Telegram Web Link
#GambellaUniversity

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 481 ተማሪዎች አስመረቀ።

156 ተመራቂዎች በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 325 ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መረሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#TVTI

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 2,100 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ስልጠናቸውን ተከተታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ኢንስቲትዩቱ ብቁ ሰልጣኞችን በማፍራት ለክህሎት ልማት ዕድገት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ አነቃቂ ንግግር ያደረጉት ባለሃብቱና ሥራ ፈጣሪው ቤጃይ ነራሽ፥ ተመራቂዎቹ ከተጠቃሚነት ወደ አምራችነት እንዴት መሸጋገር እንዳለባቸው ልምዳቸውን አካፍለዋል።

@tikvahuniversity
37A+ ያሳካችው ተመራቂ

ሠብለወንጌል መንግስቱ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የማኔጀመንት ትምህርት ክፍል ተመራቂ ናት።

ሠብለወንጌል በቆይታዋ ከወሰደቻቸው የትምህርት ኮርሶች መካከል 37A+ ውጤት በመደርደር ልዩ የማዕረግ ተመራቂ ሆናለች።

ሠብለወንጌል በሦስት ኮርሶች ብቻ A- ውጤት ስለነበራት ሙሉ አራት ነጥብ ማምጣት ባትችልም፤ 3.99 አጠቃላይ ውጤት (CGPA) በማስመዝገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ሠብለወንጌል እንደምትለው የስኬቷ ምስጢር ለትምህርት ሙሉ ጊዜ እና ትኩረት መስጠቷ ነው። በተለይም በፈጣሪ ዕርዳታ ለዚህ ውጤት በቅቻለሁ ብላለች።

በትምህርቷ ያስመዘገበችው ዕጅግ ከፍተኛ ውጤት ከተመረቀችበት ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል እንድታገኝ አስችሏታል። #ENA

@tikvahuniversity
#KabridaharUniversity

ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 848 በተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው 726 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 73 በሁለተኛ ዲግሪ እና 49 በከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። #SMMA

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመረቀ።

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በግንባታና ግብዓት በማሟላት ሒደት ላይ የቆየው ሆስፒታሉ፤ ዛሬ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መሥጠት ጀምሯል፡፡

ሆስፒታሉ 600 የህሙማን አልጋዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የህክምና ግብዓቶች የተሟላለት መሆኑ ተገልጿል።

ሆስፒታሉ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠ ሲሆን፤ በወረቀት ተፈታኞች ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲዎች ከትናንት ሰኔ 29/2016 ዓ.ም መግባት ጀምረዋል።

ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በትግራይ ክልል ፈተናው በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በዚህም በመጀመሪያው ዙር በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን የሚወስዱ 6,000 ተማሪዎች ከትናንት ጀምሮ መግባት መጀመራቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

እነዚህ ተፈታኞች ከክልሉ ምስራቅ ዞን እና በከፊል ከማዕከላዊ ዞን የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
2024/09/30 21:29:08
Back to Top
HTML Embed Code: