Telegram Web Link
ምን እየጠበቅን ነው? ቲክቶክ ላይ የሙዚቃ ችሎታችንን እያሳየን እስከ 400,000 ብር እንሸለም እንጂ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት!
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ!
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#ይመዝገቡ

በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከተጀመረ አንድ ሳምንት አልፏል።

ምዝገባው ሊጠናቀቅ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እስከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም ብቻ ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ 👇
https://NGAT.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

° " ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " - የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንትርን ሀኪሞች

° " ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " - ዩኒቨርሲቲው

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ምግብ መከልከላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት ቢያቀርቡም መፍትሄ በማግኘት ፋንታ " እናባርራችኋለን " የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው አስረድተው፣ "  ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉት 2010 ዓ.ም እንደሆነ ፤ በተለያዩ ችግሮች ሁለት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ እንደባከነባቸውና እንዳልተካካሰላቸው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተማሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ሳለ እነርሱ ህክምና መከልካላቸውን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚደንት ዶክተር መንገሻ አየነን አናግሯል።

ዶክተር እሳቸው ጋር ምንም አይነት የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለ ገልጸው፣ ለማን ቅሬታ እንዳቀረቡ ኢንተርን ሀኪሞቹ በድጋሚ እንዲጠየቁ አሳስበዋል፡፡

እሽ በማለት ቅሬታ አቅራቢዎቹን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት አሳውቃችሁ ነበር ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽም፣ " ለዶክተር መንገሻ አልደረሰም፡፡ ለተማሪዎች አገልግሎት አቅርበናል " ብለዋል።

ለምን ለዩኒቨርቲው ከፍተኛ አካላት እንዳላቀረቡ ሲያስረዱም፣ " የተማሪዎች አገልግሎት 'ይሄ ጉዳይ ከእኔ አልፎ ወደ ላይ ቢሄድ አውቶማቲካሊ ሴኔት ሰብስብቤ ፈርሜ አባራችኋለሁ' አለን " ብለዋል፡፡

" ቅሬታችንን ለዶክተር መንገሻም አላሳወቁትም ከታች ነው ያስቀሩት " ሲሉም አክለዋል፡፡

ቅሬታው ደርሷቸዋል የተባሉት አካላት ለጊዜ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቅሬታ ያቀረቡበትን ክፍል በመግለጽ በድጋሚ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ መንገሻ (ዶ/ር)፣ የኢንተርን ሀኪሞቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ያላወቀው ቅሬታ እንደሆነ አስረድተው፣ ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

" ፕሮፌሰር የሺጌታ የሚባል ሲኢድ አለን ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ሙሉውን የሚመራ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ነው እዚያ ግቢ " ያሉት መንገሻ (ዶ/ር)፣ ' ፕሮፌሰሩን ይጠይቁ፡፡ እሱ ካልፈታላቸው ወደ እኔ ይመጣሉ ወይም ደብዳቤ ካላቸው ያምጡ " ብለዋል፡፡

" ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " ሲሉ አክለዋል፡፡

(ጉዳዩ ከምን እንደደረሰ ተከታትለን መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

የPhD ትምህርት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን ለ2ዐ17 ዓ.ም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትምህርት መስክ የPhD ፕሮግራም በመደበኛ መርሐግብር አመልካቾችን ተቀብለው ማስተማር ይፈልጋሉ፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦

► የሁለተኛ ዲግሪ በተያያዥ የትምህርት ዘርፍ ከታወቀ የትምህርት ተቋም፣
► በሁለተኛ ዲግሪ CGPA ለሴቶች 3.00 ፤ ለወንዶች 3.25፣
► የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና ያለፉ፣
► የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ፅሁፍ ውጤት 'ጥሩ' የሆነ፣
► ከ10 ገጽ ያልበለጠ 'Synopsis'ማዘጋጀት ይጠበቅባችኋል፣
► ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

የማመልከቻ ጊዜ፦
ከዛሬ ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 06/2017 ዓ.ም (በኦንላይን)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#ይመዝገቡ በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከተጀመረ አንድ ሳምንት አልፏል። ምዝገባው ሊጠናቀቅ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እስከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም ብቻ ይመዝገቡ። ለመመዝገብ 👇 https://NGAT.ethernet.edu.et @tikvahuniversity
ሀገራዊ_የድህረ_ምረቃ_መግቢያ_ፈተና_አሰጣጥና_አስተዳደር_ማኑዋል_መጋቢት_2016_ዓም_GAT_Manual.pdf
6.1 MB
የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ማንዋል

አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመስከረም እና በህዳር 2016 ዓ.ም በሁለት ዙር የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ 3ኛው ዙር የ NGAT ፈተና በዚህ ወር እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

(ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉት የሚጠበቀው “አገራዊ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ማንዋል" ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የምርምር ዩኒቨርሲቲ የሆነው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለድኅረ ምረቃ እና ለምርምር ሥራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለድኅረምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች፦
- የዶርም አገልግሎት፣
- የቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣
- የዲጂታል ቤተመጻሕፍትና ኮምፒውተር ማዕከላት እና
- የ24 ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎት ያቀርባል፡፡

ተቋሙ ለፒ.ኤች.ዲ. ምርምር አወዳድሮ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጥም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

(ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች በ11 ኮሌጆች ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምርባቸው የትምህርት መስኮች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
በአዲስ አበባ ዕገዳ በተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በፈለጉት ትምህርት ቤት እንዲመዘገቡ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለፀ።

35 ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ #እንዳያካሒዱ ባለስልጣኑ ባለፈው ሰኔ ማገዱ ይታወሳል፡፡

በታገዱት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በየትኛውም የመንግሥት ወይም የግል ትምህርት ቤት ተመዝግበው መማር እንዲቀጥሉ እየተደረገ መሆኑን ተቋሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግሯል።

በዚህም የተማሪዎቹ ምዝገባ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ እንደሚገኝና ከታገዱ ትምህርት ቤቶች የወጡ ተማሪዎችም በፈለጉበት ትምህርት ቤት እንዲመዘገቡ እየተደረገ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን እና ጥፋታቸውን አርመው ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንደገና ፈቃድ መጠየቅ እንደሚችሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

ለቀጣይ 2017 የትምህርት ዘመን 1,332 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን መዝግበው እንደሚያስተምሩ ባለስልጣኑ መግለፁ ይታወሳል። #መናኸሪያሬዲዮ

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የጤና ሙያተኞች የሙያ ብቃት ምዘና ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል፡፡ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ከመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ተማሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ሰኔ 19/2016 ዓ.ም መስጠታቸው ይታወቃል፡፡ በ17 የጤና ሙያዎች የተሰጠውን ፈተና 15 ሺህ የሚጠጉ ተመዛኞች መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡ ከምዘናው…
የጤና ባለሙያዎች የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት

በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም የተሰጠው የጤና ባለሙያዎች የመውጫ እና ብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁ እና የጤና ሚኒስቴርን የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች ከነሐሴ 03/2016 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ይላካል ተብሏል።

በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ይህን ተከትሎ በሚወጣ ማስታወቂያ የተግባር ምዘና (OSCE) ፈተና የምዝገባ መርሐግብር ስለሚወጣ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የጤና ባለሙያዎች የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም የተሰጠው የጤና ባለሙያዎች የመውጫ እና ብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።…
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

የፋርማሲ መውጫ ተፈታኞች " ሰሚ አጥተናል " እስካሁን አሉ።

ዛሬ ከፋርማሲ ውጭ የሲኦሲ ሲመጣ ቅሬታ ማስገቢያ ኢሜል እና ስልክ አለ ያለቱ ተማሪዎቹ " እኛም የመውጫ ፈተናውን ቅሬታ እንድናስገባ ይደረግ " ብለዋል።

ተማሪው እስካሁን ተጨንቆ ነው ያለው የባለፈው ቅሬታ እስካሁን አልተፈታልንም። ሰሚ አጥተናል ብለዋል።

ቲክቫህ ነገ በዚህ ጉዳይ የሚመለከታቸውን ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች ለዝግጅት የሚረዳ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ሦስቱም ካምፓሶች የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች እስከ ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም በአካል ወይም በስልክ ቁ. 0921194016 በመመዝገብ ስልጠናውን በሚቀርባችው ካምፓስ ተገኝታችሁ አንድትወስዱ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የሦስቱ ካምፓሶች የስልጠና ፕሮግራም፦

ሻምቡ ካምፓስ ► ከነሐሴ 8-10/2016 ዓ.ም
ነቀምቴ ካምፓስ ► ከነሐሴ 13-15/2016 ዓ.ም
ግምቢ ካምፓስ ► ከነሐሴ 16-18/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ Social Work የፒ.ኤች.ዲ. ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ Social Work ትምህርት ክፍል በመስኩ ሙያቸውን ለማጎልበት ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የፒ.ኤች.ዲ. ትምህርት ፕሮግራም ከፍቷል፡፡

የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሙ በ Social Work ምርምር፣ አመራር እና ፖሊሲ ልማት የላቀ ስልጠና ለሰልጣኞች ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ትምህርት ክፍሉ አመልካቾችን መቀበል የጀመረ ሲሆን ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ 👉 [email protected] ኢሜይል አድራሻን ይጠቀሙ፡፡

@tikvahuniversity
#Update

"ለፋርማሲ ተማሪዎች እንዲሁም የብቃት ምዘና ፈተና በድጋሜ ለሚፈተኑ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው በቅርቡ ይሰጣል፡፡" - ጤና ሚኒስቴር

የፋርማሲ ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ከተሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና (Licensure Exam) ጋር የተያያዙ በርካታ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል በጉዳዩ ዙሪያ ተከታዩን መረጃ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰጥተዋል፡፡

ባለፈው ሰኔ የተሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና በተመለከተ ጤና ሚኒስቴር ከፋርማሲ ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጉን መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና 200 ጥያቄዎች ያሉት መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ የፋርማሲ ተማሪዎች በሰኔ ወር መጨረሻ የወሰዱት ፈተና 100 ጥያቄዎች እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በመሆኑም "የብቃት ምዘና ፈተናው የጤና ሚኒስቴርን መስፈርት ባሟላ መልኩ 200 ጥያቄዎች የያዘ ፈተና በድጋሜ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መወሰኑን" ተናግረዋል፡፡ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልፀዋል፡፡

ለፋርማሲ ተማሪዎች እንዲሁም ዲግሪ ይዘው የብቃት ምዘና ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ የምዝገባ ጥሪ ይደረጋል ብለዋል፡፡

እስከ ቀጣይ ዓመት መጠበቅ ሳያስፈልግ የብቃት ምዘና ፈተናው በዚህ ወር እንደሚሰጥ መሪ ስራ አስፈጻሚው ለቲክቫህ አረጋግጠዋል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/04 05:34:24
Back to Top
HTML Embed Code: