Telegram Web Link
Tikvah-University
Photo
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ8,500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ከሰጡ 78 የትምህርት ክፍሎች መካከል 38ቱ ያስፈተኗቸውን በሙሉ ማሳለፋቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ገልፀዋል። 16 የትምህርት ክፍሎች ደግሞ እያንዳንዳቸው ከአንድ ተማሪ በስቀር ሁሉንም ማሳለፋቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፋዊነቱን እያጎላ እንደሚገኝ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ ከአፍሪካ ምርጥ 100 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል። የውጭ ሀገራት ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑንም ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
° " በጀት አጥሮናል ቤታችሁ ቆዩ በመባላችን አላግባብ ጊዜያችን እየተቃጠለብን ነው መፍትሔ እንሻለን " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች

° " ከተወካዮቻቸው ጋር በቅርቡ እንነጋገራለን " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ት/ክፍል ተጠሪ


" ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ በመሆኑ የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል " ሲሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

" ዩኒቨርሲቲው በበጀት እጥረት ምክንያት መግቢያችን ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ትክክል አይደለም " ብለዋል ተማሪዎቹ።

በኮቪድ-19 ለአስር ወራት እንዲሁም በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት የትምህርት ጊዚያቸው መቃጠሉንና የመመረቂያ ጊዚያቸው መራዘሙን ተማሪዎቹ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት ለ12ኛ ክፍል ፈተና እንዲወጡ ተደርገው ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም እንደተጠሩና በኋላም ወደ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም እንደተገፋ፤ አሁን ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ይገልፃሉ።

አሁን የምግብ በጀት በቂ ባለመሆኑ ኢንተርን ዶክተሮች ወደ የነን ካፌ ፎርም በመሙላት ከዶርም እንዲወጡና እየተመላለሱ እንዲጨርሱ እንዲሁም ወደቤተሰብ የሄዱ ተማሪዎች በዛው እንዲቆዩ  ዩኒቨርሲቲው ማስታወቂያ ማውጣቱ አሳሳቢ እንደሆነ አንስተዋል።

በመሆኑም የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የጠየቃቸው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተጠሪ ዶ/ር ጌታሰው ጥያቄውን በተመለከተ ከተማሪዎች ጋር በተለይም ከተማሪ ተወካዮች ጋር እንደሚነጋገሩ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Tikvah-University
° " በጀት አጥሮናል ቤታችሁ ቆዩ በመባላችን አላግባብ ጊዜያችን እየተቃጠለብን ነው መፍትሔ እንሻለን " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች ° " ከተወካዮቻቸው ጋር በቅርቡ እንነጋገራለን " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ት/ክፍል ተጠሪ " ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ በመሆኑ የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል " ሲሉ የሀዋሳ…
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምላሽ !

" ማስታወቂያዉ ከኮሌጁ እውቅና ውጭ የተለጠፈ በመሆኑ በለጠፈዉ አካል ላይ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኑሮ ዉድነቱ ምክኒያት ተማሪዎችን መመገብ ባለመቻሉ ተማሪዎች የተመደበላቸዉን 22 ብር ወስደዉ እንዲጠቀሙ የሚገልጽ ማስታወቂያ ማዉጣቱን እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል ግቢዉን ለቀዉ የወጡ ተማሪዎች ጥሪ እንዳልተደረገላቸዉ መናገራቸዉን ገልጸን የተማሪዎችን ቅሬታ አቅበን ነበር።

ይህን ተከትሎ " የቀረበዉ መረጃ ትክክል አይደለም " ያሉን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ ኢንተርን ሀኪሞች ከግቢ እንደማይወጡና ዶርማቸዉን እንደማይለቁ ይልቁንም ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርስቲው የምግብ አገልግሎት በመቋረጡ በጀታቸዉን እንዲጠቀሙ ስለመገለጹ ነግረዉናል።

ይህ የሆነበት ምክኒያት አሁን ላይ ለሶስት አመት ዉል የገቡ ነጋዴዎች በእቃ መወደድ ምክኒያት ምንም አይነት የምግብ ግብአት ሊያቀርቡልን ባለመቻላቸዉና ይህን ችግር ተወያይተን መፍትሄ እስክንሰጠዉ ነው ሲሉ ይገልፃሉ።

ሌሎች ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ ትክክለኛ ቀኑንም ለተማሪዎች በይፋ የሚነገራቸው ይሆናል የሚሉት ሀላፊዉ ተማሪዎችን አሁን ላይ መቀበል ያልቻሉት ከምግብ አቅርቦትና አንዳንድ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ነዉ ብለዋል።

ከዚህ ዉጭ በየጊዜዉ ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል መዉጣታቸዉም ሆነ አሁን ላይ በቶሎ አለመግባታቸዉ የሚወስድባቸዉን ጊዜ ለማካካስም ዩኒቨርሲቲዉ መፍትሄዎችን ማስቀመጡን ገልጸዉልናል።

ይሁንና ተማሪዉን የሚያደናግር ማስታወቂያ ያወጣዉ አካል ከኛ እዉቅና ዉጭ በመሆኑ ማንነቱን አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ብለዉናል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንቱ ተማሪ ደረጀ መንገሻ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ ምንም እንኳን ኢንተርን ዶክተሮች ከግቢ ባለመዉጣታቸዉ እስካሁን መጉላላት እንዳልደረሰባቸዉ ቢገልጽም ማስታወቂያዉ ያለነሱ እዉቅና መለጠፉም ሆነ ተማሪዉን ሳይፈልግ ወደነን ካፌ መቀየር አግባብ ስላልሆነ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ዉሳኔዉ ልክ አለመሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተን ምላሽ እየጠበቅን ነዉ ብሏል።

ተማሪዎች ሀምሌ 25 ያልገቡበት ምክኒያት ዩኒቨርሲቲዉ ከበጀት ማስተካከያና ካምፓስ ዉስጥ ከሚያስተካክሏቸዉ አንዳንድ ነገሮች ጋር በተያያዘ ምክኒያት መሆኑንና በዚህ ምክኒያት በቀጣይ ተማሪዎች ላይ የሚከሰተዉን ጫና በተመለከተ ዩኒቨርሲቲዉ እንዲያስብበት ተነጋግረናል በማለት ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት ውድድር የማጠቃለያ መርሐግብር ተካሒዷል።

ውድድሩ ከ3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚማሩ ተማሪዎች መካከል ''ማይ ሶሮባን'' ኢትዮጵያ በተሰኘ ድርጅት አዘጋጅነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሔድ ቆይቷል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመጡ መምህራን ዳኝነት በተካሔደው ውድድር፤ ከ50 ከተሞች የተውጣጡ ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል።

የሒሳብ ትምህርት ከባድ ነው በሚል የሚታሰበውን የተሳሳተ አመለካከት በመቅረፍ ተማሪዎችን በትምህርት አይነቱ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ቀደም ሲል በየአከባቢያቸው በተደረገ ውድድር አሸናፊ ሆነው ለማጠቃለያው ውድድር የደረሱ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት በክብር እንግዶች የተበረከተ ሲሆን፤ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድሩ በየክፍል ደረጃው እስከ መጪው ረቡዕ ተካሒዶ ለአሸናፊዎች ዕውቅና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን የቀድሞ ተማሪዎች ጉባዔ (Alumni Conference) ሊያካሒድ ነው፡፡

ለዚህም ዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች ኅብረት ለማቋቋም እየተንቀሳቀስ እንደሚገኝና ምዝገባ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያውን የቀድሞ ተማሪዎች ጉባኤ በ2017 ዓ.ም ለማካሄድ የቀድሞ ተማሪዎቹን በማሰባሰብ ላይ ነው።

ለምዝገባ የተዘጋጀውን ቅፅ 👉 https://forms.gle/qEjb6XLEEpHGsasq6 በመሙላት የቀድሞ ተማሪዎች ኅብረቱን ይቀላቀሉ፡፡

@tikvahuniversity
ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ 'የኮዲንግ' ሰልጣኞች በአዲስ አበባ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ነው፡፡

'Addis Coder' የተሰኘው መርሐግብር ለአራት ሳምንታት በነጻ የሚሰጥ የክረምት ስልጠና መርሐግብር ሲሆን፤ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የአልጎሪዝም እና ፕሮግራሚንግ ስልጠናዎች ይሰጣቸዋል፡፡

ስለጠናው በአንጋፋ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚያስተምሩ መምህራን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚሰጥ ነው፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የአዲስ ቻምበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተለያዩ አጫጭር የቢዝነስ ስልጠናዎችን ከዛሬ ጀምሮ መስጠት ይጀምራል፡፡

ስልጠናዎቹ ከሐምሌ 29/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 9/2017 ዓ.ም እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡

ከሚሰጡ ስልጠናዎች መካከል ካፒታል ማርኬት፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የአመራር ክህሎት፣ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ኦፊስ ኦፐሬሽንስ ማኔጅመንት ይገኙበታል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0115500934 / 0911194965 / 0911343078 / 0913553393

የኢ-ሜይል አድራሻዎች፦
[email protected] / [email protected] / [email protected]

(የስልጠናዎቹን አይነት፣ የጊዜ ርዝመት እና ክፍያ መጠን የሚያሳይ ከኢንስቲትዩቱ የተገኘ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
የመምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን በዩኒቨርሲው በመገኘት የስልጠናውን አሰጣጥ ተመልክቷል።

በዩኒቨርሲቲው እየተሰጠ ባለው የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከ 2 ሺህ በላይ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

"ሰልጣኞች ከአበል ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን እንዳቀረቡና ስልጠናውም ተቋርጦ እንደነበር" የሚያሳዩ መረጃዎች ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወሩ ነበር፡፡

"በስልጠናው ተሳታፊዎች እንደ ችግር የሚነሱና አስተዳደራዊ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን በቅርበት በመከታተል መፍትሔ እንዲያገኙ ይደረጋል" ብለዋል በዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ጉብኝት ያደረጉት ሚኒስትር ዴኤታዋ።

ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በ28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሥራቸውን ለማስቀጠል የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለማግኘት እስከ ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደገና ምዝገባ ማከናወን እንዳለባቸው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል። ዳግም ምዝገባው ያስፈለገው እንደ  ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል። በዚህም በመንግሥት እና በግል ተቋማት…
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በፌደራል ደረጃ ፈቃድ የተሰጣቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ባወጣው የዳግም ምዝገባ መምሪያ መሰረት እስከ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ድረስ ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

በዚህም ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቋም፣ በካምፓስ እና በፕሮግራም ደረጃ ያሉ መረጃዎችን በሀርድ ኮፒ እና ሶፍት ኮፒ መረጃዎችን በማደራጀት በአካል እንዲያቀርቡ ባለሥልጣኑ አስረድቷል።

(የባለሥልጣኑ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የተማሪዎችድምጽ

° “ ሳንመረቅ አመታት ተቆጠሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው መቼ እንደሚጠራን ያሳውቀን ” - ተመራቂ ተማሪዎች

° “ መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ


ትግራይ ውስጥ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ጭምር የመመረቂያ ጊዜያቸው የተራዘመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመመረቅና ድግሪ ለመያዝ አመታትን እንደጠበቁ ፣ አሁንም ዩኒቨርሲቲው እንዳልጠራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ምን አሉ ?

- ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ስለጉዳዩ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቀን ነበር። የመውጫ ፈተና እንደምንፈተን እና ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ላይ እንደምንመረቅ ነበር ስኬጁል የወጣው።

- የመውጫ ፈተናውን ብንወስድም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ወጥተናል። ከዚያ ነሐሴ 2016 ዓ/ም ትጠራላችሁ ተባልን፡፡ አሁን የክረምት ተማሪዎችም ተጠርተዋል፡፡ እስካሁን የኛ ግን ምንም ነገር የለም። ዝም ጭጭ ብለዋል።

- የፌደራል መንግስትም በጦርነነቱ ጊዜ የነበሩ ተማሪዎች በዓመት 3 ሴሚስተር ማካካሻ ጊዜ ፈቅዶልን ነበር፡፡ ያኔ የተፈቀደልንን ማካካሻ በአግባቡ ያስተናግዱን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፤ “ ተማሪዎቹ እያነሱት ያለው ቅሬታ ትክክል ነው ” ብሏል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ተከስተ ብርሃን (ዶ/ር) ምን አሉ ?

በተለያዩ ምክንያቶች በተለይ ትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች አሉን።

ክረምቱን እንዲማሩ ነበር በዩኒቨርሲቲው ማኔጀመንት የወሰነው። ነገር ግን በአገር ደረጃ በተሰጠው ዳይሬክሽን መሠረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲፈተኑ መደበኛ ተማሪዎቹ ማስወጣት የግድ ነበር።

በኮረና እና በነበረውም ጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ የክረምት ተማሪዎች ነበሩ። እነርሱንም ተቀበልን፡፡ ለመምህራን የሚሰጥ ስልጠና አለ፡፡ እነርሱንም ተቀብለን እያሰለጠንን ነው።

በእነዚህ ምክንያቶች መደበኛ ተማሪዎቻችንን መጥራት አልቻልንም።

አሁን እንደ አቅጣጫ የያዝነው መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ጠርተን ማካካሽ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ባለፉት ዓመታት ሊመረቁ ለነበሩ ተማሪዎች ብቻ ካላንደር አዘጋጅተን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ነው።

መስከረም ስንት ቀን ይጠራሉ ? ቁርጥ ያለውስ ቀን መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ተከሰተ (ዶ/ር)፣ " የክረምት ተማሪዎቹ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም እንዲያጠናቅቁ ብለናል፡፡ ስለዚህ ካላንደሩ ገና አልጸደቀም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#TIkvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የተማሪዎችድምጽ

ዛሬ በርካታ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኢንተርን ሀኪሞች ወደ ቲክቫህ መልዕክት እያደረሱ ናቸው።

በዚህም አሉ ያሏቸውን ችግሮች እንዲታወቁና መላሽ እንዲሰጥባቸው ጠይቀዋል።

ኢንተርን ሃኪሞቹ ምን አሉ ?

- የ6ኛ ዓመት የሕክምና ተማሪዎች ከሐምሌ 15/11/2016  ዓ.ም ጀምሮ ወደ  ኢንተርንሺፕ የገባን ተለማማጅ ሀኪሞች (Medical Interns) ነን።

- በኢትዮጵያ ባሉ ሁሉም የህክምና ዩኒቨርቲዎች የምግብ አገልግሎት ወይም cost sharing (ወጭ መጋራት) የሚያገኙ ሲሆን የኛ ዩኒቨርስቲ ግን ከዚ በተለየ መልኩ " ከዛሬ ጀምሮ ምንም አይነት የምግብ አገልግሎት አታገኙም "  በማለቱ ያለምግብ ሆስፒታል ገብተን ስራ መስራት ስለማንችል መፍትሔ ይሰጠን ብለን ጥያቄ ስናቀርብ ቆይተናል።

-  ይሁን እንጂ " አድማ እያደረጋቹ ነዉ " በማለት " ባጭር ጊዜ ወደ ሆስፒታል ስራችሁ ግቡ ይህ ካልሆነ ግን ከዩኒቨርስቲው ትባረራላችሁ " ተብለናል።

- በ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀልን ቢሆንም በሀገራችን እነዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተከሰቱ ሁነቶች እስካሁን 2 ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ሳይካካስ ባክኖብናል።

- ያሳለፍነው ጠባሳ ሳያንስ አሁን ደግሞ ከግቢ ትወጣላቹ የሚለው ማስፈራሪያ አሳዝኖናል።

- ከሀምሌ 18/11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ በመመለስና ያለው ከሌለው በመረዳዳት ክፍያ እስኪጀመርልን ለመቀጠል በመወሰን በስራ ገበታ ላይ እንገኛለን።

- ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት ሚኒስትር በወጣ መመሪያ በ cost share ወይም ወጭ መጋራት በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለመደበኛ ተማሪዎች የነፃ ህክምና እየተሰጠ ባለበት ሰዓት የባህር ዳር የኒቨርሲቲ የኢንተርን ሀኪሞች አገልግሎቱን ተከልክለናል።

- ከሀምሌ 18 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም መፍትሔ ከዩኒቨርሲቲው ስላላገኘን ስራችንን  ለመቀጠል በጣም አስቸጋሪ አድርጎብናል።

- አብዛኞቻችን ረሀብን እንድንጋፈጥ ተፈርዶብናል ስለዚህ ፈጣን መፍትሄ እንፈልጋለን።

- ጉዳዩ በትምህርት ሚኒስትር እስኪፈታልን ሰላማዊ ጥያቄያችን እንቀጥላለን።

- የኢተርን ሀኪሞች የትርፍ ሰዓትን ጨምሮ ያለ እንቅልፍ ለተከታታይ 36 ሰዓታት የምንሰራ ሲሆን ያለ ምግብ እና ህክምና አገልግሎት መቀጠል ስለሚከብድ የሚመለከተው አካል በዋናነት ትምህርት ሚኒስትር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን በታላቅ አፅንኦት እንጠይቃለን ።

ቲክቫህ በዚህ ጉዳይ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ያነጋግራል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ለሚጀምረው የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በአራት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል፡፡

በዚህም በማስተርስ እና ፒኤችዲ ለሚሰጡ ተከታዮቹ ፕሮግራሞች ማመልከት ይቻላል ተብሏል፦

► Astronomy and Astrophysics
► Remote Sensing
► Space Science
► Geodesy

አመልካቾች የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለማስተርስ ዲግሪ ለማመልከት የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.00 እንዲሁም ለፒኤችዲ ፕሮግራም ለማመልከት የማስተርስ ዲግሪ CGPA 3.00 እና የመመረቂያ ፅሁፍ 'በጣም ጥሩ' ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የድኅረ ምረቃ ቢሮ 2ኛ ፍሉር በመገኘት ወይም የትምህርት ሰነዶችን በPDF ፎርማት በማዘጋጀት በ [email protected] የኢ-ሜይል አድራሻ ማመልከት ይቻላል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
መስከረም 6/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ቀን፦
መስከረም 14/2017 ዓ.ም

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
2024/10/04 07:37:04
Back to Top
HTML Embed Code: