Telegram Web Link
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ወደሚወስዱበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየገቡ ነው።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዘንድሮ ከ 700,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ መገለፁ ይታወሳል።

ምስል፦ ወራቤ፣ ወሎ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
በግል የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ጉዳይ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የመውጫ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤትም ከቀናት በፊት መለቀቁንና ተፈታኞቹም ውጤታቸውን እየተመለከቱ እንደሆነ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

ይሁን እንጂ ፈተናውን በድጋሜ የወሰዱ የግል ተፈታኞች ውጤትን በተመለከተ አሁንም ያልተጠናቀቁ ነገሮች መኖራቸውን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

በግል ፈተናውን በድጋሜ የወሰዱ ተፈታኞች ጉዳይ፣ የያጋጠሙ ችግሮች እና ውጤታቸው እንዴት ይገለፃል በሚለው ላይ በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ መረጃ እንደሚኖር ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#AddisAbaba ወላጆች እና ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል የኦንላይን ፈተና ጉዳይ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ እንድንጠይቅ ባዘዛችሁን መሰረት የከተማውን ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አነጋግረናል።

ሙሉ ቃላቸውን በደቂቃዎች ውስጥ እንልካለን።

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba #NationalExam

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል።

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ?

“ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።

በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት።

በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል።

የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት።

“ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል።

ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል።

ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል።

“ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2ዐ16 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ፕሮግራም ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን አሳውቋል።

ይህ ጥሪ ለቅደመ እና ድኅረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች የተደረገ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ረቡዕ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም መሰጠት ከሚጀምረው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስቀድመው ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ተቋማት በመግባት ላይ ይገኛሉ።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለፈተና የሚቀመጡ ይሆናል።

ምስል፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ተሳትፎ” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

አካዳሚው በኢትዮጵያ ከሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር መድረኩን አዘጋጅቷል።

መቼ፦ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም ቀን 10፡00 ሰዓት
የት፦ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ
(የአዳራሹ መግቢያ በኋላ በር በኖኅ ሬስቶራንት በኩል ነው)

በዙም አማካኝነት በቀጥታ መሳተፍ ይችላሉ።
Join Zoom Meeting፡
https://us06web.zoom.us/j/86599822304...
Meeting ID: 865 9982 2304
Passcode: 880397

@tikvahuniversity
35A+ ያሳካው ባለወርቅ ሚዳሊያ ተመራቂ

ነስረዲን ሙሐመድዘይን ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል፣ ኬሚካል እና ማቴሪያል ሳይንስ ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የዘንድሮ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ነው፡፡

ነስረዲን በዩኒቨርሲቲው በነበረው ቆይታ እጅግ ታታሪ ተማሪ የነበረ ሲሆን፤ ከወሰዳቸው ኮርሶች 35A+ በማሳካትና 3.99 አጠቃላይ ውጤት (CGPA) በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
መቱ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር #የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ሐምሌ 14 እና 15/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአቪዬሺን ሳይንስና ኤሮስፔስ ምህንድስና ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ለመጀመር እየሰራ መሆኑን ገለፀ።

ፕሮግራሙን በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለመክፈት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በኢትዮጵያ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ "የመጀመሪያ" የተባለውን ፕሮግራሙን ለመክፈት የሚያስችል ሀገር አቀፍ የካሪኩለም ግምገማ ተካሒዷል።

ፕሮግራሙ ሲከፈት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑ የአቪዬሺን ሳይንስና ኤሮስፔስ ምህንድስና ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚሰራ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 23:45:39
Back to Top
HTML Embed Code: