Telegram Web Link
በድሬዳዋ አስተዳደር የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በአስተዳደሩ በሁሉም የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች የሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ ማድረግ ጀምረዋል፡፡

የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በተለያየዩ የአስተዳደሩ አካባቢዎች በመገኘት ቅስቀሳና ንቅናቄ ሲያካሒድ የቆየ ሲሆን፤ የማጠቃለያ መርሐግብር ዛሬ አከናውኗል፡፡

ቢሮው በ2017 የትምህርት ዘመን በአንደኛ ደረጃ፣ በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ137 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዕቅድ ይዟል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ይመዝገቡ!


በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጋራ የተዘጋጀው 2ኛ ዙር የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያና ፈጠራሠመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀምሯል።

ፕሮግራሙ ወጣቶች ችሎታቸውን እና የፈጠራ ሐሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ሥራ እንዲለውጡ የሚያስችል ነው።

በማንኛውም መስክ የቴክኖሎጂ እና የሥራ ፈጠራ ሐሳብ ያላችሁ በሙሉ ከታች የተቀመጠው ሊንክ ላይ በመግባት መመዝገብ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ 👇
https://forms.office.com/r/CNMFUUSZZe

ከምዝገባ በኋላ በሚካሔድ ልየታ ለሚመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የሠመር ካምፕ ፕሮግራሙ፣ አዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ካምፓስ ይካሔዳል።

@tikvahuniversity
የሙዚቃ ውድድራችን የሚቆየው እስከ መስከረም 18 ብቻ ነው! አሁኑኑ ወደ ቲክቶክ 🏃‍♂️

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 86
➤ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመትና ከዚያ በላይ
➤ የሥራ ቦታ፦ ቦረና ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት

የማመልከቻ አማራጮች፦
ቦረና ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም አዲስ አበባ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ፣ አራት ኪሎ፣ የቀድሞው የጀርመን ባህል ኢንስቲትዩት ህንፃ ቢሮ ቁ. 15 የማመልከቻ ደብዳቤ፣ ሲቪ እና የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ "STEM" ማዕከሉ ሲሰጥ የቆየውን የክረምት ስልጠና አጠናቋል።

ከሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ 200 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ለ15 ቀናት የተሰጠውን ስልጠና ተከታትለዋል።

@tikvahuniversity
#TTI

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች ያስተማራቸውን ሰልጣኞች ቅዳሜ ጳጉሜን 02/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በዲግሪ እና በደረጃ ፕሮግራም በቀን እና በማታ መርሐግብር ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
በ2017 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር የአመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናውን የሚሰጡበትን ቀን ማሳወቅ ጀምረዋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
► ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
► ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
► ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም
አክሱም ዩኒቨርሲቲ
► ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም
መቱ ዩኒቨርሲቲ
► ነሐሴ 30 እና ጳጉሜን 01/2016 ዓ.ም
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
► ነሐሴ 30 እና ጳጉሜን 01/2016 ዓ.ም

ወደየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል ለፈተና ስትሔዱ የተሰጣችሁን User Name and Password እንዲሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቃባችኋል።

(ወደፈናው ስትሔዱ ልታደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#የተረጋገጠ

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጥበት ቀን እና ሰዓት

ፈተናው ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

(ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነውን የትምህርት መስኮችና የመግቢያ ፈተና የሚሰጥባቸውን መርሐግብር ከላይ ይመልከቱ።)

@tikvahuniversity
2024/10/03 19:26:25
Back to Top
HTML Embed Code: