ ተማሪዎችን የመምረጥ መብት ይሰጠዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

አዲስ ይተገበራል በተባለው የቅበላ አሰራር በ2014፤ 2015 እና 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የሚወጣውን መስፈርት ታሳቢ አድርገው በዩኒቨርሲቲው ፖርታል https://portal.aau.edu.et መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው ?

ዶ/ር ሳሙኤል ፥ አንዱ መስፈርት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 50 በመቶ በላይ ማምጣት እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህ ግን የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ 60 ወይም 70 በመቶ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል።

በመቀጠልም ዩኒቨርስቲው በራሱ የሚያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና (Undergraduate Admission Test) የሚኖረው ሲሆን ይህንን ፈተና ማለፍም ሌላው ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠው መስፈርት ነው ብለዋል።

ፈተናው ምን መልክ ይኖረዋል ?

በዩኒቨርስቲው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚቀርበው የፈተና ይዘት ምን መልክ አለው በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ሳሙኤል ፈተናው የአፕቲቲውድ (Apptitude) መልክ የሚኖረው እንደሆነ ጠቅሰው የተማሪዎችን የቋንቋ፤ የማመዛዘን እንዲሁም የቀመር አቅማቸውን የሚለካ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ፈተናው ከሌሎች የመግቢያ ፈተና ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው እንደሚችል ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ሆኖም የሚወጣው ፈተና ሙሉ በሙሉ የዩኒቨርስቲው እንደሚሆን አስረድተዋል።

የክፍያ እና የስኮላር ሺፕ ሁኔታ በተመለከተ ምን ተባለ ?

በዩኒቨርስቲው ለመማር ጥያቄ የሚያቀርቡ ተማሪዎች በሁለት አይነት መንገድ እንደሚስተናገዱ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

አንደኛው መስፈርቱን አሟልተው እና ሙሉ ክፍያ ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ ሌላው መንግስት ስፖንሰር ሺፕ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ተማሪዎች ናቸው።

ይህን በተመለከተ የተቀመጠ ኮታ እንደሌለ የገለጹት ዶ/ር ሳሙኤል እንደ እቅዳቸው ግን 50 በመቶ በመንግስት 50 በመቶ በግል ወጪያቸው የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች ለመቀበል እንደሆነ ገልጸው ካልሆነም ቁጥሩ በተወሰነ መልኩ ልዩነት ሊኖረው እንደሚችልም ጠቁመዋል።

መንግስት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለሀገር በሚፈለጉ የስልጠና መስኮች ወጪን ጭምር በመሽፈን የሚያስተናግድበት ሥርዓት እንደሚኖር እና ለሴቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ከታዳጊ ክልል ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ተመላክቷል።

ተማሪዎች በሚያመለክቱበት ወቅት ብዙ ቅጾችን እንደሚሞሉ ፤ ስኮላርሺፕ የሚጠይቁ ተማሪዎች ከፍለው መማር እንደማይችሉ የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው እና የሚያስገቡት መረጃ ትክክለኛነቱ እንደሚጣራና ሐሰተኛ ሆኖ ከተገኘ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ጭምር አንስተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ዩኒቨርስቲው በተከታታይ እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ፕሮግራም በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

አመልካቾች በሰኔ 2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ወስደው 85 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ከነሐሴ 27-30/2016 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ፕሮግራም ህንፃ ቁ. 54 ቢሮ ቁ. 114

ፍላጎቱ ያላችሁና የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ውጤት ማስረጃችሁን እንዲሁም የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒውን በመያዝ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ውጤት ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ይገለፃል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0942292425 / 0910041583

@tikvahuniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም ነባር የ1ኛ ዓመት (2ኛ ሴሚሰተር) ፣ የ2ኛ ዓመት (2ኛ ሴሚሰተር) እንዲሁም የ5ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከጥቅምት 1-3/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ትምህርት ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ዕለታዊውን የ5 ብር የኢንተርኔት ጥቅል ገዝታችኋል? ይጨመራል!

እስከ 50% ጭማሪው እንደቀጠለ ነው! ዕለታዊውን የኢንተርኔት ጥቅል እንግዛ፣ እስከ 50% ተጨማሪ ስጦታን እናግኝ!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
በኦሮሚያ ክልል የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል 12.4 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 27 እስከ ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን፤ የመማር ማስተማር ሒደቱ መስከረም 7/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
በሀረሪ ክልል የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተጀምሯል።

የተማሪዎች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም አስከ ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ይካሔዳል።

በክልሉ የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 7/2017 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡

በሐረሪ ክልል ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ የሚያስተምሩ 168 የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ።

@tikvahuniversity
2024/10/03 21:28:14
Back to Top
HTML Embed Code: