Telegram Web Link
ድጋፍ ያድርጉ!

ጣሊያን ሀገር ለትምህርት በሔደበት ህይወቱ አልፎ የተገኘውን ኢትዮጵያዊው ተማሪ አስክሬን ወደ ሀገርቤት ለማምጣት ድጋፍ ያድርጉ።

የ22 ዓመቱ አቤኔዘር ተሰማ አበበ ስኮላርሺፕ አጊኝቶ ነበር ወደ ጣሊያን፣ ሲሲሊ ግዛት ያቀናው። በመሲና ዩኒቨርሲቲም የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበር።

ተማሪ አቤኔዘር ሰኞ ማታ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን፤ የህልፈቱን ምክንያት ፖሊስ እየመረመረ እንደሚገኝ ከቅርብ ቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የተማሪ አቤነዘር አስክሬንን ወደ ሀገር ቤት ለመምጣት ወጪው ከፍተኛ በመሆኑ ቤተሰቦቹን ለመርዳት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

gofundme 👇
https://gofund.me/01490b2f

የአቶ ተሰማ አበበ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ 👉 1000020084913

አቶ ተሰማን በስልክ ለማግኘት 0911817718 ላይ መደወል ይችላል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
ችሮታው አየለ (ዶ/ር) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር መመደባቸው ይታወቃል፡፡

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ነሐሴ 21/2016 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ፥ ችሮታው አየለ (ዶ/ር) ከነሐሴ 22/2026 ዓ.ም ጀምሮ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ መመደባቸውን ያሳያል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አያኖ በራሶ (ዶ/ር) የኃላፊነት ጊዚያቸው አብቅቶ ነው? ከኃላፊነት ተነስተው ወይስ ለሌላ ኃላፊነት ተፈልገው? የሚለውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ጠይቋል።

በዚህም የአያኖ በራሶ (ዶ/ር) የኃላፊነት ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት እንዳበቃ ለማወቅ ችለናል። ይሁን እንጂ ትምህርት ሚኒስቴር በምትካቸው ምደባ ባለማድረጉ ምክንያት እስካሁን በስራቸው ላይ የቆዩ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የጀመረውን ጉዞ ሲመሩ እንደነበርም ሰምተናል።

በሌላ በኩል ባደረግነው ማጣራት ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን ተነስተዋል ለማለት አስቸጋሪ እንደሆነም ተገንዝበናል፡፡ ምክንያቱም የሥራ ዘመናቸውን ከጨረሱ የቆየ በመሆኑ።

አያኖ በራሶ (ዶ/ር)ን በመተካት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

@tikvahuniversity
ነጻ የኮዲንግ ስልጠና ይውሰዱ!

በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ስልጠና ዕድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://www.ethiocoders.et/ ላይ ይመዝገቡ፡፡

ስልጠናውን በተሰጡት ስምንት ሳምንታት ለሚያጠናቅቁ ብቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል፡፡

ይመዝገቡ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity
በኦሮሚያ ክልል ለ2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን በኦሮሚያ ክልል ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 12.3 ሚሊዮን ተማሪዎች ለመመዝገብ መታቀዱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ተናግረዋል፡፡

የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ከነሐሴ 27 እስከ ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን፤ የመማር ማስተማር ሂደቱ መስከረም 7/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር ገልፀዋል።

በክልሉ በክረምቱ ወቅት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታና ጥገና፣ የቤተ-መጻሕፍት ግንባታ እንዲሁም የአንደኛ ደረጃ የመማሪያ መጻሐፍት ስርጭት መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
እለታዊ የ150 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፓኬጅ ገዝተናል ፤በሉ ምርቃቷን ጣል አድርጉባት' ላላችሁን ፤ እስከ 50% ተጨማሪ 100 ሜ.ባ ስጦታ እንዳከልንበት ብንነግራችሁስ ? ምርቃት M-PESA ላይም አለ እለታዊውን የኢንተርኔት ጥቅል እንግዛ እስከ 50% ተጨማሪ ስጦታን እናግኝ !

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
በ2016 ዓ.ም አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች 16 ፕሮግራሞቻቸውን ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ አስደርገዋል፡፡

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አራት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለት እንዲሁም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አንድ በድምሩ 16 ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታቸውን ተሰምቷል፡፡

ይህ ዕውቅና አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተማሪ ለማፍራት እንደሚያግዝ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
33ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ "ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ሥራ ትምህርት ቤት በመካሔድ ላይ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በትምህርት ዘርፍ የተያዘውን ግብ ለማሳካት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራባቸውን አራት ጉዳዮች አብራርተዋል።

ጥራት እና ፍትሃዊነትን ማስፈን እንዲሁም ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት እና ቅንጅታዊ አሠራር ማጎልበት ላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

በዚህም በትምህርት ዘርፍ ያሉ ባለድርሻ አካላት የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያ ስኬታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሔደው ጉባኤ፤ የትምህርት ዘርፍ የ2016 ዓ.ም አፈጻጸም፣ የ2017 ዓ.ም ዕቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#ScholarshipTip

የስኮላርሺፕ ዕድል ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች ከመልቲቾይስ አፍሪካ!

በዲኤስቲቪ /መልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ/ ለአንድ ዓመት ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የሚሰጥ ነጻ የስኮላርሺፕ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ።

ዕድሜያችሁ ከ18-26 ዓመት የሆናችሁ ወጣት የፊልም ባለሙያዎች እስከ መስከረም 5/2017 ዓ.ም ድረስ በ applications.multichoicetalentfactory.com ላይ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

አመልካቾች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እና ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ሊኖራችሁ ይገባል!

@tikvahethiopia
#MoH

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ጤና ሚኒስቴር በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ቴምፓራሪ ዲግሪ ለተሰጣቸውና የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ላጠናቀቁ የጤና ባለሙያዎች በነሐሴ 2016 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ በምዝገባ ወቅት ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር የያዘ ወረቀት (ስሊፕ) ፕሪንት አድርጎ መያዝ ይጠበቅበታል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
በ2016 ዓ.ም አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች 16 ፕሮግራሞቻቸውን ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ አስደርገዋል፡፡ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አራት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለት እንዲሁም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አንድ በድምሩ 16 ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታቸውን ተሰምቷል፡፡ ይህ ዕውቅና አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተማሪ ለማፍራት እንደሚያግዝ…
አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በ2016 ዓ.ም 16 ፕሮግራሞቻቸው ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ማስደረጋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ፕሮግራሞቻቸው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ካገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ ሲሆን፤ በአራት የምህንድስና ትምህርት ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ዕውቅና በህዳር 2016 ዓ.ም ማግኘቱ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኘው Accreditation Board of Engineering and Technology (ABET) ተቋም ለአራት ፕሮግራሞቹ ዕውቅና አጊኝቷል። በዚህም አራት የመጀመሪ ዲግሪ ፕሮግራሞቹ (ሜካኒካል፣ ሲቪል፣ ኤሌክትሪካል እና ኬሚካል ምህድስና የትምህርት መስኮች) ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት መስፈረትን አሟልተው የስድስት ዓመት ዕውቅና አጊኝተዋል፡፡

ዕውቅናው የዩኒቨርሲቲውን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ከማጠናከር ባለፈ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ተቋማት መቀጠር የሚያስችላቸውን ዕድል የሚያስገኝ ሲሆን በውጭ ሀገር የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው በቀጥታ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስችል ነው።

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል?

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ የሚጠይቁ በርካታ መልዕክቶች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡

የመልቀቂያ ፈተናው ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል ስንል አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

"የፈተናው እርማት በጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሆነ" የገለፁት ኃላፊው፤ እርማቱ እንደተጠናቀቀ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

"እርማቱ በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየተሠራ መሆኑንና በቅርቡም ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ" ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።

በቀን ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተፃፈ ደብዳቤ ፤ ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) ከነሐሴ 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።

ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የምክትል ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነቶች በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸው ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ሥራ ያቆሙ መምህራን በዝውውር በሌሎች አካባቢዎች እንዲሠሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መመርያ አስተላለፈ፡፡

በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በ2016 ዓ.ም መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በሥራ ቦታቸው በመገኘት የመማር ማስተማር ሥራቸውን በአግባቡ ማከናወን ካለመቻላቸውም ባሻገር፣ በከፍተኛ የሥነ ልቦናና ማኅበራዊ ችግሮች በመጋለጣቸው ተዘዋውረው እንዲሠሩ ቢሮው
ለዞንና ለሪጂዮ ፖሊታን የከተማ አስተዳድር ትምህርት መምርያዎች ከላከው ደብዳቤ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከመደበኛ ሥራ ላይ ካለው የዝውውር መመርያ ወጣ በማለት፣ በጦርነቱ ችግሩ የገጠማቸውን መምህራንና አመራሮችን ለመርዳት ቢሮው መወሰኑን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የትምህርት ቢሮው አንድ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ነሐሴ 21/2016 ዓ.ም በክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ፣ ከዚህ ቀደም ለተመሳሳይ ዓላማ የወጣውና እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም እንዲያገለግል ተብሎ የተላለፈው ጊዜያዊ ዝውውርን የሚፈቅድ አሠራር በድጋሚ ለአንድ ዓመት መራዘሙን ይገልጻል፡፡

ደብዳቤው የፀጥታ ሁኔታው እየተሻሻለ ያለ ቢሆንም፣ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ያልተቀረፈ በመሆኑ፣ ከአሁን በፊት የወረደውን የአሠራር አቅጣጫ እንዲራዘም ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በጦርነቱ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦናና የደኅንነት ስጋት ያጋጠማቸውን መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች፣ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚያገለግል አስተዳደራዊ መፍትሔ በመስጠት፣ ከስጋታቸው ነፃ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ሰለመሆኑ ደብዳቤው ያብራራል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
2024/10/03 19:30:05
Back to Top
HTML Embed Code: